በሕብረት የወጣው የታክሲ ስራ ማቆም አድማ መግለጫ የዳላስን ሕብረተሰብና ባለስልጣናት ቲኒሹን ትልቁን እያነጋገረና ሚዲያው ከእየ ቦታው እየደወለ በዜናው እየተሻማ ነው ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰአት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ። ስለሆነም የሕብረቱ ስራ የታክሲ ነጂዎቹን ድምጽ እያስተጋባ ነው በከተማው ብሎም በአሚሪካን ከተሞች። ለአንድ ቀን እንፈቅዳለን ታክሲ ነጂዎች እንደልባቸው እንዲሰሩ ተባለ። ታክሲ ነጂዎቹ የአፍሪካ ሕብረት ድምጽም ናቸው የዳላስ ፎርት ወርዝ የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት ከሆኑት ስሮቹ ዋነኛውም ናቸው።
የዳላስ አይር ማረፊያዎች ለአንድ ቀን ለታክሲ ነጂውች (ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዎያን) ታክሲ አሶሴሽን አባላት የዘጋንውን ከፍተናል እንከፍታለንም ለአንድ ቀን ለዛሬ ብቻ ብለዋል ፈቅደዋል። ቦይካውት ከስድስት ፒኤም ዛሬ አርብ እስከ ስድስት እሁድ ነው።
የዳላስ ጋዜጠኞች ከጠየቁኝ ጥያቄውስጥ ይሄ ብዙ ገንዘብ የሚያገኙበት ቀን ነው እንዴት በዛሬ ቀን ያቆማሉ? ላለው ጥያቄ መልሴ: ለአንድ ቀን የቀምዋቸውን መብት መመለስ፡ የተቀሙትን መብት መመለስ አመት አያኖራቸውም። የቴክሳስ ሎቶሪ አይደለም የአንድ ቀን ገቢ ማታለያና ጊዜ መግዣ እንጂ። ላንድ ቀን ከተፈቀደ ዳላስ ፎርት ዎርዝ ኤርፓርትና ላቭ ፊልድ እንደተገኘውና በፈለጉ ጊዜ ሄደው መስራቱ ሁሌም እንደነበረ ሊፈቅድላቸው ይቻላል ማለት ነው። ለአንድ ቀን የዘጋንዉን በር ከፍተንላችሁዋል ማለት ላንድ ቀን፡ ይሄ በአሜሪካን የተለመደው ስለመብቱ የሚቆመውን ወይም ለተጨቆነው ለሚቆመው ቲኒሽ ጉርሻ ሰጥቶአከበርንህ ድምጽህን ሰማን ፡ ጥያቄህን ተቀብናል አይነት የተለመደ የማረሻሻ፡ ቀስ በቀስ በማስራብ ለመግደል የሰው ሞራል ይደረግ የነበረ ነው። ላንድ ቀን የሚሰጥ የአዲስ አመት ጉርሻ አመት አያኖራቸውም።
በመጀመሪያ ለታክሲ ነጆዎቹ የሚጠቅም ሳይሆን የአንድ ቀን መብት ፍቃድ ለዘላለም ዘጋን ያሉትን የዳላስን ከንቲባ በዲኤፍ ደብልዩ ቦርድ ውስጥም ተሸጉጠው ያሉትን ስልጣናቸውንና እሳቸውን ጥሩ አድርጎ የሚያሳይ ዘዴ ነው። ይሄውም ሕዝብ ታክሲ እንደልቡ ካገኘ የታክሲ ነጂዎቹ የከተማው ተሳፋሪም ይሁን ከውጭ የሚመጣውን በአለም አቅፍ ባህልና ጨዋ ስራት በማስተናገድና በሰአቱ በተጠሩበት ዱብ የሚሉ ጭምር የሚሰጡትን ትልቅ አገልግሎት በቦይካውት መክኒያት እንዳይታወቅ መቅበርያም ነው ለአንድ ቀን ፈቅጃለሁ ወይም ፈቅደናል እንደልብ እንድትሰሩ የሚለው ፍቃድ። ታክሲነጂዎቹና አሶሴሽናቸው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል፡ ከዚህ ቀደም። በሲቲኦፍ ዳላስ ሕዝብ ችግሩን በሚያሰማበት ቀን እሮብ ቀን አቤት! "ጆሮና አይን እንደሌለው ጭጭ አሉን" ብለዋል። ጆሮ ዳባ ብለው ባለስልጣኖቹ ጸጥ አሉ። አሁን ታክሲ ነጂዎቹ የሚጠይቁት በስራላይ መዋል ይኖርበታል ሁሉንም በሚጠቅም መልኩ። ታክሲ ነጂዎቹ የአንድ ቀኑን ፍቃድ አይቀበሉም!
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያና የኤርትራውያን ታክስ ነጂዎች የግብረሃይል አባላትን በጣም እያደነቅኩ በተለይ አቶ መንገሻ በአስቸክዋይ ስራን በተረጋጋ መልኩ ስራን እንደአመጣጡ ተቀብሎ አስቸክዋይ እርምጃ መውሰድና ሻለቃ ሱራፌል ደግሞ የሚመለከተውን ሰው ባስቸክዋይ በማገናኘት ስራው እንዲፋጠን ባደረገው በጣም ስራውን መስመሩን ባስቸክዋይ እንዲያያዝ ትልቅ እርዳታ አድርግዋል። የግብረሃይሉ አይኖች ጎበዝ የእኔ ወንድሞች!
Dallaseotc.blogspot.com ስም ጠርቼ ለማመስገን ማንነታችሁን ስለማላውቅ ነገር ግን በብሎጋችሁ ላይ ድጋፍ ለታክሲ ነጂዎቹ ሕብረተሰቡ እንዲተባበር በማሳሰባችሁ በጣም ልትመሰገኑ ይገባል። ይሄ የሁላችንም ጉዳይ ሲሆን እያንዳንዱ ታክሲ ነጂ ከሁዋላው ልጆችና ባለቤት ያለው መሆኑንም ልንገነዘብ ይገባል።
በሕብረት ተራራም ይገረሰሳል፡ ወደ ብርሃን ቦታም ለመውጣት መሹለኪያም መንገድ ይሰራበታል።
ይሄ ጅምር እንዲሳካላቸውና ወንድሞቻችን እህቶቻችን ታክሲ ነጆዎች በለመዱት የራሳቸው ታክሲ ባለቤትነታቸውን ይዘው እንዲቀጥሉ እግዚአብሄርን ሁላችንም መለመን ይኖርብናል መጸለይ አለብን። እነጸልይ አምላክ ይስማን እጎናቸው እጎናችን ይቁም አሜን።