Wednesday, January 19, 2011

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ባስቸክዋይ የቦርድ አባል ምርጫ ስብሰባ እንዲጠራ ሕዝቡ መልእክቱን ያስተላልፋል! ቁጥር አንድ።

የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በጋርላንድና ችግሮቹ ቁጥር አስራ ሶስት።

መግቢያ፡ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርን ከጃቸው ላለማጣትና ገንዘቡስ ሁሉ የትደረሰ? ገንዘብ የወሰዳችሁትን አምጡም  እንዳይባሉና በእድርም ስም አስገባን ያሉት ገንዘብንም አስመልክቶ፡ ከኢትዮጵያ ቀን የተገኘውን ገቢም አስመልክቶ ባጠቃላይ በገንዘብ እንዳይጠየቁ ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በተለመደው ቦርድ በድብቅ የማቁዋቁዋምና በመረዳጃ ማሕበሩ በሬዲዮ እየወጡ ማውጅ ባላቸው የማናለብን ልምድ ፡ አሁን ደግሞ  እነፍቅረማሪያምና በትሩ ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በሚል በድብቅ የምያቁዋቁሙት ቦርድና ኮሚቴ ውስጥ ሁሉ እንደ ጨው ሲያስገብዋቸው የሚተባበርዋቸውን ይዘው ቦርድ ኦፍ ትረስቲ እያቁዋቁዋሙ ስለሆነ መቆም አለበት።

ከቤተክርስትያን በስትጀርባ ሆኖ አማካሪ ምስሎ ቀርቦ ደብሩን ለበትሩና ለግብረአበሮቹ ሊያስረክብ ነው ተው! ሲባሉ ባይሰሙም ነገር ግን ውነት አይቀሬ ነውና በትሮቹን ተፈራ ወርቅን፡ በትሩን፡ ኪዳኔ አለማየሁን የቅዱስ ሚካኤልን ደብርና የከተማውን ሕዝብ አንድነት አፈራራሾች በቦርዱ ካላስገባችሁልኝ በሚል ባቀረበውመሰረት ፍቅረማርያም ማንነቱንና አላማውን ሊረዱ ችለዋል። ፍቅረ? የቤተክርስቲያኑ ቦርድ አባላት ባለመስማማታቸው ምርጫ እንዳይካሄድ ፔቲሽን ያስፍረመው ማንነቱን የደብሩ ቦርድ አባላት ሲገነዘቡና ጥያቄው ያለመውን መልስ አዝሎ ግቡን ስላልመታ  ነው፡፡ እኔ ያልክዋችሁን ስዎች ቦርድ ውስጥ አይገቡም ስላላችሁኝ ምርጫው እንዳይካሄድ አደርግባችሁዋለሁ ብሎ መዛቱምና ማስፈራራቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

የአንድ ሕብረተስሰ ተከብሮ መኖር በሚኖርብት እንደ አሜሪካን አገር ለሕብረተሰቡ ክብርና ተሰሚነትም ድምጹ ሊኖረው የሚችለው እራሱን በጋራ አስተባብሮና ተከባብሮ በግለሰቦች ወይም በቡድን ሳይሆን በሕብረተሰቡ ለምሳሌ በብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዳላስ ፎርት ወርዝ በችሎታው፡ በታማኝነቱና በፈሪሃ እግዚአብሄር ተግባሩ ፊት ለፊት መርጦ ያስቀመጣቸው ለክብሩና ለጋራ ጥቅሙ መርጦ ያስቀመጣቸው የቦርድ አባላት ስሙን ወክለው በየቦታው በመገኘት ድምጹ የሚሆኑ እንደራሴ ብሎ ሲያስተዋውቅ ብቻ ነው።

ላሁን ጊዜ ስለሌለ በዛሬውና በነገው ቀን እንዴት የጋራ መረዳጃው በልዋጭ መልክ ለእነ መለስ ዜናዊ ማገልገያ እንደገባ፡

እንዴት የጋራ መረዳጃ ማሕበሩን ስድስት ወንዶች ከሕዝብ የተረከቡትን ሳያስርክቡ ሜዳላይ ጥልውት ሊሄዱ እንደቻሉና

 የኢትዮጵያ ቀን እንጀምር በአል እናዘጋጅ ሲባል ምን ይዘው መጡ የቦርድ አባላቱ? ለምንስ  የኢትዮጵያ ካርታ ቦርዱ ከለከለ?

እንዴት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ በዳላስ ፎርት ወርዝ በተለይ በመዘጋጃ ቤቱ የተተከለውን የሕብረተሰቡን ታላቅቅነት አፍርሰው እራሳቸውን ግለሰቦች ሊክቡበትቻሉ?

ለሰላሳ ደቂቃ በሰለጠነው ስርአት በደብዳቤ ብጽፍም መላልሼ፡ አንድ አመት ስላለፈው ደጅ ጥናት ለምን?

የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ከጃቸው ፈልቅቆ መለአኩ እራሱ ቤቱን ነጻ ስላወጣ የዚህ ሁሉ ችግር ሸማኔና ደዋሪ የመበጣበጥ ጥበብ አቀነባባሪ ግብረአበሮቹን ከእነ ሴት ልጆቻችው፡ጭምር ይዞ ከዚህ ቀደም ቦርድ ኦፍ ትረስቲ ይመረጥ ብለን ስንጠይቅ አሻፈረኝ ይገለሉልኝ በሚል ያስቆምትን አሁን ግን የወሰዱት ገንዘብ ከካቶሊክ ቻሪትም ጭምር ከኢንሹራንስም ከዌልፋርጎም ባንክ እንዳይጠየቅ ስለእድርም ገንዘብ ቦርድዶፍ ትረስቲ እያቁዋቁዋሙ ስለሆነ፡

የመርዳጃ ማሕበሩ አዳራሽ ፕሮጄክት ባለቤትና ማን ፈጠረው? ኮሚቴውስ ወዴት ደርሶ በላዩ ላይ አዲስ ተፈጠረ? ገንዘቡስ የት አደረሱት? እንደቀድሞው ሕብረተሰባችን ስላምን የመተሳሰብ ፍቅሩንና አንድነቱን መልሶ ለማጎናጽፍ ምንድነው መፍትሄው? በሚል የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕብሩን አስመልክቶ ስለሚተነተን ከእነማስረጃው፡ ከላይ ባለው አረስት ቁጥር ሁለት በሚል ይቀርባል ተከታተሉት።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ምርጫ ባስቸክዋይ እንዲደረግ የሁላችንንም ጥረት ይጠይቃል። መረዳጃ ማሕበሩ ለሕዝቡ መመልስና በሕዝብ በሚመረጡ ለሕዝብ አገልጋዮች ማስረከብ አለብን! አምላክ አንድነታችንን እየመለሰልን ነው እንበርታ እናመስግነው። እራሳችንን ካከበርን ካስከበርን የዳላስ ተመራጮች ሁሉ በመዘጋጃ ቤቱም ያጣነውን ክብር ባጭር ጊዜ እናስመልሳለን አሁንም ተጀምርዋልና!