Friday, February 25, 2011

አራት ጥያቄዎች ሁለተኛ አመት እያስቆጠሩ ያሉትን ለመቅበር ቦርድ ኦፍትረስቲ ( board of trustees)

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ቦርድ ኦፍ ትረስቲ ሊያቁዋቁሙ የተነሱበት ዋና አላማቸውና መክኒያታቸው ከዚህ በታች የምትመለከትዋቸው ሁለተኛ አምታቸውን የያዙት አራት ያልተመለሱ አብይ ጥያቄዎችን በሕግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ ምላሽ እንዳይሰጡ ቀብሮ ለማስቀረት ነው። ከኢሜሉ እንደምትመልከቱት፡ በሰለጠነ መንገድና ስረአት ማለትም ቁልጭ ባለመንገድ የቀጠሮ ጥየቃ ከእነ መነጋገሪያው አረስት ጭምር አብራሩልኝ በማያሰኝ በግልጽ ቢጻፍላቸውም የሚጽፉትን በግለሰቡ አማካኝነት ኢሜል የተላከውን የምታዩት ነው። በሙሉ ስምንቱም ኢሜሉንም አመላሽቸው ሳይቀር፡ ከአንድ ጋን የተቀዱና በአንድ ቡድን ተጠንሥሠው የተጠመቁና በቦርድ ስም በግል ጥቅም ብርሌ  ተሞላልተው የተቀመጡ በመሆናቸው ለሕዝብ ጥቅም ብበትሩ ኢሜል ምመሪያ እንደሚሰሩ ማስረጃ አለ።  ለሕዝቡና ለልጆቹ የመረዳጃው ባለቤትነትና ተጠቅሚነቱን ቦታ ለርሳቸውና ለልጆቻቸው ሲጠቀምበት ኖረዋል። አሁንም ከናካቴው አራቱ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ቦርድ ኦፍ ትረስቲ ውስጥ እርስ በእርስ በመጠራራት ሁሉንም የሚመለከት ላለፈው አራቱ ጥያቄ ከቀረበላቸው ጀምሮ ጊዜ በመግደል ዝም ብለው ሲኖሩ ከቆዩ በሁዋላ ሕዝብ ለራሱና ለልጆቹ ጥቅም ሲል መረዳጃ ማሕበሩን ነጻ   አውጥቶ በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ መነሳቱን ሲያዩ ከተጠያቂነት ለማምለጥና የወሰዱትን ገንዘብ ሁሉ መልሱ እንዳይባሉ ጭምር ጉዳዩ የሚመለከታቸው ቦድ ኦፍ ትረስቲ ምሽግ ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ልጆቻቸውንም ቦርድ ውስጥ ካለው አጋብተው ባል ሚቱን ለቦርድ ኦፍ ትረስቲ ማስቅመጥ የአባትዋንና የግብረአበሮቹን ምስጥር ለማፈን አንዱ ዘዴ ነው።  የሚገርመው ትናንትና ህላችሁም እንደምታስታውሱት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያኑን ጥሎ አብሮዋቸው ባለመቆሙ፡ "በሲቨል የደርግ የመጀመሪያው ጸሃፊ ነበር የብዙ ሰው ደም ሕይወት መጥፋት ተጠያቂነው እሱን ብሎ ደግሞ አስቀጣሪ ጉዱን እናወጣለን!" በሚል ስሙን ስያነሱ የተከራከርንለትን ግለሰብን በግል ሕይወቱ በቤቱ እንዴት እንደሚኖር ሳይቀር በስልክ እያስደወሉ የምናከብረው ሰዎች እንንቀው ይመስል በእነበትሩ ወሬ ፡  ጉዱን ንገሩት እንዳላሉ እሱን ይዘው በቦርድ ኦፍ ትረስቲ ውስጥ አስገብተውታል፡፡ ሌላው የሚገርመው ይህንን ግለሰብ ባልፈጠሩት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ማእከል የሕንጻ ፕሮጄክት ኮሚቴ ውስጥም ተክለውታል።

