Monday, April 4, 2011

የኢትዮጵያ አንድነትና የሕዝብዋ ቅንቅኖች በተግባር አንድ ሲሆኑ በስም ሶስት ናቸው።

የዳላስ ንዋሪ ኢትዮጵያዊ በኤፕሪል ዘጠኝ የትግሬ ነጻ አውጪን በቦታው ተገኝቶ እንዳይቃወም ልክ በእውነት ለሕዝብ የቆሙ መስለው ትግሉን ለማኮላሸት የሚከንፉት ሌላ ሃይል መስልዋችሁ ቤታችሁ እንዳትቀመጡ። ያው የተለመዱት ሕዝቡ አንቅሮ የተፋቸው ተባብረን በቦታው በመገኝት መልእክታችንን እግቡ እንዳናደርስ ሚርውርዋጡት ከንቱዎች ናቸው። በሕብረት በቦታው በመገኘት የትግሬ ነጻ አውጭና መለስ ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይ ይውረዱ! ማለት ይጠበቅብናል። ለሚመጡትም ትምህርት መስጠት ይኖርብናል ይሄውም ከትግሬ ነጻ አውጪ የክልልና የጎሳ ዘቤ ተላቀው ስለ አንድ ኢትዮጵያና የሕዝብ እኩልነት መብት ካምፕ እንዲገቡ እዛው በአገር ውስጥ። ከታች የምታገኙት በራሪ ውረቀት በታኞቹ ባለ ጎስት ድርጅቶቹ ለሕዝቡ የፓለቲካ ፓርቲ ማህተም ያለው ድብዳቤ የሚሸጡት ናቸው። ከዚህ ቀደም እድር አይቁዋቁዋም በሚል ስማቸውንና ማንነታቸውን ደብቀው ወረቀት እንዲሁ በመበተን ብዙ ሰው እንዳጋጩ ታውቃላችሁ። አሁንም ወረቀት የበተኑት ኢትዮጵያ በሚል እነሱው መሆናቸውን ተረድተን እነሱን ወደ ታች ጥለን ለአግርችንና ለሕዝቡ መቆም ይገባናል። ስለዚህ ከሕዝብ የተውጣጣ ስብስብ ፈጥረን በቦታው እንገናኝ እያልን እነዚህ መሰሪዎች የሚሰሩትን ከዚህ በታች እንደተመለከቱ እንጋብዛችሁዋለን።

Racial segregation is the separation of humans into racial groups in daily life. It may apply to activities such as eating in a restaurant, drinking from a water fountain, using a bath ወዘተ በሚል የክልልን ምንነትና ፋሽስትነት ተግባር ግልጽ ያደርግልናል የእንግሊዘኛው አባባል። ታዲያ Racial segregation  the separation of humans into racial groups in daily life የሚለው ሊቢያን እያሰጋት ያለውና የትግሬም ነጻ አውጪ መሪ መለስ አረብ ነው ትውልዴ ብሎ  አረብነት ትውልዱን ሃረጉን ቆጥሮ ከጋዳፊ ጋር ሲዛመድ ከገንዘብ ጋር የተረከበው ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን በጎሳ ስም ብሎም ሕዝቡ በአንድ ሰንደቅ አላማው እንክውዋን እንዳይተሳሰር በክልል ባንዲራ ህግ ማለትም segregation flag laws ስራላይ በተግባር መለስና ድርጅቱ የትግራይ ነጻ አውጪ እውን እንዲያደርጉት ነበር። ይሄውም በስራ ላይ በአገራችን ሕዝብ ላይ ተጭኖበት ይገኛል። ይሄንን  በቁም  የቀበረንን የክልል መቃብር ድንጋይ ከላይችንና ከወገናችን ላይ እንዳናነሳ እንቅፋት የሆኑብን  የኢትዮጵያን ሕዝብ የቁም ስቅሉን ሸቀጥ አድርገው እንደ ጤፍ ፡ በርበሬ፡ ቡና በመቸርቸር የኑሮዋቸው ገቢና መዶጎሚያ አድርገው የሚኖሩት ከርሳሞች  በስም ሶስት ሲሆኑ በተግባር ግን አንድ የህኑት ናቸው። ጸረ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና አንድነት ፍቅር ብልጽግና ነቀርሳ በመሆን በዳላስ ቴክሳስ  ያስቸገሩን መሰሎቻቸውና ተቀጥያዎቻቸው በዋሽንግተን ፡ በሚኒሶታ፡ በአትላንታና በስያትል ባጠቃላይ ከኢትዮጵያ ውጪ በየቦታው ስለሚኖሩ አርቆና ተረጋግቶ ላተኮረው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ድብቅ አይደለም ከፋፋይ ተግባራቸው። የኢትዮጵያ አንድነትና የሕዝብዋ ቅንቅኖች በተግባር አንድ ሲሆኑ በስም ሶስት ናቸው። እንዚህም፡ የትግሬ ነጻ አውጪ፡ ደጋፊዎቹ ብሎም ተቃዋሚ ነን በሚል ሽፋን ለመለስም የሚሰሩ በደሞዝ ሲገኙበት ፡ከእነዚህ ጋር አብረው የሚያጫፍሩ ምን እንደሚፈልጉ የማያውቁ ከርስ መሙያ ወደ ነፈሰበት የሚወድቁና ጠላታቸውን ለይተው የማያውቁ ወረቀት ለመበተን መጠቀሚያ የተደረጉና ስምም ለማጉደፍ በስልክ ጭምር መጠቀሚያ የተደረጉ የዋህዎች ወንዶችና ሴቶችም ይገኙባቸዋል። ግማሾቹም ኢትዮጵያ ጉዳያቸውን እናስፈጽምላችሁዋለን ስለሚልዋቸው ደጅ ጠኝዎች መሆናቸው ነው።

