Tuesday, April 16, 2013

የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በዳላስና አመሰራረቱ (ዛሬ በጋርላንድ የቅዱስ ሚካኤል ደብር)



በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

በየሐረርወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያወርቅ)
ዳላስ ቴክሳስ።

ቁጥር አንድ።

ከዚህ በታች ያለውን ዘገባ ሊያስነሳ የቻለው ከአንዱ ከቀድሞ የቤተክርስቲያኑ ሊቀመንበርና የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ተገዝቶ እዳውን ከጨረሰ በሁዋላ በመጣ ግለሰብ ጭምር የተሰነዘረው አወዛጋቢ አባባል ከዚህ በታች እንደሚነበበው ነው። ይሄውም በቀኑ አሁን ባለው የቅዱስ ሚካኤል ደብር ቦርድ አማካኝነት፡ ሁለት አርእት የያዘ ስብሰባ ተጠርቶ ነበር። በገለልተኛ ወይስ አባት ይኑረን? ማለትም በሲኖዶስ ወይስ ያለ ሲኖዶስ ማልት ሲሆን ጉዳዩን ለማታውቁት አንባቢዎች ግልጽ እንዲሆን፡ በዚህ ስብሰባ ላይ በመገኘት የቀድሞው የቤተክርስቲያኑ ፕሬዘደንት የነበረው በበኩሉ ተነስቶ በስብሰባው ላይ አዲስ ወደ ዳላስ የመጣችሁትም ሁኑ በዳላስ የቆያችሁት በጊዜው ብትኖሩም የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሲቁዋቁዋም ምንም የምታውቁት ነገር የላችሁም በሚል ቁጣና ክህደት የተሞላበት አስተያየቱን ተናገረ።  

ሁለተኛ ግለሰብና ሌላው የቅዱስ ሚካኤል ደብር በሂሳብ ክፍል ተቀጥሮ በደሞዝ የሚሰራ ነው ተብሎ የተነገረን በበጎ ፍቃድ የሚያገለግል ነበር ብዙዎቻችን የሚመስለን እናም በቀኑ በስብሰባው ቦታ የተገኘበትን ዋና መክኒያት ሲያስተጋባው ለማመን ብዙዎቻችን እንደተቸገርን በመገረም የማያጠያይቅ ሃቅ ነው። ከተናገራቸው ሁለቱንና ዋና ዋና አስገራሚዎችን ብቻ ሃሳቦቹን ብቻ ለመጥቀስ ግልጽ እንዲሆን በቦታ ላልነበራችሁት ይረዳ ዘንድ፡ ግለሰቡ እጁን አውጥቶ የመናገሪያ ጊዜ እንደማንኛውም የቤተክርስቲያኑ አባል ጊዜ ጠይቆ ሲሰጠው የተናገራቸው ከባድና አሳዛኝ ከፋፋይ መርዝ የሆኑ ከእውነት የራቁ የምስክርንት ቃል ነበር። ይሄውም "እኔ የመጣሁት ምስክርነት ልሰጥ ነው !!!" ሲል፡ በበኩሌ አምላክ ላደረገለት ደግ ነገር እንደማንኛውም አማኝ ስለ ፈጣሪያችን እየሱስ ክርስቶስ ደግነት ሊመሰክር ነው የመሰለኝ እንጂ ስለ ግለሰቦች አልነበረም ። ቀጥሎም የቅዱስ ሚካኤል ደብር የአስራ ሁለት ሰዎች መሆኑንና ከአዲስ አበባ ለእረፍት ወደ ዳላስ በመጣበት ጊዜ ቀደም ሲል አመተምህረቱን ጠቅሦ በደንብ አንከባክበው ያስተናገዱት በጊዜው የነበሩት የቦርድ አባሎች ስለነበሩ ቤተክርስቲያኑም ግለሰቦቹም ለሱ ባለውለታ ስለሆኑ፡ ቀጥሎም ቤተሰቡንም ጠቅልሎም ሲመጣ ወደዚሁ ወደ ዳላስ ብዙ የረዱት በመሆናቸው የቤተክርስቲያኑ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ባለቤቶች እነዚህ የኔ ባለውለታዎች ናቸው አለን። ስብሰባውን በሙሉ ተጀምሮ እስኪጨረስ ቤተክርስቲያኑ በቪዲዮ እየቀዳን ነው ስላሉን በስብሰባው እለት ያልተገኛችሁ በሰፊው መረጃ ለማግኘት ትችሉ ዘንድ የቤተክርስቲያኑን ቦርድ ብትጠይቁና ተጨባጭ መረጃውን ብታዩ ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ። ለዛሬ ግን ሌሎች ጥያቄዎቻችሁን ወደ ጎን አስቀምጬ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሁዋላ ደብር እንዴት ተመሰረተ ወደ ሚለው ብቻ እወስዳችሁዋለሁ።  

