Sunday, March 27, 2011

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቀን ላይ እንዳይወጣ የተደበቀው ከሕዝብ የኢትዮጵያን ካርታ የያዘው ዚፕ ዲስክ ከተደበቀበት ተገኘ!

መግቢያ፡  እውነትን እንኑር፡ ሃቅ የሕይወት መመሪያችን ብርሃንናትና። ሌብነት ማጭበርበር ነው ማጭበርበር ስንፍና ነው ስንፍና ዋሽቶ መኖር የጭለማ ጉዞ ነው። የሃቅ አምላክን እግዚአብሄርን የተከተለና ከሃቅ ሌላ የማይናገር፡ በሃሰት የማይመስክርና ለእውነት ብቻ ምላሱን የሚጠቀም ሰው ሁሌም የእግዚአብሄር ስላም በደም ስሩ ውስጥ ይመላለሳል። በቁጥር ብሎም በሚዛን የማይተመን ውስጣዊ የአይምሮም ደስታን ይጎናጸፋል፡ በአምላክ ፊትም የተብከበረ ቦታ ይሰጠዋል። ከሃሰተኞችና አጭበርብሮ ወገንኑ የሚኖርን አካል የሚተባበር ሁሉ በብርሃን ጭለማ ውስጥ ይጉዋዛል ፡ በየሄደበት ሁሉ ሲበረግግም ይኖራል። ለሕብረተሰቡም ለልጆቹም ለባለቤቱም ለመላው ቤተሰቡም ብሎም ለጉዋደኞቹ ሁሉ አብረውት ለሚውሉት ሳይቀር ክብርና ትልቅ ጨዋንት ስይሆን ከእግዚአብሂር ተዛዝ ውጪ ሴጣንን እንዲከተሉ የዲያብሎስን የጨለማ መንግድ ተከታይ ያደርጋቸዋልና። ሕዝብን በማጭበርብር የሚኖርና የሚተባበር፡ የሚያስተባብልለት እግዚአብሄርን የማያምን ብቻ ነው።  "ሌባ አጭበርባሪ" ነው።  ሃቀኝነትን ላወረስን ምስጋናና ክብር ለአለም ፈጣሪ ለመድሃኒ አለም ይሁን። አምላካችንን ከፍ! ከፍ! የበል አሜን።
የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር በዳላስ ፎርት ወርዝና ችግሮቹ እነሆ።

ከዚህ በታች የምታይዩት ሕዝቡ የት አለ! እያለ ሲጠይቅ ፡ እስከዛሬ ከዳላስ ንዋሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደብቆና ታፍኖ የኖረ ሲሆን ለዚህም ተጠያቂ ይልማ ፈለቀ፡ ግርማ ንጉሴና ይልማ ዘርይሁን ሲሆኑ አራተኛዋ በጊዜው ከእንሱ ጋር በግል ጥቅም ተባባሪ የነበረች ስትሆን፡ ነገር ግን የሚሰሩትን ሁሉ በመረዳትዋ በሕዝብ ስም የገንዘብ ማጥመጃ መረብ ዘርጊነቱንና አጥማጅነቱን ጥላ በመሄድዋ ስምዋን ሳንጠቅስ እናልፋለን። ሆኖም "የኢትዮጵያን ካርታ ለኢትዮጵያ ቀን ማውጣት ሰው ያስቀይማል!" በሚል ለፈጸሙት ጸረ ኢትዮጵያዊነት ተጠያቂ ናቸው፡ ታሪክም ሲያስታውሳቸው ይኖራል። ዝርዝሩን በሚቀጥለው እናወጣለን ነገር ግን ለዛሬ መረዳጃ ማሕበራችንን ለሕዝብ ጥቅም ሳይሆን ለግላቸው እየተጠቀሙበት ኖረው አሁን ከቦርዱ ወንበር ላለመውረድ ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በሚል ሽር  ጉድ የሚሉት ቀደም ሲልም አሁንም ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን ልጁቹን ለመጥቀም ሳይሆን  ኪሳቸውን ብቻ በአገሪቱና በሕዝብዋ መከራ ስም ለሚያገኙት ጥቅም ተገዢዎች ናቸው። ልብ በሉ ይልማ ፈለቀ ፕሬዘደንት፡ ግርማ ንጉሴ የተባለው አስመራጭ ኮሚቲ አባል፡ ይልማ ዘርይሁን ለሶስተኛ ጊዜ ቦርድ ውስጥ ለመወተፍ እጩና ተወዳዳሪ። እነዚህ ኢትዮጵያንና የህዝብዋን አንድነት አይወዱትም።

