Monday, April 18, 2011

Thank you ESFANA! Yeharerwerk Gashaw

ሰዎች ጥሩ ሲሰሩም መመስግን ይገባቸዋል።

ይድረስ  ለመላው በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም አውታሮች። ሰዎች ሲሳሳቱ ብቻ ሳይህን ሲሳሳቱ ብቻ ሳይሆን ስለ ስህተታቸው እየተጠቀስ መውቀስ : ጥሩም ሲሰሩ ማመስገን ተገቢና የዴሞክራሲም አስተስሰብ ነው። ስለሆነም ታዲያ ኢስፋና ባንድ ድምጽ ዳኛ ብርቱካንን ለመጋበዝ ሲወስን ምነው ዝም አላችሁ? ይሄ የዴሞክራሲ አሰራርን የተከተለ ስለሆነ ውሳኔው ልናመሰግናቸው ይገባል ወንድሞቻችንን።

ይድረስ ለኢትዮጵያ እስፓርት ፈደሬሽን ምስጋና ወይዘሮ/ዳኛ ብርትኩዋንን የዚህ አመት የክብር እንግዳ አድርጋችሁ ስለመረጣችሁዋቸው። dfwethiopiancommunity.blogspot.com  የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ድህረ ገጽና በራሴም ስም እግዚአብሄር ይስጣችሁ በሚል ምስጋናዬን ዳኛ ብርቱካንን ስለጋበዛችሁ አቀርባለሁ። ልጃቸውን እንደምትጋብዝዋትም እተማመናለሁ። እንዲሁም አዲስ ቡድን ዳላስና ዳላስ ቡድንም የከተማችን ልጆች አበጃችሁ! እላለሁ።
የሐረርወርቅ ጋሻው።

ዛሪ ኤፕሪል አስራ ዘጠኝ የታከለ።
በዚህ አጋጣሚ በአትላንታ ላለፈው አስራ ሁለት አመት የተዋህዶ ድምጽ በሚል በየሳምንት የሬዲዮ ስርጭትና ዝግጅት የሚያቀርቡትን መላአከ ስላም ኤፍሬምን በጣም አመሰግናለሁ። ይሄውም አንደኛ ስለ ፈደሬሽኑ በማሰብ እንዳይፈርስና ወይም ግለስቦች እንዳይወስዱት እንደዚሁም በሰላማዊ መንገድ የፈደሬሽኑን ቦርድ ማነጋገር ሲገባ "ፈደሬሽኑ ይፍረስ!" የሚሉትን ሳይፈሩ በሬዲዮ ስርጭታቸው በመቁዋቁዋም ያደረጉትና ለዚህም እንደረዳ እኔንም በ ዲሴምበር አስራ ዘጠኝ አቅርበውኝ ከዳላስ ስለ ፈደሬሽኑ መኖርና ስለ ዳኛ ብርቱካንም መጋበዝ ቦታ ሰጥተው እንዲጋበዙና  ፈደሬሽኑንም አደጋ እንዳይድርስበት ሕብረተሰቡን ያሳሰቡ በመሆናቸው ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል።
የሐረርወርቅ ጋሻው።



ከዚህ በታች ያለው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ለኢስፋና ወደ ስድስት ወር ገደማ የተላከናለቦርድና ለቡድን ተወካዮች በሙሉ የደረሳቸው ደብዳቤ ነበር።

Sent: Mon, Nov 22, 2010 7:22 pm


የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ከግልጥቅም ነጻ ሆኖ በቴክሳስ የተመዘገበና ሕጋዊ የስዴት መንግስት ነው። በበለጠ ለመረዳት ከዚህ በታች ያለውን ዌብ ሳይት እንዲጉብኙ እንጋብዝዎታለን። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ዳላስ ቴክሳስ አሜሪካ።  
(http://www.ethiopiannationalgovernmentinexile.org/)








ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ የ2011 በኢስፋና የክብር እንግዳ ሆነው መጋበዝ ትክክለኛና ሕጋዊም ነው።
ግልጽ ደብዳቤ።
Nov 22, 2010 በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት የከበረ ስላምታ ለኢትዮጵያ እስፓርት ፈደሬሽን በሰሜን አሜሪካ አመራር (board) አባላት፡ የቡድን ተወካዮችና ቡድኖች ከነሙሉ ተጫዋቾቻው በሙሉ ሲያቀርብ ከልብ በኢትዮጵያዊነት አክብሮት ነው።
የተከበራችሁ ወንዴሞች ሆይ፡ ይችን አጭር ደብዳቤ ለመላክ ያስደገደንና የኛንም ጊዜ ውስደን የእናንተንም ወርቅማ ጌዜ ልንሻማ ያነሳሳን ዋና መክኒያት፡ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። ይሄውም በመጀመሪያ የሁላችንም እህት የሆኑትን ወይዘሮ (ት) ብርቱካን ሚደቅሳን ለሁለት ሺ አስረሃንድ (2011) የክብር እንግዳ አድርጋችሁ ለመጋብዝ የኢስፋና ቦርደ በድምጽ ብልጫ ዴሞክራቲካል በሆነ በሰለጠነው አሰራር የወሰናችሁትን ውሳኔ ስንሰማ በጣም ትልቅ ደስታ ነበር የተሰማን። ብዙም ሳይቆይ ሃሳባችሁ መቀልብሱን ስንሰማ ደግሞ ሃሳባችሁን የለወጣችሁበትን መክኒያት ማጣራት ግዴታ ስለሆነና ትክክለኛም አሰራር በመሆኑ ማጣራት ጀመርን። በመጨረሻም ወይዘሮ ብርቱካንን እንዳይጋበዙ መክኒያት የሆነው ስህተት እንዳለው ስንረዳ፡ መጀመሪያ ወደ ተስማማችሁበት ውሳኔ እንድትመለሱ ልናሳስባችሁ ወሰንን። ስለ ዚህ በትህትና የምናሳስባችሁና የምንጠይቃችሁ ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን ቢቻል ከእነ አራት አመት ልጃቸውና እናታቸው ጭምር እንድትጋብዙ እያሳሰብን አለዚያም ወይዘሮ ብርቱካንን ብቻ በመጋበዝ መጀመሪያ እንደተነገረው  የኢትዮጵያ ሕዝብ የክብር እንግድነቱ ቦታ ለማንም ሳይሰጥ ፡ ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን የ2011 የኢስፋና የክብር እንግዳ ማለትም የዲያስፓራው ኢትዮጵያዊ እንግዳ አድርጋችሁ ከኢትዮጵያ እንድታመጥዋቸው በትልቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ውይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን መጋበዝ በክብር እንግድነት ከኢስፋና ባይሎ መተዳደሪያ ጋር ይጋጫል  ለምትሉት ወንድሞቻችን ማለትና ማካፈል የምንፈልገው ፡ ያሳሰባችሁን ሕጋዊ ጥያቄ አስመልክቶ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። እህታችን ወጣትዋ ወይዘሮ ብርቱካን በክብር እንግዳነት ሊጋበዙ፡ ይገባቸዋልም በሚል ጥያቂያችንን ስናቀርብ ከላይ እንደገለጽነው፡ በኛም በኩል ማለትም በኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስትም (በኢትዮጵያ ሴቶች የተቁዋቁዋመ) የፓለቲካ ጥያቄ ሳይሆን ሕግን የአሜሪካንን ከግል ጥቅም ነጻ ድርጅቶችን ስርአት በመከተል በትክክለ ሕግ ተከተለን ሲሆን፡ በመሆኑም ከፓለቲክ ጋር ጥያቄያችንን እንደማታይይዙትም በመተማመን ነው። የወይዘሮ ብርቱካን በክብር እንግድነት በኢስፋና መጋበዝ ፈጽሞ በአሜሪካን ከ501 (c)(3) ጋር የሚጋጭ አይደለም። ለዚህም ብዙ ማስረጃና ገለጻ ከጠየቃችሁን ልናቀርብ ዝግጁነን። ሆኖም ለዛሬ ባጭሩ ለመግለጽ ያህል ማለት የምንወደው፡ የእስፓርት በአል ላይ ማንኛውም ገለሰብ ወይም የመንግስት አካል ብሎም የፓለቲካ ፓርቲ መሪ ቢጋበዝ 501 (c)(3) ፈጽሞ አይከለክልም። እንደዚህም አይነት የሕግ ድንግጋት የለውም። ማንም ሰው እንዲጋበዝ ይፈቀዳል እንደውም በፓለቲካ፡ በጾታ፡ በብሄር ወይም ጎሳና ሃይማኖት ልዩነት እንዳይኖር ነው የሚለው። የፓለቲካ ፓርቲ መሪናቸው ወይዘሮ ብርቱካን ስለዚህ በክብር እንግድነት ከአዲስ አበባ ጋብዘን በግልጽ ልናመጣ አንችልም የሚለው መክኒያት፡ ከናካቴው እህታችንን ድስክርሚኔት አደረጋችሁ ማለት ነው። ኢስፋናን የሚያስጠይቅ ይሆናልማለት ነው። የምትጋብዝዋቸው ፓለቲክ ሊያወሩ ሳይሆን የእስፓርት በአላችሁ የሕዝብም በመሆኑ በቦታው በታዋቂነታቸው ብዙም ሕዝብ ስለሚወዳቸው በሕዝብ መሃል ተገኝተው የበአሉ ተካፋይ እንዲሆኑ ብቻ ነው። መረሳትም የሌለበት ኢስፋናን ሕዝባዊና ከግል ጥቅምና ከጾታ፡ ከሃይማኖት፡ ከፓለቲካ ልዩነት የሌለው ድርጅት እንዲሆንና ግለሰቦች የግል መጠቀሚያ አድርገውት የጥቂቶች አድርገው በሚሰሩበት ጊዜ የዚህን አይነት ችግር በመፈጠሩ ነበር ከግል ጥቅም ነጻና በሕጋዊ ሕዝባዊ እውቅና እንዲኖረው ታግለን የሕዝብ ያደረግነው ሴቶቹ። ምን ማለት እንደፈለግን http://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/ ግቡና ትናንትና የወጣውን ብታዩት እንዴት ኢስፋና ሕዝባዊ ዴርጅት ሊሆን እንደ ቻለ በግልጽ ያሳያችሁዋል። ወዲያውም ታሪኩን መማር ነው ሴቶች  ለኢስፋና ያደረግነውን አስተዋጽኦና የከፈልነውን መሰዋእትነት። ሆኖም የኢትዮጵያ ሴቶች በመሆናችን የሕዝባዊ እንዲይሆን የታገሉት ወንድች ጀግኖች ተለው እውቅና ሲሰጣቸው የኢስፋና የ501 (c)(3)ባለቤት እንዲሆንና ሕዝቡን ኢስፋና የኔነው የሚለውን ባለቤትነት ያጎናጸፍነውን ፡ የታገልነው ግን አሁንም እንደወንጀለኛ እንቆጠራለን የግል አድርገው ለመኖር አላማቸው በሆኑት። ስለዚህ ኢስፋናንምን ያህል እንዲኖር እንጂ እንዲፈርስ የማንፍልግም መሆናችንን በዚሁ እንድትረዱልን እናሳስባለን። የወይዘሮ ብርቱካንን መጋበዝ በኢስፋና ድርጅቱን የሚያፈርስና በሕግ የሚያስጠይቅ ቢሆን እኛም ስለሕግ የተሰለፍን በመሆናችን ጣታችንን አንስተን ይችን ደብዳቤ ባልጻፍን ነበር። የወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን መጋበዝ በእንግድነት ኢስፋናን ሕገ ወጥ እንደማያደርገው ማስረጃና ማሳመኛ ከዚህ በታች እንዳለው በተጨባጭ ልንገልጽ እንወዳለን። በሁለት ሺ ሰባት ዳላስ ላይ ባደረጋችሁት በአል በጣም የምንወዳቸው እንደ ወንድማችን፡ አብረናቸው በከተማው የሰውልጅ መብትን በማስከበር በምናደርገው ትግል የምናውቃቸው ሴኔተር ሮይስ ዌስት ከወይዝሮ ብርቱካን ጋር ሲነጻጸሩ በፓለቲኩ መድረክ ከመጣን ምንም አይገናኙም ሰውየው ያደጉበት ነው በዚህ የማያውቃቸው የለም። ከጥብቅናው ይልቅ በፓለቲካው አለም ይታወቃለ። እህታችን ወየሮ ብሩቱካን ወደፓለቲክ የገቡት በ2005 ነው፡ ከዛ በፊት ዳኛ ነበሩ ቀሎም በተነገርን የፓለቲካ ፓርቲ ጠበቃ ሆነው ነበር። ከሴኔተር ሮይስ ጋር የሚያመሳስል ነገር አላቸው በሞያቸው ይሄውም፡ ሴኔተር ሮይስም ጠበቃም ናቸው። ሮይስ ከተጋበዙ ብሩትካን የማይጋበዙበት መክኒያት የለምለማለትና ያሳሰባችሁ ሕገ ወጥ የማያደርጋችሁ ላይ ያተኮረ ነው ለማለት ነው። ሴነተር ሮይስ በኢስፋና በአል ላይ ንግግር እንዲያደረጉ መጋበዝና መናገራቸውና የጋርለንድ ሜርም እንደዚሁ ንግግር አድርገዋል። ከናካቴው በኢትዮጵያ ቀን ለጸሎት ሰአት ለእኛ ለሴቶቹ ድርጅት የተሰጠንን ፕሮግራም ለፓለቲካ መሪዎች ተሰጥትዋል በጊዜው። የሚናገሩት ፓለቲክ ነክ ሳይሆን ሕዝባዊ በመሆኑ ሕገ ወጥ አልነበረም።

