Friday, April 3, 2015

ማንኛውም ድርጅት ነኝ የሚል የፓለቲካ ፓርቲነኝ ወይም አባል እና ደጋፊነን ፡ ሚዲያነን በሚል ቢቀርቡዋችሁ ገንዘባችሁን እንዳትሰጡ እናሳስባለን።

የመን ያለው የኢትዮጵያ ስደተኞች በውጪ ጉዳይ አስፈጻሚ እና አለም አቀፍ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቲ።

ጥብቅ መግለጫ እና ማሳሰቢያ፡
April 1, 2015

የመን የሚገኙትን 5000ሺ ቀደም ስንል እንደገለጽነው የኢትዮጵያ ስዴተኞች 1000 ትግሪኛ ተናጋሪ ኢዮጵያውያን ከኤርትራ የተሰደዱ ትናንትና ጨምረናቸዋል ጉዳዩ አሳሳቢ በመሆኑ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ። ሕዝቡ በስዴቱ አለም አብሮ እየተጋገዘ ነው ያለ ኢትዮጵያ ኤርትራ እያለ አይደለም። በጥቅሉ 6000 ኢትዮጵያውያን ስዴተኞችን አስመልክቶ ገንዘብ ለመላክ በሚል  ወይም ቁሳቁስ መግዣ የሚንቀሳቀሱ በተለመደው እንደተነሱ እንድናውቅ ተደርጉዋል ሕዝቡን እናመሰግናለን። ለዚህም ይፋ ያደረግንው ሁለት መግለጫዎች አንድ ከየመን አንድ ከዳላስ ለሕብረተሰቡ በፌስቡክ እና በተለያዩ መገናኛዎች በመድረሳቸው የተለመደው አወዛግቦ ገንዘብ መሰብሰብ ቦታ እንዳይኖረው እያደረገ ነው። ገንዘብ የሚጠይቃችሁ ማንኛውም ድርጅት ነኝ የሚል የፓለቲካ ፓርቲነኝ ወይም አባል እና ደጋፊነን ፡ ሚዲያነን በሚል ቢቀርቡዋችሁ ገንዘባችሁን እንዳትሰጡ እናሳስባለን። በውጪ የመን ላለው የኢትዮጵያ ስዴተኛ ወይም አረብ አገር ገንዘብ የሚሰበስብ አንድም አካል ወይም ግለሰብም እንደሌለም እንገልጻለን። ይሄንን መግለጫ የሚያወጣው ኮሚቲ ሊቀመንበር ወይዘሮ የሐረርወርቅ ነድፈው ባቀረቡት መሰረት የመን ላለው ኮሚቲ እራሱ ኮሚቲው ብቻ ገንዘብ የሚጠይቀውም የሚሰበስበውም የሚቀበልውም እንዲሆን አድርገው በመሆኑ የሁለቱም ኮሚቲ በአንድነት መስራት አንዱ ስምምነት መሆኑ ነው። ማንም ሰው ወይም ድርጂት የኢትዮጵይዊም ይሁን ይውጪ አገር ሰው፡ በየመንም ይሁን ከየመን ውጪ በስዴተኛው ስም ገንዘብ ሲቀበል ወይም ሲሰበስብ ቢገኝ በሕግ ያለፈውን ሁሉ ገንዘብ በማስረጃ በማቅረብ ብሎም በምስክር ገንዘቡን የወሰዱትን እያንዳንዳቸውን እንደምናደርግ እንደሚጠየቁበት እናሳስባለን። ድንገት የድርጅታቸው አባል በመሆናችሁ አዋጡ ቢልዋችሁ እና ብታስረክቡ ገንዘባችሁን እኛን ወይም የመን ያለውን ኮሚቲ የሚመለከት እንደማይሆን ከወዲሁ በግልጽ እዚህ ላይ እናስቀምጣለን። የመን ያለውን ሰዴተኛ ለመርዳት የሚፈልግ ሁሉ በግልጽ በምን መንገድ መርዳት እንደሚፈልግ ችሎታውን ማለት አቅሙን ፡ እና ከዚህ ቀደም በተግባር ለስዴተኞች ያደረገውን ሁሉ በፊለፍት ጠይቀን አቅርቦ የሚለው ወይም የምትለው በማስረጃ ከተገኘ እና ከዚህ በፊት በሕዝብ ስም በስዴተናው ምንም አይነት ጥቅም ያላካበተ ወይም ያልወሰደ መሆን እንዳለበት ከወዲሁ እናስታውቃለን። ዝምብሎ እረዳለሁ ብሎብቻ ስሙን በሚዲያ ካስታወቀ እና እራሱን እና ድርጅቱን አንጸባርቆ በመጨረሻም እጄን አንስቻለሁ የሚለውን ወይም የሱን አይነት አንቀበልም መክኒያቱም ሰው ባጋጣሚ እንደ የመን አይነት ቦታ ስላለ ነብሱ መጫወቻ ስላልሆነ ወይም መቀለጃ መነገጃ፡ እራስን ማስተዋወቅያ። ግልጽ እና ሃቀና ኢዮጵያዊ ብቻ ነው ወገኑን ለመርዳት እንዲተባበር የሚያስፈልገው ይሄውም በኮሚቲያችን ስር።

