Saturday, February 12, 2011

በሃላፊነት ሕዝብ የመረጣቸው በሃላፊነት እንደሚጠየቁበት ጠንቅቀው ያውቃሉ።

መግቢያ፡
"ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ!
ከሰማየ ሰማያት ወርደህ በስጋ ብእሲ በሕጻን አርአያ በተገለጽክበት ወራት፡ እናታችን ሔዋንን ያሳተ ከይሲ ድያብሎስ ፈራ፡ ደነገጠ፡ በሃዘንና በለቅሶ ተዋጠ"
ከመልክ አመድሃኔ ዓለም፡ በተስፋ ገብረ ስላሴ።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርና አፍራሾቹ ቁትር አራት።

የመረዳጃ ማሕበሩ ችግሮችና አፍራሾች በሕዝብ ሳይመረጡ ማሕበሩን በትብብር ሕዝብ ሳያውቅ ዘርፈው እየተፈራረቁበት ያሉት አሁንም በቦርድ ውስጥ ያሉት ፈረቃ ዎች ናቸው። ስለዚህ ከቦታው እንዲለቁ ሕዝብ ጠይቀሃል ነገርን ግን የስራውም ተካፋይ መሆን ማሕበሩን ነጻ የማውጣት ይጠበቅብሃል ተነሳ! ተነሺ!

የተወደዳችሁ ወገኖች ጤና ይስጥልን እንደምን ከርማችሁዋል። ጅንጀሮ መጀመሪያ መቀመጫዬን! አለች እየተባለ ያደግንበት አባባል እንዳለ ሆኖ በዚህ በኛ ጊዜ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አንግብጋቢ ጉዳዮች በሚል የምንጠቀምበት አነጋገር ሃቅ ነው። በፈረንጅቹም ቢሆን First thing comes first እንደሚሉት ማለት ነው። ታዲያ አባባልን እንጣቀማለን ወይ? የሚል ጥያቄ ቢመጣ መልሴ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል።
ሰሞኑን ያፍሪካ ተወላጆች አገር በቀሎቹን ጨርሰው (እየጨረሱም) ሰሚን አፍሪካን የሰረቁን ያው እንደሚታወቀው ሃቁ ሴንትራል አረቢያ ወይም መካከለኛው አረቢያ፡  ዛሬ የመን፡ ከሁለት መቶ  ሺየሚበልጡ በእራሳቸው ወገኖች ተባረው በኑቢያ የገቡት አረቦች ዛሬ በግፈኞችና ጨቁዋኝ መሪዎቻቸው ላይ የወሰዱት የስልጣን ልቀቁ የአንድነት ንቅናቄ የኢትዮጵያዊውም የአለም ወሬ በመሆኑ፡ ምነው ስለ ትኩሱ ውሬ አልጻፍሽም ብትሉ መልሱ የጅንጀሮዋና ከዛም ቀጥሎ ያስቀመጥክዋቸው ናቸው።

ቅድሚያው ስለራስችን አገርና በክልል ስለተሸነሸነው ሕዝባችን፡ ስለ አንድ ሰንደቅ አላማና መላዋኢትዮጵያ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚለው ላይና በዚች በዳላስ ከተማ ደግሞ የምንኖረው ኢትዮጵያውያን በከርሳሞች የተነጠቅነውን የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር በህብረት ነጻ አውጥተን ለመላው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ የሚጠቅም ማለትም፡ ያለ ሃይማኖት ፡ ያለ ጾታ፡ ያለ ጎሳ፡ ልዩነትና የፓለቲካ መድረክነትና የግል ንግድ ማፋፋሚያ መተባበሪያ የሌለበት መረዳጃ ማሕበር ብቻ እንደነበረው መልሰን በሃቀኞች በአንድነትን በሕብረት መልሰን ባስቸክዋይ እንድንገነባው ማሕበሩን ነጻ ለምውጣት ከከርሳሞች ቅድሚያችን አድርገን እንነሳ!
ጨቁዋኞችና በዝባዦች ከፋፋዮችን አንፈልግም እምቢ!! ብሎ ከተነሳው አረብ ማዳነቁን ሳይሆን የራስን ችግር ችግር መሆኑን ፈትሸው ሃቁን አግኝተው መረዳጃውን የሕዝብ እንዲሆን አግገግልቱም ለሕዝብ እንዲሆን ለማድረክ ከሚታገልሉት ጎን እንቁም። ቅድሚያው ይሄ ነው። በሃላፊነት ሕዝብ የመረጣቸው በሃላፊነት እንደሚጠየቁበት ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ሁሉንም መልካም ሃሳብ አስጀምረህ የምታስጨርስ አምላክ ፈጣሪዬ ከዚህ በላይ ያስቀመጥክዋትን ሃቅ ለወገኖቼ እንዳካፍል ስለፈቀድክልኝ ምስጋና ይግባህ። አሜን።