Sunday, January 2, 2011

"New Year Gift"

ከየሐረርወርቅ ጋሻው።

የተከበራችሁ ወገኖቼ መልካም የአሜሪካን አዲስ አመት ይሁንልን ለሁላችንም። ብዙ አዲስ አመት አምላክ ያበርክትልን። በያለንበት በእውነት የታቀፈን ፍቅር ፈጣሪያችን ይስጠን።

ስጦታ ።

ለብዙ ወዳጆቼ እንደያመጣጡ የምሰጠውን ስጦታ ልለግስ እወዳለሁ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአሜሪካን አዲስ አመት። በሚቀጥለው አመት አይደለም ይችን ስጦታ ካነበባችህ ጀምሮ መጀመሪያ ሰላማችሁን የምታገኙት እራሳችሁን ስትጠይቁ ነው።  ይሄውም ባነጋገር ከራሳችንና ከዎዳጆች አብረን ከምንሰራቸው፡ ቤተሰብና ጉዋደኛ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ሳይቀር ሳናስተካክልና ግልጽ ባልሆነ ልምድ የምንናገረው ዘቤ፡ ኢትዮጵያውያንን ብዙ የምላስ ማዳለጥ ግጭት ስለሚያጋጥመን ከእርስ በእርስም አልፎ ከውጪውም አገር ሰው ጋር በአነጋገር ጠማማነትና ሽፍንፍን አባባል ልምድ መክንያት ጥላቻ እንቀርጻለን።  ይሄንን የማይገባ አነጋገርና ሳይገባን እንዲህ ማለቱ ነው እከሌ ወይኔ ምነው ልክልኩ በነገርኩት! ብሎ ከመቆጨት እዛው ፊት ለፊት ለምሳሌ፡ አንድ ወንድሜ ዛሬ ይሄ የፓለቲካ ጥያቄ አይደለም አለኝ።  በጥቅሉ በማስቀመጡ ሊገባኝ አልቻለም ስለዚህ ምንማለት ፈልገህ ነው አልገባኝም አስረዳኝ አልኩት። የመለስልኝ ግልጽና ገንቢ ነበር። እሱም ጨዋ ሰው በመሆኑ ለእኔም ትምህርት አስተማርሽኝ ብሎ ተለያየን። ባጭሩ "ምን ማለት ፈልገሽ ነው?" የሚለው ያብራሩልኝ ጥያቄ ዘላለማዊ ትልቅ ስጦታ በመሆኑ እንደምትደሰቱበት አልጠራጠርም። ይመስላል በሚል አንሄድ።

እግዚአብሄር ምስጋና ይግባህ ለሁሉም ስጦታህ የእኔ ንጉስ። ሰው ያሰበው በምንም መልክ ሊፈጸም አይችልም ያላንተ ፍቃድ ወገኖቻችንን እርዳቸው አሜን።