Wednesday, January 19, 2011

እንክዋን ለጥምቀት በአል የአለም ፈጣሪ አደረሰን ሁላችንንም!

እንክዋን ለጥምቀቱ በአል አለመንና በውስጥዋ ያለንውን ሁሉ የፈጠረና ሰማይና ምድርን የዘረጋና የፈጠረ አምልክ አደረሰን ሁላችንንም! ሰላም ከጤናና ከደግነት ጋር ለሁላችንም እንዲያበዛልንና የታመሙትን ሁሉ በየቤቱ ያሉትን ስለሚያውቅ እንዲያድንቸውና በአዳኝነቱ፡ በፈዋሽነቱ ሃይል ያለው በእጁ ስለሆነ ልጁንም አዋቂውንም እንዲፈውስ እማጸነዋለሁ። በሃዘንም በተለይ ሳይኖሩ ከፊታቸው የትቀጠፉባቸውን ልጆቻቸውን ላጡት ቤተሰቦች አምላክ ምንም ስለማይሳነው ጽናቱን ባስቸክዋይ እንዲለግሳቸው እለምነዋለሁ። ቤተሰቦቻቸውንም ላጡት አምላክ ብርታቱን እንዲሰጣቸው እለምናለሁ።

እግዚአብሄር ብዙ ጥምቀት ያሳየን ደግ ስራ እንድንሰራና ለግላችን ብቻ ሳይህን ለሚቸገረው ሁሉ ምንም ይሁን ምንም ችግሩ የመከራው ቀራፊ እንድንሆን። ለራስ መኖር ግዴታ እንደሆነ ሁሉ ወገን ወይም ማንኛውም የሰውል ልጅ ብሎም እንሰሳን ከችግር ማዳንና መከራ ውስጥ ያለውን ቅድሚያ በመስጠት ማገዝ አንዱ ከእግዚአብሄር የተሰጠ ትእዛዝና የሚያስደስትም ትግባር እንጂ የሚያሳፍር አይደለም። እሩህሩህ መሆን የሚያሳየው አምላክን በልብ ውስጥ ይዞ መጉዋዝን ነው። ክፉና ጨካኝ ለራስ እንጂ ስለሌላው ወገኑም የማራራ አዋቂነት ሳይሆን፡ አምላክን ያልተከተለ ልብን ይዞ በንፋስ የሚሄድ ብቻ ነው። ደግ እንሁን፡ ጥሩ እንስራ፡ አንቀናቀን፡ አንንገብገብ፡ በውለታ ውለታ ወለታን አንጠብቅ። ለምንሰራ ደግ ስራ ሁሉ በአምላክ ፊት ቢታፈስና ቢዛቅ የማያልቅ የተባረከ ሃብት እናጠራቅማለን። ፈጣሪያችን ይከፍለናል ለኛ በመድረስ። ከእግዚአብሄር እንጂ ከሰው ልጅ ምንም አንጠብቅ ማሰብ እንክዋን ሃጢያት ነው። ቸር እንሁን አምላክ ይጨምርልናል። በመጨረሻም፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሃሰት አማኞችን አንካብ ፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጸብ አንጠንስስ አንደግስ። በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚያጋጥመን በግልጽ እንነጋገር ይሄም ቦርድ ውስጥ አገልጋዩንም ጭምር ማለት ነው። የቦርድ አባላት
ምእመናንን ጠርተው በግልጽ ማናገር እንጂ በጎዋሮ ማውራት ማቆም ይኖርባቸዋል ችግር እንዲታረም ስለሚረዳ። ምእመናንም በግልጽና በጹሁፍ ስማችንን ከእነስልክ ቁጥራችን ጭምር ጽፈን እርማት መደረግ ስላለበትና ስለሚያሳስብን ጉዳይ በግልጽ መነጋገር ይገባናል። ስለ ቤተክርስቲያን ፈራጅ አምላክ ስለሆነ ፍርድ ቤት መካሰስ መቆም አለበት። ክስም ላይ ያለውን ጉዳይ በቅርብ ተነጋግሮ ከፍርድ ቤት ውጪ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተነጋግሮ በግለሰቦች የተጀመረውን የእርስ በእርስ ግጭት ከቤተክርስቲያኑ ደህንነት ጋርም የተያያዘ ባለመሆኑ በመነጋገር ማቆም ነው ውጊያውን። ቤተክርስትያኑ ማለትም ደብረምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል አደጋ ላይ ቢሆንኖሮ ወይም እንደተባለው ጴንጤ ወይም ባፕቲስት ሊያደርጉት ነው የተባለውና ብሮሹር እንደተላለፈው ውነት ቢሆን ኖሮ ምእመናኑ የደብር አባላት ቦርድ ውስጥ ያሉትን በሙሉ መንጥረን ባስወጣን ነበር። ዲሲ ላሉት ፓትሪያርክ ሊያስረክብ ነው ተባለ ያውም ገደብ ተሰጥቶት "በሚቀጥለው ሳምንት የሚካኤልን ደብር ቦርድ ዲሲ ላለው ሲኖዶስ ሊያስረክቡት ነው!" ሳምንቱ አለፈ ወራትም። ምነው ወንድሜ የታል ያስረከቡት ሃሰት ነው አላልክህም? ብዬ አበቃ። አንድ ሰው አንድ ጥፋት ካለው ብዙ የውሸት ጥፋት በሚጨመርበት ጊዜ አንድ ጥፋትን ለማክበድና ሕዝብን ለማነሳሳት ተብሎ አንዱን የውነቱን ጥፋት ወይም ወንጀል ከማቃለሉም ይበልጥ፡ ስለ አንዱ ጥፋትም ምን ያህል ውነተኛነት አለው ይሄ ሰው? የሚለው ጥያቄ ውስጥም ይከታል። አይዋሽ! ውሸትን ተባብረን እንግደለው ሴጣን ስለሆነ። ውነተኛ እንሁን እውነት እግዚአብሄር ስለሆነ!

አምላኬ ባንተ ፍቃድ ስለህነ ከዚህ በላይ ያለቺውን መል እክት በሃቅዋ ያስቀመጥኩት ለሚያነብዋት ሁሉ መጠቀሚያ አድርጋት። አስጀምረህ ስላስጨረስከኝ እንደስፍም ይችን መልእክት ፍቃድህ ስለሆነች ተመስገን።