Worldwide Ethiopian Refugees' Rights Advocate Group USA
Dallas, Texas USA (Founded in September 15, 1983 in Dallas, Texas by Actress & Human Rights Activist Yeharerwerk Gashaw
Phone # 214-642-0394
email: yehar9@aol.com
መግለጫ እና ማሳሰብያ
ከሊቢያ የታሰሩትን ብናስፈታም : ከሊብያ መንግስት ጋር አሁንም ቀጥሎ እየተሰራ ያለ ስዴተኛውን ወገናችንን የሰው ልጅ ክብር እና መብቱን ለማስጠበቅ ያላለቀ እናም ቀጣይነትም ያለው በመሆኑ ጥረት እየተካሄደ በመሆኑ አንዴ ሁኔታዎች እስኪቁዋጩ ፡ አንድ ጉዳይ አስፈጽሞ ዞር ማለት ሳይሆን ፡ የዲፕሎማስይ ግንኙነት ሕዝባችን እንዲኖረው ጠንካራ ስረመሰረት መጣል አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ይሄውም በአረቦቹ መሪዎች እና በባለስልጣኖች አካባቢ። የአንድ አገር ሕዝብ ወይም ፓሊስ ሰዎችን የሚያከብረው ወይም የሚጎዳው የአገሩ መንግስት የተባለው በሚሰጠው መመርያ ነው እንደሚታወቀው።
ስለሆነም ለሊቢያ መንግስት ፡ አምባሳደር እና የጦር መኮንኖች እና ባለሌላ መእረጎች ጭምር ስላደረጋችሁት መተባብር እና ግብጽንም አስተባብራችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ባለፈው ታስረው የነበሩትን እንዲፈቱ ስለረዳችሁ ሁላችሁንም እናመሰግናለን። ይሄውም በኢትዮጵያውያን እና በሊቢያ ሕዝብ መሃል አዲስ መቀራረብን የሚከፍት መእራፍ ነው ብለን እናምናለን።
በመጨረሻም ፡ እላይ ከፍ ብሎ ስሙ የሚገኘው ድርጅት እና ኮሚቲው በጠየቀው መሰረት፡ ጊዜያዊ መታወቅያ እና የይለፍ ወረቀት አሁንም በሊብያ ለሚገኙት ለቀሩት የኢትዮአጵያ ስዴተኞች እንዲሰጣቸው እንደምታደርጉ ተስፋ እናደርጋለን። በሚል ብትጽፉ ሕዝቡ እራሱ ለሕዝቡ ሲቆም እራስን አክብሮ ማስከበር በመሆኑ አስፈላጊነው።
በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ ወገኖች ኮሎኔል ጋዳፊ በይፋ ጋብዘውኝ ለአፍሪካ አንድነት ታጋይነቴን መነሻ በማድረግ ብሎም ድራግ አፍሪካ አያስፈልጋትም በሚለው አለም አቀፍ ዘመቻዬ፡ ዛሬ በዚህ ፌስቡክም ላይ ያላችሁት ወንድሞቼ ለረጅም ጊዜ የማውቃችሁ ስህተት ነው ግብዣውን ያለመቀበልሽ ብላችሁኝ ነበር። አንዴ ብሳሳት እንዴት አራት ጊዜ ልሳሳስት እና ግብዣቸውን ወድቅ አደርጋለሁ? ኢትዮጵያን የሚጎዳ የመላው አፍሪካን ነገር ግን የአረብን አዲስ ትውልድ አንገቱን ቀና አድርጎ የሚያኮራው ብቻ በመሆኑም ጭምር ነው። ሆኖም ያሁሉ ዶኩመንቱ አሁን ለስዴተኛው ጉዳይ ጠቅምዋል። ይሄውም ተቀባይነቱን በሊብያ ሽግግር መንግስት በኩል ቶሎ ለማግኘት እና እምነትም ለመጣል ከማስቻሉም በላይ ፡ እንደሚታወቀው ይሄ በግማሽ ጎኑ የቆመው መንግስት ትልቅ እርዳታ ይፈላግል ። በተለይም የአሜሪካንን ኮንግረስ አስመልክቶ የመን የምትፈልገው ወይም የሽግግሩ መንግስት የሊብያን ሰራዊት በጦር በደንብ ማስታጠቁ ላይ እርዳታ ነው። ችግራቸውም የሚፈታው ሊብያም ሰላም ልታገኝ የምትችለው ጎረቤት አገሮችም፡ ሊቢያ ወታደሮችዋን በደንብ እንደገና ገንብታ ግብዋን ስትመታ ብቻ በመሆኑ እግቡ ለማድረስ የጀመሩትን አሜሪካን የተጠየቀችውን እንድታሙዋላ ተቀባይነት እና ተሰሚነት ያላቸውን ግለሰቦች ፓለቲካ አክቲቪስቶችን የሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎችን እናም በሞያቸው በአሜሪካን ፡ በአውሮፓ በተለይ ትልቅ እውቅናን ያገኙን ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ ። ስለሆነም እነሱ ወገኖቼን ከረዱልኝ እኔም በኮንግረስ በዋይት ሃውስ እናም በሴነት ጭምር በተገኘው እተባበራለሁ። ጋዳፊን ደጋፊብሆን ኖሮ ወይም የነደፉት የአፍርካ ወጣት ትውልድ ፕሮግራም ይዤ አለም አቀፍ ሊቀመንበርነቱን ተቀብዬ ቢሆን ኖሮ፡ 0 ቀርቼ ነበር ወገኖች ዛሬ የገቡበትን መከራ በሊብያ አስመልክቶ። አምላክ ንቁ ስላደረገኝ በሚያሳየኝ በትክክሉ መንገድ እንጅ ፡ ብዙዎች በሚያዩት ስህተት መንገድ ስለማልሰለፍ ለገንዘብም ሕሌናዬን እና አፍሪካን ስለማልሸጥ ፡ ክትዮጵያዬንም አሳልፌ ሳላስደፍር ለኢትዮጵያ እና ለተቀረው የአፍሪካ ሕዝብ የሚጠቅመውን ብቻ ስለምደገፍ አማልክን አመሰግነዋለሁ። በመጨረሻ ገንዘብ እና መሰሪ ስራ በተለይ ኢትዮጵያ ላይ የፈጸሙት እራሳቸው ኮሎኔል ጋዳፊንም ይሁን ሳዳም ሁሴንን አላስከበራቸውም በሚያሳፍር ሁኔታ ከመሞት ይልቅ ። እኔስ የአጼ ቴዎድሮስን እጣ እና ጽዋ መጠጣቱን እመርጣለሁ ሁሌም ፡ ለምን ዘለዓለማዊ ክብር ነው ለሌላው መድማት እና መሞት።
ምስጋና መላኪያ ኢሜል አድራሻ እንደሚከተለው ነው።
Ambassador ኢብራሂም ደባሺ (Dabbashi), in New York, svc.libyamission@gmail.com
Phone # 212-752-5775.
Libyan Charge d' affairs Mr. Wafa Bugaighis in washington D.C. aujalimedia@gmail.com
Phone # 202-944-9601
ከምሳጋና ጋር፡
የኢትዮጵያውርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው
የተግባር አቀነባባሪ እና ሊቀመንበር።
መግለጫ
የመን ያለውን ኢትዮጵያዊ ስዴተኛ ለማውጣት የወጣውን ፐቲሺን እና ሊቢያ የታሰሩትን ለማስፈታት የተደረገውን ጥረት ሳቦታጅ ያደረጉ ድረገጾች መግለጫ
ቁጥር አንድ።
ቁጥር አንድ።
የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዲያሳትፍ አስበን ያወጣንውን መግለጫ ቀደም ሲል ፡ በግል ጥላቻ እና በፓለቲካ ልዩነት ላይ ቂም በቀል ይዘው በአድማ የወገኖቻችንን ድምጽ አፍነው በተለመደው ያላወጡትን ድረገጾች እናም የሬድዮ ፡ የዩቱብ ዜና ማሰራጫቸው ጭምር ከእነስማቸው በቅርብ ይወጣል። ሕዝብ እነዚህን መሰሪዎች በደንብ እንዲያውቃቸው ይደረጋል ከመቼውም ይበልጥ። ወገን ታርዶ ደሙ እንደጎርፍ ፈስሶ እራሱ ተቆርጦ በሜዳላይ እንዳልተጣለ ፡ ሰበር ዜና እያሉ እንዳላወሩ የተቀረውም የመታረድ እጣ ሳይደርስበት እናድነው ለሚል ጥረታችን ለሊብያ መንግስት ያቀረብነውን የወገኖቻችን መፈታት ጥያቄ ይሄውም ማንም ኢትዮጵያዊም ይሁን የኢትዮጵያ መንግስት ተብሎ ቤተመንግስት የተቀመጠው ሳይጠይቅ ፡ ለመጀመርያ ጊዘ ለሊብያ መንግስት የቀረበውን በእኛ በኩል ---ከምንም ሳይቆጥሩ፡ የወገንን ነብስ በቂም በቀል ፡ በግል ጥላቻ ላይ ብቻ ተሞርኩዘው አሁን የተለቀቁት በታረዱ ኖሮ ሰው አላወቀብንም ብለው በተለመደው ድርጌታቸው ደስ ብልዋቸው ሊተኙነበር። አምላክ ደግነው ጥያቄያችንንም ሰማ፡ የሊብያም የሽግግር መንግስት ተባበረን። ወዳጆቻችን ወደፊት ስማቸውን የምንገልጽ ሁሉ በየፊናቸው አጣደፉት ጉዳዩን። አለም አቀፍ ሚዲያ ኮሚቲያችን ውስጥ እንዳሉም ቀደም ሲል ግልጽ አድርገናል እነሱም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ሰዎቹም ተፈቱ። ያሰቡት ማዳከም ሳቦታዥ አልሰራም ። ምንም እንክዋን ኤጅብት ሰንደቅ አላማዋን ወንድሞቻችን አሲዛ ከአይርመንገድዋ ሲወጡ የፓለቲካ መጠቀሚያ ብታድርጋቸውም ዋናው ነገር ነብሳቸው ተርፍዋል። ስለሆነም ኤጅብትንም መውቀስ ማቆም ይኖርብናል እኛ ኢትዮጵያውያን።
ብዙ ታጋይ ለኢትዮጵያ አንድነት የቆመው በፋሽስትነት በወሮበልነት ከሚያውቃቸው የሶሻል ሚዲያ መሃል የብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ የተለመደው እርህራሄ ያላቸው እና ትክክለኛ የሶሻል ሚዲያ ስርአትን የሚያራምዱ፡ ለግልጥላቻቸው እና ቂም በቀል መወጫ በማድረግ ድህረገጻቸውን የማይሞክሩ ኢትዮጵያን እና ሕዝብዋን ጎጂ የሆነውን እና ጠቃሚውንም በግልጽ ጎን ለጎን በማስቀመጥ የሚታወቁት፡ ኢትዮጳትሪኦትስ ዳትካም፡ ሳቦታዥ ላደረጉት ሲላክ ለኢትዮፓትርዮትስ ዳትካምም በአንድላይ ነበር የተላከው። ሆኖም የየመኑንም ስዴተኛ የስም ፊርማ ዘመቻችንን እናም በሊብያ የታሰሩት እንዲለቀቁ የጨመረውን ጥያቄያችንን እና ሕዝቡ ሊሳተፍ እንዲያስችለው ወገኑን በሊቢያ ይረዳ ዘንድ መግለጫችንን በሚገባ አውጠተዋል። ኢትዮፓትሪኦትስን በየመን ነጋ ጠባ በስጋትላይ ባለው እና ሕይወቱ በቦምብ ተረብረቦ ሕይወቱን ከእነልጆቹ ባጣው እና ቀጥሎም በግፍ በታረደው እና በተረሸነው አዲሱ ትውልድ ኢትዮጵያዊ ስም ፡ በሕይወትም እዛው ሊብያ በተስፋ እየተጠባበቁ ለመውጣት ባሉት ወገኖቻችን ስም ፡ ትልቅ ምስጋና አቀርባለሁ መከራቸውን ሳታፍኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ወገናቸው መግለጫችንን በሚገባ ስላቀረባችሁ።
የመን ያለውን እናም ሊብያ የኢትዮጵያ ስዴተኛ ጉዳይ አስፈጻሚ ኮሚቲ እና ከእኔጋር በመተባበር በአንድነት በተለመደው እየተሳተፉ በግልጽ የወገናቸው ቀኝ እጅ በመሆን አስተዋጽዎ የሚያደርጉ በድጋሚ ከዚህ ብታች እነሆ። ስማችንን አንደብቅም። የምንሰራውም ማንነታችንም፡ የምንኖርበትም አገር ፡ ከተማበግልጽ ነው። እነዚህ የኮሚቲ አባላት እነዚህ ዝምብለው በማንኛውም መድረክ ብቅ ጥልቅ የሚሉ ሳይሆን ፡ ቆራጥ ኢትዮጵያውያን የግምባር ሰጋ የሆኑ ፡ ስለገራቸው ኢትዮጵያ እና ሕዝብዋ አንድነት እና የእኩልነት መብት በመታገል፡ በማታገል ብዙ የለፉ ናቸው። እነዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ሳቦታዥ ልምዳቸው የሆነው ከሃዲ ጨካኞች እና ግብረአበሮቻቸው ፡ የእነዚህን ጨዋ አኩሪ ኢትዮጵያውያን አንዳስረኛ እንክዋን የኢትዮጵያ ፍቅር ወይም የሕዝቡ የላቸውም በኢትዮጵያዊነት ሚዛን ሲመዘኑ ገለባነት እንጅ። ምስጋና ስማቸው ከዚህ በታች ላለው እህቶቼ ወንድሞቼ በጣም የከበደ ነው። የእናት አገራችንን የኢትዮጵያን እና የሕዝብዋን ክብር አክብረው ስለሚያስከብሩ። አምላክ እድሜ እና ጤናቸውን ያርዝመው ለኢትዮጵያ እና ለሕዝብዋ ሲል። የሚመኙትን የኢትዮጵያን እና የሕዝብዋን ሰላም እና አንድነት ያሳያቸው። አሜን።
ከምሳጋና ጋር፡
የኢትዮጵያውርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው
የተግባር አቀነባባሪ እና ሊቀመንበር።
ከዚህ በታች የምታዩት የስም ዝርዝር በግልጽ ምንም ድብብቆሽ በሌለው መልኩ በመስራት በየመን እና በሊብያ በደቡብ አፍሪካ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ መክኒያት በተቁዋቁዋመው ኮሚቲ ውስጥ በበጎ ፍቃዳቸው ገብተው እያገለገሉ ያሉ ለወገናቸው የክፉቀን ደራሽ ኢትዮጵያውያን በመሆን በሚኖሩበት እና ከዛም ባሻገር የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት የሚታወቁ ጨዋ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ያካተተ ነው።
ኮሚቲውን ያቁዋቁዋመው፡ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ስዴተኞች መብት አስከባሪ እና ጉዳይ አስፈጻሚ ሲሆን ፡ በዳላስ ቴክሳስ ተቁዋቁሞ ያለምንም የግል ጥቅም ወይም የገንዘብ እርዳታ ለኢትዮጵያውያን ስዴተኞች ችግር ግንባር ቀደም እና ብቸኛው በመሆን ላለፈው 33 አመት ብዙ አስተዋጽዎ በማድረጉ በብዙ የአለም ድርጅቶች እና መንግስታት የኢትዮጵያ ስዴተኞች ጉዳይ አስፈጻሚ እና የመብት ተከራካሪ ሆኖ በመቆየቱ በሚታወቀው ነው።
ኮሚቲችንያ ስምዝርዝር ፡
የኢትዮጵያውርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው።
ዶክተር ማንከልክሎት ሃይለስላሴ ዋሽንግተን ዲሲ።
ዶክተር ጋሹ ሃብቴ አርካንሳስ።
አቶ ነብዩ ዳምጤ ዳላስ ቴክሳስ።
አቶ መሰለ ከለል ዳላስ ቴክሳስ።
ዶክተር አበባ ፈቃደ ዋሺንግተን ፡ዲሲ::
ዶክተር ተዘራ ጸጋዬ አትላንታ።
ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ አትላንታ።
ዶክተር አረጋህኝ ሴፉ መንፊስ።
ወይዘሮ ንግስት ተወልድ ዳላስ።
ሻምበል አሸብር ገብሬ ዋሽንግተን ዲሲ።
ዶክተር ለማ ክብረት ዋሽንግተን ዲሲ
ሻምበል ሰለሞን ጋዲሳ ዳላስ ቴክሳስ።
ድል ያደርጋል;; ዋሽንግተን ዲሲ።
አቶ እዝራ በለጠ ላስ ቬጋስ ነቫዳ።
ውዴ አድገህ ዳላስ ቴክሳስ።
ሃይሌ ካሳ ሲዊስ።
ደምመላሽ ግርማ ስዊስ።
ጌታቸው ረዳ ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ።
ሻለቃ ሱራፌል ዘውዴ፡ ዳላስ ቴክሳስ ።
የኢትዮጵያውርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው።
ዶክተር ማንከልክሎት ሃይለስላሴ ዋሽንግተን ዲሲ።
ዶክተር ጋሹ ሃብቴ አርካንሳስ።
አቶ ነብዩ ዳምጤ ዳላስ ቴክሳስ።
አቶ መሰለ ከለል ዳላስ ቴክሳስ።
ዶክተር አበባ ፈቃደ ዋሺንግተን ፡ዲሲ::
ዶክተር ተዘራ ጸጋዬ አትላንታ።
ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ አትላንታ።
ዶክተር አረጋህኝ ሴፉ መንፊስ።
ወይዘሮ ንግስት ተወልድ ዳላስ።
ሻምበል አሸብር ገብሬ ዋሽንግተን ዲሲ።
ዶክተር ለማ ክብረት ዋሽንግተን ዲሲ
ሻምበል ሰለሞን ጋዲሳ ዳላስ ቴክሳስ።
ድል ያደርጋል;; ዋሽንግተን ዲሲ።
አቶ እዝራ በለጠ ላስ ቬጋስ ነቫዳ።
ውዴ አድገህ ዳላስ ቴክሳስ።
ሃይሌ ካሳ ሲዊስ።
ደምመላሽ ግርማ ስዊስ።
ጌታቸው ረዳ ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ።
ሻለቃ ሱራፌል ዘውዴ፡ ዳላስ ቴክሳስ ።