የስዴተኛው ሲኖዶስ ዋና ጽሕፈት ቤትና የፓትሪያርካችን የብጹህ አቡነ መርቆሪዮስ መኖሪያን ለመስራት እንተባበር!!!!
ከየሐርርወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያወርቅ)
ትክክለኛውን በስዴት የሚገኘውን በብጹህ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራውን
ሲኖዶስ ፡ ሲኖዶሴ ብለው ምርጫቸው ካደረጉት ምእመናን
አንድዋና በዳላስ የቅዱስ ሚካኤል ደብር አባል።
ፕሌኖ ቴክሳስ።
የውጪው ሲኖዶስና ፓትሪያርካችን ቁዋሚ ቦታ ስለሚያስፈልጋቸው ባስቸክዋይ እየተደረገ ላለው የገንዘብ መዋጮና ድጋፍ የዳላስ ፎርት ውርዝ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ገነዘብ በማዋጣት እንደአቅማችን የግንባታው ገንቢ መሆን ይጠበቅብናል። ስለሆነም በተለይ ዳላስ ፎርት ውርዝ ለምትኖሩና በቅዱስ ሚካኤል ደብር የምታስቀድሱ ታስታውሱ እንደሆነ አንድ ሚሊዮን ዶላር የቤተክርሲያኑን እዳ ከፈልን ተብሎ በመድረክ ላይ በጊዜው የነበረው የቤተክርስቲያኑ ሊቀምንበር ሲያስረዳን ያላጨበጨብን አልነበረንም። ቀጠልም አድርጎ በግራማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ተሹመው የሃያማኖታችን አባት በመሆን በውጪ ብዙ የኖሩት ብጹህ አቡነ ይስሃቅን የቤተክርስቲያኑ ሰገነት ላይ ተቀምጠው እንዳለ ለሳቸው የቤት ክራይ የሚከፍሉላቸው ጃማይካውያን ወገኖቻችንነንደሆኑና አቡኑ ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸው ተነገረን። ሆኖም በተለመደው ዝም ከማለት ሌላ የቦርዱን መልክት ሰምቶ ለሃያማኖት አባታችንና ቤተክርስቲያኑም ቢሆን በሳቸው አባትነት ስር እንደነበረ የማይካድ ነው። ይሄውም የሃያማኖት አዋቂዎች የተባሉት በእንግድነት የመጡት በጥቅሉ እነ ዶክተር ጌታቸው ሃይሌ ሳይቀሩ የሰሞት ነው ከእነም እመናኑ ማለት ነው ያየማይረሳ ሃቅ ነው። ሆኖም ብዙዎች ዝም ቢሉም ከዚህ በታች ያለውን እዛው ከምእመናኑ መሃል ተነስቼ ያልኩትንና ውጤቱን ልገልጽ እወዳለሁ ለሁሉም ጊዜ አለው እንደተባለው ዛሬ ደግሞ ካለፈው በመነሳት ለአሁኑ መልካም ስራ ይጠቅማል በሚል ነው ያለፈውን የማሳስባችሁ። ይሄውም ለእኔ ሳይሆን ለሁላችንም ስለምናምንበት ስለፈጠረን አምላክ ነው።
"ሻለቃ ክፍሌ፡ በጣም ያሳዝናል የሃይማኖታችንን አባት ሰገነት ላይ አስቀምጣችሁ ስለ አንድ ሚሊዮን ቤተክርስቲያን መግዛትና መክፈል ታወራላችሁ? ለመሆኑ ዋናው የሃይማኖታችን አስተማሪ አቡኑ ለቤት ኪራይ የሚከፍሉት አጥተው ጃማይካውያን እየከፈሉላቸው ነው ስትሉን ዛሬ ያሳዝናል። ጃማይካዎያን እየከፈሉላቸው እየተቸገሩ እንዴት ይኖራሉ እኛ ሁሉ እያለን? ለምን ይሄ ጉዳይ አልተነገረንም? ምንድነው ለቤተክርስቲያን ግንብ መግዛት የሃያማኖት አባቱ ያለሃሳብ የሚያገለግሉበት የሚኖሩበት መኖሪያ ሳይኖራቸው? አሁኑኑ ዛሬውኑ እዚህ ሁላችን ባለንበት ለአባታችን (አቡነ ይስሃቅ) ወራዊ ውጪ ከሕዝብ ሳይሆን በቀጥታ ከቤተክርስቲያኑ ከሚካኤልና ከሌሎችም ከተሞች ወጪ ተወስኖ እንዲላክላቸው እንዲወሰን አሳስባለሁ!!! ሕዝቡም ለቤተክርስቲያኑ ገንዘብ በመስጠት የአቡናችን በውጪ አገር ተወካያችን በመሆናቸው ጭምር ይሄን ተገንዘቦ አቡን ይስሃቅ በምድር ላይ ስለገንዘብ ፈጽሞ ስለ ቤትኪራይም ይሁንሌላ ወጪ ማሰብ አይገባቸውም!!"
ከላይ ያለውን ከእንባ ጋር ተናገርኩኝ። ያጥያቄ ነበር ለሃይማኖት አባታችን ለብጹህ አቡነ ይስሃቅ ደሞዝ ያስወሰነላቸውና ሌሎቹም የሃይማኖት አባቶች ደሞዝ አስፈላጊነቱ ልማድ ሆኖ ያስቀጠለው።
አሁንም ዝም ብሎ መቀመጥ ሳይሆን ከሁላችንም የሚጠበቀው፡ ወይም ጥቂቶች በሚያዋጡትና በሚረዱት እሁድ እሁድ ቤተክርሲያን ተጠቃሚ መሆን ሳይሆን፡ ልክ ሞርጌጅ ወይም የቤት እዳ በእየወሩ ወይም መኪና እዳ በየወሩ እንደሚከፈለው ሁሉ ቅድሚያውን ለቤተክርስቲያን በመስጠት እንደእያቅማችን በምንችለው የፓትሪያርካችንን ወጪና ዋና የውጪው ሲኖዶስ መኖሪያ ከእነ ጽሕፈት ቤቱ ማሰራት ይገባናል። ለዚሁም እስክንጠራ መጠበቅ የለብንም እንዴት እራዳታ እንስጥ? ለማን ወዴት? የሚለውንና ቤተክርስቲያን በአካባቢያችን ያለን ደግሞ ለምሳሌ ለቅዱስ ሚካኤል ደብር ዳላስ ቦርድ የገንዘብ መዋጪ ዝግጅት የሚያዘጋጅ ኮሚቲ ባስቸክዋይ እንዲመርጡና ሁላችንም ተሳታፊ በመሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የስዴተኛው ሲኖዶስ ዋና ጽሕፈት ቤት ግንባታ ሃይል እንደንሆን አሳስባለሁ ። አሜን!!!