በመጨረሻም፡ ለሚመጣው እሁድ ሶስት ጉዳዮችን መነግገሪያ አድርገው እነ ይልማ ፈልቀና በሁዋልዮሽ አመራር የመረዳጃ ማሕበሩን የሚመሩት ካቀረቡት አንዱ ስለሕንጻ ኮሚቴውና ስለቦርድ ኦፍ ትረስቲም ይላል። ይህ ህለቱም ጉዳይ ከሕዝቡ አንድ ግበረሃይል መረዳጃ ማሕበሩን ለሕዝቡ ለማስረከብ የተቁዋቁዋመ መኖሩን ይሄ የሕዝቡ ብሎግ ስላረጋገጠ ሕዝብ ስብሰባ ተጠርቶ ስለ የሕበረተሰቡ ሴንተር መሰራት ፕሮጄክት የነብረውን ኮሚቴ ይልማ እንደተረከበው ሳያስረክብ ገንዘብ ሲሰበስቡ ከኖሩ በሁውላ ኮሚቴውን ከእነ ገንዘቡ ዶክመንቱን ሁሉ ላለማስረክብ የፈጠረው የሕንጻ ኮሚቴና እራሱንም ያስቀመጠበት ቦርድ ኦፍ ትረስቲ ፈጽሞ ቦታ እንዳይንረውና በቀኑ እንዳያልፍ የማድረግ ሃላፊነትና ተጠያቂነትም እንደሚያጋጥማችው እያሳሰብን፡ ቦርድ በሕዝብ ለመርዳጃ ማሕበሩ ከተመረጠ በሁዋላ ስለ ሕንጻው ኮሚቴ ቀርቦ ስራው የሚጀመርበት ውሳኔ ይደረጋል።ይልማ ፈለቀ ፕሬዘደንት ከእነ ገንዘቡ ማስረከብ አለበት የሕንጻውን ኮሚቴ። እሱና ግብረአብሮቹ ያቁዋቁዋሙት ቦታ የለውም እውቅናም አይኖረውምም የለውምም። የቦርድ ኦፍ ትረስቲውም ይሁን የሕንጻው ኮሚቴ ቦታ የሌለውና መረዳጃ ማሕበሩ በሕዝብ ተመራጮና በህብረተሰብ ውስጥ የድርጅታዊ አሰራርን በሚያውቁ ለሕዝብ ጥቅምና የጋራ ጥቅም ብቻ ላይ ያተኮሩና ቅድምሚያ ለሕዝብ የሚለውን ስርአትና ልብ ያላቸውን ሕብረተስቡ እራሱ ሃቀኞችን መርጦ ለራሱ የሚያገለግሉት እጅላይ ማሕብሩን እንዲረከብ በሃቅ ከሕዝቡ ጎን እዲቆሙና ደጀኔ የተባለውምና ብጤዎቹም የእነበትሩና ተፈራ ወርቅ ሕዝብን ጎጂ ቅርንጫፎች ባላዎች ስለሆኑ በአስመራጭ ኮሚቴውስጥና በመረዳጃው ቦርድም ውስጥ እነሱም ይሁኑ የሚጠቁሙዋቸውን ግለሰቦች ማስገባት ታጥቦ ጭቃና በእርግጠኛነትም በእጅ አዙር መልሶ ጸረ የህዝብን አንድነትን ብልጽግናን የልጅቹን እድል ሰባሪዎችን  መትከል ስለሚሆነ ለህዝብ ቆሜአለሁ የሚለው አዲሱ ስብስብ እንዲሰጋበት እናሳስባለን። ሕብረተሰቡ አስተባብሮ ማሕበሩን እስኪገነባው አሁን እራሳቸውን በህግና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ከተጠያቂነት ማምለጫ ስለሆነ ቦርድ ኦፍ ትርስቲው/ሕንጻ ኮሚቲ፡ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።

