Friday, April 3, 2015

የመን በሚገኘው ስዴተኛ ስም ገንዘብ ከማንኛውም አገር ከተማ ውይም ቦታ ብትጠየቁ ገንዘብ እንዳትሰጡ እናሳስባለን።

የመን ያለው የኢትዮጵያ ስደተኞች በውጪ ጉዳይ አስፈጻሚ እና አለም አቀፍ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቲ።

ዳላስ ቴክሳስ ዩኤስ ኤ።
April 3፡ 20015 በአሜሪካን አቆጣጠር።

ይድረስ መልክታችን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ።

የመን በሚገኘው ስዴተኛ ስም ገንዘብ ከማንኛውም አገር ከተማ ውይም ቦታ ብትጠየቁ ገንዘብ እንዳትሰጡ እናሳስባለን። ገንዘቡ በቀጥታ ለስዴተኛው የሚደርስበት የራሱ ኮሚቲ አቁዋቁሞዋል። በውጪም ከየመን የሚወጣበትን መንገድ እና ለመብቱ የሚታገሉለትን ወይዘሮ የሐረርወርቅን ጋሻውን ወክልዋል። ወይዘሮ የሀረወርቅ ጋሻው ለኢትዮጵያ ስዴተኞች መብት ያልተቁዋረጠ መታገል ሲያደርጉ ብቸኛዋ ናቸው። ስዴተኛው ወደ አሜርካን ካናዳ ሲውዘርላንድ፡ ፈረንሳይ ፡ እንግሊዝ አገር እና በሙርከኝነት በኤርትራ እስር ቤት ከነበሩት መለዮለባሹችንም ጭምር ወደ አውስትራልያ እንዲገቡ ያደረጉ ላለፈው 33 አመት ምሉ ያለምንም የግል ጥቅም ፡ ከማንም የገንዘብ እርዳታ ሳይደረግላቸው በስራቸው ያገኙትን እውቅና መድርክ በመጠቀም ለስዴተኛው ወገናቸው ከ18 አመት እድሜያቸው ጀምረው በፓሪስ ፍራንስ እስከዛሬም ሳያቁዋርጡ ድምጽ እና ተሙዋጋቹ ሆነው በማገልገል ይታወቃሉ። ሌላው አስተዋጽቆቸው በአረብ አገር በባርነት ሲኖሩ የነበሩትን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለተባበሩት መንግስታት እና ለአለም መንግስታት በማቅረብ  በባርነት ቀንበር ተይዘው መንግስት የሚሙዋገትላቸው የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው እንዳሉ እና ፓስፓርታቸው እየተቀማ በስቅላት ሳይቀር በአረቦች ሲደርስባቸው ለነበረው የባርነት ቀንበር ግፍ እንዲጋለጥ እና ሰዎቹም ነጻነታቸውን እንዲያገኙ ባደረጉትም የማይረሳ ለወገን ደራችነት ይታወቃሉ። ስዴተናው የኢትዮጵያ ስዴተኞች እናትም አባትም በሚል ስም ይጠራቸዋል። በቅርብም ከወጣቱ ትውልድ በሚል ስዴተኞች በስዊስ የሚገኙት በፌስቡክ ፔጅ በምስጋና ሸልመዋቸዋል። ዛሬም ቀጥለውበት በየመን የሚገኘውውን 5000 የኢትዮጵያ  ስዴተኛ 1000 ኤርትራውያን እና 19 በየመን የተረሱትን የቀድሞው የባሕር ሃይል ባልደረቦች ጉዳይ እንዲያስፈጽሙ ስዴተናው በውጪ ወኪላቸው አድጎዋቸዋል። ለዚሁም ከዚህ በታች ያለውን መግለጫ ይመልከቱ።

ገንዘቡ ሲያስፈልግ በቅርብ በየመን መረጋጋት እንደመጣ በሶስተኛ እጅ በስመአበሎ ሳይሆን በቀጥታ ከሕብረተስቡ ከአለም ዙርያ የመን ላለው ለስዴተኛው ኮሚቲ ለባለጉዳዩ ገንዘቡ የሚላክበት የተለመደው ለምሳሌ ከአሜሪካን እንድ እዌስተርን ዩንየን እና መኒግራንት ብሎም ከባንክ ወደ ባንክ ስራውን እስኪጀምር ድረስ በስዴተኛው ስም ገንዘብ አዋጡ ብሎ የሚጠይቃችሁ ብቅ ቢል ትናንትና እና ዛሬ እያደረጉ እንዳሉት በፌስቡክክም ዳርዳር እንደሚሉት በመልክተኞች እና እራሳቸው ሌላ ሰው ደጋፊዎቻቸው እያስመስሉ ስለሚመጡ እንዳትሞኙ፡ ገንዘባችሁን ጠበቅ አድርጋችሁ አስቀምጡ ለስዴተኛው እና ለልጆቹ እንላለን።

ከአክብሮት ጋር
ለማ ክብረት
ሕዝብ ግንኙነት።