Sunday, November 14, 2010

አይ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር በዳላስ ፎርት ወርዝ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላሽ እንደ ኢትዮጵያ? የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ? የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ለማዳን በመፋለሜ? በሕዝብ ያልተመረጡ ሁለት ግለሰቦች ተፈራ ወርቅ የተባለውና ዮናስ ሊበን የተባለው እንዴት በህገወጥ ሁለት ወንበር የያዙ የቀድሞው ወታደሮችንን ባዮች፡ ባልወከላቸው የዳላስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስምና በመረዳጃ ማሕበሩ ስም ምንም አይነት ውሳኔ ወይም የውሳኔ ብለው መፈረማቸው በአሜሪካን አገርና ሕግ ወንጀል መሆኑን ተምረው ይሁን ባለፈው ሶስት አመት ውስጥ? እረ የቀድምው የኢትዮጵያ ሰራዊትን ወኔና ወንድነት ፈጽሞ አይወክሉም እነዚህ የትናየት ጉድ ነው።


ይህ ገጽ ቲኒሽ ማሻሻያ ተደርጎበታል።
በመጀመሪያ ግን ከሕዝብ የቀረበ አስተያየት እነሆ።
 ዳላስ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ብሎግ የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥና ሕብረተሰቡ ከዳላስ በተየቀው መሰረት የተከፈተ በመሆኑ ሕብረተሰቡ የሚለውንና የሚጠይቀውን ትክክለኛ ለጋራ ጥቅም የሚያገለግል አስትተየትና ምክር በሚሰጥ ጊዜ በዛመንገድ ይሄዳል። ስለሆነም አይርዘም አጫጭር ይሁን በዚህ ብሎግ የሚወጣው በተለይ መረጃዎች የሚለጠፉ ከሆነ አጭር ማብራሪያ ብቻ በመስጠት መረጃዎችን ብቻ አስነበቡ በሚል የሰጣችሁትን ገንቢ ሃሳብ በዲኤፍደብልዩ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ብሎግና በራሴ ስም ከምስጋና ጋር ተቀብያለሁ ስራም ላይ መዋል ይጀምራል።


አምላክ ምስጋና ይግባው ለዚህ ለተባረከና ለሳቀ እሁድ ያደረሰን። የከበረ ሰላምታ በእግዚአብሄር ስም  ሳቀርብ ከኢትዮጵያዊነት አክብሮት ጋር ነው።

የቅዱስ ሚካኤል ክቴድራል በጋርላንድና ችግሮቹ ቁጥር አምስት፡

ጠቅላላ ጉባኤ ሪዞሉሽን በሚል 12-23-07 ሃምሳ የማይሙሉ ግለሰቦች ስማቸውንሥማቸውን ሰጥተውናል እኛንም ከመረዳጃ ማሕበሩ ይልቅቁ የተባልነውን ተፈራ ወርቅንና ዘውገን ለመደገፍ አባልነት ዛሬ ገቡልን ያልዋቸውና ስማቸው ምንም ቦታ ባይኖረውም ሰላሳ ሺ ኢትዮጵያዊ ብዛት ባለበት የዳላስ ከተማ፤ ነገር ግን ለክህደትና ሕብረተሰብ አንድ ኢትዮጵያን ለመቁረጥ ብሎም ሕዝቡን የአንድ ሴጣን የለገሰ ዜናዊ ፍፊርማ፡እደበቃ ሁሉ ዛሬ በቅዱስ ሚካኤል ደብርና በመረዳጃ ማሕበሩ ላለው አሳዛኝ  ሁኔታ እንክርዳዶቹን ዘርተው አረሙን ግን ለብዙዎቻችን አሸክመውን ኩኩሉ የሚጫውቱት ግልሰቦች በጊዜው የዛሬ ሶስትታመት ተፈራ ወርቅ ዘውገ ከነግብረአበሮቻቸው ሊነቀሉ ሲሉ ተግል ጥቅማችው ብቻበመነሳት  አይናቸውን ጨፍነው ያለቦታቸው ገብተው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሚጎዱት ጋር በመተባበራቸው ሴቱም ወንዱም የጥፋቱ ተሸካሚ ናቸው።