በሚመጣው እሁድ ገና እንዳልተመራረጡ አድርገው በተለመደው ሕዝቡን "የሰጠንውንና ያቀረብንለትን መቀበል ነው ምን እውቀትና ልብ አለው ማንም አይጠይቀንም አቅርቦ ተቀበሉ ማለት ብቻ ነው" በትሩና ግብረአበሮችቸው።

እግዚአብህር ስለውነትና ስለክብሩ ስለሕዝብ ስለልጅቹም ጥቅም ብቻ የቆምነውን ሃሰተኞችን ለራሳቸው ከርስ ሲሉ ልጆቻቸውን እንክዋን ማሳደግ ያቃታቸው ለሌላው ልጅ መጥፍያውን እያመቻቹ ወጣቱን ከመረዳጃ ማሕበሩ ያባረሩትን ሁሉ ፍርዳችቸን ይሰጣቸው ዘንድ ፍርዱን ለሱ ለአለም ንጉስ ቤዛ እናስረክባለን። በስላም አስጀምሮ አስጨራሽ ስለሕዝብ ድምጽና መበደል ከዚህ በላይ ያለውንና ከስርም የተቀመጠውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማቅረብ እደሉን እንደሰጠን ለጥሩ ስራ ለሁላችሁም ይስጣችሁ ይመስግን አምልክ አሜን!።
-----Original Message-----
From: yehar9@aim.com
To: ttolla2002@yahoo.com
Sent: Sun, Mar 21, 2010 10:40 pm
Subject: Re: Meeting request reminder March 21, 2010



-----Original Message-----
From: tariku bedane <ttolla2002@yahoo.com>
To: yehar9@aim.com
Cc: Abraham Tefera <EBROCON@SBCGLOBAL.NET>; Ameha Tameru <dr.amehas@yahoo.com>; Ethiopian Community <maaecdfw@gmail.com>; Nasra Omar <omarnasra@yahoo.com>; Neguse Kefyalew <nkefyalew@sbcglobal.net>; Solomon Hamelmal <sohaz020@sbcglobal.net>; Yilma Feleke <ydfeleke@yahoo.com>; soha2020@sbcglobal.net
Sent: Wed, Jan 6, 2010 9:53 am
Subject: Re: Meeting request
 Ato Tariku Tolla, Ato Solomon Hamelmal and all board members,greetings.
As you all know, I have requested a meating on December the 28, 2009 in order to meet with for a short 30 munite meeting to discus the 4 topics that I listed on my inisal request. Since your first e-mail recponce dated Jan 6, 2010,  dispite my efforts and communicomunication with Ato Tariku several times in order to meet with you on your own confotble and schadual in the month of Janeuary,and after,today is March 22, 2010, almost four monthes I stil have no recived an answer from you the board.  before and after your responce letter dated January 6, 2010, to meet wit  on your own schadual in the monthe of Janwary . But it has been now almost 4 months there is no effort been shown on your part (all board member) at all. Requesting a meeting in sucah way in wrting with a clear agenda, is a posetive, peacful, and sivilized way. I have done my part as usual in a civilized manner. Now, I am aking you For your informatio and there is no relevent effort on your side to meet. Therefore, I am requesting a responce from you with the next two weeks.

Cc:


     Selam Yehararwerk Gashaw:

     Thank you very much for interest in the community. After reviewing your request to meet with the Board of MAAEC, the Board assigned Mr. Solomon Hamelmal and Mr. Tariku Tola to listen/discuss and possibly resolve you concerns regarding the community. We hope that these two Board members have the ability to resolve your concerns. If these two Board members can't resolve your concerns, they will report the matter to the Board immediately.Then, the MAAEC Board will decide the next step. The MAAEC Board will appreciate your effort to resolve your concerns in civilized manner.


