Thursday, April 23, 2015

Worldwide Ethiopian Refugees' Advocate Group የኢትዮጵያ ስዴተኞችን አስመልክቶ ጥበቃ እንዲደረገላቸው ከሊቢያ መንግስት ጋር መነጋገር ጀምርዋል።

Worldwide Ethiopian Refugees' Advocate Group
Dallas, Texas USA (Founded in 1983 in Dallas, Texas)
Phone # 214-642-0394
email: yehar9@aol.com

አጭር መግለጫ
April 21, 2015

 Worldwide Ethiopian Refugees' Advocate Group የኢትዮጵያ ስዴተኞችን አስመልክቶ ጥበቃ እንዲደረገላቸው ከሊቢያ መንግስት ጋር መነጋገር ጀምርዋል

     በኢትዮጵያ ስዴተኞች ላይ የደረሰውን የግፍ ግዲያ በጥብቅ እንቃወማለን። ግፈኞችም ወደ ፍርድ ተፈልገው እንዲቀርቡ ሰላም ወዳድ የአለም ሕዝብ እንዲተባበርም እናሳስባልን። 

    አሁንም ግድያውን ለመድገም ግፈኛው ፋሽስቱ አይሰስ ወደ ሁዋላ እንዳላለም በመገንዘችን በሊብያ መንግስት በኩል በተለይ ኢትዮጵያውያን ስዴተኞችን ላይ በሊቢያ ወታደሮች እና ፓሊሶች በግፍ እየተያዙ መታሰር እና መደብደብ ከዛም አሳልፈው ለአይሰስ መስጠታቸውን እንዲያቁሙ የሊያን መንግስት ማለትም በአለም መንግስታት በመንግስትነት ተቀባይነት ያለውን ቀርቦ ከማነጋገር ሌላ ምንም መፍትሄ የለም :: ስለሆነም አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ስዴተኞች መብት ተከራካሪ እና ጉዳይ አስፈጻሚ ስብስብ (Worldwide Ethiopian Refugees' Advocate Group founded in 1986) ንዋሪነቱ በዳላስ ቴክሳስ አሜሪካ : ከሊብያ መንግስት ጋር እየተነጋገረ ይገል።


      እንደሚታወቀው በአሁን ጊዜ ሊብያ ሁለት ሃይል ነው የያዛት። ሆኖም በአለም መንግስታት እና ሕዝብ በሃያሉም መንግስትነትም በአሜሪካን እውቅና ካለው የሊቢያ መንግስት ተወካዮች ጋር አምባሳደር ኢብራሂም ደባሺ እና ሌሎች ዲፕሎማቲኮችን በመጨመር በኢትዮጵያ ስዴተኞች ላይ የሊቢያ ወታደሮች እያደንዋቸው እናም ለአይሰስ አሳልፈው እየሰጥዋቸው በመሆኑ መንግስታቸውን አምባሳደሩ እና በጉዳይ አስፈጸሚነት የተቀመጡትን ጭምር አንደኛ ወታደሮቻቸው ኢትዮጵያውያንን ከሚኖሩበት እየወሰዱ በእስር ቤት ውስጥ በማጨቅ የሚደረገው እስራት እንዲቆም እና ለአይሰስም አሳልፈው መስጠታቸውን እንዲያቆሙ በሰራዊቱም ይሁን ፓሊስ መንግስትነት የሚታወቀው አካል ከማንኛውም ጥቃት እንዲከላከልላቸው ጥበቃ እንዲደረገላቸው ዛዝ እንዲሰጥ እና እንዲተባበረን ግልጽ ደብዳቤ አቅርበናል::  ከሶስት ቀን በፊትም በጉልበት የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ስላሉ ከተያዙበት ባስቸክዋይ እንዲለቀቁ። ኢትዮጵያውያንን ክርስቲያኖችን በግፍ ለመግደል ለአይሰስ በቀላሉ እንዲያመቼው መንገድ የከፈተለት በግፍ እንደወንጀለኛ እየታሰሩ ወደ እስር ቤት በመጣላቸው ስለሆነ ባስቸኩዋይ የልቢያ መንግስት ያሰራቸውን እንዲፈታ። አይሰስም ክርስቲያን በመሆናቸው ወስዶ በግፍ የሞት ቅጣት የፈጸመባቸውን  ኢትዮጵያውያንንም ማን አሳልፎ እንደሰጣቸው እና እንዴትስ ለሞት ሊዳረጉ እንደተደረገ መልስ ከሊብያ መንግስት ይሰጠን በሚል ጭምር ጠይቀናል። ስለሆነም ሌላውም ኢትዮጵያዊ እና መላው ሕዝባችን ይሄንን መግለጫ ያገኘ ሁሉ ከስር ባስቀመጥነው የአምባሳደሩ እና የጉዳይ አስፈጻሚው የኢሜል አድራሻ እንዲሁም ስልክ ቁጥር በመጠቀም የኢትዮጵያ ስዴተኞች ወደ እስር ቤት መወር ወር እና በሊብያ ፓሊሶች እና ወታደሮች እየታደኑ ለአደጋ በእስር ቤትም ይሁን በማንናውም ቦታ እንዳያጉርዋቸው የሊብያ መንግስት እንዲተባበርን በትህትና እንድታሳስቡ በአለም አቀፍ የኢትዮጵያ ስዴተኞች መብት ተከራካሪ እና ጉዳይ አስፈጻሚ ስብስብ ስም እንዲሁም በራሴ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼን አሳስባለሁ። 

የሐረርወርቅ-የኢትዮጵያወርቅ ጋሻው።
መስራችና ሊቀመንበር።


Ambassador ኢብራሂም ደባሺ (Dabbashi), in New York, svc.libyamission@gmail.com
Phone # 212-752-5775.
Libyan Charge d' affairs Mr. Wafa Bugaighis in washington D.C. aujalimedia@gmail.com
Phone # 202-944-9601