Thursday, May 14, 2015

ከሊብያ የታሰሩትን አስፈሪ ቦታ የነበሩትን ብናስለቅቅም ፡ አሁንም ገና የታሰሩ ስላሉ ለማስፈታት እየታገልን ነው። በየኢትዮጵያወርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው።


Worldwide Ethiopian Refugees' Advocate Group USA
Dallas, Texas USA (Founded in 1983 in Dallas, Texas)
Phone # 214-642-0394
email: yehar9@aol.com

ማሳሰቢያ
ከሊብያ መንግስት ጋር አሁንም ቀጥሎ እየተሰራ ያለ ስዴተኛውን ወገናችንን የሰው ልጅ ክብር እና መብቱን ለማስጠበቅ ያላለቀ እናም ቀጣይነትም ጥረት እየተካሄደ በመሆኑ አንዴ ሁኔታዎች እስኪቁዋጩ ፡ ጉዳይ አስፈጽሞ ዞር ማለት ሳይሆን የዲፕሎማስይ ግንኙነት ሕዝባችን እንዲኖረው ጠንካራ ስረመሰረት መጣል አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ይሄውም በአረቦቹ መሪዎች እና በባለስልጣኖች አካባቢ። የአንድ አገር ሕዝብ ወይም ፓሊስ ሰዎችን የሚያከብረው ወይም የሚጎዳው የአገሩ መንግስት የተባለው በሚሰጠው መመርያ ነው እንደሚታወቀው።
ስለሆነም ለሊቢያ መንግስት ፡ አምባሳደር እና የጦር መኮንኖች እና ባለሌላ መእርጎች ጭምር በ ስላደረጋችሁት መተባብር እና ግብጽንም አስተባብራችሁ ኢትዮጵያይዋን ባለፈው ታስረው የነበሩትን ስለረዳችሁ ሁላችሁንም እናመሰግናለን። ይሄውም በኢትዮጵያውያን እና በሎብያ ህዝብ መሃል አዲስ መቀራረብን የሚከፍት መእራፍ ነው ብለን እናምናለን።

በመጭረሻም እላይ ከፍ ብሎ ስሙ የሚገኘው ድርጅት እና ኮሚቲው በጠየቀው መሰረት ጊዜያዊ መታወቅያ እና የይለፍ ወረቀት አሁንም በሊብያ ለሚገኙት ኢትዮአጵያ ስዴተኞች እንዲሰጥ በተጠየቀው መሰረት እንዲሰጣቸው እንደምታደርጉ ተስፋ እናደርጋለን።
በሚል ብትጽፉ ሕዝቡ እራሱ ለሕዝቡ ሲቆም እራስን አክብሮ ማስከበር በመሆኑ አስፈላጊነው።

በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ ወገኖች ኮሎኔል ጋዳፊ በይፋ ጋብዘውኝ ለአፍሪካ አንድነት ታጋይነቴን መነሻ በማድረግ ብሎም ድራግ አፍሪካ አያስፈልጋትም በሚለው አለም አቀፍ ዘመቻዬ፡ ዛሬ በዚህ ፌስቡክም ላይ ያላችሁት ወንድሞቼ በተለይ ለረጅም ጊዜ የማውቃችሁ ስህተት ነው ብላችሁኝ ነበር። አንዴ ብሳሳት እንዴት አራት ጊዜ ግብዣቸውን ወድቅ አደርጋለሁ። ሆኖም ያሁሉ ዶኩመንቱ አሁን ጠቅምዋል። ይሄውም ተቀባይነቱን በሊብያ ሽግግር መንግስት በኩል ቶሎ ለማግነት እና እምነትም ለመጣል ከማስቻሉም በላይ እንደሚታወቀው ይሄ በግማሽ ጎኑ የቆመው መንግስት ትልቅ እርዳታ ይፈላግል በተለይም የአሜሪካንን ኮንግረስ አስመልክቶ የፈለጉት ወታደሩን ማስታጠቁን እግቡ ለማድረስ። ስለሆነም እነሱ ወገኖቼን ከረዱልኝ እኔም በርኮንግረስ በዋይት ሃውስ እናም በሴነት ጭምር በተገኘው እተባበራለሁ። ጋዳፊን ደጋፊብሆን ኖሮ ወይም የነደፉት የአፍርካ ወጣት ፕሮግራም አለም አቀፍ ሊቀመንበር 0 ቀርቼ ነበር ወገኖችን አስመልክቶ። አምላክ ንቁ ስላደረገኝ በሚያሳየኝ በትክክሉ እንጆ ብዙዎች በሚያዩት ስህተት ስለማልሰለፍ ለገንዘብም ሕሌናዬን እና አፍሪካን ስለማልሸጥ ኤትዮጵያዬንም አመሰግነዋለሁ። ገንዘብ ጋዳፍንም ይሁን ሳዳም ሁሴንን አላዳነም ። የአጼ ቴዎድሮስን እጣ እመናለሁ ለምን ዘለአላማዊ ክብር ነው ለሌላው መድማት መሞት።
ምስጋና መላኪያ ኢሜል አድራሻ እንደሚከተለው ነው። 

Ambassador ኢብራሂም ደባሺ (Dabbashi), in New York, svc.libyamission@gmail.com
Phone # 212-752-5775.
Libyan Charge d' affairs Mr. Wafa Bugaighis in washington D.C. aujalimedia@gmail.com
Phone # 202-944-9601

በአድማ ሊብያ የታሰሩትን ለማስፈታት የተደረገው ጥረት የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዲያሳትፍ አስበን ያወጣንውን መግለጫ ቀደም ሲል በግል ጥላቻ እና በፓለቲካ ልዩነት ላይ ቂም በቀል ይዘው በአድማ የወገኖቻችንን ድምጽ አፍነው በተለመደው ያላወጡትን ድረገጾች እናም የሬድዮ ፡ የዩቱብ ዜና ማሰራጫቸው ጭምር ከእነስማቸው በቅርብ ይወጣል። ሕዝብ እነዚህን መሰሪዎች በደንብ እንዲያውቃቸው ይደረጋል ከመቼውም ይበልጥ። ወገን ታርዶ ደሙ እንደጎርፍ ጎፈሶ እራሱ ተቆርጦ በሜዳላይ እንዳልተጣለ ሰበር ዜና እያሉ እንዳላወሩ የተቀረውም ያየመታረድ እጣ ሳይደርስበት እናድነው ለሚል ጥረታችን ለሊብያ መንግስት ያቀረብነውን የወገኖቻችን መፈታት ጥያቄ ለመጀመርያ ጊዘ ለሊብያ መንግስት የቀረበውን ከምንም ሳይቆጥሩ የወገንን ነብስ በቂም በቀል በግል ላቻ ላይ ተሞርኩዘው የተእቱት በገደሉም ኖሮ ሰው አላወቀብንም ብለው በተለመደው ድርጌታች ደስ ብልዋቸው ሊተኙነበር። አምላክ ደግነው ጥያቄያችንንም አምላክ ሰማ የሊብያም የሽግግር መንግስት። ሰዎቹም ተፈቱ። ምንም እንክዋን ኤጅብት ሰንደቅ አላማዋን አሲይዛ የፓለቲካ መጠቀሚያ ብታድርጋቸውም ዋናው ነገር ነብሳቸው ተርፍዋል።
ሆኖም ከእነዚህ ብዙ ታጋይ በፋሽስትነት ከሚያውቃቸው መሃል የብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ የተለመደው እርህራሄ ያላቸው እና ትክክለኛ የሶሻል ሚዲያ ስርአትን ለግልጥላቻቸው እና ቂም በቀል መወጫ በማድረግ የማያምኑት ኢትዮፓትርዮትስ ዳትካም የየመኑንም ስዴተኛ የስም ፊርማ ዘመቻችንን እናም ከዛ በሁዋላ ያወጣንውን በሊብያ እንደለቀቁ የጨመርውን ጥያቄያችንን እና ህዝቡ ሊሳተፍ እንዲያስችለው ወገኑን በሊቢያ ይረዳ ዘንድ መግለጫችንን በሚገባ አውጠዋል። እናመሰግናቸዋለን ።
እነማን ከእኔጋር እንደተሰለፉ ከዚህ ብታች እነሆ። እነዚህ ዝምብለው በማናውም ቦታ ብቅ ጥልቅ የሚሉ ሳይሆን ቆጥ ኢትዮጵያውያን የግምባር ሰጋ ስለገራቸው ኢትዮጵያ እና ሕዝብዋ አንድነት እና የእኩልነት መብት በመታገል : በማታገል ብዙ የለፉ እና እነዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ከሃዲ ጨካኞች እና ግብረአበሮቻቸው ፈጽሞ አንድ አስረቸው እንክዋን በኢትዮጵያዊነት ሚዛን ሲመዘን የገለባ ያህል እንክዋን ተደምረው ቀል ከመሆን ሌላ በተግባር ከብደው አይገኙም። ምስጋኔ ስማቸው ከዚህ ታች ላለው እህቶቼ ወንድሞቼ በጣም የከበደ ነው የእናት አገራችንን የኢትዮጵያን እና የሕዝብዋን ክብር አክብረው ስለሚያስከብሩ። አምላክ እድሜ እና ጤናቸውን ያርዝመው። የሚመኙትን የኢትዮጵያን እና የሕዝብዋን ሰላም እና አንድነት ያሳያቸው። አሜን።
ከምሳጋና ጋር፡
የሓረርወርቅ ጋሻው ሊቀመንበር።
ኮሚቲችንያ ስምዝርዝር ፡
የኢትዮጵያውርቅ-የሐረርወርቅ ጋሻው።
ዶክተር ማንከልክሎት ሃይለስላሴ ዋሽንግተን ዲሲ።
ዶክተር ጋሹ ሃብቴ አርካንሳስ።
አቶ ነብዩ ዳምጤ ዳላስ ቴክሳስ።
አቶ መሰለ ከለል ዳላስ ቴክሳስ።
ዶክተር አበባ ፈቃደ ዋሺንግተን ፡ዲሲ::
ዶክተር ተዘራ ጸጋዬ አትላንታ።
ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ አትላንታ።
ዶክተር አረጋህኝ ሴፉ መንፊስ።
ወይዘሮ ንግስት ተወልድ ዳላስ።
ሻምበል አሸብር ገብሬ ዋሽንግተን ዲሲ።
ዶክተር ለማ ክብረት ዋሽንግተን ዲሲ
ሻምበል ሰለሞን ጋዲሳ ዳላስ ቴክሳስ።
ድል ያደርጋል;; ዋሽንግተን ዲሲ።
አቶ እዝራ በለጠ ላስ ቬጋስ ነቫዳ።
ውዴ አድገህ ዳላስ ቴክሳስ።
ሃይሌ ካሳ ሲዊስ።
ደምመላሽ ግርማ ስዊስ።
ጌታቸው እረዳ ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ።