በዳላስ ስለተከሰተው የቤተክርስቲያናት መከፋፈልና ክስ ብሎም የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ማኮላሸት የወያኔ ተቀጣሪ በመሆን ተጠያቂ ናችሁ ይቅርታ ጠይቁ በሚል በዚህ ብሎግ ባለፈው ጥሪ በዚህ ሕዝባዊ ብሎግ ማቅረቤ ይታወሳል ። አሁንም ላላነበባችሁት ገብታችሁ እንድታነቡ አሳስባለሁ። ታዲያ እነ አቶ እንትናዬ ማነው ደጄኔና አለቆቹ የድርጅት ስም አለቀባቸው መሰለኝ ፡ ስማቸውን ቀይረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቁርቁዋሪ ነን በሚል ባዲስ ስም ይቅርታ የኢትዮጵያን ይጠይቁ የተባሉ እለት የፍጠሩት የዳልስ ፎርት ወርዝን ሕዝብን ጥሪ ኢትዮሚዲያ በሚለው ዌብሳይት ላይ አስለጥፈው መጥሪያ ላይ እራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን ቀላምደዋል ሞክረዋልም። አይ ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል የተባለው ቢጤ ደረሰ። እንክዋን ኢትዮሚዲያ ላይ አይደልም ሕዝቡ መልስ ለዌብ ሳይቱ ባለቤት አብረሃ በላይ በሚሰጥበት ፡ በሲኤን ኤን በያስወሩ ሃቁ ስራቸውንና ማንነታቸውን የዳላስ ሕዝብ ስለሚያውቃቸው ሌላውንም እንክዋን በሌላ ቦታ ሲያታልሉ የኖሩት ጭምር አክትምዋል። ስለዚህ ተፈራ ወርቅን ከሳሾች ጎራ አስቀምጠው አብሮ የኖረውን እያከፋፈሉ ባቁዋራጭ የቅዱስ ሚካኤልን ቦርድ ለመቆጣጠርና ለወያኔ ለማስረከብ መሆኑ እየታወቀ ጥረታቸው፡ ማንን ለማጭበርበር ነው በተደጋጋሚ ተፈራ ወርቅ ከኛ ጋር አይደልም በሌላ በኩል ተፈራ ወርቅ ተለውጥዋል በሚል የሚያስወሩት? ተፈራ ወርቅ ሲመጣም የወያኔ ተቀጣሪ ነው አሁንም እዛው ካምፑ በግልጽ ገብቶ አረጋግጥዋል ግዳጁን ይሄው ነው። ማንነቱም ታውቆ በቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ ቦርዱ ውስጥ አስገብተው እነፍቅረማሪያምና መንግስቱ በመረዳጃ ማሕበራችን ውስጥ የወያኔ ኢንፎርሜሽን ሴተርና ኢንቬስትመንት ኒትዎርክ እንዳደረጉት ቤተክርስቲያኑንም በዛው መልክ ፊት ፊት እየሮጠ ግባቸውን እንዲመታላቸው ለማድረግ በተወዳዳሪነት ሲያቀርቡት የነቁት ም እመናን የቅዱስ ሚካኤል ደብር አባላት እንዳይገባ አድርገውታል። ያሕዝብ ሳይመርጣቸው በመረዳጃ ማሕበሩ የሚሸገሸጉበት አልሰራም። የራሳቸውን ቆሻሻ ስራ ከሳሾቹ እራስና ትክሻላይ እነደጀኔና ከሁዋላው ፊት ፊቱን የሚመሩትና መሸፈኛ አድርገውት ወረቀት ተሸካሚ በታኝ ያደረጉት አይደሉም ወደ ፍርድ ቤት ከሳሾቹ እንዲሄዱ የሚካኤ ደብርን ለፍርድ ቤት ያዳረሱት? ማስርጃው አለእኮ።
