በየሐረርወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያወርቅ)
My e-mail? yehar9@aol.com
ከዚህ በታች ባለፈው እሁድ በእየሳምንቱ እሁድ ከዋሽንግተን ዲሲ በአቢሲኒያ ሬዲዮ ላይ "ምንይሻላል?” በሚል በሚቀርበው ሬዲዮ ላይ ዛሬ ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን ላጋጠመን ችግር ከብዙ ትግል በሁዋላ መድሃኒት ሆኖ ያገኘሁት ታሪኩን ግልጽ አድርጎ ጎልጉሎ የሚያስተምረው፡ የሚያስረዳው፡ የሚያስነብበው እና ለታሪኩም በመቆም የሚታወቅ ሙሁርን በሰፊው በተገኘው መድረክ ሁሉ ሕዝብ ጆሮ እንዲገባ ማድረግ ነው በመረጃ:: አንድን ሕዝብ በመከፋፈል ነጻ አውጪህ ነኝ እያሉ አማራ ኦሮሞ፡ ትግሬ ፡ ጉራጌ ፡ ወላይታ፡ ከንባታ ወይም ደቡብ ሰሜን እያሉ ሕዝቡን ለሚያወናብዱት ሁሉ ማሸነፊያው ታሪካችንን ማወቅና ለማያውቀው ከላይ እንዳስቀመጥኩት ማሳወቅ ነው በመረጃ። ስለሆነም ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ የታሪካችን መድሃኒት በኢትዮጵያዊነቱ እንጂ በጎሳ በሽታ ያልተነደፈና የጎሳን በሽታ ወይም ቫይረስ መከላከያ በእጁ ያለውን በሬዲዮ ቀርቦ እንዲያክመን በጠየኩት መሰረት የምንይሻላል የሬዲዮ ስርጭትም ባለቤት አቶ አያሌው ብሩም እንደኔው የአንድነት ጉዳይ የሚያንገበግበው በመሆኑ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳን አቅርቦ ነበር። አሁንም በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ ኤፕሪል ሰባት (April 7, 2013)በዋሽንግ
7: PM ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳን እናቀርባለን፡፤ እናቀርባልን ስል ግልጽ ማድረግ የምፈልገው ንገር አለ ይሄውም የምንይሻላል የሬዲዮን ስርጭት በአስተያየት በጣም የተለያየን ሰዎችን ማለትም የወያኔ መንግስትን ስርዓት ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎቹን ብሎም ልንገጠል የሚለውን ጭምር በስልክ በጠረቤዛ ዙሪያ መልክ እያቀረበ አገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቡ ካለው ችግር ለመውጣት የሚያስችለው መፍትሄ ለማግኘት "ምንይሻላል?" በሚል በሃሳብ እርስ በእርሳችን የምንታገልበት የሬዲዮ ስርጪት ሲሆን፡ የሚተላለፈውም "ሬዲዮ አቢሲኒያ" ላይ ማልት ነው። እኔም ከተሰብሳቢዎቹ መሃል ነኝ። ዶክተር ፍቅሬን ለማዳመጥ ከዲሲና አካባቢዎ ውጪ ለምትኖሩ በስልክ ቁጥር 218-862-1300 code 126285 በመደውል ጥያቄም መጠየቅ ትችላላችሁ። ከአካባቢያችሁ ስልኩ ይሰራላችሁ እንደሆነ ለማውቅ በማንኛውም ቀን በመደውል ስልኩን ከእነ ኮዱ እንድትሙክሩት አሳስባለሁ።
በምንይሻላል ላይ የቀረበ ማስትዋወቂያ።
ዛሬ ቀኑ በአሜሪካን አቆጣጠር፡ ማርች ሰላሳ አንድ ሁለትሺ አስራ ሶስት ነው።
የአንድ አገር ሕዝብ ያለፈውን ታሪኩን በደንብ ካላወቀ አንድነቱን ለመነደል ከሚመታበትና ከሚያጋጥመው የውጪም ይሁን የውስጥ ተቀጣሪ ጠላት መቁዋቁዋም አይችልም። በተለይም ኤትኒክ ሰግሪጌሽን ወይም የጎሳ ብሎም የብሄር ክልልን ለማጥፋት መድሃኒቱ ታሪክን ማወቅ ማለትም እራስን ማንነትን ማወቅ ነው። ስለሆነም የዛሬ የምንይሻላል ሬዲዮ ስርጭት በዚህ በኢትዮጵያውያን ማንነትና ታሪክ ላይ በተመሰረተ ትምህርታዊ ገለጻ በተጨባጭ ሊያበረክቱልን ይረዳን ዘንድ እንግዳ የጋበዝነው። ይሄም እንግዳ በብዙ ዘርፉ አይምሮውን በተግባር ላይ የማዋል ችሎታ ያለው፡ የመጀመሪያው በአሜሪካን አገር በአማርኛ የቴሌቪዥን ስርጭት የጀመረና ዋና አዘጋጅና አቅራቢ፡ ፊልምና ቲያትር ደራሲ፡ ተዋንያን ወይም አክተር፡ ፕሮዱሰርና ዳይሬክተርና ክራር እየመታ የአገሩን ታሪክ በሲዲ በሙሁር አቀራረብ ያቀረበ፡ የታሪክና የቁዋንቁዋ ምርምር ብሎም የደራሲዎች ምርምር ፕሮፌሰርንና በተለያየ ቦታ በኢትዮጵያውያንም ይሁን በውጪ ሰዎች እየተጋበዘ በብዙ መድረክና አርእስት ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና የሕዝብዋ ማንነት በመናገር ተሳታፊነቱን ያጠቃልላል። ስለሆነም በበኩሌ ባለ ሁለገብ አይምሮ በዚህ አገር አነጋገር መልቲ ፐርፐዝ ማይንድድ ብዬዋለሁ።
በዛሬው እለት የምናቀርብላችሁ የቀኑ እንግዳችን "ቲኒሹ ልጅ ደራሲ" በሚል የኢትዮጵያ ቴሌቪዢንና ሬዲዮ የዛሬይቱ ኢትዮጵያና እነ አቶ በሁዋላ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እነ አቶ ከበደ እና ሌሎቹም ያደነቁት፡ በልጅነቱ በተፈጥሮ ችሎታው የተደነቀና በድርሰት በደራሲነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይምሮ ውስጥ ተቀርጾ የኖረና አሁንም ቀጥሎበ በመሃላችን የሚገኘውን፡ የአገሩን የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያቆሽሽና የሚያዋርድ ሲነሳ ብሎም ሲመጣ በሙህርንት ጦር እየተዋጋ የኢትዮጵያን አንድነት በማስጠበቅ የታወቀው የታሪካችን አባትም ወንድማችንን ነው። በሌላ በኩል የሶቭየት ሙሁራን እሱን በሕይወት ሳያዩት ነገር ግን ድርሰቱን አንብበውና አይተው "የዛሬ አሌክሳንደር ፑሽኪን አገኘን" በሚል ስራዎቹን ወደ ሞስኮ ለላከው የኢትዮጵያና የሶቪየት ሕብረት ደራሲዎች መሃበር በመጻፍ "ወደ ሶቪየት ላኩልን በጣም ተስፋ ያለው ወጣት ስለሆነ ነጻ ትምህርት ልንሰጠው ወስነናል" በሚል በጠየቁት መሰረት፡ በግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ጊዜ መሆኑ ነው እድሉ ተሰጥቶት ወደ ሞስኮው በመሄድ ሶስት ሺ ደራሲዎች ተወዳድረው አርባ አምስት ተማሪ ብቻ በመቀበል በሚታወቀው ትምህርት ቤት (ዩንቨርስቲ) ከአርባዎቹም አንደኛ በመሆን የከፍተኛውን ትምህርት ሊቀናጅ ችልዋል። መሬት ላራሹ በሚል ለሕዝቡ በቀዳምዊ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከሚታገሉት አንዱ እንደነበረ ቢታወቅም፡ የደርግ ስርዓት እሱ እንዳሰበው ሆኖ ባለማግኘት ወደ ጀርመን በመሄድ ዶክትሬት ድግሬዎን በእናት አገሩ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቁዋንቁዋ በአማርኛ አጥንቶ የዶክትሬት ማእረግ ደርስዋል። ይህ ወንድማችን ብዙ ኢትዮጵያዊ የታሪካችን ጠበቃና ወታደር በሚል የሚጠራው ብዙ ኢትዮጵያዊ በአገር ቤትም በውጪም በአለም ላይ በሚኖርበት ሁሉ ባያየው በነብስ ነገር ግን ስለአገሩ ታሪክ ጥብቅናና አስተማሪነት ስሙን የማያውቅ ብዙም የለም። ይሄውም ወንድማችን ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ይባላል። ስለ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ በዚህች አጭር የማስተዋወቂያ በተሰጠኝ ጊዜ ተናግሬ ልጨርሰው የምችለው አይደለም ልሞክረው ብል እንክዋን አዳጋች ነው ጥቂት ባለመሆኑ ባጭሩ መጸሃፍ ማንበብ ስለሚሆንብኝ ለዛሬ ለማስተውዋወቅ ያህል ለምንይሻላል ሬዲዮ አድማጮች ፡ ነደፍ ነደፍ በማድረግ ከተለያየ ማስረጃዎች የወሰድክዋቸውን ወይም ያገኘሁዋቸውን ፈልጌ ላቀርብ እወዳለሁ። እኔም የቀሰምኩትን ከሱ መጸሃፎችና ብዙ ጊዜ ካቀረባቸው የኢትዮጵያ ተሰምቶ የማናውቀው ታሪክ ጭምር እናንተም እንትጠቀሙ አድማጮች ስለጉዋጉዋሁ ጊዜውን ለአድማጮች ብቆጥብ እወዳለሁ። ሁኑም ከዚህ በታች በብእር የሻይ ማንክያ ያህል ጨልፍ አድርጌ የወሰድኩትን እነሆ።
በሶቪየት ሕብረት በአስራ ሰባት ዘጠኛ ዘጠኝ ተወልዶ በሰው እጅ በአስራ ስምንት መቶ ሰላሳ ሰባት ሕይወቱን ያጣው የኢትዮጵያዊነት ደም ያለው በኢትዮጵያዊነቱም የኮራ የነበረው ትልቁ የሶቪየት ደራሲ አሌክሳንደር ፑሽክን በጊዜው ከደረሳቸው አንደኛ፡ ዘቴል ኦፍ ቤልኪን አስራ ስምንት ሰላሳ፡ ሶሻል ሳይኮሎጅካል ስቶርይ ና። ሁለተኛ፡ ኩዊን ኦፍ ስፓድስ አስራ ሰምንትመቶ ሰላሳ ሶስት፡፡ ሶስተኛ፡ ዘካፕቴንስ ዶውተር አስራ ሰምንት መቶ ሰላሳ ስድስት ከደረሳቸው ጋር የሚወዳደርና እንደውም የሚበልጥ በሚል እራሳቸው የፑሽክንን ታሪክና አስተዋጽዎ ታሪኩ ያደረገው ሶቪየት የዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳንም የተፈጥሮ ችሎታና ጉብዝና ንቃትና ደፋርነት ሳይቀር በማህደራቸው አስቀምጠውት ይገኛል።
ዶክተር ፍቅሬ ድሬ ደዋ ከተማ ተወልዶ እዛው ከአንድ እስከ አስራሁለተኛ ክፍል እድሜው ገና ለሁለተኛ ደረጃ መጨረሻ ሳይደርስ በጠዋቱ ጨርሶ በጊዜው ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ በመግባት ትምህርቱን እየተከታተለ እያለ በድርሰት መጀመሪያ ድሬደዋ ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ሁሉ ማለትም አገር አቀፍ በሚወዳደሩበት የድርሰት ውድድር ተወዳድሮ በአንደኝነት አሸንፋል። የሚደርሳቸው ሁሉ በጋዜጣ ላይ ለሕዝብ ከመቅረባቸውም በተጨማሪ ከእነ አቶ ከበደና አቶ ጸጋዬ ገብረመድህን እኩል በቴለቪዢን እየቀረበ ችሎታውን ለሕዝብ እንደገልጽ እየተጋበዘ በእድሜው ቲኒሽ ነገር ግን በችሎታው ትልቅ የነበረና ታሪኩን ኢትዮጵያ መዝግባለታለች በጊዜው በነበሩት ጎብዝ ኢትዮጵያዊያን ታዳጋ ወጣቶችን ወደ ሁዋላ ሳይሆን ወደ ፊት እንዲያድጉ ባህሪያቸው አድርገው በሚታወቁ ጥሩ ዜጎች። ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ በጀርመን አገር በሚማርበት ጊዜ ለአማርኛ ምርምር የሚረዱት የታሪክ ጥረዛ ወይም ማህደር በጊዜው እንብዛም ባይኖርም ኢትዮጵያ የሌላትንና በእያንዳንዱ የዓለም የታሪክ ክፍል ወይም መጽሃፍ መገኘት የነበረበትን ባለማግኘቱ ፡ ብዙ ይቆጭ ስለነበር ከሱ በሁዋላ ለሚመጣው ተማሪም ይሁን መርማሪ ወይም ታሪክ ጸሃፍ መንገዱን አቅልልዋል። ይሄውም አስፈላጊውን ሁሉ ከተደበቀበት ታሪካችንን እየበረበረ እያወጣ በሚገባ በማስቀመጥ።
ከላይ እንዳልኩት የዶክተር ፍቅሬን ታሪክና በቲንሽ እድሜው በደራሲነት ወደ ራሺያ የደራሲዎች አገርና የታሪክ ቤት ወደ ሆነችው ተመርጦ ከሶስሽ ሰዎች መሃል አሸንፎ ያውም በሰው ቁዋንቁዋ እዛው ሄዶ ተምሮ በሁዋላም እስከ ፔኤች ዲ መድረስ ማለት ብዙ የአማርኛ ቁዋንቁዋ መመርመሪያ ለፒኤች ዲመስሪያ በሌለበት በማይገኘብት ታሪካችንን እንደይገኝ ተደርጎ በሌላ በኩል የራሳችን አገር ሰዎችም ቢሆኑ በማወቅም ይሁን ባላማወቅ ታሪካችንን ከያለበት ፈልገው በአግባቡ ባለማስቀመጣቸው ያንን ሁሉ አርሞና ስረመሰረት አስቀምጦ በእራስ ቁዋንቁዋ ዶክትሬት ድግሪ መስራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በትምህርቱ ውጣ ወርድ ውስጥ ያለፈው ሁሉ የሚያውቀው ነው አንደኛ ከጊዜው በፊት የነቃ ለመባል ያውም በአሮፓውያን።
ስለሆነም በቅርብ በታሪክ ብእሩ ከታገልው ብናስታውስ ፡ ኢትዮጵያና ሕዝብዋ ባጋጠመን የታሪክ ከዳተኞች እራሱ ሕዝቡና አገሪቱ ያስተማርዋችው፡ ከነዚህም መሃል ለገሰ ዜናዊ ወይም መልስ ዜናዊ የፋሲል ግንብ ለኦሮሞ ምኑ ነው እና የአክሱም ሃውልት ለጉራጌ ምኑነው? ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ ናሽናሊስት አይደለም ማለትም ብሄራዊ ስሜት አለው የሚባለው ውሸት ነው ለግሉ የቆመነው ለሚለው የመለስ አነጋገር ለውጪ ሰዎች በሰጠው የጥያቄ መልስ፡ አብዛኛው ከንፈሩን ሲመጥ በተለመደው ነገር ግን ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ይሄንን ሲረዳ ማንም ሳይሆን በጊዜው ግንባር ቀደም ሆኖ በማስረጃ ለመለስ ለራሱ ታሪኩን እንዲያውቅና ሕዝቡንም በመዳፈሩ ይቅርታ እንዲጠይቅ በግልጽ የጻፈለትና ደብዳቤውንም ብዙ ኢትዮጵያው ያነበበው ነው።
ዶክተር ፍቅሬ ከአርባ የበለጡ መጽሃፎችና ድርሰቶች በስራ ላይ ያዋለና አሁንም ለእትም የደረሱ የኢትዮጵያ ታሪክ ከዚህ ቀደም አግኝተንው የማናው ለማሳተም እየተዘጋጀ ነው እንደታተመ ግልጽ ያደርገዋል። ሆኖም ሁለት መጽሃፎች ይቺናት የኔ ምድር the Hidden and Untold History of the Jewish People and Ethiopians የሚለውን በኢሜል አድራሻቸው በመጻፍ ልታገኙ ስለምትችሉ ትልቅ ታሪክና ከተለመደው የብዙ ገጽ የተለየ ባጭሩ በሃምሳ ሶስት ገጽ የተጻፈ ነገር ግን ከአንድሺ ገጽ ያላነሰ መጽሃፍ ሊወጣው የሚችል ታሪክ በልዩ መልኩ ቶሎ ሕዝቡ ታሪኩን ማንበብ ሳይሰለቸው እንዲረዳና እንደገነዘብ አውቆም ለማያውቅ ታሪኩን አስተማሪ እንዲሆን በማሰብ የጻፈው በመሆኑ ሁላችንም እድለኞች ነን። ስለሆነም ገዝታችሁ ታሪካችሁን እንድታዳብሩ አሳስባለሁ። የሃሰት ታሪክ ለሚደቅኑብን ሁሉ አንድነታችንን ለማፍረስ መድሃኒቱ ሃቁን ይዞ መገኘት ብቻ ነው ከእነ ማስረጃው። ዶክተር ፍቅሬ በኢሜል አድራሻው ftolossa@aol.com በመጻፍ ብዙ ለማሳተምና ወደ ሕዝባችን እጅ እንዲገባ ለማድርግ ይረዳው ዘንድ ብሎም ወጪውን ያሳተመበትን እስካሁን ይሸፍንለት ዘንድ ይቺነች የኔምድር የሚለውን ግጥም አዘልዋን ድርሰት አስር ዶላርና the Hidden and Untold History of the Jewish People and Ethiopians አስራ አምስት ዶላር በመላክ በድምሩ በሃያአምስት የአሜሪካን ዶላር መጸሃፎቹን ታገኛላችሁ።
