Sunday, April 5, 2015

የኮሚቲ ስም ዝርዝር (የመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ስዴተኞች አለም አቀፍ ጉዳይ አስፈጻሚ እና የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቲ ዳላስ ቴክሳስ ዩኤስኤ:)

                                                                                             
ይድረስ በየመን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ስዴተኞች ኮሚቲ ሊቀመንበር አቶ ግሩም ተክለሃይማኖት
እና ስለስዴተኛው ከልቡ ለሚቆረቆረው የኢትዮጵያ ሕዝብ።

 እንድታውቁት ያህል
April 5, 2015

ክዚህ በታች ስማቸው በከፊል ተጽፎ የሚገኘው፡ (በተለያዩ አገሮች የኢትዮጵያን ስዴተኞች ፡ የስዴተኛነት መብታቸው ተከብሮ ተቀባይነት እንዲኖራቸው እና ካሉበትም ከአፍሪካ፡ ከመካከለኛ ምስራቅ ወደ አውሮፓ ፡ አሜሪካን ካናዳ እናም አውስትራልያ ተቀባይነት እድኒኖራቸው ለማደርገው ትግል እንደያስፈላጊነቱ እጎኔ ቆመው የስዴተኛውን ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ጉዳይ አስመልክቶ በስራ የሚተባበሩኝ)የኮሚቲ አባላት ናቸው።  ስለሆነም በአሁን ጊዜ የመን የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ስዴተኛ ጉዳይ አስመልክቶ ወደ አራት አገሮች ተቀባይነት እንዲያገኙ በቅርብ የጀመርኩትን ተግባር አብረውኝ ለመስራት ቆርጠው መነሳታቸውን እና በጉዳዩም እኔም እነሱም በትናንትናው ምሽት ሳይቀር በስልክ ቅደም ተከተሉን የነደፍኩትን ስልት ለ5000 ሺ ስዴተኞች ይረዳ ዘንድ ባቀረብኩላቸው መሰረት ተቀብለውት እነሱም የበኩላቸውን አስበውበት ጠቃሚውን ሁሉ ሃሳብ አክለውበት ባስቸኩዋይ በኤሜል ሊልኩ ተስማምተን ስራው በእኔ ብቻ ሳይሆን በኮሚቲው ጭምር ተጀምርዋል።

ከኮሚቲው አባላት መሃል ከአቶ ነብዩ ዳምጤ የቀረበ ሃሳብ አለ ። ይሄውም ለሚመለከተው ሁሉ ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ ስዴተኛው ያለበትን ሁኔታ በበለጠ ይረዳው እንዲችል ስዴተኞቹ ያሉበትን ስቃይ ፡ ከተቻለ ከስዴተኞቹ መሃል የተወሰኑትን ቃለመጠየቅ በቬዲዮ እራሱ አቶ ግሩም እንዲጠይቃቸው ቢያደርግ ለምንሰራውም የስዴተኛውን ጉዳይ ማስፈጸም እንደሚረዳን እና እንደዚህ መከራ እንደበረዶ እየዘነበባቸው ያለውን ወገኖቻችን የኢትዮጵያም ሕዝብ ተመልክቶ እያንዳንዱ በቀጥታ ለባለጉዳዮቹ በኮሚቲያቸው በኩል በጎአድራጎት እንዲያደርግም ይረዳል በሚል አሳስበዋል።

ጋዜጠኞች።
እንደምታወቀው ታዋቂነት ያላቸው የአሜሪካን አገር እና የሌሎቹም አገሮች ጋዜጠኞች እራሳቸው ትልቅ እርዳታ ናቸው። ስለሆነም በየመን ያለውን በአቶ ግሩም ሊቀመንበርነት የሚመራውን እና እኛም የምንመራው ውስጥ በናኡስ ኮሚቲነት የሚተባበሩንን አካተናል:: ከአክብሮት ጋር
የኢትዮጵያወርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው
ሊቀመንበር።

ኮሚቲ ስም፡
የኢትዮጵያውርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው።
ዶክተር ማንከልክሎት ሃይለስላሴ ዋሽንግተን ዲሲ።
ዶክተር ጋሹ ሃብቴ አርካንሳስ።
አቶ ብዩ ዳምጤ ዳላስ ቴክሳስ።
አቶ መሰለ ከለ ዳላስ ቴክሳስ።
ዶክተር አበባ ፈቃደ ዋሺንግተን ፡ዲሲ::
ዶክተር ተዘራ ጸጋዬ አትላንታ።
ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ አትላንታ።
ዶክተር አረጋህኝ ሴፉ መንፊስ።
ወይዘሮ ንግስት ተወልድ ዳላስ።
ሻምበል አሸብር ገብሬ ዋሽንግተን ዲሲ።
ዶክተር ማ ት ዋሽንግተን ዲሲ
ሻምበል ሰለሞን ጋዲሳ ዳላስ ቴክሳስ።
ድል ያደርጋል;;
አቶ እዝራ በለጠ ላስ ቬጋስ ነቫዳ።
ውዴ አድገህ ዳላስ ቴክሳስ።
ሃይሌ ካሳ ሲዊስ።
ደምመላሽ ግርማ ስዊስ።
ጌታቸው እረዳ ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ።


የውጪ ጋዜጠኞች ኮሚቲ ስም ዝርዝር ይቀጥላል።