እንደሚታወሰው መቼም የኢትዮጵያን የጋራ መረዳጃ ማሕበርን
በሚመለክት  የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና እንደዚህ ከሰላሳሺ በቁጥር ሳንደርስ ነገር ግን በጊዜው በ1983 በፈረንጆች አቆጣጠር፤ አራት መቶ አዲስ የመጣንና ከሃያ የማይበልጡ ደግሞ በአጼ ሃይለስላሴ መንግስት ጊዜ መጥተው እዚህ ዳላስ ፎርት ወርዝ ይኖሩ የነበሩትንም አጠቃሎ እርስ በእርስ የምንገናኝበትና ችግር ቢያጋጥመን የምንረዳዳበት በሚል፤ በትብብር ጥቂት ግለሰቦች የጀመረርነውን የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበራችንን አፍርሰው በግል ጥቅም ድርጅት በመተካት በትግሬ ነጻ አውጪ የጉዳይ ማስፈጸሚያና በኢንቪስትምንት ኒያላ ኢኝሹራንስ (ጋሻ ኢንሹራንስ-እድር)ሊተኩትና ሳምንታዊ የአንድ ሰአት የሬዲዮን ስርጭቱንም በጥቅም ተጋሪያቸው ስም በማድረግ ሕዝቡን ወይም ግለሰብ ኢትዮጵያውያኖችን ያገባኛል ብለን ፈጽሞ ልንጠይቅ በማንችልበት መብታችንን ሁሉ ዘግተው፤ ተፈራ ወርቅ በሕዝብ ያልተመረጠው የጋራ መረዳጃ ማሕበሩ ፕሬዘደንት ነኝ ብሎ አምስት ግብረአበሮቹን ከመረዳጃ ማሕበሩ አስተባብሮ በድምጽ ብልጫ ሌሎቹ ሶስቱ ሳያውቁ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን የግል ጥቅምና ታክስ ነጻ ድርጅትነቱን አፍርሰናል በሚል ጽፈው በማስገባት ሊፈጽሙት የነበረውን ግባቸውን ለመምታት ሲሉ ደርሼባቸው የፈልጉትን ቢደነፉም ላቆማቸው ችያለሁ  በእውነተኛ አምላክፍቃድ። ማየት ማመን ነውና እስቲ ከላይ ለወሰድኩት እርምጃ መልኩን አስቀይርው ጠቅላላ ጉባኤ በሚል ስም የፈረዱብኝንና የፍየል ወጠጤ ያዘፈኑብኝን የፍርድ ገምድልና የካንጋሩ ፍርድ ቤት ዳኖችና ፍርድ ማሕበሩና ሬዲዮን ዝግጅቱን እናድን በሚል የታገልኩዋቸውን የጉዳዩን ዜግነት ውነቱን ለውጠው ያቀረቡትን ተመልከቱ። ሬዲዮን ዝግጅት ካዘጋሁባቸውና ቴረሪስት ብዬ ፍርድ ቤት ከከሰስክዋቸው  ለምን በፍርዳቸው በጽኍፋችው አልጨምሩትም ምስክር ሆኖ እንዳያስወነጅላቸው ፍረተው ነው?  ለመሆን ውሸቱ ምኑነው? ተፈራ ወርቅና በትሩ የኒያላ ኢንሹራንስ የትግሬ ነጻአውጪ ኢንቬስትመንትና መረጃ መሰብሰቢያ መስራታቸው? አዎን እንሰራለን ታዲያ ምንይጠበስ ያሉት በጉልበት በወረሱት ሪዲዮ ስርጪት? የት ፍርድ ቤትነው የተከሰሱት? የፍርድ ቤት መጥሪያ ነው አለን ያሉትስ በሬዲዮ በጊዜው እንዴት ሶስት አመት ፈጀ መቼ ይሆን ለዋሹት ሕዝብ የሚያቀርቡት?