 ልናስታውሳችሁ የምንፈሌገው ነገር ከዚሁ ጋር የተያያዘ በኢስፋና ቦርዴ ስለተወሰነ ውሳኔ ነው። ካለፈው ሃቅ አዲስ በቦርድ ውስጥ ያላችሁ ሊረዳችሁ ስለሚችል በተጨማሪ በማሰብ የምንወደው ተጨባጭ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። ይሄውም፡ በኢስፋና በራሱ ቦርድ ስለተወሰነ ሃቅ ነው። ኢስፋና በ2007 በዳላስ-ጋርለንድ ላይ በቴክሳስ ባደረገው በአለ ላይ ዝግጅት ይዘን በመቅረብ የቦርደ በአለ ከመድረሱ ሶስት ወር በፊት "እስረኞች በኢትዮጵያ ስለአገራቸው ጉዲይ የታሰሩት በሙሉ ለኢትዮጵያ ሚሉንየም ይለቀቁ ያአቶ መለስ ዜናዊንም ልብ አምላክ ያራራልን" በሚሌና ሰላም በኢትዮጵያ ሕዝብ መሃል እንዲሰፍን የጸሎት ፕሮግራም ልናደርግ ስለምንፈልግ የአምስት ደቂቃ ጊዜ ይፈቀዴልን ብለን በ"የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላምና ለዴሞክራሲ" ስም ጠይቀን እንደነበረ ነው። የኢስፋና ቦርድ ስብሰባ አድርጎ በጹሁፍ ያቀረብነውን ሁለም ተመልክቶ አጽድቆት የፈቀልን ሲሆን ጉዳዩ አሁን ከምትነጋገሩበት ወይም ግማሾች ይጋበዙ ስትሉ ግማሾቻችሁ ፓለቲካዊ ነው በሚል። የምትከራከሩበት ከወይዘሮ ብርቱካን ይጋበዙ ከሚሌው ጥያቄ ጋር የተመሳሰለና እንደውም እሳቸውንም ጭምር ለማስፈታት በጸሎት የተደረገና የተፈቀደልን ትልቁ ምስክር ነው ። ይሄውም ሕገ ወጥ ያለ መሆኑን የፓለቲካ ሰዎችን በኢስፋና መጋበዝ ወይም መድረክ ላይ የፓለቲካ መልክት ያልሆነ ንግግር ሕብረተሰብን የሚደግፍ ማቅረብ ። ይሄውም በድጋሚ ለዚህ ማስረጃ፡ "በጸሎት እስረኞች ይፈቱ!" በሚል ካቀረብነው ሴቶች መሃል፡ የመጀመሪያ ሴት በኢትዮጵያ ታሪክ ለአገር መሪነት እወዳደራለሁ በሚሌ የቀረብን፡ የመጀመሪያ አፍሪካዊ ሴት የፓለቲካ ፓርቲ በሰማኒያ ስድስት በነጮች አቆጣጠር ዳላስ ውስጥ የመሰረትን፡ ከአለም የመጀመሪያ ሴት ከአገርዋ ውጪ የስዴት መንግስት ያቁዋቁዋመች በሚል በአለም ታሪክ ውስጥ ለአገራቸው አስተዋጽኦ ያደረጉ ታጋዮች ሴቶች ማህደር ውስጥ የመዘገቡን እንገኛለን። ይሄ ሃቅ ሁሉ እየታወቀ ነው ጸሎት እንድናደርግ የተፈቀለን በኢስፋና መክኒያቱም ጥያቄያችን ፓለቲካል ሳይሆን የሰው ልጅ መብትን አስመልክቶ ስለሆነ። ww.ethiopiannationalgovernmentinexile.org ብትጎበኙ ምን ማለት እንደፈለግን ትረዳላችሁ። ይሄውም፡ ወይዘሮ የሐረርወርቅ ጋሻው ከዳላስ፡ ወይዘሮ ጸሃይ በቀለ ከአትላንታና ወይዘሪት ልእልት ሳሙኤል ከዳላስ በጊዜው አስራ አምስት አመት እድሜ  ጭምር የጸሎቱ አቅራቢዎች ሆነን ተፈቅዶልን ነበር። በጊዜው ከዳላስ ዘውገ ቃኘው ኪሮስ ወልደስላሴ የተባለት የኢስፋና ቦርድ ውስጥ ከነበሩት ሁለት ሰዎችን አስተባብረው ጽሎቱን እንዳለ ለማደናቀፍና ከናካቴው እንዲቁዋረጥ ያላረጉት አልነበረም። አሁንም እያደረጉት እንዳሉት  ማለት ነው ብርቱካን እንዳይጋበዙ።  