Tuesday, June 16, 2015

አሁንም በእውነት በእኛ ስም ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ እንዲገታ፤ እንጠይቃለን፡፡ By Ethiopian Refugees in Yemen to all Ethiopians/ሌላው በስማችን ገንዘብ ለመሰብሰብ ከሚሯሯጥ ቅድሚያ የማዳን ስራ ለምን ሊሰሩ አላሰቡም፡፡

  •  በየመን የኢትዮጵያ ስዴተኞች ኮሚቲ ሳና።

  • አለም አቀፍ መግለጫ 
  • ከሳውዲ ወደ የመን የገቡትም እኛም በየመን የቆየነው ከአንዱም የኢትዮጵያ ድርጅት በስማችን ገንዘብ ከሰበሰቡት እንክዋን ገንዘብ ልናገኝ ገንዘብ ሲሰበስቡም ይሁን ሲጣሉ በስማችን እራሳቸው ወስነው ባቁዋቁዋሙት ኮሚቲ እንጂ እኛን የጨመረ ምንም አይነት ውሳኔም ይሁን የሃሳብ ውጥን አነጋግረውን እንዳለሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ እኛን ለመርዳት ነው ሲሉት ለሚለግሰው ሁሉ ማሳወቅ እንወዳለን። 
ቀመጫው በሰሜን አሜሪካን የሆነው
 "Worldwide Ethiopian Refugees' Rights Advocate Group USA (Founded in September 15, 1983 in Dallas, Texas፣ by Actress & Human Rights Activist Yeharerwerk Gashaw Phone # 214-642-0394.email: yehar9@aol.com" ነው፡፡ በቁርጥ ቀን ከጎናችን በመሆን አይዟችሁ እኛ አለን ከሚለው በሞራል ጀምሮ ሌት ተቀን አብሮን እየደከመ እኛን ካለንበት ለማውጣት እያደረገ ያለውን ትብብር እያደነቅን ብቸኛ አማራጫችን መሆኑን ልናስታውቅ እንወዳለን። ምክንያቱን ሁሉም በየአቅጣጫው ሊሮጥልን ሲገባ ብቸኛ አለን ከጎናችሁ ባይ እነሱ ሆነዋል፡፡

በአሁን ሰአት በተለያየ የአለም ክፍሎች ተበትነው ካሉ ወገኖቻችን በእኛ ስም ገንዘብ ለማሰባሰብ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ መሆኑን በመስማታችን፣ በመረጃም በማረጋገጣችን በጣም አዝነናል። ቀደም ባሉት የተለያዩ መግለጫዎቻችን የገንዘብ እርዳታ ሳይሆን ህይወታችንን የማዳን ለጊዜውም ቢሆን ወደ ሌላ የምንጠለልበት ቦታከተቻለም በትብብር ዘላቂ መፍትሄ ፈልጉልን በሚል ጥሪያችንን አሰምተናል። (በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃኖች ላይ በነበረኝ ቃለ-መጠይቅም ይህንኑ ገልጫለሁ) የገንዘብ እርዳታ በአሁን ሰአት ያላስፈላጊነቱ እሙን ነው። በቅርቡ በደረሰን መረጃ በአሜሪካን አገር በቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማና አካባቢዋ በእኛ ስም በአሜሪካን ዶላር እያንዳንዱ ትኬት $100 (መቶ ዶላር)የሚያወጣ በግልጽ በአደባባይ እየተሸጠ መሆኑ ነው። ለምን? ችግር የለብንም እያልኩ አይደለም፡፡ በጦርነት እየረገፍን በአየር ድብደባው ቤት ንብረታችንን እያጣን እየተሰደድን እየሞትን ነው፡፡ ታዲያ ለዚህ ችግር መፍትሄው ምንድን ነው ገንዘብ? ለምን ህይወት ማዳን አይሞከርም?

የመን ያለን ስደተኞች ኮሚቴ በድጋሚ አበክረን የምናስታውቀው እኛ ችግሩ ከፍቶ በመራብም፣ በጥይትም ከምንሞት በሚያስፈልገን ጊዜ የገንዘብ እርዳታውን ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡ በምን መልኩ ተደራጅቶ እንዲሰባሰብ የምናስታውቅበትና አለማቀፋዊ መግለጫም የምናውጣበት ጊዜ ይኖራል፡፡ "Worldwide Ethiopian Refugees' Rights Advocate Group USA Dallas, Texas USA" በኩል የሚገለጽ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን። አሁንም በእውነት በእኛ ስም ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ እንዲገታ፤ እንጠይቃለን፡፡ "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንደሚባለው የሁላችሁም የኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሕብረትና አንድነት እኛን የኢትዮጵያን ስደተኞችን ወደ ዘላቂው መፍትሄ ታሸጋግሩናላችሁ የሚለው እምነታችን የጠበቀ ነው። ለዚህም አላማ ከዚህ እኛን አለሁ ብሎ ጉዳያችንን እየተከታተለልን ካው ኮሚቴ ጋር እንድትተባበሩ ወገናዊ ድጋፋችሁንም በሚያስፈልገው መልኩ ብታደርጉልን ስንል እንጠይቃለን፡፡ ኢትዮጵያ አገራችንና ሕዝብዋን ፈጣሪ ይጠብቅልን።
የመን ያለን ኢትዮጵያዊ ስደተኞች

የመን ያለውን የስዴተኞች ኮሚቲ ለማግኘት በኢሜል አድራሻችን ጻፉልን girum_tekl@yahoo.com 

ከምስጋና ጋር ግሩም ተክለሃይማኖት 
ሊቀመንበር
የመን ሳና ።