ከዚህ በታች አቶ ታደሰ ግዛው ነብሳቸውን ይማረውና ፈጣሪያችን ፤ ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን መመስረትን አስመልክቶ በስልክ ጥሪ አድርገውልኝ ሴት ልጃቸው ቤት አለን ቴክሳስ ይኖሩ ወደ ነበረው ቤት ሄጄ የቁርስ መብያው ጠረቤዛ ዙሪያ ተቀምጠን ተንትነው በሳቸው በኩል ያለውን በሙሉ ልጽፍ ችያለሁ።

የሐረርወርቅ ጥያቄ፡
ጋሼ ታደሰ እኔ እስከማውቅ ማለትም አቶ ታደሰ ጸሃዬን አስመልክቶ የዛሬውን አያድርገው እንጂ ለሁሉም ኢትዮጵያዊና ለአንድ ኢትዮጵያ ተቆርቁዋሪ እንጂ የአንድ ጎሳ ድምጽና አጋር አልነበረም እኔ እስከገባኝ ድረስ በጊዜው። ይሄንን ስል በወሬ ሳይሆን እራሴ ከማውቀው በተግባር ከማውቀው ነው ይሄውም፡ አቶ ታደሰ ጸሃዬ በየጊዜው እየደወለልኝ ኢትዮጵያውያን ላይ አደጋ ሲጣል በእየሱቁ ፡ ድምጽ እንድሆን ወይም እንድቆምላቸው እንደሚደውለው ሁሉ አዲስ ከተለመደው የተለየ ሌላ ትልቅ ቁም ነገር ይዞ ይደውልልኛል። ይሄውም ከተናገራቸውም መሃል ለእርሶ ለማስረዳት "ቤተክርስቲያን መግዛት አለብን ለዚህም ገንዘብ ባስቸክዋይ አስፈላጊ ነው ባንች በኩል ለሕብረተሰቡ ለምታውቂው ጭምር የዚህን ጉዳይ የሕዝብ ግንኙነት አድርገሽ የገንዘብ እርዳታ እንዲያደርጉ አስተባብሪ ቤተክርስቲያን አግኝቻለሁ ገንዘብ ነው የሚያስፈልገው" አለኝ። እኔም ሃሳቡን ተቀብዬ ወዲያው በተግባር እንዳለው ማድረግ ጀመርኩኝ ማለት ነው። በበኩሌ ቤተክርስቲያን እንግዛ ብሎ እናንተን ያሰባሰበው ይሄው ታደሰ ጸሃዬ ነው። በእርሶ በኩል ከዚህ የተለየ አለ?

መልስ፡ አቶ ታደሰ ግዛው
"አዎን ሃሳቡን ያመጣው እንዳልሽው ታደሰ ጸሃዬ ነው ይሄውም የራሺያው ቤተክርስቲያን ውስጥ ልጆቻችንን ቄሱ ሲያመናጭቃቸው ስላዬ ተናዶ እዛው ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ወዲያው ሰውዬው አይወደንም ለምን የራሳችንን ቤተክርስቲያን አንገዛም በሚል በቁጪት የተነሳው። በዚህ መልክ እኔም ተስማማሁ ዮሴፍንም አነጋገርን ሌሎችንም አሰባሰብን ማለት ነው።

የሐረርወርቅ ጥያቄ፡
በገንዘብ በኩል እናንተስ ያዋጣችሁትን አልሰማሁም ገንዘብ እርሶስ ስንት አወጡ?

መልስ አቶ ታደሰ ግዛው፡
ሳቅ ብለው "እረ የለም! ቤተክርስቲያን ሲገኝ ቦታው መጥፎ ነው በሚል ያስቸገሩ ነበሩ በተለይ ወይዘሮ--- ሆኖም አቅማችን አልፈቀደም ሌላ ቦታ በመጨረሻ ታደሰ ጸሃዬ ኪንግ ስትሪት ላይ ያገኘንውን ቤተክርስቲያን ገዝተን ለማደስና ለማጽዳት ወሰንን። አደገኛ ነው የጥቁር ሰፈር ነው በሚል ብዙ ውጣ ውረድ ደረሰብን ሆኖም ይሄንን ለመግዛት መጀመሪያ አየንውና አንዳንድ ሺ ዶላር እንሰጣለን ብለን ነበር። ሆኖም እኛም ሳናዋጣ ሕዝቡ ባዋጣው በአንድ ቀን አባ ፍቅረማሪያምን ይዘን በመዞር በእየነጋዴው ሱቅ ጭምር የመነኩሴው መኖር እምነትም በሁሉም ሰላሳደረ ሁሉም ተባበረን በዚህ መልክ ተገዛ እንጂ ከመሃላችን አውጦ ገንዘብ የሰጠ አልነበረም"

የሐረርወርቅ ጋሻው ጥያቄ፡
ዮሴፍ ሚካኤል ይባል ቤተክርስቲያን ያለው ማነው?

መልስ አቶ ዮሴፍ ረታ፡
ስሙን አሁን አላስታውስም ነገር ግን እሱንና አቡነ ጳውሎስን ይዤ መኪና ውስጥ እየሄድን እያለን፡ እሱ ነው ለምን ሚካኤል አትሉትም የሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚል በሌላም ከተሞች የለም ያለው ከዚሁ ሰው ነው ሃሳቡ ሚካኤል ይባል የሚለው የመጣው። አቡነ ጳውሎስም ጥሩ ሃሳብ ነው ብለው ሚካኤል በሉት የምትገዙትን ቤተክርስቲያን አሉ እዛው መኪና ውስጥ።"

በሚቀጥለው በዙሁ መልክ ቀንጨብ አድርጌ እካስነብባችሁ በተከታታይ እንዳስፈላጊነቱ አንደኛ ቤተክርስቲያኑ የክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን እስልምና ሃያማኖት ተከታዮች ሳይቀሩ ባዋጡት ገንዘብ የተገዛ ነው።

በእርግጥ የቅዱስ ሚካኤልን ቤተክርስቲያን ባለቤት ሕዝቡ አዋጥቶ የገዛው መሆኑ ሃቅ ቢሆንም ዝም ብሎ የተገዛ ያለመሆኑንም በመረዳት የቤተክርስቲያን ባለቤቶች ያደረጉንን የምስጋና ቀን በማዘጋጀት እግዚአብሄር ይስጥልን ልንል ይገባል ይሄንን ለማድረግ ሰው ሲሞት መጠብቅ የለበትም አሁን ነው ጊዜ። የሰሩ ሰዎችን በሰሩት ቦታ ተቀምጠን ውለታቸውንም መብላት መካድ ስለሚሆንብን የቅዱስ ሚካኤል ደብር አባላትን ሁሉ ማሳሰብ እወዳለሁ።

አሰቃቂ ነገር። የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሕይወቱ ታሪክ ማህድር ምን በላው?

የሕይወት ታሪክ ያልኩት አማርኛው ጠፍቶኝ ሳይሆን ቤተክርስቲያን ለሕይወታችን በመንፈስ ሕይወታችንን ውሃ የምታጠጣ እራስዋ ሕይወት ነች ብዬ ስለማምን ነው።

ከትክክለና የቦርድ አመራረጥና መረካከብ ልጀምር። በድምጽ ብልጫ መመረጥ እንዳለ ሁሉ ለተመረጠበት ቦታ አንድ ሰው ወይም ስብስብ ከስራው ሃላፊነት ጋር ይሚረከበውም አለ በተለይ፡ መተዳደሪያ፡ እስከተረከበበት ጊዜድረስ አስረካቢው የሰራቸውና ከዛም በፊት ካስረከቡት የተረከበው፡ የተግባርና የድርጅቱ ታሪክ ወይም የቤተክርስቲያኑ ብሎም ገንዘብን ይጨምራል ባጭሩ። ይሄ በተለይ በኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን የተለመደ አይደለም። ይሄውም በመረዳጃ ማህበርም የታየ ነው ስቆ መቶ ምረጡኝ ብሎ ወይም ተግደርድሮ ቦርድ ውስጥ ከገባ በሁዋላ ቦታውላይ ላስቀመጠው ሕዝብ ሳይነግር በስነስርዓት እንዳላደገ ልጅ ከተቀሩት የቦርድ አባላት ካልተስማማ ወይም ሕዝብ ጎጂ መሆናቸውን ሲያውቅ አኩርፎ ቦታውን ጥሎ የመንደር ወሬ በድብቅ እያወራና እያስወራ በሃላፊነት የተረከበውን ሳያስረክብ ለጎጂዎች ቦታ ትሎ ይቀራል። ሕብረተሰቡም እምነት የማይታልብህ ከንቱ አይለውም አይ ጥሎ ወጣ ለምን? ከማለት በስተቀር። ይሄ የተለመደ አሰቃቂ አሰራር ሲሆን መቆም አለበት። በማኩረፍ ወይም መቁዋቁዋም ለተመረጠበት ሰው በቂ ካልሆነና የተረከበውን የማያስረክብ መጠየቅ ይኖርበታል ብቃት የሌላቸውም ሰዎች ቦርድ ውስጥ ባአፈጮሌኔትም ማስገባት አይገባም። የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንም ችግር ከዚህ የተለየ አይደለም ባብዛኛው።

የቅዱስ ሚካኤልን ታሪኩን ከመጀመሪያው ጀምሮ ያለውን ታሪኩንና በየጊዜውም ለቤተክርስቲያኑና ለምእመናኑ ይጠቅማል በሚል ያቀረብናቸው ደብዳቤዎች ሳይቀሩ መወሰድም ይሁን ወይም መሰረቅ የሌለባቸው የዋይት ሃውስ ዶኩመንቶች ሳይቀሩ ውሃ እንደበላቸው ነው የተረዳሁት። እንዴት? ቢባል ሌላውን ልተወውና አባት ይኑረን ወይስ ገለልተኛ ሆነን እንቀጥል በሚል ስብሰባ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ስበሰባ አባላትን ጠርቶን በቦታው ተገኝቼ ስለነበር ከሰማሁዋቸው አሰቃቂ መልሶች አንዱ ከዚህ እንደሚከተለው ነበር።

አንድ ወንድም ተነስተው ቤተክርስቲያኑ በገለልተኛነት እንዲሆን በጊዜው የነበረው ቦርድ ሕዝቡን አማክሮ ወይም ስብሰባ ተጠርቶ በስብሰባ ተወስኖ ነው ወይስ እንዴት ሆኖ ነው በማን ውሳኔ ነው ኢንዲፔንደንት ሊሆን የቻለው? የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። የጠያቂውን ስም ወይም ማን እንደሆኑ አላውቅም በአይን ባያቸው እንጂ ለዚህ ነው አንድ ወንድም ያልክዋቸው።

የቤተክርስቲያኑ ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ ቀጥተኛ መልስ ሰጠ። ይሄውም፡ በበኩሉ ቦርዱም ይሁን እሱ የተረከቡት ምንም ማስረጃ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እንደሌለና በገለልተኛነት የቅዱስ ሚካኤል ደብር እንዲሆን ማን እንደወሰነ ወይም እነማን ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ነው። ይሄንን መልስ ሙሉጌታ ሲሰጥ ቦቦታው የቀድሞው ሊቀመንበር በገለልተኛነት ቤተክርስቲያኑን ለማድረግ የተስማማው እዛው ነበር። ከያዘው ደብተር ላይ መልስ ለመስጠት ሲሞክር ነበር። ጉዳዩ አሰቃቂ ነው። ታዲያ ቤተክርስቲያኑን እነ ሻለቃ ክፍሌ ሙላትና አቶ ምስክር ሲመሩት የአመታዊ የስራ ተግባር ሳይቀር ገና ወደ ቤተክርስቲያኑ ጽፈት ቤት ሲገባ ግድግዳ ላይ ፊትለፊት ይታይ ነበር ብዙ መስሪያ ቤት ውስጥ እንደሚታየው። ያሁሉ አሰራር የትደረሰ?

ያም ሆነ ይህ የቤተክርስቲያኑ የአስተዳደር ሄደትና የወጣ የወረደበት በእርግጠኛ የትነው ያለው? ለምን አሁን ላለው ቦርድ የቤተክርስቲያኑን የታሪክና የተግባር ማህደር ሲጀመር ጀምሮ ያለውን ያለፉት አላስረከቡም ውይም አያስረክቡም? የቤተክርስቲያኑ አካል አይደለም ወይ ታሪኩ? ማን ወሰደው? የት ነው? ምን ሲጥ አደረገው?

ምክር፡
አሁን ያለው ቦርድ በሚገባ ቅደም ተከተሉን የተግባርም ይሁን ታሪካዊ ማህደርን ለሚቀጥለው ቦርድ ማለትም ለወጣቱ ትውልድ ጭምር ጥያቄ ቢቀርብለት የተረከብኩት የለም ብሎ የሚያልፈው ሳይሆን የተላለፈልኝ አኩሪ ስራና ታሪክ ብሎ ቤተክርስቲያኑ ገና ሲገዛ ጀምሮ እስከዛሬ ያለውን ታሪክ ትፈረው ቀጥተኛ አሰራር ማለትም ሁሉንም በተግባር መመዝገብ ልምዱ እንዲሆን ይረዳው ዘንድ የቦርድ አስተዳደር ትክክለኛ የሙያ አሰራርና የመረከብና የማስረከብ ባህሉን ግዴታንም በመቸመር አስተማሪ ለሚቀጠለው ተረካቢ እንዲሆን አሳስባለሁ። በትክክሉ ስራዎች እንዲሰሩ ምክር መስጠትም ትልቅ አስተዋጽዎ መሆኑንም መረዳት ያስፈልጋል። መረከብ እናዳለ ማስረከብም መለመድ ይኖርበታል ግዴታም ነው።

ከዚህ በላይ ያሰፈርኩት ፍቃድህ በመሆኑ ዛሬ አሜን!!!