Wednesday, February 2, 2011

When did the undetected TPLF agents took over the MAAEC? And how?

መድሃኔ ዓለም ሆይ!
ከሁለቱ ቀራንብቶችህ ጋር ለሚያንጸባርቀው አመጸኛንና ከዳተኛን በማስደንገጥ ብቻ ለሚገድል ለገጽህ ግርማ ሰላም እላለሁ። አሜን።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር በዳላስና አፍራሾቹ! ቁጥር ሶስት።

እንዴት ሰነብታችህ ክቡራትና ክቡራን ወገኖች።
በመጀመሪያ በቅዱስ ሚካኤል ደብር ለማገልገል በበጎ ፍቃዳቸው በምርጫ ቦታውን ለተረከቡት ሁሉ ክርስቶስን ብቻ የሚያገለግሉበት አይምሮ  እንዲሆኑ አምላክ ይርዳቸው ይምራቸውም። ከሁዋላ ሁዋላ እየተከተሉ ሴጣናዊ ተግባር እንዲሰሩ ከሚያደርጉ የስው ሴጣንኖች ይሰውራቸው፡፡
ባለፈው የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ቦርድ ባስቸክዋይ ስብሰባ እንዲጠራና ምርጫ እንዲደረግ ሕብረተስቡ በጠየቀው መሰረት በዚህ የሕብረተሰቡ የእውነት ድምጽ ከሆኑት ጥቂት ብሎጎች አንዱ ጥሪው የሕዝቡን ማስተላለፉ የማይዘነጋ ነው። ይሄውም ማሕበሩን በሕዝብ በሚመረጡ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት፡  በሕዝብ የሚመረጡና ታማኝነታቸውና ተጠሪነታቸው አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲ ላለው የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት የሚያገለግል ሳይሆን ይሄውም፡ አሁን ያለው ቦርድ ሲሰራ እንደኖረው አንዱ ሲወጣ ሌላውን እየተካ እንደሚሰራው ሳይሆን፡ ነገር ግን ተጠሪነታቸውና አገልግሎታቸው ባለማወላወል ለዳላስ ፎርት ወርዝ ለምንኖር የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ብቻ የሚሰሩ የቦርድ አባላት ለመምረጥ ፡ ሃላፊነትን ክብር አድርገው ለሚያዩ፡ በሃላፊነት መመረጥ ከከርስ በላይ መሆኑን በከባድ ሚዛን ለሚመዝኑ ጨዋ ኢትዮጵያውያን ሴቶችና ወንዶች ለማስረከብ ነው።

