Friday, December 24, 2010

ከደብረምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል አሁን ካለው ቦርድ፡ የዳላስ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ቦርድ class , 101/202 organizational, leadership and decision making መውሰድ አለባቸው።

ዛሬ ይህ ብሎግ የሚያተኩረውና ማጠቃለያም የሚሰጠው ሰሞኑን ላለንብት ሃዘን አስመልክቶ ይሆናል።

የተለመደው በተከታታይ ሲቀርብ ከነበረው "የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በጋርላንድና ችግሮቹ" በሚለው አርእስት አቶ አበበ ንጋቱ (ጤፉ) በቤተክርስቲያኑ በኩል የተጣለባቸውን አደራ አግዋድለዋል ወይ? በሚል አረእስት ነገ ይቀጥላል።


በመጀመሪያ ሁላችንንም የሕጻን ማትያስ ከመሃላችን በጠዋቱ መለየት መሪር ሃዘን እንክዋን ለወለዱትና ላሳደጉት በጣም ተጠግተን እንክዋን ለማናውቀው ወይም ባጭር ሕይወቱ ጊዜ ጥቂት ጊዜ አልፎ አልፎ ያየንዋና ፊታችን አድጎ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ሆኖ መጽሃፍ ቅዱስ እሁድ እሁድ ያሳለመንና አይተውት የማያውቁትንም ጭምር ያሳዘነ ነው የደረሰበት አደጋና ከመሃላችን የተቀጠፈው አቀጣጠፍ። ለዚህ ቀውጤና አስደንጋጭ ሰቅጣጭ ሃዘን በመሃላችን ተገኝተው አይምሮ አችንን በእግዚአብሄር ት አዛዝ መሰረት እንድንመራ ያሳሰቡን ያስተማሩንን የሃይማኖት አባታችንን ስያስተምሩ በጣም የሚደነቁ በመሆናቸው እንዴት እንዳጽናኑ ሕዝቡን ስንት ጊዜ መለቀስ እንደተፈቀደ ሁሉ በሚል ለተነገረው አባባል ከዚህ የሚከተለውን ማቅረቡ ምን ማለት እንደፈለኩኝ በግልጽ ያስቀምጠዋል፡

"የመምህር አባ ምሕረት ሙሉ በኩለሄ መክኒያቱም አቅዋቁዋም የሚያውቁ፡ ቅዳሴንም እንዲሁ አበጥረው የሚያውቁ፡ ስብከትን ወንጌልንም በደንብ አበጥረው የሚያውቁ በመሆናቸው የዳላስ ደብረምህረት የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራልና ምእመናን እድለኞች ናችሁ በአሁን ጊዜ ህሉንም የቤተክርስትያንችንን እውቀት አሙዋልቶ የሰጠውን ካህን ማግኘትታስቸጋሪ ነው። በጸባያቸውም ቢሆን ከህሉም ጋር ተግባቢ ብመሆናቸው እኝህን ካህን እንዳታስቀይምዋቸው በደንብ ያዝዋቸው።"  መላከ ሰላም ኤፍሬም ከበደ፡ አትላንታ ጆርጅያ በትናንትናው እለት ። 

