Tuesday, February 22, 2011

የታክሲ ነጂውን ወገናችንን የእንተባበር ጥሪ ከሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎች።

በታክሲ ሞያ የሚተዳደሩት ወንድሞቻችን (እህቶቻችን) መብት መረገጥ የእያንዳንዳችን ጉዳይ አድርገን መውሰድና ከጎናቸው መሰለፍ ከሰው ልጅ መብት ማስከበር አኩዋያ ብቻ አድርገን የምናየው ሳይሆን፡ በአምላክም ሁላችንን በፈጠረውም ንጉስ ስም ደግ መስራትና መደጋገፍ ይጠበቅብናል። ሌላው መታወቅ ያልበት ታክሲ መንዳት እንደማንኛውም ሞያ በአለም ውስጥ ትልቅ ዘርፍና እራሱን የቻለ ሞያ በመሆኑን አንገብጋቢነቱን መቀበል ይኖርብናል። ከታክሲው ስራ ጋር የሚመጡ ብዙ አይምሮን ሰላም ከሚሰጡት ነገሮች ውስጥ የራስ ተቀጣሪ ሆኖ በመስራት ነገ እባረር ይሁን? ከሚለው ጭንቀትና የፈረንጅን ፊትም እያዩ ከምሳቀቅም ነጻ መኮኑ ይገኝበታል። ታክሲ ነጂ ትግስትንና እራስን በዲሲፕሊን መምራትን የሚጠይቅና አስተማሪ ሞያም ነው።  ታክስ ነጂዎች የሚኖሩበት ከተማና የኢኮኖሚው የቱሪስት የጀርባ አጥንትም መሆናቸውን አንዘንጋ። የታክሲ አሽከርካሪዎቹ ስራ እራሱን የቻለ ሞያቸውን በተፈጥሮ ጋዝ ስም ሽፋን፡ ትልቁ አሳ ቲሹን ዋጠ እንደተባለው የሎ ካብ የግል ታክስ ነጂዎን እንዲውጥ ከንቲባው ለፐርት መተባበራቸው ባለሞያዎቹን መተዳሪያቸውን ተነጥቀዋል ፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ባለው በፊርማ የድጋፍ መስጫ በመግባት ስምዎንና ዚፕ ኮድውዎን ያስቀምጡ። ከአክብሮት ጋር በታክሲ ነጂውና በቤተሰቡ ስም። ታክሲ ነጂው ሃቁን ስለያዘ የጠየቀውን እግዚአብሄር ይፈጽመዋል!

http://www.gopetition.com.au/petition/43138.html