Sunday, December 5, 2010

የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደረቅ!

መድሃኒአለም ካወጣው ሕግ ውጪ በሰላም የሚኖር ማንም አይኖርም፡ ኖሮም አያውቅም ሊኖርም አይችልም።  በሃይማኖትና ቤበተክርስቲያን፡ በአገራቸው ሕዝብ  ስም  የሚነግዱ እግዚአብሄር በንጹህ ከሰሩ አብዝቶ እንደሚባርክላቸው የላባቸውን ዋጋ የማያምኑ ናቸው።


የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በጋርላንድና ችግሮቹ ቁጥር ስምንት።
የቅዱስ ሚካኤል ደብር ችግሮች ተዘርተው የበቀሉት በኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ውስጥ በመሆኑ አሁንም ጉዳዩ ተያይዞ ይገኛል።

መረዳጃ ማሕበሩን የመቆጣጠሪያና የመኖሪያ ትምህርት ቤት ነው ያደረጉት ሆዳሞች። ከመረዳጃ ማሕበሩ ቀጥሎ ልክ ከሁለተኛ ደረጃ ቀጥሎ ዩንቨርስቲ እንደሚገባ ተማሪ: መረዳጃውን ከተሸጋገሩበትና የቦርድ አመራር  ረዝሜያቸውን ከሰሩበትና እነማን ላይ በር መዝጋት እንዳለባቸው ሳይቀር የከፋፋይነትና የመከፋፈል መርዝ ከወግዋቸው በሁዋላ እነ ፍቅረማሪያምና መንግስቱ ሙሴ ብሎም ሌሎች ምስዮቻቸው ቀጣዩ  ወደ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ቦርድ በመግባት በመረዳጃ ማሕበሩ እንዳደረጉት ቤተክርስቲያኑንም የእነሱ ብቻ አድርገው ሌላውን የቤተክርስቲያኑን ባለቤት በሙሉ እድር ግባ፤ እዚህ ድርጅት ግባ ኒያላ ኢንሹራንስ የወያኔና ያላሙድኒን ድርጅት በውጪ የሚገኘው ኢትዮጵያዊንና ባገር ቤት ያለውን ቤተሰቡን በትግሬ ነጻ አውጪ ቁጥጥር ስር ለማድረግ እንዲረዳ መረጃ መሰብሰቢያን ማስፋፋትን ሁሉ የሚያጠቃልል ስራ ለመስራት ማለት ነው። ለዚህም ተፈራ ወርቅና በትሩ በግልጽ በኮንትራትና ደሞዝ ሰራተኛ ሲሆኑ ለኒያላ እነስሱን ደግሞ በየቦታው አጥር ላይ እንደሚሰካኩ የጠርሙስ ስብርባሪዎች በየቦታው የሰክዋቸውና የሚሰክዋቸው ፡ እራሳቸውን አስመራጭ ኮሚቴ ብለው ማንም ሳይመርጣቸው መራጭና አስመራጭ ሆነው እነተፈራ ወርቅን በየቦርዱ ያስገቡና የሚካኤል ደብር ቦርድን መያዝ ደማቸው ውስጥ ያለበመሆኑ ለሃይማኖቴና ወይም ለአገሬ እስከመጨረሻው የደሜ ጠብታ ድረስ እታገላለሁ እንደሚል ቆራጥ ወንድ ወይም ሴት ፡ በዚህ መልክ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ቦርድ ለመግባትና በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ ያላደረጉትና ይማያደርጉት የለም በሩ ክፍት እንዲሆንላቸው። ጥሩ ምስክር ተፈራ ወርቅን በውሸት ለሚካኤል ደብር ለሃይ አመት ያገለገለ አስመስልው ለብዙሃኑ በማቅረብ እንድሸለም ማድረጋቸው አንዱ ዶክመንት ወይም በቤተክርስትያኑ ታሪክ ውስጥ የገባ የውሸት ታሪክ ነው።  