ነጻነት ባለበት አሜሪካ ስም ደብቀው ማንነታቸውን ሳያስቀምጡ ከዚህ በታች የበተኑትን ወረቀትና መለክት ተመልከቱ። መልክቱ የእነሱንም ተግባር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ስለሆነ እነዚህ ትግሉን በዳላስ ከተማና በየቦታው ያኮላሹና እያኮላሹ ያሉ በመሆናቸው በሃቀኞች ለኢትዮጵያ አንድነት በታጋይነት ብዙ መስዋእትነትን በከፈልን ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው በተለይ ዳልስ ላይ ሊጋለጥ ችልዋል። እንደሚታወቀው የትግሬ ነጻ አውጬ መንግስትና ባለስልጣኖች በዳላስ ዝር አይሉም ነበር። ለከርሳቸውም በመለስ የተገዙት እንደ አይጥ የተደበቁ ነበሩ ሆኖም እነ ዚህ ዛሬ "የኢትይጵያን ህዝብ እውነትኛ የዲሞክራሲና የነጻነት ትግል እናግዝ" በሚል መለክት አስተላላፊዎች የመለስን ባለስልጣናት ድግስ ከደጋሾች ጋር አንድ በመሆን የሚሰሩና መለስንና ድርጅቱን ከሕዝባችን ትከሻ ላይ ለማውረድ የምንታገለውን ሲታገሉን የነበሩ አህንም ያልተኙልን ጸረ ኢትዮጵያና ሕዝብዋ ናቸው። ለትግሬ ነጻ አውጪ መንግስት ዳላስ መመላለስ የልብ ልብ ማግኘት እነዚሁ ዛሬ ከዚህ በታች የለጠፍነውን መልእክት የበተኑ ጥቂት ሁዋላ ቀሮችና  ከርሳሞች ለትግል አኮላሽነት የተቀጠሩ ናቸው። በዳላስ ለማትኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመግለጽ ነው እንጂ እዚህማ እነዚህን ከንቱዎችና ማንነታቸውን የማያውቅ የለም። ለምሳሌ በዳላስ ማንኛውም ጥሩ ኢትዮጵያዊ ተነስቶሕዝቡንና ወጣቱን ሲያስተባብር ሲያዩ ዛሬ የመለስን ባለስልጣን ሊያመጡ ነው ብለው ወረቀት ከሚበትኑባቸው ጋር ባንድነት ይሆኑና ቡድን ፈጥረው  ስለሕብረታችን እያሰባሰቡ ያሉት መሃል ደጋፊ መስለው ይገቡና በደንብ ካጠኑ በሁዋላ አላማቸውን፡ ይሄንንማ አስመልክቶ ቀደም ሲል የጀመርነው ኮሚቲ ስላለ ለምን እኛ ኮሚቲ ውስጥ ገብታችሁ አብረን አንሰራም አንድ አይነት ሃሳብ ስለሆነ በሚል ኮሚቲውን ይውጡና በቁጥር ስራው የአንድነት ጥቅሙም ሰላሙም እንዳይሰራራ በማድረግ አኮላሽተው ግለስቦቹንም አስከፍተው አበሳጭተው አንድነትን ሰንሰለቱ እንዳይጠብቅ በዳላስ ትልቅ ሚና ለመለስ ሲጫወቱ የኖሩ ናቸው። ጥሩ ምስክር ሻለቃ ተፈራ ወርቅ የተባለውን ከተማውን ገና እንደረገጠ ካዲስ አበባ መጥቶ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብን አንድነት መበታተኛ ብይ አድርገው ለጥፋት ፊት አውራሪ አድርገው በኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ቦርድ ውስጥ እንዲገባና ህዝብ ሳይመርጠው ስብሰባ ሳይደረግ ፕሬዘደንት እንዲሆን ያደረጉት የወያኔ ተቀጣሪ መሆኑን እያወቁ ነበር የተጫወቱት የትግል ማኮላሸትና ለወያኔ በር ማመቻቸት ሚና። የኢትዮጵያ አምላክ ትልቅ ነውና ተፈራ ወርቅና ሌሎቹ ወያኔን ታጋይ ነን በሃሰት ነው የወያኔ ቅጥረኞችና ደጋፊዎች የተባልነው ብለው የመሸታ ቤት ፍርድ ቤት ከፍተው እራሳቸውን ንጹህ አድርገው እንዳልቀረብ የዲያስፖራ ስብሰባ ብሎ መለስ በእያመቱ በሚያዘጋጀው የቅጥረኞቹ ድግስ በአል ላይ በድብቅ ገብተው በቪዲዮ ከተያዙት ከአሜሪካን አንዱ ተፈራ ወርቅ ነበር የሄደውም ከሌሎች ምስያዎቹ ጋር ለሁለት ሳምንት በተከፈለለት ትኬት መሆኑነው።