ግርማ ንጉሴ የተባለውን አስመልክቶ እንዴት የአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ገባና ከይት መጣ ማነው ግርማ ንጉሴ? የሚል ጥያቄ ከየአቅጣጫው ሰሞኑን ቀርቦልናል ስለሆነም ይህ ብሎግ ለሕዝብ በተጨባጭ በስሙ ስለሚደረግ ማንኛውንም ጉዳይ አቅራቢ ቢሆንም፡ አብዛኛውን ጥያቄያችሁ የግርማ ንጉሴን የግል ኑሮውንም ስለሚነካ እዛ ውስጥ dfwethiopiancommunity.blogspot.com አይገባም የሕዝብም ችግር ሆኖ አላገኘንውም። ሌላው " ግርማ ንጉሴ  ማንንቱን እየደበቀ ሕብረተሰባችንን ሰላም ከነሳው መዳፍ ውስጥ በመቀላቀል ከቦስተን ከመጣ ጀምሮ ሲያደርስ የኖረው አሳዛኝ ድርጊት" በሚል ኢሜል "አበራ ጌታቸው" በሚል ስም የላካችሁልን ጭምር ሕዝባዊ ሳይሆን ግላዊ ሆኖ ስላገኘነው ለሕብረተሰባችን ልናቀርብ አንችልም። ስለዚህ
ይቅርታ እየጠየቅን ሕብረታችንንና የጋራ ጥቅማችንን  ፡ አንድነታችንንና ሰላማችንን አስመልክቶ ብቻ ሲያደርግ በኖረውና አሁንም የመረዳጃ ማሕበሩ አስመራጭ ኮምቴው ውስጥ በተለመደው የሕዝቡ ሬዳር ሳያየው ከማህብሩ ቦርድ አልወርድም ባሉት የተተከለው የእነሱንና የእራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ የገቡትን የሕዝብ ወገን በመምሰል እየቀረበ እንዲከፋፍላቸው በተለመደውእንዲረዳ  ብቻ ነው። በነግራችን ላይ እንክዋን ሕብረተሰባችንን እያደሙት ያሉት ይቅሩና በሕዝብ የተመረጡት የአሜሪካን መሪዎች እንክዋን ስማቸው እየተጠቀሰ ስላደረሱት በደል በሕዝብ ላይ የገለጻል ከእነማስረጃው ይሄም ብሎግ የሚከተለው የአሜሪካንን ሕግ እንጂ ሕገ ወጥነታቸውን የኢትዮጵያዊነት መብት አድርገው የሚያዩ ነገር ግን ስማቸው ከእነ ተግብራቸው ስናቀርብ ሕገ ወጥነት የሚመስላቸውን አይደለም።

የዳላስ ንዋሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠየቀውና በስብስባ ባጸደቀው መሰረት የተሰራውን በራሪ "የኢትዮጵያን ካርታ ለኢትዮጵያ ቀን ማውጣት ሰው ያስቀይማል!" በሚል ይልማ ፈለቀና ግብራአበሮቹ ለኢትዮጵያ ቀን የከለከሉትን ከዚህ ቀጥሎ  ላለፈው አስር አመት ደብቀውት ከሕዝብ የኖሩትን ሃቅ እነሆ!


እነዚህ ሕዝብ አብሮ የኖረውን እየተጠራሩ መጥተው የወገናቸውን አበሳ ያለአቅማቸው ለሚኖሩበት ኑሮ መክፈያ ለማድረግ ሕዝቡን በሃሰት ግራ ሲያጋቡት ሲኖሩ አሁን ማንነታቸውን ሕብረትስቡ በሚገባ ሊያውቃቸው ችልዋል። መረዳጅ
ማሕበሩና እራሱንችሎ ባንክም የራሱን በስሙ ከፍቶ ያለውን እድርና እድርተኞቹንም ከወዲሁ ሃቁን በስብሰባ ጠርቶ ማስረዳትና በእንዚህ ሕግ ወጥ ስራ በተካኑት ገደል ውስጥ ሊጨምሩዋቸው እንደሆነ በማስገንዘብ መረዳጃ ማሕበሩንም እድሩንም ነጻ ማውጣት በትብብር ይንርብናል ለዚህ የተሰለፍን በሙሉ። እድሩን በፊትም አሁንም ማንም አይቃወምም እንደግፋለን እንጂ።

አምላክ ምስጋና ይግባህ ለዚህ ሃቅና የእውነት ምስክርንት!