(Ethiopian Natioanl Govenment In Exile)
Founded in Dallas Texas in 2008 Legally.
Dallas, Texas U.S.A
July 3, 2015
ይፋ
መግለጫ።
ከፕሬዘደንት
ኦባማ ጋር በግልጽ ለመነጋገር:
የኢትዮጵያ በሔራዊ
የስዴት መንግስት ከፕሬዘደንት በራክ ኦባማና ከአምስት የአሜርካን መክር ቤት አባሎች ጋር የኢትዮጵያና ሕዝብዋን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በይፋ ለመነጋገር ባቀረበው የሃያ ደቂቃ ቀጠሮ ጥያቄ መሰረት ፡ መልሳቸውን እየተጠባበቀና እየተከታተለ መሆኑን ለጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስታውቃል።
የስዴቱ መንግስት
ለመነጋገር ካቀረባቸው የመነጋገርያ ነጥቦች መሃል አንደኛ፡ ስለ ፕሬዘደንት ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ እቅዳቸውን እንዲሰርዙ። ሁለተኛ፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ተደረገ የተባለውን የዚህ ዓመት ምርጫ ፡ የሃሰት ምርጫ ከመሆኑ በተጨባጭ ፡ የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ተወዳዳሪውም፡ አሸናፊዎችም 100% ፡ ለማሸነፉም አጽዳቂ በጠመንጃ በማስፈራራትና በመግደል ላይ የተፈጸመ በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መግንስት እንዳልተቀበለ። ሶስተኛ፡ በግፍ በትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ስለተገደሉት የተቃዋሚ ፓርትይ ተወዳዳሪዎች፡ አባላትና መሪዎች። አራተኛ፡ በእስር ላይ እየተሰቃዩ ስላሉት ጋዜጠኞችና የፓለቲካ
እስረኞች ይለቀቁ የሚል ጥያቄን ያካተተ አርስቶች ይገኙበታል።
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት የአሜሪካን ሕግ በሚፈቅደው መሰረት በሕግ ተመዝግቦ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2000 የምርጫ ዘጠና ሰባትን ድል ተቀዳጅቶ የነበረው የድሉ ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአገር ቤትም ይሁን በውጪ ያለው እንደተደሰተ ያህል ፡ ብዙም ሳይቆይ በማግስቱ ድሉን ሲቀማ በአገር ቤትም በውጪም የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሞራሉ ያልወደቀ ተስፋ ያልቆረጠ ሰው አልነበረም። በመሆኑም ለኢትዮጵያና ሕዝብዋ መብት የሚቆም አንድም ድርጅት የሚነቃነቅ በጊዜው በመጥፋቱ ፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ የድሉ ባለቤትነቱን መልሶ እንዲረከብ በማሰብ "የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት" በሚል ሕጋዊ እውቅና ያለው የስዴት መንግስት ማቁዋቁዋም ብቸኛውና ትክክለኛው አማራጭ ነበር። በመሆኑም የስዴቱ
መንግስት ብዙ አተዋጽዎ አድርግዋል እስከዛሬ። አሁንም ልክ እንደምርጫ ዘጠና ሰባት የሕዝቡ ሞራል ከመነካቱም ባሻገር በሃዘን ላይ ሃዘን ስለተደራረበበት፡ ልጆቹም በአይሰስ ፋሽስት ስለታረዱበት፡ በመትረየስም ስለተፈጁበት፡ በየመንም ስላለቁበት፡ መከራውን መሸከም አቅቶት የወገን ያለህ እያለ በሚገኝበት ጊዜ የለመደው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት የ2015 ምርጫ አሸናፊንኝ ፡ መቶ በመቶ አሸነፍኩ በሚል ሕዝቡና አገሪቱ ላይ ተፈናጦ ማን ያነቃንቀኛል በሚል የሕዝቡ ሃዘን ላይ ሌላ ከባድ ሃዘን አከናነበው። ታሪክ የጣለብን ሃላፊነት ነውና ግዴታ የኢትዮጵያንና የሕዝብዋን ችግር አንጋፋ ድርጅቶች ጥሪያችንን ተቀብለው በቅርብ የትግሉን ሜዳ በሕዝቡና በአዲሱ ትውልድ አድሰው ትግሉን እስኪጀምሩ ድረስ ሜዳላይ የአገርና የሕዝብ ጉዳይ ስለማይጣል ሃላፊነት ተረካቢው እስኪመጣ በቅርብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ስራውን በመቀጠል የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት በሚያደርገው በማንኛውም ስምምነትና ውሳኔ ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ የማይወክል መሆኑን ለአሜሪካንም ይሁን ለአለም መንግስታት ብሎም የንግድ ድርጅቶች ጭምር ውላቸው በሕዝቡ በኩል ቦታ እንደሌለው እናስታውቃለን ለአገሪቱና ለሕዝቡ እንቆማለን።
በዚህ አጋጣሚ የአንጋፋ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ድርጅቶች በስምምነት አንድ ወጥ የሆነ የፓለቲካ ድርጅት በማቁዋቁዋም ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን ከትግራይ ነፃ አውጪና ከግብር አበሮቹ እጅ ነጻ እንዲያወጡት፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት አንጋፋዎቹን እያነጋገረ መሆኑን ይገልጣል።
የኢትዮጵያም
ሕዝብ እነዚህ አንጋፋ ድርጅቶችና መሪዎቻቸውን በከፍተኛ የድረሱልን ጥሪ ጮሆ እየጠራቸው ይገኛል። እነሱም ሕዝቡን ሊያዳምጡትና ሊሰሙት ይገባል። አንጋፋ ድርጅቶች እንደሚታወቀው አራት ናቸው ሚኤሶን፡ ኢፒአርፕ፡ መድህንና የመላው ኢትዮጵያ።
አንጋፋ ድርጅቶቹ እንደ ወርቅ አንባር ተጨፍልቀው አንድ ድርጅት ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን ነፃ አውጪ ድርጅት እንዳቁዋቁዋሙ፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ድርጅቱን አስረክቦ ባዶ ሜዳላይ ተጥሎ የነበረውን የኢትዮጵያንና የሕዝብዋን ጉዳይ ክብርና ሞራል ቀና በማድረግ የሰራውን ታሪክ ለወጣቱ ትውልድ እዲተላለፍና ለወደፊትም ትምህርት ይሆነው ዘንድ ለሚተካው ትውልድ በሕጋዊ መንገድ እንደሚያስረክብ ያስታውቃል።
ኢትዮጵያና ሕዝብዋ አንድነታቸውንና ነጻነታቸውን አስከብረው ለዘለዓለም ይኖራሉ።
የኢትዮጵያወርቅ
ጋሻው (የሐርርወርቅ)
መስራችና
ሊቀመንበር።
For more information please, visit dfwethiopiancommunity.blogspot.com