ሌላው ፡ የጸብም ይሁን የሰላም ድግስ ጥሪ ወረቀት ባለቤት አለው። ነጻነት ባለበት በአሜሪካ ለምንድነው ስም ሳይስቀምጡ ከዚህ በታች ያለውን መልእክት የሚያስተላልፉት? ኢንቪስት ያደረጉትና የሰሩት ቤታቸው እንዳይወረስ ይሁን ወይስ ሕዝቡ አሁንም ያላወቃቸው መስልዋቸው ይሆን? ስማቸውን ደብቀው በሌላ በኩል ስለ አረብ ወንዶች ጀግንነት ያወራሉ ምነው እነሱን ማን ከለከላቸው አረቡን ጭምር ካንበረከኩ ጅግኖች የአግሪቱን አንድነትና ነጻነት በሕይወታቸው ጠብቀው ካስረከቡን ጀግኖች አገር አይደል የተፈጠሩት? ማንነታቸውን ጽፈው የትግሬ ነጻ አውጪንና መለስን እሱን ወክለው የሚመጡትን ኤፕሪል ዘጠኝ እንቃወማለን በሚል በግልጽ መቆም ያልቻሉ አልጫዎች ከርሳሞች ነጋዴዎች ለዴሞክራሲ ቆመናል በሚል በመጻፍ በተለመደው ሕዝብ ሊያታልሉ አይችሉም። ቃሉን እውነተኛ ዲሞክራሲ ብለው የጻፉትን እንክዋን ትርጉሙንና ተግባሩን ገና ያልተረዱ ናቸው። ለዴሞክራሲና ነጻነት የሚታገል፡ ዴሞክራሲ የሰፈነበት አገር ውስጥ አሜሪካን እየኖረ ስሙንና ድርጅቱን እየደበቀ እራሱን ነጻነት ነስቶ ጥሪ አይበትንም።  የአረብ ወንዶች ስለከፈሉትና እይየክፈሉ ስላሉት መስውእትነት ከማዳነቅ ከዶላር ተገዢነትና ካቅም በላይ በመኖር ከሚያስጨንቅ ወራዊ የቤት እዳክፍያ ተላቆ በአቅም እየኖሩ አገርን በገንዘብ ከለዋጭነት ተግባር መላቀቅና ሰርቶ በሃቅ በመኖር ለኢትዮጵያ ለጋራ ቤታችን ነጻነት መሰለፍ ይገባል።  ምን አለበት ስቸውንና የጎስት ድርጅታቸውን ስም በሙሉ ባይጠሩም ከውረቀት በታኞቻቸው መሃል እነ ደጀኔ ነን ቢሉ? ወይም እነ አበበ? እነዚህ ስም የሌለው ድግስ ጠሪዎች እንደሚታወሰው ገና በኦክቶበር ጀምረን የትግሬ ነጻ አውጪ ባለስልጣን ዳላስ ሊመጡ ስለሆነ ምን ማድረግ እንዳለብን ስናቀርብ ሃሰት ነው ብለው ሲያስተባብሉ እንደነበር የማይዘነጋ ነው። ዳላስ ኢኦቲሲ ብሎግም የእነዚህን ትግል አኮላሽ ቡድን ማንነት በየጊዜው የሚያወጣ ስለ ኤፕሪል ስብሰባ ሲያወጣና ከጀርባውም እነዚሁ ትግል አኮላሾቹም እንዳሉበት በገልጽ በማስቀመጡ ደስተኛ አልነበሩም። ለምን ቢባል የትግል ማኮላሸቱን ኮንትራት ስለአዛባባቸው። እነዚህ ግለሰቦች ቅንጅትን አሳርደው ደሙን ከአራጁ ጋር የጠጡና አሁንም ያንኑ ተግባራቸውን በውስኪና በሄንከን ቢራ በመታጀብ ስለ ኢትዮጵያ ግዳይ ታጋይ ነን በሚል የመሸታ ቤት ዲስኩር አድራጊዎችም ናቸው።  እነዚህ ግለሰቦች በሁሉም አቅጣጫ አንድነታችንን በማደፍረስ ተልኮዋቸው በአበመጨረሻም ጸሃፊዎቹ ተቃዋሚ ነን በሚል ስም የሚያጭበረቡትና የትግሬ ነጻ አውጪ የድብቅ ደጋፊዎች፡   የትግሬ ነጻ አውጭም የኢትዮጵያ አንድነትና የሕዝብዋ ቅንቅኖች በተግባር አንድ ሲሆኑ በስም ሶስት ናቸው።

