Thursday, May 21, 2015
ወይዘሮ ዊንዲ ሸርማን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ ደብዳቤ አቀረብን። (Wendy Sherman)
ከኢትዮጵያ አንድነት የሕዝብ ድምጽ ምክር ቤት
አጭር መግለጫ።
ወይዘሮ ዊንዲ ሸርማን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ ደብዳቤ አቀረብን።
(Wendy Sherman)"Ethiopia is a democracy that is moving forward in an election that we expect to be free, fair and credible and open and inclusive in ways that Ethiopia has moved forward in strengthening its democracy. Every time there is an election it gets better and better."
መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ እና አሜሪካን ዜግነት ያለውን ጭምር ወይዝሮ ዊንዲ ሸርማን ይቅርታ ይጠይቁ በሚል ጥያቄ በደብዳቤ ቀርቦላቸዋል በትናንቱ እለት። ደብዳቤውን ያቀረብነው የኢትዮጵያ አንድነት የሕዝብ ድምጽ ምክር ቤት (የኢትዮጵያ ብሄራዊ የስዴት መንግስት)በሚል የሚታወቀው ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ሴቶች ለሰላም እና ዴሞክራሲ የመጀመርያው ድርጅት በአሜሪካን በሕጋዊነት በ1986 በአሜሪካን አቆጥጠር በዳላስ የተቁዋቁዋመው ሲሆን የአሜሪካን ሲቪል ራይትስ ሙቨመንት ድርጅትን በተለመደው በማስተባበር ነው። ደብዳቤውን በሁላችንም ስም ወስደው ያቀረቡት በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ሶስት የሲቪል ራይት ሙቨመንት ድርጅት ተወካዮች ማለትም አፍሪካን አሜሪካን እና የድርጅታችን አባል ንዋሪነታቸው በዲሲ ናቸው። የሲቪል ራይትስ ሙቨመንት መሪዎቹ ለረጂም ጊዜ በኢትዮጵያ የእኩልነት እና ዴሞክራሲ መንግስት እንዲወለድ አብረውን በመስራት የሚታወቁ ናቸው።
አክለንም 6 ጥያቄዎች አቅርበናል ይሄውም በወይዘሮ ዊንዲ አማካኝነትን የሚፈጸሙ ባስቸኩዋይ በሚል። የፓለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲለቀቁ ቀጥሎም በከተማ ልማት ስም ገበሬውን እና ንዋሪውን እያስነሱ ሜዳ ላይ ሲጥሉት ከእነልጆቹ ፡ አላስችል ብሎት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የወያኔን የመንገድ ልማት አልቀበልም ባለው ከሕዝቡ አብራክ በወጣው ተማሪላይ ኦሮሞነህ ተብሎ የተደረገውን የግፍ ግድያ ወንጀል መሆኑን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማይረሳው በመግለጽ ፡ ከሞት ተርፈው በእስርላይ የሚገኙት ወንጀለኞች ሳይሆኑ ፡ እራሱ ወያኔ የኦሮሞ ክልል ብሎ ባሰመረው ወሰን ላይ ብቻ ተመርኩዘው ለገበሬው እና ለአካባቢው ንዋሪ ለሆነው ፡ ለወለዳቸው እና ላሳደጋቸው ሕዝብ መብት በመቆማቸው፡ በግፍ መሬታቸው አይነጠቅም ማለታቸው እንደወንጀል ተወስዶ የታሰሩ በመሆናቸው ይለቀቁ ባስቸኩዋይ የሚል ይገኝበታል። ኢትዮጵያ በሃቀኞች ልጆችዋ በአንድነትዋ ተጠብቃ ለዘላለም ትኑር። ትግሉ ቀትልዋል!
ሊቀመንበር
የኢትዮጵያወርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው።
http://www.bbc.com/news/world-africa-32804267?SThisFB&fb_ref=Default