ዶክተር ፍቅሬን ልዩ ከሚያደርገው ነገሮች ባጭሩ።
ዶክተር ፍቅሬ ወደ አሜሪካን አገር ከመጣ በሁዋላ ትዳር መስርቶ የልጅም አባት ነው። ባለቤቱ ዶክተር ማርታ አባተ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለአባቶች እርቅና ሰላም በጣም የምትጥርና በአቡነ መልከጻዲቅ የሚመራውንም ቤተክርስቲያንና ለአባታችን ለአቡነ መልከጻዲቅም ጭምር ታዛኝና አገልጋይ ነች። ወደ ፊት ስለእስዋና ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰላም እርቅን አስመልክቶ በግንባር ቀደምትነው የርቁ ኮሚቲ ጀማሪዎች በመሆናችን በዚህ ጉዳይ ተባባሪዎች ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ፡ ወይዘሮ ዶክተር ማርታ አባተንና ወይዘሮ ኤልሳቤት አብዲሳን በዚሁ ይሬዲዮ ስርጭት በእንግድነት የሚቀርቡበት እድል ይኖራል ብዬ አምናለሁ ይሄንን አስመልክቶ ለአዘጋጅና አቀራቢው ለአቶ አያሌው ብሩ በመተው ውሳኔውን፡ ዶክተር ፍቅሬን ማስተዋወቁን እዚህ ላይ እደመድምና በመጨረሻም ከዚህ በታች እንዳለው በእኔ በኩል በማቀርባቸው ጥያቂዎች አጠቃልላለውሁ።
በመጀመሪያ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ የምንይሻላላን ሳምታዊ የሬዲዮ ስርጭት ግብዣ ተቀብለህ ላለን የጎሳ ችግር መፍትሄ ይሆን ዘንድ ስለታሪካችን እንድታስረዳን ፍቃደኛ ሆነህ በሬዲዮ ዝግጅቱ ላይ ዛሬ በመቅረብህ በሁላችን ስም ሆኜ አመሰግናለሁ። ጥያቄዎቼ አንደኛ እስቲ ስለ ማራ ፡ ማጂ፡ ጅማና ዛሬ አማራ ኦሮሞ ትግሬ ጉራጌ ወዘተ ክልል የሚለው ጋር ግንኙነቱን ለሚወድህ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንድታብራራ እጠይቃለሁ።
ሁለተኛ፡ ኦሮሙኛ በጎጃምና በፋሲል ቤተመንግስት የነበረውን የስራ ቁዋንቁዋነት ላይ ገለጻ ብታደርግልን?
ወንድም አያሌው ቦታውን ላንተ እለቃለሁ አመሰግናለሁ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳን የማስተዋወቁን እድል ስለሰጠህኝ።
Who Is Ethiop? Who is Melketsadik? Where do all ethnic names in Ethiopia including the name Amhara and Oromo came from? Dr. Fikre has all the answer for you. Know who you are and what your history is for real.
The following is copied from Ethiopia.org
"Tolossa, Ph. D., is a poet-playwright, critic, essayist and educator. His latest book entitled,The Hidden and Untold History of the Jewish People and Ethiopians, as well as his original songs that he himself has composed and plays on the Kirar, will be released soon to the public at large. His film in English, “Multi-colored Flowers” was featured with great resonance in the