 አሁን ያለው ቦርድ ዲሴምበር ሰላሳ አንድ ጊዜው እንዳለፈበት ከሕዝቡ በማረጋገጫ ተነግርዋል። እንደ አለቃቸው እንደ ለገሰ ዜናዊ ወይም ሙባረክ በአምባ ገነንነት መቀመጡ አብቅትዋል! ሕዝቡ በዳላስ ፍቅሩን የሚገነባለት እንጂ ለጋራ ጥቅም ለግል ጥቅም በሃሰት ስለወገን የሚቆረቁሩትን ኢትዮጵያውያን እየኮነኑ ሰላሙንና የጋራ ጥቅሙን በግል ኪሳቸው በሚያካብቱ መታለሉ አብቅተዋል!  ቦታውን የማስረክብ ሃልፊነት የሚሰማቸው አይደሉም በሕዝብ ሳይሆን በቡድን በመመረጣቸው ለይስሙላ።  አሻፈረኝ ካሉ ወደ ሚመለከተው አተርኒ ጀነራሉ መሄድ አይቀሬ ነው። በተፈራ ወርቅ ቦታ የተቀመጠው ይልማ ፈለቀና ከሕዝብ የተሰጣቸውን አደራ እረግጠውና ሜዳላይ የጋራ መረዳጃውን ጥለው በነጮች አቆጣጠር በዘጠና ስድስት  ከጠፉት ስድስት ወንዶች የዛሬው ምክትል ፕሬዘደንት ተብዬው ይገኝበታል ። ያኔ የጸሃፊነት ወንበር ላይ ነብር የተቀመጠው። እንደነዚህ አይነት ሰዎች መረከብን እንጂ ማስረከብን በስነስራት ስለማያውቁ ሕብረተሰቡ መረዳጃ ማሕበሩን በእጁ መልሶ ለማስገባት ስብሰባ ጠርቶ፡ አስመራጭ ኮሚቲ አቁዋቁሞ ፡ የቦርድ አባላት መርጦ መረዳጃ ማሕበሩን ለሚጠቅሙት ጨዋ ሰዎችና የኢትዮጵያዊነት ስነስራት ላላቸው ማስረከብ ነው። ይሄውም ሕግ ይፈቅዳል።
When did the undetected TPLF agents took over the MAAEC? And how?
በዘጠና ስድስት ስድስቱ ወንዶች መረዳጃ ማሕበሩን አስረክቡ እየተባሉ በተከታታይ በጊዜው በአቶ ቴዲ የሬዲዮ ስርጭት ጥሪ ቢያደርግም አቶ  ሰለሞን ሃመልማል ጭምር ባነጋግራቸው ማሕበሩን እንደተረከብን እንድናስረክብ ፍቃደኛ አልሆኑም ሁሉም። ሆኖም ሃላፊነትን መወጣት ከኢትዮጵያዊነት ዜግነት ክብር ጋር የተጣመረ በመሆኑ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርን ለሕዝብ ለማስረከብ "አስረክቡን!" በሚል መልእክት ከሕዝብ የመጣ ነው ብሎ ስያሰራጭ ወደነበረው አቶ ቴዲ የሬዲዮ ዝግጅት በመደወል የመረዳጃ ማሕበሩን ለሕዝብ ብቻዬን ለማስረከብ በመገደዴና ለሕዝቡ ስላምና አንድነትም በማሰብ መረዳጃ ማሕበሩ በእኔ እጅላይ ብቻ መጣሉን ነግሬ መረከብ ለሚፈልግ እንደማስረክብ በሬዲዮ ቀርቤ ይፋ አደረኩኝ። ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለነበረ ስብሰባና ምርጫም የማሕበሩ የሚደረገው ያንን ልማድ ማሕበሩ ኢትዮጵያ ማለት ስለሆነ፡ ለሁሉም ኢትዮጵያዊም ያለሃይማኖት ልዩነት በቦርዱ ገብቶ እንዲያገለግል ሴቱም ወንዱም ለመጀመሪያ ጊዜ በትክክል መረዳጃ ማሕበሩን ለማስተካከልም እድሉ ስለተፈጠረ በሃሊደይ ኢን የመረዳጃ ማሕበሩን ስብሰባ በፕሬዘደንትነት፡ በምክትል፡ በሕዝብ ግንኙንትና በጸሃፊነቱ ቦታ አርራቱን የስራ ሃላፊነት በመስራት ለሕዝቡ በሬድዮ ቦታና ሰአት ሴንትራል ላይ ባለው ስብሰባ ብቻዬን ጠርቼ ስብሰባው ተካሄደ። በቦታው አስረክቡኝ ያለውን ባላይም ሃያሶስት ሰዎች የማውቃቸው መጡ። ምንአልባት አስረክቡን የሚሉት በሚቀጦለው ይመጡ ይሆናል ሌላ ስብሰባ ጥሪ ተባልኩኝ። በሁለተኛው ስብሰባ ከናካቴው አስራ ሰባት ስዎች ከበፊቶቹ መጡ እነዚህ መረከብ የማይፈልጉ ናቸው። አሁንም ሶስተኛ ስብሰባ አዘጋጂ ተባልኩኝ በመጡት ሰዎች። አሁንም እዛው ሃሊደይ ኢን አደረኩኝ። አስራ ሁለትሰዎች ብቻ መጡ ከሰለሞን ሃመልማል ጭምር። የማላውቃቸው በግዜው መረዳጃ ማሕበሩን ተረክበን ባስመራጭ ኮሚቴ ስም ምርጫ እናካሄዳለን የሚሉ ከኦክላሆማ የመጡ ነብሳቸውን ይማረውና አቶ ሴፈ ታደስ  ሳይቀሩ በሰለሞን አማካኝነት ተዘጋጅተው ለመጡት ሰዎች በአራተኛው ስብሰባ መረዳጃማህበሩን አስረከብኩኝ። ልብ በሉ የግርግር ቤት ለሌባ ይመቻል የተባለው መረዳጃውን አስረክቡን አሉ የተባሉትን ባለሬዲዮን ዝግጅቱም ቢጠየቅም አላገናኘኝም ። ማሕብሩንም በፓለቲካ ስምና በውጭ ግፊትም በመደናቆር፡ ስራውንም ባለማውቅ ፡ አዋቂውና አላዋቂው አንድ ላይ ተቀላቅሎ ስራ ሊሰራም ባለመቻሉ፡ አንዱ ከሌላው መማርን እንደ ነውር በመቁጠሩ በመጨረሻም ፡ ተጣልተው በመበተናቸው፡ የትግሬ ነጻ አውጪ የድብቅ አገልጋዮችና ደጅ ጠኝዎቹ  አገር ቤት በሰሩት ላለመጠየቅና ቤታቸውንም ለማስመለስ በደርግ መንግስት የተወሰደውን ለማስመለስ እንዲረዳቸው መረዳጃ ማህበሩን በመሳሪያነት ለግል ጥቅማቸው በልዋጭ! ልዋጭ! ዘቤ ስምምነት  አስርረከቡት ከእነሬድዮኑ።

ከዚህ በታች ሜዳ ተጥሎ የነበረውን የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ልክ እንደጀነራሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሲወጡ አገሪቱን በሃላፊነት እንደተረከቡ እኔም በተመስሳይ አጋጣሚ መረዳጃ ማሕብሩን እንዳይፈርስ ጀማሪም ስለነበርኩኝ ጭምር ሕዝብ የጣለብኝን እምነትና ሃላፊነት በሚገባ ከራሴ አውርጃለሁ። የወንዶቹንም ጭምር። ሃቁን ከመረዳጃ ማሕበሩ አውጥተው ጥለው፡ ብምትክ እነበትሩ፤ ተፈራ ወርቅ፡ ፍቅርማሪያም፡ ኪዳኔ አለማየሁ፡ አመሃ ታምሩ፡ ዘውገ ቃኘው፡ ይልማ ፍለቀ በመተባበር የራሳቸውን ፍርድ ብለው ባስቀመጡት የቆሻሻስራቸውን በመደበቂያ ውሸትና የውሸት ታሪካቸው ተክተውበታል በእኔ አኩሪስራ ቦታ። አንድነት አፍራሽና መረዳጃ ማሕበሩን አፍራሾች ሻጮች ዛሬ የመረዳጃ ማሕበሩን ሊያንቁ የቻሉት ጥፋቱ የማን ነው የኔ ውይስ የእናንተ ውገኖች? ሆኖም ሃቁን በከፊል እነሆ፡

When did the undetected TPLF agents took over the MAAEC? And how?


.