ከዚህ በታች የወያኔ ቅጥረኞች የሌለ ክስ ያልተከሰሱትንና ያልተባሉትን ያልተደረገ እንደተፈጸመባቸው በማድረግ  የዳላስ ንዋሪ ሳያውቅ የሕዝብ የቅዱስ ሚካኤል ደብርን ሲበዘብዙና ወያኔን ለማስገባት ውስጥ ለውስጥ ስር ሲዘረጉ ይሄንንም ለማድረግ የተጠቀሙት የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ቦርድ ውስጥ በከተማው በቆዩ ልጆቻቸውን ባጋቡ ስልጣንና ገንዘብ በጠማቸው ሁለት ግለሰቦች አማካይነት ነበር። ሆኖም በግዳዩ ደርሼበት ለሕብረተሰቡ በስሙና በሃይማኖቱ የሚደረገውን ደባ እንዲያውቅ በማድረጌ እነሆ ከዚህ በታች ያለው ፍርድ ተፈርዶብኝ ነበር ከሶስት አመት በፊት። በማን? በወያኔ ተቅጣሪዎችና በወያኔ የካንጋሩ አመራር መሰረት ነገር ግን እዚህ የምኖርበት ዳላስ ቴክሳስ። በዚህ አጋጣሚ መግለጽ የምወደው እነዚህ ሰዎች ሌላም ወንጀል ማለትም ለኢትዮጵያ ስዴተኞች ተከራክሬና በሃቅ አሳምኜ ያስፈቀድኩላቸውን የሬፉጂ ቪዛ በመሸጥ የሚኖሩና ቤተሰቦቻቸውንም በዚሁ መልክ ገንዘብ በመክፍል ካንድ ሳምንት ባልበለጠ ጊዜውስጥ ከአዲስ አበባ ኬኒያ ካስገብዋቸው በሁዋላ ወደ አሜሪካን ዘመዶቻቸውን ያስመጡትም "እኛ ተከሰናል ልታሲዘን ስለሆነ ስብሰባ ስንጠራችሁ ኑና ስለኢትዮጵያ ሕዝብ አያገባትም ብላችሁ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ በሚል ከፈረድንባት ፈርታ ትተወናለች አለበለዚያ ግን እናንተም ዘመዶቻችሁም ሁሉ በአሜሪካን ፍርድ ቤት አለቀለን" ባልዋቸው መስረት ግለሰቦቹም አይናቸውን ጭፍነው ተስማምተዋል ከዚህ በታች በተወሰነው የመሸታ ቢት ፍርድ ቤት ፍርድ በሚል ስማቸውንም አያይዘው ከላኩትን እኔ ለመረዳጃ ማሕበርና ሬዲዮኑን ስርጭቱን ለማዳን ያደረኩትን የሰለጠነ የሁለት የወያኔ ቅጥረኞች ከድርጅታችንና ከሬዲዮን ስርጭቱ ይልቀቁ ጥያቄ ተመልከቱ። በነገራችን ላይ እነዛ ባንድነት እኔን ሊያጠፉ ወይም ዝም ሊያሰኙ የሚችሉ መስልዋቸው በግል ጥቅማቸው የገመድ ጨዋታ ይጫወቱ የነበሩት ፡ ገመዱ የቱሻ ገመድ ለግድግዳ አገር ቤት ቤት ሲሰራ የምንጠቅምበት አይነት በመሆኑ ትብብራቸው፡ ዛሪ አንድ ቦታ አይደለም አምስት ቦታ ተበጣጥሰው እርስ በእርስ እየተኮናነኑና እየተገፍፈጡ ሲሆን  ውነቱን የያዝነው ግን አይ ውነት አንቺ አሸናፊ የሴጣኖች እመቤት እያልን እንስቃለን። በሌላ በኩል የሕብረተሰብ ተሙዋጋች ኮሚኒቲ አክቲቪስት ለሚኖርበት ሕብረተሰብ ጎጂም ይሁን ጥቅም የሚያገኝበትን ይሙዋገታል ያሳውቃል እኔም ያንን አድርጌአለሁ የቅዱስ ሚካኤልን ደብር እናድን ሊወስዱት ነው ስል የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርንና  የሬዲዮ ስርጭቱን እናድን ስል ሁሉንም ከትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች ያወንጀል አይደለም። አክቲቪስቶች ሕዝብ መርጦን ሳይህን ሕዝባችን ወይም የምንኖርብት ሕብረተሰብ ሲበደል ተሰሚነት ባለው ዴሞክራቲክ በሆነና በተለይ ታዋቂ የሆንን ሰዎች ድምጻችን ከሚጨቆነው ሕብረተስብ መሃል ስንጮህ ስለምንሰማ ሕዝቡን አስተባብረንና በየቤቱም ሆኖ የራሱን መብት የሚያስከብርበት መል እክት እናስተላልፋለን።

በዚህ ደብዳቤላይ በጌዜው የፈረመው በማንም ያልተመረጠና የጋራ መረዳጃ ምርጫ ቀን በቦታው ያልነበረ ሕዝቡ ሊመርጥ እንክዋን በቀኑ የነበረው የማያውቀ በሕግወጥ መንገድ ዝም ብሎ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት እሱ ምክትል አቶ ወይም ወታደር ኮሎኔል ዮናስ ሊበን በሚል ምክትል ፕሬዘደንት ተብሎና አቶ ወይም ወታደር ብሎም ሻለቃ ተፈራ ወርቅ የተባለው ፕሬዘደንት ተብለው ማንም ያልመረጣቸው ሲሆኑ ዮናስ ሊበን ስሙን በማን አለብኝነት ከዚህ በታች ስሙን ያስቀመጠው ባልተመረጠበት የመረዳጃ ማሕበር ፍሮድ ሕገወጥና ማጭበርበርን ከማስፋፋቱም ሌላ በመሃበራችን ውስጥ የመረዳጃ ማሕበሩ አባል በሆንኩት ላይ አባል ያልነበሩ ግለሰቦችን አባልናቸው ብሎ በዛኑ እለት ፎርም ሙሉ ብሎ በማስሞላት ግለሰቦቹን አባል ስለሆንን ዛሬ በሚወሰድባት እርምጃ ስማችንን በማስቀመጥ መስማማታችንን በውሳኔው ስማችንን በማያያዝ እናረጋግጣለን የሚል ሕገ ወጥ ስራ በመሆኑ በሕግ የሚያስቀጣው ወንጀል ፈጽምዋል (ጉዋድኞቹምስድስቱ የቦርድ አባልላት  ፈጽመዋል). ከወንጀሉ ንጹህ የሆኑት አቶ ንጉሴ ጋረድ ፓስተር ፈርኦንና አቶ ውድነህ ሲሆኑ ቀደም ብላ ከቦርዱ የለቀቀችው አልፈልግም ብላ ወይዘሪት የኔነሽንም ከሕገ ወጡ ስራ ነጻ ነች።

ይችን ሃቅ ለሕዝብ እንዳካፍል እድሜና ጤና ለሰጠኝ ደግነቱ ወሰን የሌለው አምልካ ይመስገን። በራስ ወዳድነትና በገብጋባነት፡ አገርን ወገንን በገንዘብ በሚለውጠው ልክስክስነት ልክፍት ብሎም መርዛው የያዘውን ሁሉ አዋራጅ በሽታን ታጋይ እንድሆን አይምሮዬን በእግዚአብሄር መንገድ ብቻ እንድሄድና በንጹህ ሰርቼ ባቅሜ መኖርንም ልቤ ውስጥ ስላስቀመጠልኝ ንጉስ የፈጠረኝ አምላኬ የአለም መድሃኒት የማያልቅ ምስጋናና ክብር ይድረሰው። አስጀምሮ ይችን ደብዳቤም ላስጨረስኝ ፍቃዱ ደግነውና እፊቱ በግንባሬ ተደፍቼ አመሰግነዋለሁ ።