ገንዘቡ ሲያስፈልግ በቅርብ በየመን መረጋጋት እንደመጣ በሶስተኛ እጅ በስመአበሎ ሳይሆን በቀጥታ ከሕብረተስቡ ከአለም ዙርያ የመን ላለው ለስዴተኛው ኮሚቲ ለባለጉዳዩ ገንዘቡ የሚላክበት የተለመደው ለምሳሌ ከአሜሪካን እንድ እዌስተርን ዩንየን እና መኒግራንት ብሎም ከባንክ ወደ ባንክ ስራውን እስኪጀምር ድረስ በስዴተኛው ስም ገንዘብ አዋጡ ብሎ የሚጠይቃችሁ ብቅ ቢል ትናንትና እና ዛሬ እያደረጉ እንዳሉት በፌስቡክክም ዳርዳር እንደሚሉት በመልክተኞች እና እራሳቸው ሌላ ሰው ደጋፊዎቻቸው እያስመስሉ ስለሚመጡ እንዳትሞኙ፡ ገንዘባችሁን ጠበቅ አድርጋችሁ አስቀምጡ ለስዴተኛው እና ለልጆቹ እንላለን።

ከአክብሮት ጋር
ለማ ክብረት
ሕዝብ ግንኙነት።

Press Release Dallas Texas U.S.A
by Yeharerwerk Gashaw
Ethiopian Refugees' In Yemen Advocate Group USA
ግልጽ መግለጫ።
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለስዴተኛው ከልብ ለተቁውርቁዋሪው።
በአሜሪካን አቆጣጠር ማርች 29፡ 2015
Dallas, Texas USA
ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ ከድካም እና በተለይ በተለያየ ቦታው ያለውን ኢትዮጵያዊ ስዴተኛ ጉዳይ የምሰራው ብዙ በመሆኑ አንዳንዴ ሲበዛብኝ በምጽፍበት ጊዜ ቃላቶች ሊዛነፉ እና ፊደሎት ሊጉድሉም ስለሚችሉ የማቶክረው መልክቱ ላይ እና ዋናው ቁምነገሩ ላይ እንጂ ቃላቶችን ማሳማር ላይ ስላለሆነ ስህተት ካያችሁ ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ። የማደርገው ሁሉ መተባበር ለገንዘብ ወይም ለግልጥቅም እንዳልሆነ እና ምንም አይነት የግልጥቅም ከድካም በስተቀር እንደማላገኝ ነገር ግን አምላክን እና ኢትዮጵያን አገልጋይ ብቻ መሆኔን በግልጽ ላስቀምጥ እወዳለሁ። ጊዜው ለወገን ቀኝ እጅ መሆን ምንጥቅም ቢኖረው ነው ወይም ጥቅም ስለሚገንበት ነው የሚል አባባል የተለመደ ሆንዋል ። መክኒያቱም ለጥቅም ስዴተውንም የአገሪቱንም ጉዳይ መነገጃ መኖሪያቸው ብዙዎቹ ስላደረጉት አልፎ አልፎ ደግሞ የዛሬ መቶ አመት እንደነበሩት አይነት ኢትዮጵያውያን ብንኖርም ልቆ የሚታየው አጭበርባሪው በመብዛቱ በመሆኑ። ሃቁን በማስቀመጥ አምናለሁ።
ይሄ ኢትዮጵያን ሪፊጂስ ኢን የመን አድቮኬት ግሩፕ ዩ ኤስ ኤ የጀመርኩት።
በአመሪካን አቆጣጠር ማርች 30፡ 2004 ከየመን የነበሩትን ስዴተኞች ባሕር ሃይሉን እና ሲቪሉን ወደ አሜኢርካን ለማስገባት ጉዳይ የሚያስፈጽም ኮሚቲ በማስፈለጉ የተቁዋቁዋመ ነበር። ከዚህም በታች የምንገልጸውን ጉዳይ አስመልክቶ በወጪ የሚደረገውን የስዴተኛውን ጉዳይ ማስፈጸም አስመልክቶ በዚሁ በአሜኢርካን ፡ በጄኔቫ በየመን በሰራው ስም የሚከናውን ይሆናል።