ነገር ግን በአምላክና በቦታው በተሰበሰበው ሕዝብ ብርታት በኛም በሴቶቹ ጥንካሬ ጸሎቱን ሕዝቡን አስተባብረን ከወጣንበት መድረክ ሳንወርድ ባደረግነው፡ ስታድየሙ ጸጥብሎ ጸሎቱን ልንጨርስ ችለናል በጊዜው። የሚገርመውም ለብዙ ሰው እስከዛሬ፡ የተደረገው ጸሎት "ሜራክል" በሚል የተሰየመው፡ አርብ ጁላይ ስድስት በጋርልለንድ በኢትዮጵያ ቀን ዝግጅት ላይ ሲሆን ፡ በሳምንቱ አርብ እስረኛቹን እነ ወይዘሮ ብርቱኩዋንን፡ ወይዘሮ ንግስትና ወይዘሮ መሰበወርቅ እንጂነር ሃይሉና ድክተር ብርሃኑ ነጋን፡ ጭምር ሲፈቱ ያልተገረመ ሰው አልነበረም ከአምላክ ሌላ ማን ይሄንን ሊያደርግ ይችላል በሚል። ሃቅም ነው አምላክን በጠየቅነው መሰረት ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም ከቤተሰባቸው ጋር አውላቸው ብለን በአንድ ድምጽ ከአስር ሺያላነሰ ኢትዮጵያዊ ሁሉም ያለ ጾታ፡ ያለ ሃይማኖት፡ ያለ ጎሳ፡ ያለፓለቲካልዩነት በሕብረት በጸለይነው መሰረት ሁላችንንም ሰምቶናል። ባጭሩ ጋብዝዋቸው ብለን ልናቆም ስንችል በዝርዝር መጻፉን የመረጥንበት መክኒያትና ማለት የፈለግነው እኛ በፓለቲካው፡ ሳይሆን በሰው ልጅ የእኩለነትና የሰው ልጅ መብት ታጋይነት የጠየቅነውን የጸሎት ጊዜ ፓለቲክ ያለመሆኑን በዚሁ መልክ በማስረዳት በጻፍነው ሲሆን ለኛ የሚሰራው ሕግ ለወይዘሮ ብርቱካንም ይሰራል ለማለት ነው። አሁንም ምንም እንክዋን አንዳንድ ችግር የሚፈጥሩባችሁና ጫና እያደረጉ ያሉ ቢኖሩም ከራሳችሁ መሃል በቡድኖች የመጣም ጥያቄ በመሆኑ ፡ አምላክ የኢስፋናን ቦርድ አባላት በሙለ የቡድን ተወካዮችን፡ ተጫዋቾችን ጭምር ሃቁን ውነቱን ሕጉ 501 (c)(3) የሚፈቅደው ላይ ብቻ እንድታተኩሩ እንዲረዳችሁ አምላክን እንለምናለን፡፤ በ2007 እንደዚሁ በቦርድ አባላት መሃል ከወጪ ሆነው ጸሎት እንዳይደረግ ግፊት እየፈጠሩ ሲያስቸግርዋቸው ነበር ፓለቲካ ነው የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች ናቸው በሚል  ። እኛንም አስመልክቶ፡ በትክክል በሕጉ በመሄድ ትክክለኛ እርምጃ  እንደወሰዳችሁ የኢትዮጵያ ሴቶች  ለሰላምና ለዴሞክራሲ አሁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የስዴት መንግት ጸሎቱን እንድናካሄድ እንደ ፈቀዳችሁልን ሁለ አሁን ደግሞ በሁለት ሺ አስረሃንድ እህታችንን ወጣትዋን ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳን ከላይ እንዳልነው ቢቻል ከነልጃቸውና እናታቸው ካሌያም እራሳቸውን ብቻ ጋብዛችሁ በአትላንታ ስታዲየም የሚደረገው የኢስፋና በአል ከመቼውም የበለጠ የበራና ያሸበረቀ የደመቀ እንዲሆን እንድታደርጉ በትህትና እየጠየቅን  ደብዳቤያችንን እዚህ ላይ እንደመድማለን።

በመጨረሻም፡ በእኛ በኩል የምንተባበራችሁ ማንኛውም አይነት ጉዳይ ካለ የእስፓርት በአለንና የወይዘሮ ብርቱካንን መምጣት ስመልክቶ ልንተባበራችሁ ሙሉፍቃደኞች መሆናችንን ስናረጋገጥ ከልብ ነው። እግዚአብሄር ይስጥልን እያልን መልሳችሁን በቅርብ በዚሁ ኢሜል አድራሻችን እንድትልኩልን እንጠይቃለን።

ከአክብሮት ጋራ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግስት ስም
የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው
ፕሬዘደንት።