ይድርስ ከኢትዮጵያ ስዴተኞች የመን እና ሊብያ በውጪ ለሚገኘው የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ።
ቀደም ስንል ከአንዴም ሁለቴ ገንዘብ ሳይሆን የምንፈልገው ተባብራችሁ ካለንበት የመከራ አጣብቂኝ እንድታድኑን ነው ማለታችን ይታወሳል። ሆኖም በዳላስ ቴክሳስና በአትላንታ በተለያዩ የአሜሪካን ከተሞች በስማችን $100 ዶላር በትኬት በመሸጥ ገንዘብ እየተሰበሰበ መሆኑን በማስረጃ ተረድተናል ይሄም በጣም አሳዝኖናል። የት እንዳለን እንክዋን ያልፈለጉን ያልጠየቁን እኛ ስላለንበት መከራና ስቃይ ያልተቀበሉት ያልደረሱልን ገንዘብ ሰብስበው ምን ልያደርጉት ነው? ግማሾቻችን በቦንብ ላሸቅን ከእነልጆቻችን፡ ገማሾቻችን ታረድን ባዳው እንክዋን ሲያዝንልን ይሄ እንክዋን እንዴት በውጪ በተለየም በአሜሪካን ያለው ውገናችን አይተባበርንም ? ገንዘብ ከዚህ ቀደም ከእየከተማው ከአሜሪካን ተዋጣ ሰማን እናንም ቃለመጠየቅ ተደረገል ሆኖም ገንዘቡን የተቀበሉት በስማችን አንድም ሳንቲም ከሳውዲ ወደ የመን የገባው ጭምር አላገኘንትም።
የኢትዮጵያን ሕዝብ በአሜሪካንም ይሁን በመላው አለም የምትገኙትን ለስዴተኞች በመን፡ በሊብያ ባለውና በሳውዲ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን ወዘተ በሚል ስም ገንዘብ ለእኛ ለስዴተኞች አዋጡ ለሚልዋችሁ ሁሉ ለፓለቲካ ድርጅቶች፡ የኢትዮጵያ ሚዲያ፡ የመረዳጃ ማሕበር፡ የሃይማኖት ድርጅቶችና ማንኛውም የውጪ ድርጅት ሳይቀር ገንዘብ በስማችን እንዳትሰጡ። መቼ እና እንዴት እንደምትልኩልን በእየ ድርጅቶቻችሁ እራሳችን ከየመንና ከሊብያ በጥምረት አሜሪካን ዳላስ ካለው የወከልነው ብቸኛው አማራጫችን በችግራችን ከተገኘለን ---ጋር በምናወጣው መግለጫ እናስታውቃለን። እስከዛሬም የሰጣችሁትን መልሳችሁ እንድትቀበሉ ገንዘባችሁን እናሳስባለን።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አሜሪካን ዳላስ መቀመጫው የሆነውን በውጪ ወኪላችንን
በ214-642-0394 ማናገር ይቻላል። ቀደም ሲል ያወጣናቸውን ከዚህ በታች ይመልከቱ።
የስዴተኞች ኮሚቲ
ከየመን።
20 hrs ·