     Tariku Tola

     Board Member
--- On Mon, 12/28/09, yehar9@aim.com <yehar9@aim.com> wrote:

From: yehar9@aim.com <yehar9@aim.com>
Subject: Meeting request
To: ttolla2002@yahoo.com
Date: Monday, December 28, 2009, 12:40 PM
To the board members of the DFW Ethiopian Community Mutual Assistant Association.

December 28, 2009.

To Ato Tariku Tolla, Ato solomon Hamelmal and all other board members. First of all, thank you for your volunteer work in our community.
I am writing you in regard to our telephone conversation last week regarding the following:

1.Ethiopian Community Center Project.
2. Youth Program at the Ethiopian Day event.
3. Christi Tefera Memorial Day project.
4. Ongoing Legal issues regarding the DFW Ethiopian Community Mutual Assistant Association.

I am requesting to meet with you, the board, as soon as is convenient for you, in order to discuss the four topics above. I would like to meet preferably within the next month. Thank you.

With Ethiopian sisterly respect,
Yeharerwerk Gashaw
one of the founders of the DFW ECMAA.

Tuesday, February 22, 2011

የታክሲ ነጂውን ወገናችንን የእንተባበር ጥሪ ከሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎች።

በታክሲ ሞያ የሚተዳደሩት ወንድሞቻችን (እህቶቻችን) መብት መረገጥ የእያንዳንዳችን ጉዳይ አድርገን መውሰድና ከጎናቸው መሰለፍ ከሰው ልጅ መብት ማስከበር አኩዋያ ብቻ አድርገን የምናየው ሳይሆን፡ በአምላክም ሁላችንን በፈጠረውም ንጉስ ስም ደግ መስራትና መደጋገፍ ይጠበቅብናል። ሌላው መታወቅ ያልበት ታክሲ መንዳት እንደማንኛውም ሞያ በአለም ውስጥ ትልቅ ዘርፍና እራሱን የቻለ ሞያ በመሆኑን አንገብጋቢነቱን መቀበል ይኖርብናል። ከታክሲው ስራ ጋር የሚመጡ ብዙ አይምሮን ሰላም ከሚሰጡት ነገሮች ውስጥ የራስ ተቀጣሪ ሆኖ በመስራት ነገ እባረር ይሁን? ከሚለው ጭንቀትና የፈረንጅን ፊትም እያዩ ከምሳቀቅም ነጻ መኮኑ ይገኝበታል። ታክሲ ነጂ ትግስትንና እራስን በዲሲፕሊን መምራትን የሚጠይቅና አስተማሪ ሞያም ነው።  ታክስ ነጂዎች የሚኖሩበት ከተማና የኢኮኖሚው የቱሪስት የጀርባ አጥንትም መሆናቸውን አንዘንጋ። የታክሲ አሽከርካሪዎቹ ስራ እራሱን የቻለ ሞያቸውን በተፈጥሮ ጋዝ ስም ሽፋን፡ ትልቁ አሳ ቲሹን ዋጠ እንደተባለው የሎ ካብ የግል ታክስ ነጂዎን እንዲውጥ ከንቲባው ለፐርት መተባበራቸው ባለሞያዎቹን መተዳሪያቸውን ተነጥቀዋል ፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ባለው በፊርማ የድጋፍ መስጫ በመግባት ስምዎንና ዚፕ ኮድውዎን ያስቀምጡ። ከአክብሮት ጋር በታክሲ ነጂውና በቤተሰቡ ስም። ታክሲ ነጂው ሃቁን ስለያዘ የጠየቀውን እግዚአብሄር ይፈጽመዋል!

http://www.gopetition.com.au/petition/43138.html

Saturday, February 12, 2011

በሃላፊነት ሕዝብ የመረጣቸው በሃላፊነት እንደሚጠየቁበት ጠንቅቀው ያውቃሉ።

መግቢያ፡
"ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ!
ከሰማየ ሰማያት ወርደህ በስጋ ብእሲ በሕጻን አርአያ በተገለጽክበት ወራት፡ እናታችን ሔዋንን ያሳተ ከይሲ ድያብሎስ ፈራ፡ ደነገጠ፡ በሃዘንና በለቅሶ ተዋጠ"
ከመልክ አመድሃኔ ዓለም፡ በተስፋ ገብረ ስላሴ።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርና አፍራሾቹ ቁትር አራት።