አገለገለ በሚል መቅደስ ፊት በመነኩሴ እጅ ላላገለገለ ቤተክርስቲያን መሸለሙ የረዝሜ ግንባታቸው ምስክር ነው። የዚህ ሁሉ ተጠያቂዎች ብዙ ሲሆኑ፡ አስመራጭ ኮሚቴ በሚል ያታለሉት ሕዝቡን ፍቅረማሪያም ደረስ፡ መንግስቱ ሞሴና ጴንጤናዊትዋ ብርሃን ዳኛቸው ይገኙበታል። ይቺን ሴት ልብ በሉ በሰማንያ ዘጠኙም ሕገ ወጥ ስራ ከእነኪሮስ ጋር የቆመች ላለፈው ሃያ አመት በሚደረገው ሕገ ወጥ ተግባር ከሕገ ወጥ ወንዶች ጎን ከጉዋደኝዎችዋና ለራስዋ ጥቅም ከሚትባበርዋት ጋር ለጥቅም ከመታገል፡ ስራ እንድታገኝ በስሙ እድል ለሰጣት የኢትዮጵያ ስዴተኛ በሃቅ አጥር ስር እንድትቆም ብትመከረም እራስ ወዳድ ለራስዋ ጥቅም እንጂ ስለማንም የማትደነግጥና ጎበዝ ሴቶችንም ይሁን ለራሳቸው ሆነው መቆም የማይችሉትን እንደ እነ ክርስቲ ተፈራ አይነቶቹን አገት ካስደፉት ወንዶችጋር አንገት የምታስደፋ ስለ ውነት የማትቆም ሴት ነች እራስ ወዳድ ነች።  ብርሃን ዳኛቸው ሴቶችን የሚጨቁኑ ወንዶችን የምታከብር ነች። ለዚህም ብዙ እውነታ ማቀረብ ይቻላል።
 ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቀን በአል አዘጋጅ በሚል ወደ ስራዋ ለመመለስ ይጠቅማት ዘንድ የተሰራው ማጭበርበር አንዱ ምስክር ነው። ለክርስቲ ተፈራ ነብስዋን ይማራትና ቸሩ እግዚአብሄር ሶስት ደቂቃ ተፈራ ወርቅ፡ ፍቅረማሪያም፡ ይልማ ፈልቀ ሲክለክልዋት ሕዝቡን አንዳንድ ዶላር እንዲረዳት እንክዋን እንዳትጠይቅ፡ ብርሃን ግን አዝጋጅ ኮሚቴ ውስጥ የነበረች እየሰማች እርጅያት ብላትም ብዬ ባሳስባትም መድረክ ላይ ከስራዋ ከዳላስ እስኩል ድስትሪክት ያመጣችው እንግዳ በሰአቱ እንዲቀርብላት ትርዋርዋርዋጥ ነበር። ክርስቲ ሶስት ደቂቃ መከልከልዋን ብርሃን ፊት ተፈራ ወርቅንና ይልማ ፈለቀን ስከራከር ብርሃን  ስለ እራስዋ ስራነክ እንግዳ እንጂ በሞትና በመኖር መሃል የነበረችው ኢትዮጵያዊት በዝሙት አልውደቅም በማለትዋ የእርዳታ በሩ የተዘጋባት ክርስቲ ተፈራ አልጋዋ ላይ ሆና ታዳምጥ ነበር የእነ ብርሃንን ደስታና እርስ በእርሳቸው የመጠቃቀም የኢትዮጵያ ቀን ከበሮ ሲጮህና ፍቅረማሪያም ገዘቡን ሲቆጥር፡ ዘውገና ኪሮስ ንግዳቸውን ሲያጥዋጥፉ።