ከዚህ በታች ያለው ከላይ በሶስተኛ ያስቀመጥናቸው የበተኑት ሲሆን የእነሱንም ማንነትና ተግባር ከትግሬ ነጻ አውጪና ከግብረአበሮቹ ደጋፊዎቹ ድርጊት ጋር አንድ በመሆኑ ከድግስ አስተናጋጆቹ ተለየተው የማይታዩ ነገር ግን በስም እንጂ በድርጊት እነሱም ጸረ አንድ ኢትዮጵያ ናቸው። በትክክል ማንነታቸውን የሚገልጽ በመጻፋቸው ብዙ ስለ እነሱና የትግሬ ነጻ አውጪን እያነጻጸርን ከመጻፍ ጊዜአችንን ቆጥበውልናል። ስታነቡት ሶስቱም አንድ መሆናቸውን እንዳትረሱ እናሳስባለን። እነዚህ ግለሰቦች የሕብረተሰባችን አንድነት የጀርባው አጥንት ነቀርሳዎች መረዳጃ ማሕበራችን አስመልክቶ ትልቅ ብጥብጥ እየፈጠሩና መረዳጃ ማሕበሩን ለግል ጥቅማቸው ይዘው መከራ እያበሉ ሕዝቡን ያሉ ናቸው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፈጽሙ የማያስቡ አስመሳይ ነጋዲዎች እንጂ። የመረዳጃ ማሕበሩን ነጻ ለማውጣት አብረናችሁ ነን ብለው ከእውነተኛና ለግል ጥቅም አገራቸውን የማይለውጡ ኢትዮጵያውያን መሃል ገብተው እነማን አብረው እየተባበሩ መሆናቸውን ካረጋገጡ በሁዋላ፡ ሕዝቡ አንድነትና ሰላሙን እየገነባ መሆንኑ ካረጋገጡ በሁዋላ ሚስጥሩን ውስደው የመረዳጃ ቦርዱን መልቀቅ ላለብቸው ለትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች የዶላር ተገዦዎች ጊዚያቸው ዲሲምበር አልፎ እሻፈረኝ ብለው ለተቀመጡት ወስደው ያስረክባሉ። አብረውም በመቆም ከቦታው እንዳይለቁ  አዲስ የእክል መንገድ ይቀይሳሉ። ይሄውም ድርጊታቸው  በሕዝቡ መሃልና ቦታውን አለቅም ቦርድ ኦፍ ትረስቲ አቁዋቁሜ ካልመራሁ በሚለው ቦርድ ትልቅ አደገኛም ሊሆን የሚችል ችግረ የፈጠሩ ናቸው። እነዚህ መለስንና ደጋፊዎቹን ሳይህን አንድነቱን እያስተባበረ ያለውን የዳላስ ሕዝብ ነው በተቃዋሚ ነትሽፋን ስም እየታገሉን ያሉት።

በመጨረሻም ከኦክቶበር ጀምረን ስንሰራ የነበር ነው ኤፕሪል ዘጠኝ ተቃውሞዋችንን አስመልክቶ፡ የስልክ ስብሰባችን ነገም ይቀጥላል አዲስ ፒን ቁጥር ስለምንልክላችሁ በኢሜል ማየት አትርሱ ።

አስጀምሮ አስፈጻሚ አምላክ ምስጋና ይግባህ አሜን።