የመረዳጃ ማሕበሩ ችግሮችና አፍራሾች በሕዝብ ሳይመረጡ ማሕበሩን በትብብር ሕዝብ ሳያውቅ ዘርፈው እየተፈራረቁበት ያሉት አሁንም በቦርድ ውስጥ ያሉት ፈረቃ ዎች ናቸው። ስለዚህ ከቦታው እንዲለቁ ሕዝብ ጠይቀሃል ነገርን ግን የስራውም ተካፋይ መሆን ማሕበሩን ነጻ የማውጣት ይጠበቅብሃል ተነሳ! ተነሺ!

የተወደዳችሁ ወገኖች ጤና ይስጥልን እንደምን ከርማችሁዋል። ጅንጀሮ መጀመሪያ መቀመጫዬን! አለች እየተባለ ያደግንበት አባባል እንዳለ ሆኖ በዚህ በኛ ጊዜ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አንግብጋቢ ጉዳዮች በሚል የምንጠቀምበት አነጋገር ሃቅ ነው። በፈረንጅቹም ቢሆን First thing comes first እንደሚሉት ማለት ነው። ታዲያ አባባልን እንጣቀማለን ወይ? የሚል ጥያቄ ቢመጣ መልሴ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል።
ሰሞኑን ያፍሪካ ተወላጆች አገር በቀሎቹን ጨርሰው (እየጨረሱም) ሰሚን አፍሪካን የሰረቁን ያው እንደሚታወቀው ሃቁ ሴንትራል አረቢያ ወይም መካከለኛው አረቢያ፡  ዛሬ የመን፡ ከሁለት መቶ  ሺየሚበልጡ በእራሳቸው ወገኖች ተባረው በኑቢያ የገቡት አረቦች ዛሬ በግፈኞችና ጨቁዋኝ መሪዎቻቸው ላይ የወሰዱት የስልጣን ልቀቁ የአንድነት ንቅናቄ የኢትዮጵያዊውም የአለም ወሬ በመሆኑ፡ ምነው ስለ ትኩሱ ውሬ አልጻፍሽም ብትሉ መልሱ የጅንጀሮዋና ከዛም ቀጥሎ ያስቀመጥክዋቸው ናቸው።

ቅድሚያው ስለራስችን አገርና በክልል ስለተሸነሸነው ሕዝባችን፡ ስለ አንድ ሰንደቅ አላማና መላዋኢትዮጵያ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚለው ላይና በዚች በዳላስ ከተማ ደግሞ የምንኖረው ኢትዮጵያውያን በከርሳሞች የተነጠቅነውን የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር በህብረት ነጻ አውጥተን ለመላው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ የሚጠቅም ማለትም፡ ያለ ሃይማኖት ፡ ያለ ጾታ፡ ያለ ጎሳ፡ ልዩነትና የፓለቲካ መድረክነትና የግል ንግድ ማፋፋሚያ መተባበሪያ የሌለበት መረዳጃ ማሕበር ብቻ እንደነበረው መልሰን በሃቀኞች በአንድነትን በሕብረት መልሰን ባስቸክዋይ እንድንገነባው ማሕበሩን ነጻ ለምውጣት ከከርሳሞች ቅድሚያችን አድርገን እንነሳ!
ጨቁዋኞችና በዝባዦች ከፋፋዮችን አንፈልግም እምቢ!! ብሎ ከተነሳው አረብ ማዳነቁን ሳይሆን የራስን ችግር ችግር መሆኑን ፈትሸው ሃቁን አግኝተው መረዳጃውን የሕዝብ እንዲሆን አግገግልቱም ለሕዝብ እንዲሆን ለማድረክ ከሚታገልሉት ጎን እንቁም። ቅድሚያው ይሄ ነው። በሃላፊነት ሕዝብ የመረጣቸው በሃላፊነት እንደሚጠየቁበት ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ሁሉንም መልካም ሃሳብ አስጀምረህ የምታስጨርስ አምላክ ፈጣሪዬ ከዚህ በላይ ያስቀመጥክዋትን ሃቅ ለወገኖቼ እንዳካፍል ስለፈቀድክልኝ ምስጋና ይግባህ። አሜን።

