20 hrs ·
፡ አሁንም ደግሜ ደግሜ የምገልጸው የመን ያለ ስደተኛ ሀገሪቷ በአየር ድብደባ እየተደረገባት በመሆኑ ስደተኛው ላይ ሊደርስ የሚችለውን አስቦ የህይወት ማዳን ተግባር ከወገኖቹ ይጠብቃል እና ኢትዮጵያዊ ነን ያላችሁ በጦርነት መካከል UNHCR ጥሎት የወጣውን ስደተኛ ታደጉት ነው ጥሪዮ፡፡ በተለያየ መገናኛ ብዙሀን እንደተናገርኩት አሁንም እደግመዋለሁ UNHCR ጥሎት የወጣውን ስደተኛ ነፍስ ታደጉት፡፡ ለጊዜው የመን ያለ ስደተኛ የገንዘብ የምግብ ወይም መሰል ችግር አልገጠመውም እና ገንዘብ አሰባስቡ ለሚሏችሁ ገንዘባችሁን እንዳታወጡ፡፡ ለበላተኛ እንዳትሰጡ፡፡ ችግር ሲኖር ወቅቱን ጠብቆ ጥሪ እናደርጋለን፡፡ ስለዚህ ጥቅማቸው የተነካ ሰዎች ሲሳደቡ ተቆጭታችሁ መልስ አትስጡ ያጣ ለማኝ ይሳደባል ነው ነገሩ፡፡ እንዲያውም እባካችሁ የሚሰድቡኝን አድንቁልኝ፡፡ በእኔ በኩል ግን ያለኝ መልስ ‹‹..ውሻ ጮኸ ብሎ የሚጮህ ቢኖር ውሻ ነው…›› የሚል ነው፡፡ እባካችሁ ለችግር ጊዜ ከተማራችሁት ስድብ ደጋግሙኝ….በስደተኛው ስም ግን ገንዘብ አዋጡ ብሎ መብላት አይቻልም!!!