Tuesday, October 3, 2017

ፊንፊንኔ መንደር እንጂ ከተማ ሆና አታውቅም።
አላማዬ በተለመደው ሃቅን በማስረጃ በማቅረብ እዚህ ላይ ሕዝብን ለማስተላለቅ ወያኔ ያዘጋጀውን ሁለተኛ ዙር ፊንፊንኔ :ፊንፊንን እንዳወጀው ለማቅረብ እና ኦሮሞው አሁንደግሞ ሌላ ሃሳብ አቅርቧል በሚል ሕዝብ ሊያጫርስ ስለሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ጉዳዩን ከሃቁ በማስረጃ ባቀረብኩት በመነሳት ለወያኔ ምንም እድል እንዳንሰጥ ሁላችንም በጥንቃቄ ልናየው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አሳስባለሁ።
ወያኔ እራሱ በሚገባ ያውቃል  ፊንፊን ወይም ፊንፊኔ  ፊንፊንኔ: ኦሮሙኛ ወይም የኦሮምኛ አባባል እንዳልሆነ ልብ በሉ።  ፊንፊን  ከተማ ሆና አታውቅም መንደርነች : ይሄንን አንደግፍም በሚል ኦነገን ስለተቋቋሙት የኢትዮጵያ ልጆች : አገራቸውን ከብሄር በፊት የሚያስቀድሙ : ኦነግ ሃሳቡን ለውጦ ኦፒዲኦም ጭምርሸገር”አሉ አልሸሹም አሉ እንደተባለው ነው። ሸገርም የውሸት የፊንፊንኔ መለወጫ ሆነ ተብሎ የተቀመጠ ነው። ሸገር የሚባል ከተማ በኢትዮጵያ ኖሮም አያውቅም።
በነገራችን ላይ በኦሮሞኛ (አፋን ኦሮሞ) ምንጭ ቡርቃ ነው የሚባለው። ፊንፊንኔ ፊንፊኔ እናም ፊንፊን አባባሉም ይሁን አጠራሩ ፊንፊንን ለመግለጽ ሲሆን ኦሮሙኛ ግን አይደለም።
ልብ በሉ ግንፍል ግንፍሌ ኦሮሙኛ አይደለም።
አቧራማ አቧሬ ኦሮሙኛ አይደለም ቀብና ቀበና አማርኛ እንዳለሆነ ሁሉ። ሃቁ አማራው በራሱ የቦታ ስም በአማርኛ የነበረውን እና የታሪክ ቦታን ከሕዝብ ጥቅም አንጻር ብቻ ነው የሚያስፋፋው ለምሳሌ የማይጮ አደባባይ የሜክሲኮ አደባባይ ብለው አጤ ኃይለስላሴ ቀይረውታል ከታሪክ እንደምንረዳው የማይጮው አደባባይ መቀየሩን አልደግፍም ነገር ግን በጊዜው ሌላ ቦታ ቢፈልጉለት ጥሩ ነብር። ሆኖም ሜክሲኮ ቁምነገሩ ጣሊያን ኢትዮጵያን ገዢነኝ ብሎ ሲያውጪ ሜክሲኮ እውቅና አልሰጥህም ብላ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆምዋ እና እንደውም በኢትዮጵያ ስም መንገድ ሁሉ በመሰየምዋ ኢትዮጵያም ሜክሲኮ አደባባይ ብላ የማይጮውን አደባባይ ሰየመች ማለት ነው። እስከዚህ ነው ሃቁ።
 አማራ እና ትግሬ መጤ ነው ብሎ ለሚያጉዋራው ግለሰብ እና ምስዮቹ በቁጥር ሁለት ከእነ አብረሃ እና አጽበሃ ወንደማማቾቹ ንጉሶች እስከ ዘረያቆብ ልብነድንግል ኃይለስላሴ ድረስ ያለውን ይዤ ብቅ እላለሁ። በድጋሚ እስከዛው አዲስ አበባን እና በውስጥዋ ያሉትን ቦታዎች ሰፈሮች እና መንደሮች ይቅር እና ቡና ቤቶች ሳይቀሩ በሚያስገርም ሁኔታ ስማቸው እንዲለወጥ የኦሮሞ ሕዝብ ጠየቀ ተብሎ በሚስጥር የተቀመጠውን ለውሳኔ የሚቀርበውን ተመልከቱት። ይሄንን የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጭ ብሎ ያያል ማለት ነው? ወይስ ኦሮሞን ለማስጨፍጨፍ?። ከኦሮሞ ሕዝብ የመጣ እንዳልሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊረዳው ይገባል በሚል አሳስባለሁ።
ይቀጥላል።
የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው።
ዘብሔረ አንዲት ኢትዮጵያ።
Email: yehar9@aol.com




ሚስጥር : ወያኔ : በኦሮሞ ስም ሊያውጀው ያሰናዳው በአዲስ አበባ : የስም መቀያሪያ ጥያቄ እነሆ።
 Image result filwuha before the building of filwuha building in Addis Abeba

ፊንፊን ( ፊንፊንኔ) ከተማው የተባለው ይሄ ነው። ፍልውሃ ፊንፊኔ ቡልቅልቄ፡ አጤ ምንይልክ እፍ ብለው ካነቃቁዋት በኋላ መሆኑ ነው።