በቦታው በመገኘት የተዘጋጀ ዘገባ።
በበቀለ ወዳጆ።
የኢትዮጵያ ስደተኞች ኮሚቲ አባል ዳላስ።
የተባበሩት ፡ መንግስታት፡ ድርጅት ፡ ሰባኛ የምስረታው በአል ኖቬምበር 3፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣንና ተወካይ በተገኙበት በዳላስ ቴክሳስ በደመቀ ስንስርአት ተከብሮአል። የክብር እንግዳውና፡ ንግግር ያደረጉት ፡ ዶክተር ፡ ሰርጃን ፡ ከሪም ፡ ወደ ዳላስ እንደገቡ በተዘጋጀላቸው ልዩ ስፍራ የእንክዋን ደህና መጡ የክብር አቀባበል የአበባና አጭር ገለጻ በየሐረርወርቅ ጋሻው ተደርጎላቸዋል። በቅርብ የተባበሩት ፡ መንግስታት ፡ ዋና ጸሃፊ ፡ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ዶክተር ሰርጃን ከሪም በበአሉ ላይ አዳራሹን ለሞላው ሕዝብ ሲገልጹ ፡ የመነጋገሪያቸው ዋና ትኩረት አድርገው ያቀረቡት የሲሪያንና የኣፍሪካን ስዴተኞች አስመልክቶ ነበር። ኢትዮጵያ የተባበሩትን መንግስታት ከጥንሡ ካቁዋቁዋሙት አገሮች አንድዋ ነች።
ከዚህ በታች ፡ ያሉት ፎቶግራፎች ፡ የሚያሳዩት ፡ የሐረርወርቅ ጋሻው ፡ የተባበሩትን መንግስታት ድርጅትን ፡ ድህነትን ለማጥፋት ፡ የሚደረገውን ዘመቻ ፡ መፈክር ይዛ እንድትነሳ ፡ በተጠየቀችው መሰረት ፡ የምርጫዋን ይዛ ፡ የተነሳችውና ለዶክተር ካሪም የእንክዋን ደህና መጡ አቀባበል ፎቶግራፍ። ፎቶ በማይክል ዌብስተር ዩኤን።
Below, Yeharerwerk Gashaw, Actress and International Human Rights Activist,
welcoming Dr. Kerim of UN.
Pictures by Michael Webster UN