ቀጥሎም በመድረክ ላይ እንዳመጣጡና ቅድመ ተከተሉን ይዝው ብቻ ሳይህን ያልተዘግጁ ሰዎችና ልጆች ሳይቀሩ ለማትዮስ ታሪክ ጥሩነት የእግዚአብሄር አግልጋይነትና የሁሉም ጉዋኛ የሕጻን መካሪነቱን ሁሉ በየፊናው በድምጽ ማጉልያው በተዘጋጀው ቦታ እየቀረቡ የሚፈልጉትን እንዲናገሩ በመጠየቅ ያሳዩት በሰፊው ብዝት ያለውን ሕዝብና ትልቅ መከራን አብሮ የመቁዋቁዋሙ ችሎታችው በድንገት እንደተወረረች አገር አስተዋይ ንጉስ ይመስል ነበረ እንድመጣጡ ሁኔታውን ሲያስተናግዱ ተጽፎ ሳይሆን ባይን በሚያዩት ወዲያው እርምጃ ውስዶ በተግባር ሲተረጉሙት ላየናቸው። በሌላ በኩል አንድ የፊልም ዲሬክተርን ትልቅ የሚያሰኘውና ሽልማት የሚያሰጠው ተዋንያንን በትክክሉ እንዳመጣጡና ችሎታቸውን አመዛዝኖ በሰከንድ ውስጥ የሚያሰተካክለው ብሎም የሚወስደው እርምጃነው ከእስክሪፕት ተጽፎ ከቀረበው ውጪ ስለሚያጋጥም ክስተቶች። ብዙ ምሳሌ መስጠት ይቻላል ሰለ ወጣቱ ዳቆን ያንን ሁሉ ሕዝብ በአገራቸው ብሄራዊ ቁዋንቁዋና በእስክሪፕት ወደ እንግሊዘኛ ተጽፎ ባልተሰጣቸው ከሚሰሙት ብቻ በተረጋጋና በኢትዮጵያዊ የኩሩ ጸባይ በከተማው ካጣንው ቢይንስ አስራ አራት አመት ያልታየውን ያሙዋላ ኩራትን የጨመረሕዝብ ከግራ ከቀኝ በማዳመጥ በመተርጉም የአማርኛውን ወደ እንግሊዘኛ ለማድረግ ሃሊውድና ወይም በተባበሩት መንግስታት ቃልን በቃል በየቁዋንቁዋው የሚተረጉሙት እንክዋን ባንድ ጊዚ ብዙ ሕዝብን በማስተናገድ ሳይሆን እያንዳንዱ ቀደም ብሎ በተዝጋጀብት የሚያስተረጉመው እንጂ የፕሮግራም አመራር እንዳመጣጡ ለመምራት ትልቅ የእግዚአብሄርን ችሎታ ይጠይቃል። ይሂንን አድናቆታችንንና ኩራታችንን ስንገልጽ የብዙዎቻችን መነጋገሪያም እንደሆነ ሰሞኑ በማስደግፍ ነበር።፡ ታዲያ ይሄንን አስመልክቶ   መለአከ ሰላም ኤፍሬም ከበደ ላለፈው አስራሃንድ አመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ድምጽ ሬዲዮ ስርጭት አዘጃና አቅራቢ ብሎም መስራች በአትላንታ ፡ ቤተክርስቲያን ሕዝቡን አሰባስብው የከፈቱም እንዲህ አሉ።


"ዳቆን አንዱለም በአዲስ አበባ ጠባዩ የተፈተነውን ሕዝብ መሰብሰብ የሚችል ትልቅ ሙሁር መንፈሳዊና ቴዎሎችጂ ያስተማረ ነው። ከዛም ወደ ካናዳ ለከፍተኛ ትምህርት ተልኮ እንደሄደ አውቃለሁ።"

የቅዱስ ያሬድ አካዳሚ ተማሪዎችና መዘምራን ያቅረቡትና አቀራረቡ ቤተክርስቲያኑን የተሙዋላ አካል እንዳለውም አስመስክራዋል። ልጆች በዚህ መልኩ በትምህርት ገበታ መኖራቸውን ብዙዎቻችን የተረዳንው ባሳዩት የመድረክ ዝግጅት ነው።
ያዩትንና የተሰራን የሰራንም ማመስገን በእግዚአብሄርና አምላክን በሚሰግዱለት ጭምር የሚያስደስት ነው። ይህ ብሎግ የሕዝብ ስለሆነ ብዙሃኑን ስለሚጠቅም ጉዳይና ስለሚጎዳውም ያቀርባል።