Wednesday, February 2, 2011

When did the undetected TPLF agents took over the MAAEC? And how?

መድሃኔ ዓለም ሆይ!
ከሁለቱ ቀራንብቶችህ ጋር ለሚያንጸባርቀው አመጸኛንና ከዳተኛን በማስደንገጥ ብቻ ለሚገድል ለገጽህ ግርማ ሰላም እላለሁ። አሜን።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር በዳላስና አፍራሾቹ! ቁጥር ሶስት።

እንዴት ሰነብታችህ ክቡራትና ክቡራን ወገኖች።
በመጀመሪያ በቅዱስ ሚካኤል ደብር ለማገልገል በበጎ ፍቃዳቸው በምርጫ ቦታውን ለተረከቡት ሁሉ ክርስቶስን ብቻ የሚያገለግሉበት አይምሮ  እንዲሆኑ አምላክ ይርዳቸው ይምራቸውም። ከሁዋላ ሁዋላ እየተከተሉ ሴጣናዊ ተግባር እንዲሰሩ ከሚያደርጉ የስው ሴጣንኖች ይሰውራቸው፡፡
ባለፈው የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ቦርድ ባስቸክዋይ ስብሰባ እንዲጠራና ምርጫ እንዲደረግ ሕብረተስቡ በጠየቀው መሰረት በዚህ የሕብረተሰቡ የእውነት ድምጽ ከሆኑት ጥቂት ብሎጎች አንዱ ጥሪው የሕዝቡን ማስተላለፉ የማይዘነጋ ነው። ይሄውም ማሕበሩን በሕዝብ በሚመረጡ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት፡  በሕዝብ የሚመረጡና ታማኝነታቸውና ተጠሪነታቸው አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲ ላለው የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት የሚያገለግል ሳይሆን ይሄውም፡ አሁን ያለው ቦርድ ሲሰራ እንደኖረው አንዱ ሲወጣ ሌላውን እየተካ እንደሚሰራው ሳይሆን፡ ነገር ግን ተጠሪነታቸውና አገልግሎታቸው ባለማወላወል ለዳላስ ፎርት ወርዝ ለምንኖር የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ብቻ የሚሰሩ የቦርድ አባላት ለመምረጥ ፡ ሃላፊነትን ክብር አድርገው ለሚያዩ፡ በሃላፊነት መመረጥ ከከርስ በላይ መሆኑን በከባድ ሚዛን ለሚመዝኑ ጨዋ ኢትዮጵያውያን ሴቶችና ወንዶች ለማስረከብ ነው።

 አሁን ያለው ቦርድ ዲሴምበር ሰላሳ አንድ ጊዜው እንዳለፈበት ከሕዝቡ በማረጋገጫ ተነግርዋል። እንደ አለቃቸው እንደ ለገሰ ዜናዊ ወይም ሙባረክ በአምባ ገነንነት መቀመጡ አብቅትዋል! ሕዝቡ በዳላስ ፍቅሩን የሚገነባለት እንጂ ለጋራ ጥቅም ለግል ጥቅም በሃሰት ስለወገን የሚቆረቁሩትን ኢትዮጵያውያን እየኮነኑ ሰላሙንና የጋራ ጥቅሙን በግል ኪሳቸው በሚያካብቱ መታለሉ አብቅተዋል!  ቦታውን የማስረክብ ሃልፊነት የሚሰማቸው አይደሉም በሕዝብ ሳይሆን በቡድን በመመረጣቸው ለይስሙላ።  አሻፈረኝ ካሉ ወደ ሚመለከተው አተርኒ ጀነራሉ መሄድ አይቀሬ ነው። በተፈራ ወርቅ ቦታ የተቀመጠው ይልማ ፈለቀና ከሕዝብ የተሰጣቸውን አደራ እረግጠውና ሜዳላይ የጋራ መረዳጃውን ጥለው በነጮች አቆጣጠር በዘጠና ስድስት  ከጠፉት ስድስት ወንዶች የዛሬው ምክትል ፕሬዘደንት ተብዬው ይገኝበታል ። ያኔ የጸሃፊነት ወንበር ላይ ነብር የተቀመጠው። እንደነዚህ አይነት ሰዎች መረከብን እንጂ ማስረከብን በስነስራት ስለማያውቁ ሕብረተሰቡ መረዳጃ ማሕበሩን በእጁ መልሶ ለማስገባት ስብሰባ ጠርቶ፡ አስመራጭ ኮሚቲ አቁዋቁሞ ፡ የቦርድ አባላት መርጦ መረዳጃ ማሕበሩን ለሚጠቅሙት ጨዋ ሰዎችና የኢትዮጵያዊነት ስነስራት ላላቸው ማስረከብ ነው። ይሄውም ሕግ ይፈቅዳል።
When did the undetected TPLF agents took over the MAAEC? And how?
በዘጠና ስድስት ስድስቱ ወንዶች መረዳጃ ማሕበሩን አስረክቡ እየተባሉ በተከታታይ በጊዜው በአቶ ቴዲ የሬዲዮ ስርጭት ጥሪ ቢያደርግም አቶ  ሰለሞን ሃመልማል ጭምር ባነጋግራቸው ማሕበሩን እንደተረከብን እንድናስረክብ ፍቃደኛ አልሆኑም ሁሉም። ሆኖም ሃላፊነትን መወጣት ከኢትዮጵያዊነት ዜግነት ክብር ጋር የተጣመረ በመሆኑ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበርን ለሕዝብ ለማስረከብ "አስረክቡን!" በሚል መልእክት ከሕዝብ የመጣ ነው ብሎ ስያሰራጭ ወደነበረው አቶ ቴዲ የሬዲዮ ዝግጅት በመደወል የመረዳጃ ማሕበሩን ለሕዝብ ብቻዬን ለማስረከብ በመገደዴና ለሕዝቡ ስላምና አንድነትም በማሰብ መረዳጃ ማሕበሩ በእኔ እጅላይ ብቻ መጣሉን ነግሬ መረከብ ለሚፈልግ እንደማስረክብ በሬዲዮ ቀርቤ ይፋ አደረኩኝ። ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለነበረ ስብሰባና ምርጫም የማሕበሩ የሚደረገው ያንን ልማድ ማሕበሩ ኢትዮጵያ ማለት ስለሆነ፡ ለሁሉም ኢትዮጵያዊም ያለሃይማኖት ልዩነት በቦርዱ ገብቶ እንዲያገለግል ሴቱም ወንዱም ለመጀመሪያ ጊዜ በትክክል መረዳጃ ማሕበሩን ለማስተካከልም እድሉ ስለተፈጠረ በሃሊደይ ኢን የመረዳጃ ማሕበሩን ስብሰባ በፕሬዘደንትነት፡ በምክትል፡ በሕዝብ ግንኙንትና በጸሃፊነቱ ቦታ አርራቱን የስራ ሃላፊነት በመስራት ለሕዝቡ በሬድዮ ቦታና ሰአት ሴንትራል ላይ ባለው ስብሰባ ብቻዬን ጠርቼ ስብሰባው ተካሄደ። በቦታው አስረክቡኝ ያለውን ባላይም ሃያሶስት ሰዎች የማውቃቸው መጡ። ምንአልባት አስረክቡን የሚሉት በሚቀጦለው ይመጡ ይሆናል ሌላ ስብሰባ ጥሪ ተባልኩኝ። በሁለተኛው ስብሰባ ከናካቴው አስራ ሰባት ስዎች ከበፊቶቹ መጡ እነዚህ መረከብ የማይፈልጉ ናቸው። አሁንም ሶስተኛ ስብሰባ አዘጋጂ ተባልኩኝ በመጡት ሰዎች። አሁንም እዛው ሃሊደይ ኢን አደረኩኝ። አስራ ሁለትሰዎች ብቻ መጡ ከሰለሞን ሃመልማል ጭምር። የማላውቃቸው በግዜው መረዳጃ ማሕበሩን ተረክበን ባስመራጭ ኮሚቴ ስም ምርጫ እናካሄዳለን የሚሉ ከኦክላሆማ የመጡ ነብሳቸውን ይማረውና አቶ ሴፈ ታደስ  ሳይቀሩ በሰለሞን አማካኝነት ተዘጋጅተው ለመጡት ሰዎች በአራተኛው ስብሰባ መረዳጃማህበሩን አስረከብኩኝ። ልብ በሉ የግርግር ቤት ለሌባ ይመቻል የተባለው መረዳጃውን አስረክቡን አሉ የተባሉትን ባለሬዲዮን ዝግጅቱም ቢጠየቅም አላገናኘኝም ። ማሕብሩንም በፓለቲካ ስምና በውጭ ግፊትም በመደናቆር፡ ስራውንም ባለማውቅ ፡ አዋቂውና አላዋቂው አንድ ላይ ተቀላቅሎ ስራ ሊሰራም ባለመቻሉ፡ አንዱ ከሌላው መማርን እንደ ነውር በመቁጠሩ በመጨረሻም ፡ ተጣልተው በመበተናቸው፡ የትግሬ ነጻ አውጪ የድብቅ አገልጋዮችና ደጅ ጠኝዎቹ  አገር ቤት በሰሩት ላለመጠየቅና ቤታቸውንም ለማስመለስ በደርግ መንግስት የተወሰደውን ለማስመለስ እንዲረዳቸው መረዳጃ ማህበሩን በመሳሪያነት ለግል ጥቅማቸው በልዋጭ! ልዋጭ! ዘቤ ስምምነት  አስርረከቡት ከእነሬድዮኑ።