በሰማኒያ ዘጠኝ ሕገ ወጥ ስራ የሰሩት በአጼ ሃይለስላሴ መንግስት ግዜ የመጡ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ጎበዝ ተማሪ ሆነው ሳይሆን ለጎበዝ ተማሪ የመጣውን በዘመዶቻቸውና በመተዋወቅ የምይግባችውን የነጻ ትምህርት እድል ተሰጥቶዋቸው ወደ አሜሪካን የመጡ ከነበሩት በዳላስ ካሉት ናቸው። ይሄ ባለፉበት መኖር የመጡበት በመሆኑ መንግስትም ሲቀየር የነጻው ትምህርትም በአሜሪካን፡ በፈረንሳይ፡ በግሪክ፡ በእንግሊዝና ጀርመን ጭምር በደርግ መንግስት መክኒያት በምቁዋረጡ ምቾታቸው ሊቁዋረጥ ችልዋል። ታዲያ በስዴት ወደየቦታውና ወደ አሜሪካን በንቃቱና በብልህነቱ ያለዘምድ ግፊት በራሱ ጥረት የገባውን የኢትዮጵያ ስዴተኛ ዘቦት ፒፕል እያሉ በመጨረሻም በእስፓርት ስም ሊነግዱበት ሲሉ የእስፕፓርት ድርጅቱን የስዴተኛው እንዲሆን ከግል ጥቅም ነጻ ይሁን በሚል የመጀመሪያውን ሃሳብ በጹሁፍ ካቀረብኩትና ካደረኩት ትግል ያነበባችሁት ነው ከሁለት ሳምንት በፊት። እነዚህ ሰዎች ከእነሱ በሁዋላ በደርግ መንግስት ጀምሮ እስካሁን በዲቪም በስዴተኛነትም ወደ አሜሪካን ዳላስ ፎርት ወርዝ በሚገባው ኢትዮጵያዊ ስም መነገድና የሚያቁመውን ቤተክርስቲያንና ድርጅት ከመሃሉ እንደነሱው ሆዳም እያጠመዱና በክፋትና ማጭበርበር እያሰለጠኑ በመከፋፈል የሚፈልጉትን ጥቅም ማግኘት፡ የቆሙለትን የትግሬ ነጻ አውጪ ስራ እግቡ የማድረስ መብት ያላቸው አድርገው ነው የወሰዱት እኛ ፕሮዳክት እነሱ ብዛታችንን በመጠቀም፡ የሚሸጡን በጅምላና በችርቻሮ መሆኑ ግልጽ ነው በተለይ ዛሬ። ይሄውም፡ ጥቂቱን ለምማታወስ ያህል ልጥቀስ፡ ኒያላ ኢንሹራንስ + ጋሻ ኢንሹራን+ እድር= የትግሬ ነጻ አውጪና ባንክ እንከፍታለን ፡ የኢትዮ አሜሪካን ቻምበር ኦፍ ኮመርስና ደጀን  ዳላስ ፎርት ወርዝ ሊደርሽፕ ካውንስል፡ የም እመናን ጎባኤ፡ የኢትዮጵያ አመራር ጉባኤ (ኢትዮጵያን ሊደርሽፕ ካውንስል) ይገኙባቸዋል።




የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር የእስፓርት ክለብ መጀመሪያ በመረዳጃው ስም ለአስራ ሁልት ቀን የነጻ ስታድየም ጠይቆ ያገኙበት ማመልከቻ ሁለተኛው ገጽ ነው የመጀመሪያውን ገጽ አይታችሁታል።



ከዚህ የስር ያለው ገጽ የሚያሳየው አራት እድል ሰጥቻችው አሻፈረኝ ስላሉ በማጭበርበር የተጠቀሙትን የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ስም ነጻ እንዲያደርጉ በጠየኩት መሰረት ጥፋታቸው ታውቆ የኢዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ነጻ አውጥቼ እርዳታ የሚያስፈልገው ኢትዮጵያዊ ብቻ እንዲጠቀምበት አድርጌአለሁ። ስለሆነም ኪሮስና ግብረ አበሮቹ ከዚህ ቀጥሎ እንደምታዩት ከላይ ካለው ማመልከቻቸው ጋር ብዙም ልዩነት የሌለው ባዲስ መልክ ሌላ እስታዲየም እንዲጠይቁ ጭምር በመገደዳቸው በዚህ መልክ ማመልከቻ ሊያቅርቡ ችለዋል በግዜው በሰማኒያ ዘጠኝ እንደ አሜሪካን አቆጣጠር።  ይሄንን ነው በሃሰት ወንጅላን ነበር በሰማኒያ ዘጠኝ እ.አ.አ. በሚል ጠቅላላ ጉባኤ ብለው ሲኮንኑኝና ትሰቀል፡ ትገደል ፡ትገልል ሲሉ የነበረው።




አተርኒ ጀነራል ኦፊስ ኪሮስንና ሕገ ወጥ አባሪዎቹን የመረዳጃ ማሕበሩን ስምና ከግል ጥቅም ነጻ የሚያደርገውን ማንኛውንም ማህተሙንም ይሁን ሰርተፍኬቱን ሁለትኛ እንዳይጠቅሙና ቦርድ ውስጥም ያሉት የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ህሉውናና ሕጉን እንዲከተሉ ለግል ጥቅማቸው ድርጅቱን እንዳይጠቀሙ የሚል ከተወሰነባቸው በሁዋላ  በጠበቃ አጽፈው ለመረዳጃ ማሕበሩ ያአቀረቡት። ታዲያ በሰማኒያ ዘጠኝ በአሜሪካን አቆጣጠር  እነኪሮስ፡ ዳዊተ የተባለው ብሎም ግብረ አበሮቻቸው በሃሰት ተወንጅለን ነበር ብለው በካንጋሩ ፍርድ ቤት ችሎት እነሱው በፈጠሩት ሰገነት ከሳሾች፡ ምስክሮችና ዳኞችም ሆነው ሲቀርቡ ለደጋፊዎቻቸው ምን አቅርበው ነው ደጋፊዎቻቸው እኔን ለማጥፋት ከስላሳሺ ሕዝብ መሃል አርባ ሁለቱ ከዳዊት አለማየሁ ጭምር ሊያድሙብኝ የቻሉት? ዳዊት እንደደግፊ ሆኖ ለምን ቀረበ ተፈራ ወርቅና ዘውገ ከቦታቸው ይልቀቁ ስላልኩኝ?

የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ ነው የተባለን አባባል ትክክለኛነት ከዚህ በታች ቃኙጥ።
ይሄ ደብዳቤ ለአተርኒ ጀነራል ጽህፈት ቢት ያቅረቡት ሳይሆን ጥፋተኛ ነን ብለው፡ በመረዳጃ መሕበሩ መዝገብ ውስጥ ወደፊት ሃላፊነት በቦርድ የሚረከቡትን ስዴተኞች በሃሰት ነው የሐረርወርቅ የተቁዋቅዋመችን በጊዘው የነበሩት የቦርድ ሊቀመንበርና ቦርዱ እንዳለ ፈቅዶልን ነው። በመጨረሻም የመረዳጃ ማሕበሩ የስዴተኛን ጉዳይ ብቻ ማሳኪይ እንዲሆን በሕግም እንዳይጠየቅ አስበን ከተሰጠን ስሙን ከእስታዲየሙ ከዳላስ እስኩል ድስትሪክት ነጻ አድርገንዋል ማንም ሳይጠይቀን በራሳችን አንነስሳችነት ለማለት ይጠቅማቸው ዘንድ የተጻፈ ሌላ ውሸት ነው።
ሆኖም ኪሮስ ወልደስላሴ የጀመርኩትን ስለጨረሰው ሰማንያ ዘጠኙን አስመልክቶ ይሄ መረጃ ማጠቃለያዬ ይሆናል። እኔ በእንኪሮስና በአርባ ሁለት ደጋፍውቻቸው ብወነጀልም ክብደት የሌለው ቁጥርን መብዛት ሳይሆን የእውነተኛ አማኙን በእሱ ሕግ ብቻ የምንኖረውን ደጋፊ እግዚአብሄር ይመስገን ሃቁን በኔ አቅም ሳይሆን በራሱ የክሮስን የግብርረበሮቹን ማንንነት ፌመስ አድርጎ ሳይሆን ኢንፌመስ አድርጎ ለአለም አብቅቶዋቸዋል። ይሄንን ስል ተደሰትኩኝ ማለቴ አይደለም አምላክ አለ ነጻ ያወጣችህዋል ውነትን ብቻ እሱ እንዳዘዛችሁ የምትኖሩ ከሆነ ለማለት ነው በተለመደው አነጋገሬ።
በመጨረሻም ውነትን ብቻ በጣቴ በዚህ መልክ እንዳስቀምጥና ስለእሱም የማይዛባ ዳኝነቱ ጭምር እንድመሰክር አስጀምሮ ያስፈጸመኝ አምላክ ትልቅ ምስጋና ይግባው አሜን እንጂ።