እንግዲህ  ከላይ የደብርምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በአሁኑ ጊዜ ቀደም ብለውም ከነበሩት ጋር ተቀላቅሎ ወይም ተበውዞ የሚሰራው ቦርድ መልካም ስራና አንድ ቦርድ የቤተክርስቲያንም ይሁን የጋራ መረዳጃ ማድረግ የሚጠበቅበትን ትክክለኛ ትብበር አድርገው አሳይተውናል።
መቼም መጽናኛ አንድ እግዚአብሄር ብቻ መሆኑ ግልጽ ነው። በጣም ከልብ ላንገበገበንና በየቤታችን በጠረቤዛ ዙሪያ ተቀምጠን አሁንም እየተንሰቀሰቅን እርስ በእርስ እንባ ለምንራጨው ሕጻኑን ያጋጠመው ያሳዘነን ብሎም ቤተሰቡን፡ኢትዮጵያውያን ትልቅ መጽናኛ እያደረግነው ያለነው በደብሩ የተደረገው የሃዘን መስተንግዶ ነው። ከእንባ ቀጥሎ ተንፈስ የሚያደርገን በቅዱስ ሚካኤል ደብረምሕረት ካቴድራል ለማትያስና ለስጋ ዘመዶቹ ለመላው ሕብረተሰባችን መላቀሻና ሃዘናችንን መግለጫ እንዲሆን ልክ እንዳገራችን እንደልብ ያለምንም የአካባቢ ንዋሪ መሳቅቅና የሰአት እላፊ ሳንል ይሄንን መራራ ሃዘን ለመቁዋቁዋም ህላችንም እንችል ዘንድ የቅዱስ ሚካኤል ደብረምሕረት ካቴድራልና አሁን ያለው የአመራር ወይም ቦርድ አባላት በአንድ ድምጽና ባስቸክዋይ የወሰዱት ውሳኔ ነው።በጣም ሊያስመሰግናቸው ይገባል። ላደረጉት ሁሉ በጎ አስተዋጽዎ ሃዘኑን የእራሳቸው አድርገው በመውሰድ አምላክ ከክፉ ይጠብቃቸው ከእነ ልጆቻቸው ጭምር እድሜም ከጤና ጋር የተደጋገፈ ያብዛላቸው። ጥሩ መስራት እግዚአብሂርን ያስደስተዋል። ጥሩ መስራት ስለሆነ እሱ የሚወድው የሚጠይቀንና የሚያዘንም ጥሩ ምስራትንና ለማንኛውም በምንም መልኩ ችግር የደረሰበትን ሰው ነብስ ያለውን ሁሉ የችግሩ ደራሽ እንድንሆን ታዘናልና፡፡ ዲኤፍድብልዩ ኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ብሎግ በሕብረተሰቡ ጠያቂነት የተከፈተ በመሆኑ የሕዝቡን ድምጽ ነው የሚያስተጋባው። በመሆኑም ሕዝቡ ያለሃይማኖት ልዩነት የቅዱስ ሚካኤልን ደብር የሕጻን ማትያስ ከበደ ብርሃኑን ከዚህ አለም ባጭሩ መቀጠፉን አስመልክቶ ላደረጉት ትብብር  "የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ቄሳውስትና የቦርድ አባላት እጅለእጅ በተግባር ተያይዘው የአካዳሚው ወጣቶች ሳይቀሩ ላሳዩት "የሕብረተሰባችን የአንድነትና የሃዘናችን ደራሾችና መጽናኛችን ጀግኖች" ብሎ አቸዋል።