ከላይ ያለው ግሩፕ እንዴት እና ለምን እንዲቁዋቁዋም በጊዜው አስፈለገ አሁን ከዚህ በታች የማስቀመጠው ኮሚቲ አስፈላጊነት እና ጥቅሙ ባለጉዳዮቹን የራሳቸው ጉዳይ ተከታታይ የማድረጉ ጥቅም የጉዳያቸው ባለቤትንት አስፈላጊነቱን ሰሙኑን ጊዜ ሲፈቅድልኝ አስረዳለሁ።
የዚህ መግለጫ ዋና አላማ በየመን የሚገኙት ወገኖቻችን የኢትዮጵያ ስዴተኞች ካሉበት ከየመን ወደ አራት አገሮች የመሄድ ዘላቂ እድል እንዲኖራቸው ለማድረግ በየመን 4000 ስዴተኞችን ጉዳይ ለማስፈጽም ፡ የመንን በአሁን ጊዜ አስመልክቶ አምላክ የተመሰገነ ይሁን በስዴተኝነቱ እሳት ቀልጠው በፈተናው በመከራው ከተፈተኑት መሃል ወንድማችን አቶ ግሩም ተክለሃይማኖት ይገኝበታል። እሱም ቀደም ሲል ያቁዋቁዋመው ኮሚቲ የመን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ስዴተኞች ባለቡት የመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ቅርንጫፍ ኮሚቲ እንዳለው ልረዳ ችያለው። ስለሆነም የተረሱትን 19 የቀድሞ ባህር ሃይል ባልደረቦች ጉዳይም በ4000 የስዴተኞች ጉዳይ ውስጥ በማጣመር በአንድ መሃከለኛ ኮሚቲ ስር ተባብረን አብረን ልንሰራ በእኔም በባህር ሃይሉ ባልደረቦች ከሲቪሎቹም ከአቶ ግሩምም ጋር በመነጋገር ተስማመተን ትግሉን ወይም ስራውን መጀመራችንን እገልጻለሁ።
በዚህ አጋጣሚ መግለጽ የምፈልገው የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ዓለም አቀፍ ማህበር የመን ያለውን መለዮለባሽ አስመልክቶ የሚያስፈልጉ እርዳታዎች ስለሚጠበቀበት መረጃዎችን አስመልክቶ እስፓንሰርም የሚጠይቀውን ለማሙዋልት ይረዳ ዘንድ እንደሚተባበር ሙሉ ቃል ገብትዋል። ይሄ ማህበር ዋና ዓላማው የተጣመመውን የቀድሞውን ጦር ሃይሎች ታሪክ በሃቁ ለመጪው ትውልድ ተጽፎ እንዲተላለፍ እና ሌላው በእየአገሩ በስዴተኝነት እስካሁንም እየተንከራተተ ያለውን መለዮለባሽ የባህር ሃይሉን ጭምር ወደ ተሻለ አገር እንዲገባ የሚሰራ ሲሆን ይሄንን ክፍል እንድመራ በአምባሳደርነትም ድርጅቱና መለዮለባሹ ስለጣለብኝ የዜግነት ግዴታ እና እምነት በጣም አመሰግናለሁ። ይሄ ማሕበር ሲቁዋቁዋም በቀደሞው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ስም የመጀመሪያው ሕግ ተመዝግቦ ትልቅ ሚና እያደረገ ያለ ብቸኛው ማሕበር ነው በ25 አገሮች እውቅና በዛሬ ጊዜ ተሰጥቶት ጉዳይ እያስፈጸመ ያለ። በበለጠ ለመረዳት ዌብ ሳይት ተመልከቱ።