ደጀኔ በዳላስ ፎርት ወርዝ እሱና ግብረ አበሮቹ በጣም ተሰሚነት ያላቸውና ሕብረተሰባችንን በቁጥጥራቸው ያደረጉና ሕዝቡ ተቀመጥ ስንለው የሚቀመጥ፡ ተነሳ ስንለው ት እዛዛችንን የሚቀበል፡ ገንዘብ አዋጣ ለአይን ማብሪያ ስንለውና እንደፈለግነው የሚታዘዝ ስለሆነ ዳላስ ውስጥ ስለኢንቭስትመንትና ስለፓለቲክ ጉዳይ አስመልክቶ ከኛ ጋር ብቻ ስትሆኑ ነው ሕዝቡ የሚሰማው ሬዲዮኑ በጃችን የቅዱስ ሚካኤል ደብር በጃችን በሚል አንቅሮ የተፋቸውን የዳላስ ኢትዮጵያዊ ሌላው ታጋይ መጥቶ ከሕዝብ ጋር ለመነጋገር እንዳይችል በተለመደው በፍቅረማሪይም ዘቤ ትግሉን ማኮላሸቱን ቀጥለውበታል። ስሙን እየደበቀ የሰፌድ ባርሜጣ እያደረግ ፡ እንዴት ለምንስ ለሕዝብ ጥሪ ያቀርባል ለሕዝብ የሚቆረቆር መጀመሪያ እራሱን ለሕዝብ ጉዳይ አሳልፎ የማይሰጥ፡ ሕዝቡስ እንዴት ያምነዋል ምንድነው የሚያስፈራው ዶላሩ? ደጀኔና እነ በትሩ የከተማውን ሰው እንደጎተት የሚጎተትላቸው ቢሆን ኖር ለምን እነሱ ጭምር ተቆጥረው አርባ ሰውች ብቻ ሊመጣ ቻለ በሪዲዮን ጥርተው ያውም? በግንቦት ስባት በአላቸው አስራ ሰባት ሰዎች ብቻ ናቸው የነበሩት። ከዚህ ቀደም የጴንጤው ሃይማኖት ተከታዮች በጸሎት እንጂ ለአገር በመታገል አናምንም ቢሉም ፡ ብርቱካን ትመጣለች ሲልዋቸው እነደጀኔ ወጣቶች ጊዜና የቤተክርስቲያናቸውን ሰዎች አስተባብረው ሴቶቹም ወንዶቹም በመተባበር ዝግጅቱን በሙሉ ከነወጪው ያዘጋጁ እነሱ ናቸው። የኦክላሆማውንም ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጀን ብለው ከመረዳጃ ማሕበር ገንዘብ ቢወስዱም ሃቁ ግን ሁሉን ወጪ ችለው ቫኖች ያዘጋጁትና ያገኙት እነዚያው ወጣቶ ብርቱካን የቤተክርስቲያናቸው ሰው በመሆንዋ ነበር። ደጀኔ የፓለቲካ ስራ መስራት ወይም አያውቅም ልክ እንደግብረአበሮቹ ሰው የራው ላይ ስሙን እያስቀመጠና እየወጣ ሃሳባቸውን በመቀማት አብረውት የሰሩትን እንዲሸሹት ከማድረግ ሌላ።
ከዚህ በላይ በሃቅ ያስቀመጥኩዋቸውን ጀምሬ ላስጨረሰኝ አምላክ ፊቱ በግንባሬ ተደፍቼ ስለደግነቱ አመሰግናለሁ። ከላይ ስማቸው ለተቀመጠው በዝህ ብሎግ በተለያያ ግጽ ላይ ብዙው መጥፎ ተግባራቸው በጥቂቱ የተዘረዘረ አምላክ ወደ እሱ መንገድ እንዲያስገባቸውና እንደእኔው ለሃይማኖታቸውና ለአገራቸው ብሎም ሕዝቡ ተቆርቁዋሪና የሚነግዱበትን በዳዮቹን ሁሉ የሚከላከሉለት ያንድነት ክንድ እንዲያደርጋቸው አምላኬን እማጸናላቸዋለሁ ስላምም እንዲያገኙ ውነትን እንዲኖሩ ከልቤ።