Tuesday, December 21, 2010

የማይብራራ ቃል ፈልገን ያጣንለት ሃዘን ውጦናል Dallas, Texas።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅዱስ ሚካኤል ደብረ ምሕረት ካቴድራል አገልጋይ የአስራ ሁለት አመት እድሜ የነበረው ሕጻኑ ማትያስ ከበደ ብርሃኑ ከዚህ አለም በድንገተኛ አደጋ ከመሃላችን በመሄዱ ልበለው፡ መሪር ሃዘን በቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን ለመላው  የዳላስ ፎርት ወርዝ ንዋሪ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጭምር ትልቅ አስደንጋጪና በመናገር የማይብራራ ቃል ፈልገን ያጣንለት ሃዘን ውጦናል።
የማትያስ ድንገተኛ ውጥት ብሎ ቅርት ሁኔታ ሁላችንንም ግራ አጋቢ ሲሆን ባጭር እድሜው ባደረገው አስተዋጽዎ በቅዱስ ሚካኤል ደብር፡ በቅዱስ ያሬድ አካዳሚ፡በትምህርት ቤቱና በእግር ኩዋስ ቡድኑ ሳይቀር የተደረገለት የጸሎትና የሕይወት ታሪኩን ገለጻ  አስመልክቶ የአስራ ሁለት አመት ሕጻን ሳይህን በጣም አቻ የማይገኝለት ደግነት በጎ ስራን እንደሰራ አዛውንት እንጂ። ብሎም ትልቅ ሰውና ሰላማዊ የእግዚአብሄር አገልጋይ የመኖክሴም ታሪክ ይመስል ነበር በቦታው ተገኝቶ ላዳመጠው ከእያንዳንዱ የአሚሪካን ልጅና ከኢትዮጵያውያን ልጆች ማለትም ከጉዋደኞቹ የተነገርው ስለ ተባረከው ጸባዩና ስለሌላው ሰው ማሰቡ። የትምህርት ቤቱ ልጆች የክፍሉ ልጆች ከተናገሩት ለመጥቀቅስ ያህል፡ "ማቲው በጣም ትሁት፡ የቤትስራውን ማንም ሳይነግረው በመስራት የሚታወቅና ሰላም አስፋኝ የነበረ ነው በክፍላችን።  ማቲው አንድ ቀን አስቀይሞን አያውቁም ሁሌም ጥሩ ሰው ነበር" የሚል ይገኝበታል።


ከቅዱስ ሚካኤል ደብር "ማትያስ መጸሓፍ ቅዱስ ከቅዳሴ በሁዋላ ሲያሳልም ጎንበስ ብሎ እንጂ ቀና ብሎ የምእመናን አይን እያየ የማያሳልም አንገቱን ደፍቶ እንጂ የሚልና ለአምላክ አገልጋይነት አጭር እድሜውን የሰጠ እንደነበረ በምድር ላይ እያለ! " ሲሉ አባታችን ስለ ማትያስ የሚያውቁትን በሰፈው ገልጸዋል። በሌላ በኩል፡ እንደውም ማትያስ ቤተክርስትያኑን ወደፊት ተረክቦ ይመራዋል ተብሎ ተስፋም የተጣለበት ሕጻን ነበር ይሄሁሉ ሲያደርግ በነበረው የቢተክርስቲያን አገልጋይነትና ስለአምላክ ባለው ፍቅር የተነሳ ነበር።

ሁለት ቀን መደዳ የወሰደ፡ ጽሎትና ታሪኩን ማቅረቢያ ብሎም  የክብር ስንብት ጸሎትና መዝሙር ተዘምሮለት በመጨረሻም ዛሬ ዲሴምበር ሃያ ብዙ ሕዝብ በተገኝበት እንባ በእንባ እየተራጨ የመጨረሻ ማረፊያው ቦታ ተቀምጥዋል። የማትያስ አሳዛኝ የደረሰበት አደጋ ብዝምታ የማይታለፍ በመሆኑ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቹ በተጨማሪ ለመላው ቴክሳስ ትምህርት እንዲሆን ጭምር በማሰብ የአሜሪካን ጋዜጠኞችና ቴሌቪዥን ቅድመ ዜናላይ ሰሞኑን ሲቀርቡ ከነበሩት ትልልቅ ዜናዎች አንዱ ሆኖ ሰንብትዋል። ብዙው ኢትዮጵያዊ ያልሆነውን በመንካት አሳዛኝ አደጋው የዳላስ ፎርት ወርዝ ሃዘንም ሆንዋል። የመገርመው፡ ማትያስ በቤተሰቡ ሳይሆን ሕይወት ታሪኩ በአስራ ሁለት አመት እድሜው ስላደረገውና ስለሰጠው አገልግሎት በራሱ በጎስራና ትጉነት፡ ልክ የስራ ግዳጁን ጨርሶ እንዳለፈ ሰው ታሪኩ የተቁዋጨለት ሕጻን ነው።
አምላካችን እናቱን ፡ አባቱን፡ እህቶቹንና ዘመድ አዝማዱን በሃዘኑ የተነካንውን ሁሉ ሳይቀር ጽናቱን ያውርድልን። ማትያስ ደግነትም ሰርቶ እንዳለፈ ሁላችንንም ለተቸገረና ማንኛውም እርዳታ ለሚያስፈልገው ወገናችንና ለማንኛውም የአምላክ ፍጡር እረዳት እንድንሆን ያድርገን።

አባታችን እንዳሉት ቅዱስ ነውና እግዚአብሂር ከጎኑ ከሃዋሪያቱጋር ያስቀምጥልን። አሜን!

የሐረርወርቅ ጋሻው።


ከዚህ በታች በማትያስ ቤተሰቦች ተዘጋጅቶ ለክብሩ ለተገኘው ሕዝብ የታደለውን አጭር የሕይወት ታሪኩን እንድታነቡት እነሆ።