Friday, February 5, 2016

ከዚህም ከዛ። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ይሄ ሁሉ ትልቅ ትግል?

ከዚህም ከዛ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ፡ በአገሩ እና በስሙ ስለሚደረገው ማንኛውም ተግባር ሁሉ የማወቅ መብት አለው። አንድ ቦታ ላይ ብቻ ያተኮረ አይምሮ በዛሬ ጊዜ ዋጋ የለውም። የኢትዮጵያ ጠላቶች ብዙ እና በብዙ አቅጣጫ ስለሚመጡ ወዳጅ መስሎ የሚቀርበውን ጠላትንም ማዳመጥ እራስን ለማዳን የሚጠቅም አንዱ ትልቁ የመጀመርያው መነሻ እና በተጨባጭ መረጃ ነው። ስለሆነም ከዚህ በታች ያለውን አጭረ መግቢያ ከቪዲዮች ጋር በማጣመር እነሆ።

በአገራችን ፡ በስማችን ግለሰቦች እየተነሱ የሶሻል ሚዲያን እየተጠቀሙ ሊበታትኑን ብዙ ሰርተዋል አሁንም ቀጥለውበታል ። እንደውም በባሰ መልኩ ቁዋንቁዋ እየቀያየሩ ስፓንሰር በሚያደርጉዋቸው የወያኔ መንግስት ፡ የአረብ እና የአውሮፓ በሚሰጥዋቸው መመሪያ እና ገንዘብ መሰረት ማለት ነው። ከዚህ በታች ያሉትን ቪዲዮዎች ስናይ ሃቅም ፡ ውሸትም፡ በፓለቲካ ስም  ነጋዴነትን ፡ ወሮበላነትን ፡ ከስልጣን ላለመወረድ ትግልን፡ ስልጣን ላይ ለመንጠልጠል በውሸት፡ አስመሳይነትን ፡ ጥላቻን ፡ ወገናዊነትን ፡ በሃይማኖት ስም መነገድን ፡ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ አረብነትን ማብለጥን ፡ ከኢትዮጵያዊነት ይበልጥ ብሄርን ፡ የመሳሰሉትን ሁሉ በአሜእሪካን ፡ በአውሮፓ ፡ በአፍሪካ እናም በካናዳ ከያሉበት ሁሉ በመጠራራት ጭምር እንደምታዳምጡት አገር ለመጥቀም ሳይሆን እራሳቸውን ለመጥቀም ሲሉ ኢትዮጵያን እና ሕዝብዋን በምታዩት መልክ በማበጣበጥ መከፋፈሉ በተግባር እንዲውል  የሚያናፍሱ ኢትዮጵያውያን ወንዶችን እናያለን።  እዚህ ላይ ሂትለርን  ማሰብ ይኖርብናል ። ይሄውም እንግሊን ከኢራክ ለማስወጣት የተጠቀመው የሃይማኖት መሪ ጀርመን ወስዶ ሬዲዮን ስርጭት አዘጋጅቶ አያቶላው በአረብኛ እንዲያነቡ ተደርገው ነበር። የኛዎቹም በተለያየ የኢትዮጵያ ቁዋንቁዋ በብሄራዊ ቁዋንቁዋ ጭምር የሚያስተላልፉት ከዚሁ የተለየ ሳይሆን ከዛ የቀጠለ መሆኑን ነው።  ሂትለር ስል ፡ የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ፡ የእንግሊዙ ቢቢሲ እና የጀርመኑን ዲደብልዩ ጥሩ የፓለቲካ እና የመከፋፈል ፡ በተለያየ ቁዋንቁዋ በእያገሩ የሚያዳምጣቸውን ሁሉ ሕዝብ አይምሮን የማወናበጃ የሚፈልጉትን መልክታቸውን የማሳመኛ ምሳሌዎች ነው ።

ኢትዮጵያ እና ሕዝብዋ በመድሃኒትዓለም ሃይል እና በሃቀኛ ልጆችዋ ከወያኔ እና ከአወናባጅ ነጋዴ የፓለቲካ ድርጅቶች መዳፍ ነጻ ይወጣሉ።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!