ይህንን አስመልክቶ ነገ የምናወጣው ቢኖርም ለዛሬ ግን ፡Dallaseotc.blogspot.com ያወጣውን ስለ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕብር የሚመጣው የኢትዮጵያ ቀንና ውሳኔ አስመልክቶ ወይም ጭካኔ የተሞላበት ልብና አይምሮ አስመልክቶ።  ከዚህ በታች ስለምታይዋት  የአስራ ሁለት አመት ልጅ የጋራ መረዳጃው ማሕበር ፕሬዘደንት የደብረምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ደብረምህረት የሶሻል ኮሚቴ ሊቀመንብር ነኝ የሚለው የስራውን ግፍና ጭካኔ መመልከት አንዱ ትልቅ ድብቅ ምስክር ነው። ይችን ልጅ ልክ እንዲህ ሆና ያያት ሰው ገና ሳትታከም ነው እንደመጣች።  ለህዝብ እንክዋን ሳይነግርላት  ወዲያው ያያት እለት መልሶ ደውሎ አባትዋም ይሁኑ ልጅትዋን ሕዝቡ እንዲጠይቃቸው ሳይሆን  የተጨነቀላቸው፡ የልጅትዋን አባት የኢትዮጵያ ቀን በአል ስለማዘጋጅ ለሕክምና እርዳታ ያመጣችሁን ስውዬ ስምና የስልክ ቁጥር ስጡኝ ኦነር ላደርገው እፈልጋለሁ ትልቅ ስልጣን አለኝ በመረዳጃ ማህበሩ የሚል ነው። ወጣጣቱ መምሬ ፈረንጁን ቢያስጠይቁት ፡ እኔ ምንም ሽልማት አያስፈልገኝም አንተን ይርዱህ ኢትዮጵያኖች። የሚል መልስ በመስጠቱ፡ የመረዳጃው ፕሬዘደንትን አላስደሰተውም።  በዛው ጠፋ። ይሄ ሁሉ ሲህን ለህዝብ  አልነገረላቸውም።  ከሰባት ወር በሁዋላ ግን ልጅትዋ ታክማ ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ ስራ ከተሰራ በሁዋላ ልጅትዋ ወደ ኢትዮጵያ ከእነአባትዋ ልትመለስ ስትቃረብ ሳምንት ሲቅራት ብቅ! አለ ይቀጥላል በነገው ላይ።


እስቲ ሰው እግዚአብሄር ያየኛል ብሎ አያሳብም? ልጆች አለኝ የሚል ይቅርና ሳንወልድ ጀምሮ ከልጅነት እድሜያችን አስር አመት እድሜ ከኛ በታች ላሉት እንረዳ የነበርን ብዙ ነን። እንደዚህ ሆና መተንፈስ ስትቸገር የነበረችን ልጅ ጠይቁ አይባልም? ችግርስ እንዳለ ሲታወቅ ልንረዳ ለምንችለው ለምን አይነገርም?

 ገንዘባቸውን ሳይከፍሉ ኮሌጅ ሳይገቡ በነጻ class , 101/202 organizational, leadership and decision making  ከላይ በደብሩ ቦርድ የተወሰደውን እንደትምህርትና ክፍል በመውሰድ እራሳቸው የቤት ስራ ሰርተው የመረዳጃ ማሕበሩን ለመረዳጃ ተግባር ብቻ ማዋል ይገባቸውል።

የአለም ፈጣሪ ፡ ሁሉንም የፈጠረ ውነተኛ እግዚአብሄር በተለይ ፎቶዋን ስለምታዩት ከዚህ በላይ ያደረገው ትልቅ ምሕረትና የተመኘሁላትን ሁሉ ብዙ ውጣ ውረድ ቢያጋጥመኝም በጸሎት በአምላኬ ፍቃድ ሊሳካ ችልዋል። የጀመርኩትን ላስጨረስከኝ ከዚህ በላይ ያለውን ምስጋና ይግባህ የእኔ አይን፡ የአይምሮዬ ብርሃን ደግ ምስራትን ካንተ ነው የተቀበልኩት ለተቸገሩ ደግ በመስራቴን ወንጀል አድርገውና የተቸገረን እንርዳ በማለቴ ለተቸገረው ቀኝ እጅ በመሆኔ ወንጀል አድርገው በመረዳጃ ማሕበሩ አገልግሎት እንዳትሰጥ ብለው የወሰኑትንና ስማቸውንም ጽፈው ተስማምተናል ያሉት ግለሰቦች ይቅር በላቸው ደግ እንዲሰሩ ልቦና ስጣቸው አምላኬ ደግ ከመስራት የበለጠ ምንም አስደሳች ነገር ስለሌለ በአለም ውስጥ። አሜን።