ከዚህ በታች ሜዳ ተጥሎ የነበረውን የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር ልክ እንደጀነራሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሲወጡ አገሪቱን በሃላፊነት እንደተረከቡ እኔም በተመስሳይ አጋጣሚ መረዳጃ ማሕብሩን እንዳይፈርስ ጀማሪም ስለነበርኩኝ ጭምር ሕዝብ የጣለብኝን እምነትና ሃላፊነት በሚገባ ከራሴ አውርጃለሁ። የወንዶቹንም ጭምር። ሃቁን ከመረዳጃ ማሕበሩ አውጥተው ጥለው፡ ብምትክ እነበትሩ፤ ተፈራ ወርቅ፡ ፍቅርማሪያም፡ ኪዳኔ አለማየሁ፡ አመሃ ታምሩ፡ ዘውገ ቃኘው፡ ይልማ ፍለቀ በመተባበር የራሳቸውን ፍርድ ብለው ባስቀመጡት የቆሻሻስራቸውን በመደበቂያ ውሸትና የውሸት ታሪካቸው ተክተውበታል በእኔ አኩሪስራ ቦታ። አንድነት አፍራሽና መረዳጃ ማሕበሩን አፍራሾች ሻጮች ዛሬ የመረዳጃ ማሕበሩን ሊያንቁ የቻሉት ጥፋቱ የማን ነው የኔ ውይስ የእናንተ ውገኖች? ሆኖም ሃቁን በከፊል እነሆ፡

When did the undetected TPLF agents took over the MAAEC? And how?


.