ቀጥሎም የቀደሞው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አሶሴሽን በሚል የሚታወቀው አባላቶቹ የመን ላሉት ለ19 የባህር ሃይል ባልደረቦች እስፓንሰር እስከመሆን ድረስ እንደሚተባበሩ ሃሳብ አቀርበዋል በእኔ በኩል እነሱንም በጣም አመሰግናለሁ በዚህ አጋጣሚ።
ከየመን ከመጡት ውስጥም በላስ ቪጋስ በኩል ያሉት ሙሉትብብር እንደሚያደርጉ በትናንትናው እለት አስታውቀውኛል።
በመጨረሻም የስዴተኛው ጉዳይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚመለከት ስለሆነ ፡ በየጊዜው ወንድማችን አቶ ግሩም ሲያቀርብ በነበረው ያልተነካ አልነበረም ካነበብኩት ስለሆነም እቀጥታ እያንዳንዳችሁ በዚህ ጉዳይ ገብታችሁ ከባለጉዳዮቹ ጋር ከአቶ ግሩም ጋር በመነጋገር የምትሰሩት ወይም የምታደርጉት አስተዋጽዎ ይኖራል። በመሆኑም ለወገን በመድረሳችሁ ያለሶስተኛ እጅ ወይም ሁለተኛ እኔንም የማይጨምር ማለት የምታደርጉት እርዳታ ለዝለአለም የሚያስደስታችሁ እና ምናልባትም በህይወታቸው የመጀመሪያው ስለሚሆን ስሜቱን በገንዘብ የማይገኝ ደስታውን ምንያህል ከውስጣችሁ እንደሚያለመልማችሁ ትገነዘባላችሁ። ለሁሉም አምላክ እንደሚረዳን እተማመንበታለሁ።
ከየመን ከስዴተናው ኮሚቲ እራሳቸውም መግለጫ ስለሚያወጡ በቀጥታ እንዴት እንደምታገኙዋቸው ይሰልክም ይሁን የኢሜል አድራሻ ታገኛላችሁ። ወንድም ግሩም ተክለሃይማኒትን፡ ወንድም መስፍን ባዩን፡ ወንድ ልኡልሰገድ አውጋቸውን ወንድም ጥላሁን እና ሌሎቹንም ጥይት በጆራችሁ ላይ እየተርዋርጠ የኤርፕሌን ድብደባው ወደ ሁዋላ ስታትሉ በቆራጥነት ሌት ተቀን ከእኔጋር በስልክ በመነጋገር መብራት በጠፋ ቁጥር ጭምር ያለባችሁን ስቃይ ስለተገነዘብኩኝ በእውነት የናንተ ጠንካራነት እኔን የበለጠ ስለጉዳያቸው ወገቤን አሰር አድርጌ የሚደርስብኝን ሁሉ ተቀብዬ በተለመደው እኔ ለጥሩ ስነሳ ተመሳሳይ ኮሚቲ እየፈጠሩ እኔ ለማዳከም የሚጥሩትን ትቼ ጉዳያችሁን ያለኝ አምላክ የሰጠኝን የአይምሮ ጠንካራነት ጉልበቴን በበለጠ እንድጠቀምበት እንዳነሳሳኝሁኝ እንድትውቁት እና ምስጋናም አቀርባለሁ ስለሁሉም በዚህ በሶስት ሳምንት ውስጥ ባሳለፍነው እናተ በየምን ምድር እኔ በአሜኢርካን ፕሌኖ ቴክሳስ ብሎም ዳላስ። በበኩሌ እዚህ ላይ አጠቃልዩ የሚቀጥለውን የስራውን ጅምር ይዤ እስካገኛችሁ ደህና እደሩልኝ መልካም የእሁድ ምሽት ይሁንላችሁ። ለዚህ መግለጫ ተጀምሮ መፈጸም እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ።