Saturday, October 23, 2010

www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com በዳላስ ፎርት ወርዝ የኢትዮጵያ ሕብረተስብ ስም በሕዝቡ ጥያቂ የተከፈተ ሲሆን አገልግሎቱ በግልጽ ለሕብረተሰቡ እንጂ ለግልሰቦች ወይም ለግልጥቅም አይደልም።

የቅዱስ ሚካኤል ክቴድራል በጋርላንድ ቴክሳስና ችግሮቹ ቁጥር ሁለት እነሆ።

በየሐረር ወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው
ዳላስ ቴክሳስ፤ አሜሪካ።

        በመጀመሪያ ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ስለ ብሎግ ሕግና ስርአት ውነታ ባጭሩ ማስገንዘብ እወዳለሁ። ብሎግ ባጭሩ ሰዎች እራሳቸውን ማነነታቸውንና ትክክለኛ ስማቸውን ሳይደብቁ ሃሳባቸውን እንደልብ በነጻነት የሚጽፉበትና ሕዝቡም ወይም ሕብረተሰባቸው ሃሳቡን በነጻ የሁሉንም መብት አክብሮ ሃሳብ የሚሰጥበት ። ይሄም እኔ በይሆናል ወይም መሰለኝ በሚል የምለው ሳይሆን ባለብሎግ ድርጅቱ ያወጣው ሕግ ነው። ገብቶ መንበብ ይቻላል። እያስመሰሉ መጻፍና የሌላውን ጽሁፍ የራስ አድሮ ማቅረብና ማንነትን ደብቆ ሌላሰው በማስመሰል pretending to be someone else) መጻፍ  ሕገ ወጥ ተግባር መሆኑን የብሎግ ሕግና ስርአት ብሎግ ለሚከፍት ሁሉ ያስረዳል። ብሎግ የሚከፍተውም ማንኛውም ሰው ሕጉቹን ተቀብያለሁ የሚለውን ካላመለከተ መቀበሉን ካላረጋገጠ ባለብሎግ ሊሆንም አይችልም። የእኛ ወንድሞች ግን ፊት ለፊት ግቡ ሲባሉ በጐዋሮ ዙሪያ ዞረው ተሸፋፍነው ነው ብሎግ ላይ አዳምጡን የሚሉን። መጀመሪያ እራሳችሁን ለሕዝብ ስታስታውቁ ነው ለሕዝብ የምትቆሙ ተቆርቁዋሪዎች ልትሆኑ የምትችሉት። ክርስቶስ ስንት መከራ እንደደረሰበት እንክዋን ክርስቲያኑ ሌላውም የሚያውቀው ነው ስለዚህ ላመናችሁበት ፊትለፊት ወጥታችሁ ውነት ሰው ሆናችሁ ተገኙ መጀመሪያ። ከብሎግ ሕግ በከፊል የወሰድኩትን ሃቅን እነሆ፡፡ 

Blogger Content Policy

Impersonating others: Please don't mislead or confuse readers by pretending to be someone else or pretending to represent an organization when you don't. We're not saying you can't publish parody or satire - just avoid content that is likely to mislead readers about your true identity.
Blogger is a free service for communication, self-expression and freedom of speech. We believe Blogger increases the availability of information, encourages healthy debate, and makes possible new connections between people.
The boundaries we've defined are those that both comply with legal requirements and that serve to enhance the service as a whole.
Violence: Don't threaten other people on your blog. For example, don't post death threats against another person or group of people and don't post content encouraging your readers to take violent action against another person or group of people.)


     የቅዱስ ሚካኤል ደብረምሕረት ካቴድራል በጋላንድ ቴክሳስና ችግሮቹ ቁጥር ሁለት እነሆ።

ሰው ሰሚ ካጣ ወደ ሚሰማው ይሄዳል። በጊዜው ቦርዱ በቦርድ አሰራር ሳይሆን በጉልበት አስተሳሰብ ጡንቻ በመታገሉ ክሱ በያይነቱ ሊከሰት ችልዋል። በሃላፊነት የተቀመጡ ሰዎች አንድ ሰው ብቻ እንደፈለገው በሚሰጠው መልስ ሳይሆን በቦርድ ስብሰባ በመገኘት ተነጋግረው ለቤተክርስቲያኑ አባላት ምንም ይሁን ጥያቄው ማንም ይጠይቀው መልስ ለጥያቄ መሰጠት ነበረብት ያአልተደረገም ቀደም ሲል በቤተክርስቲያኑ ቦርድ። ትርፉ እንግዲህ አብሮ የኖረው በማያውቀውና ባላጣራው ጉዳይ ማጋጨት ሆንዋል እንደሚታየው። አንዳንድ ስር የለቅቁ ውሸቶችም እንደውነት ቀርበውም ነብር ቤተክርስቲያኑን ፕሮቴስታንት ሊወርሱት ነው በሚል ያአሁን ውነት ለመናገር አጣርቼ ሃሰት ሆን አግኝቼዋለሁ። ሌላውን ለግል ጉዳይ ለማሳመን መዋሸት የለበትም። በተለይ አንዳንድ እህቶቼ በዚህ አይነት ውሸት ብዙ ተርዋርጠዋል የተታለሉ ይመስላል። ጉዳዩ ፍርድ ቤት የሚይስኬድ አልነበርም በፍጹም። ባንድ የቦርድ ስብሰባ  የሚፍታ ነበር።


       ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያውያን በአንድ አምላክ ስም የከበረ የኢትዮጵያዊነት ስላምታ እንዴት ናችሁ ብዬ ሳቀርብ ከልቤ ነው። ለሰጣችሁኝ ማበረታቻ ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ። አንዱም ብሎግ አስተያየት ሰጥቶል ክሪቲክ ጥሩ ነው መጥፎ የሚሆነው ሃሰት ፈጥሮ ውነት አስመስሎ ማውራት ነው። አስተያየት እቀበላለሁ ጉዳዩ የዚህ ብሎግ ሕዝባዊ በመሆኑ ግላዊ ሳይሆን። ከዚህ በታች ያለውን በፍርድ ቤት ውስጥ እራሳችሁን አስቀምጣችሁ በኔ ቦታ አስቡት የትኛው አጠገብ ነው የምቀመጠው ብላችሁም አስቡት። መሃል ላይ መቀመጫ የለም ከከሳሽም አይደለሁም ችግሩንም ከፈጠሩት ከአንዳንድ የቦርድ አባላትም አይደለሁም አንዳቸውም የእኔ አጋዢነች የሚሉትን እምነታቸውን ልተባበር አልፈለኩም ስላልሆንኩም። ሆኖም ወደ አገኘሁት ሰው በጣም ተጠግቶኝ ሊቀመጥ ወደ ማይችልበት ባዶና ሰፊ መቀመጫ ተቀመጥኩኝ። የመጀመሪያ ጊዘ ያገኘሁት ቦታ በሚካኤል ካቴድራል ቦርድ በተቀመጡበት ነበር የተቀመጥኩት። ሁለተኛ ጊዜ ስሄድ ደግሞ ቦታው ተመቻችቶ ብቻዬን ያገኘሁት በከምለት በከሳሾቹ በኩል ስለነበር በከሳሾቹ በኩል ተቀመጥኩኝ። ነገሩ ለሁለቱም እኩል እራሴን ያካፈልኩኝ ይሚስል ነበር። ከፍርድ ቤቱም ስንወጣ ሁሉም ሰላም ብዬ በመሳምም ስላም የምላቸውን በተለመደው አቅፌ የኢትዮጵያዊነት ሰላምታዬን አቀርበኩኝ። የማላቃቸውንም ክሳሽና ሌላውንም በመተዋወቅ ሰላምታዬን ከልብ አቀረብኩኝ እንግዲህ ይሄ መንደርደሪያ ሲሆን የፍርድ ቤቱን ወይም የችሎቱን ሲኒማ እነሆ ። በነገራችን በሁለቱ ወንዶችና ባንዲት ሴት ክስ ቀረበ ስለተባለው የማውቀው ነገር ምንም የለም።


     ፍርድ ቤት የመጀመሪያው ክስን አስመልክቶ ዳኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀርብለት ያለውን  ላካፍላችሁ ባጭሩ። ዳኛው ለተካሰሱት እንደዳኛ ሳይሆን መካሪና እንደውም የኢትዮጵያን ሕብረተሰብ በጣም ያውቅ ይመሰል እነእንትናና እነእንትና እንዴት ምን ሲደረግ ለዚህ ለማይረባ ጥያቄ ፍርድ ቤት ወረዳችሁ አይነት ነበር ያለው በተቆጣ መልኩ ስራ ፈቶች ስንት ነገር እያለ ከባድ ይሄንን መፍታት አቅትዋችሁ ወደ ፍርድ ቤት የሚያስመጣ ስንት ትልልቅ ጉዳይ እያለ እናንተ የደላው ሙቅ ያኝካል እንደተባለው ሁለት ጠበቃ ይዛችሁ ፍርድ ቢት ትዳረሳላችሁ አታፍሩም? በሉ ከዚህ ሄዱ ጉዳያችሁን እዚያው ጨርሱ ከፊቴ ሄዱልኝ የሚል አይነት አነጋገር ነበረው በቀጥታ ያጥሩ ዳኛ ስላም ለሁሉም ሰው የሚመኝና ጊዜውን ለማይረባ ጉዳይ ያጠፉበት የተናገረው።

     ዳላስ መሃል ከተማ ፍርድ ቤት ሄድኩኝ። ትመጣለች ብሎ የጠበቀ ከቅዱስ ሚካኤል ደብርም ቦርድ ይሁን የቅዱስ ሚካኤልን ቦርድ ከከሰሱትም አልነበረም። ከሁለቱም ጋር በፈጸሙት ተግባር የማልስማማበት አለኝ። ታዲያ ዳኛ ገብቶ የሌላ ተካሳሾች ጉዳይ እየሰማ ነበር ትልቅ የወርካ በር ድምጽ የሌለው ከፍቼ የገባሁት። አንድ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ነው አግድም መቀመቻዎች ያሉት። በኔ ቦታ ሁኑና አስቡት ያለችን በሰከንድ የሚትቆጠር ጊዜ ነች ዳኛው እያዳመጠ ስለሆነ የኔ ውር ወር ማለት ችግር ሊያመጣ ይችላል ጣልቃ በመግባቴ ፍርድ ላይ እያለ። ወዴት ነው የምቀመጠው ብዬ አሰብኩኝ። ቀኝ ሳይ አቶ ተኮላና አቶ ጸሃይ ጽድቅና ወይዘሮ ጥሩ አይርን ጨምሮ ከዚህ ቀደም ማላውቃቸው ሁለት ሰዎችም አብረዋቸው ተቀምጠዋል፤ ፊታቸውን ዞር አድርገው ሲያዩኝ ሳቄ መጣ መክኒያቱም ከማውቃቸው ጋር ሁሌም ስለምስቅ። ክሱን አክብጄ ማየት አቃተኝ ለደቂቃ። በቀኝ ደግሞ ዞር ስል የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ እዬልና እነ ዶክተር ግርማ ብሎም አቶ አበራ የተባሉት ፊት ቁጭ በማለታቸው መግባቴን አላዩኝ። እንዳልኩት በሩ ሲከፈት ዝም ያለ ሰላማዊና አርፍዶ ሊሚመጣ ባለጉዳይ አውቀው የተሰራ ይመስላል እግዜር ይሰጠው በሩ ለሁሉም እረድቶኛል ዝም በማለቱ። ከቦርዱ በኩል ከሁዋላ የተቀመጡት ወይዘሮ ፈትለወርቅና አቶ ዮሴፍ የአቶ ዮሴፍ ባለቤት ወይዘሮ እመቤት ነበሩ ሲሆኑ ዮሴፍና ፈትለቀርቅ በተለይ ሳቅታ የተሞላበት እንክዋን ደህና መጣሽ አይነት ፊትዋላይ አነበብኩኝ። በመጨረሻም አዳምጥ ጀመር። ግራ እና ቀኝ እያየሁኝ የሁለቱንም ወገን የሰውነት ንግግርና የፊታቸውን ድምጽ የሌለው ንገግር አይጀመረ በደንብ ተደላድዬ። ነገሩ ገረመኝ እልህና ያለመከባበር ምንያህል እሳት እንደሆነ። ለነገሩ ፍርድ ቤት ሰውከስሼ ባላውቅም ብዙ ጊዜ የሄድኩበት በመሆኑ በሰውልጅ መብት ተከራካሪነቴ በልጅነቴም የአውራጃ ፍርድ ቤት ሱስ ነበረብኝ በትምህርት ሰአት ከተስፋ ኮከብ ጥፈኛና ደጃች በቀለ ወያ ትምህርት ቤት ሌላው ወደ ምግብ ሲሄድ እኔ ወሬና ብዙ ቲያትር ወደ ማይበት አውራጃ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት በመሄድ እታወቅ ነበር ዳሩ ግን አንድ ቀን ያጠኑኝ ዳኛ የማን ልጅ ነሽ ለምን እዚህ ትመጫለሽ ሁልቀን ብለው እስካባረሩኝ ጊዜ ደረስ ማለት ነው። ታዲያ ያልማድ ብዙ እረድቶኛል ፍርድ ቤት ጋር ተለማምጃለሁ ፓሪስም እንዲሁ። ይሄንን ስታነቡ እየተዝናናችሁ ታተኩሩበት ዘንድ ነው በዚህ መልክ የማቀርብላችሁ። በመጨረሻም የመጀመሪያው ባለጉዳዩች ጉዳይ አለቀና የኛዎቹ ጠበቃዎቻቸው ማለት ከሳሽ ኢትዮጵያዊ ኦርቶዲክስ ተዋህዶ አማኝና የኢትዮጵያ ኦርቶዲክስ እዋህዶ ቤተክርስቲያን ቦርድ ተከሳሾች። አሁን ክሱ ውነት መሆኑን ልቤ ተቀበለው በጣም ማዘንም ጀመርኩኝ ልገልጸው ከሚገባው በላይ።  በበኩሌ ሁለትትቱ ወገኖች የያዛቸው አባዜ እያሳመማቸው በመሆኑ አዝኜላቸው ወደ እግዚአብሄር ጽለይኩላቸው።

ዳኛው ወዳለው ልሂድ::
     በእድሜ ገና በመጨረሻው አርባዎች ውስጥ ያለ የሚመስለው ፈረንጅ  ዳኛ ጠበቃዎቹን በስም ጠራ በተለይ የቤተክርስትያኑን ጠበቃ በጣም እንደሚያውቀው ባነጋገሩ ማወቅ ቀላል ነው የዳላስ ዳኛና ጠበቃዎችን ጸባይና ልምድ ለሚያውቀው ለእንደ እኔ አይነት የመብት ተከራካሪ ጊዜ አልፈጀብኝም ስራዳው። ዳኛው የቤተክርስቲያኑ ጠበቃ ስሙን ጠርቶ ምነው ይሄ ጉዳይ አሁን ፍርድ ቤት የሚያመጣ እንዳልሆነ እያወቅህ ለምን እዚህ ተዳረሰ? ይሄ ጉዳይ በሁለት ወንድማማቾች መሃል የተፈጠረ ችግር ነው በመነጋገር የሚፈታ ነው። ፍርድ ቤት ፈጽሞ የሚያመጣ ጉዳይ አይደለም። እኔ የምፈርደው ለሁለታችሁም ለከሳሾችም ለተከሳሾችም የሚጎዳ ይሆናል። ስለዚህ በከሳሽና በተከሳጭ መሃል ገብቶ ጉዳዩን አይቶ አስታራቂ ሃሳብ የሚያመጣ አንድ ሚዲዬተር ፈልጉ አለና ስም ጠርቶ እከሌ ለዚህ ጉዳይ ጥሩ ይመስለኛል በሚል እንደዳኛ ሳይሆን አንድ ሰላማዊ የሃይማኖት አባት የተጣሉ ሰዎችን አንተም ተው አንተም ተው ብሎ እንደሚያስታርቅ ማለት ነው በትክክሉ ለማስቀመጥ። ከናካቴው ዳኛው እኔም ቤተክርስቲያን አለኝ እኮ ይገባናል ስለቤተክርስቲያና ስለእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች በሚል በመደጋገም ይሄ በፍጹም ፍርድ ቤት የሚያስመጣ ጉዳይ አልነበረም ጠበቃ እክሌ አንተም ታውቀዋለህ በሚል ለቤተክርስቲያኑ ጠበቃ ሃሳቡን ሰጠ ። ቀጥሎም፤ ሆኖም ጉዳያችሁን ወደ እኔ ችሎት ማምጣታችሁ ትክክለኛ እርምጃ ነው የወሰዳችሁት አላቸው ከሳሾቹን። ይሄውም በቦታው ሆኖ ለተረዳው ሕጉን በእራሳችሁ እጂ እንክዋን ያልወሰዳችሁ ለማለት ነው። በመጨረሻም ጎበዝ ሚዲየተር የሆነ ጠበቃዎቹም ዳኛውም በሚያውቀው ጉዳዩ እንዲታይ እና ውጤቱን በሚቀጥለው አቅርቡልኝ ብሎ ችሎቱን ዘጋና አሰናበተን።

      ከሳሾቹም ይሁኑ ተከሳሾቹ፡ የቅዱስ ሚካኤል ደብርን አስመልክቶ ከሁለቱም ወገን ስለሚከሰተው ጎጂ ውጤት ፈጽሞ ዞር ብለው ሊያዩት እንዳልቻሉና በእልህ ሁሉም የአሳይሃለሁ ወይም የአሳይሻለው የእናሳያችሁዋለን አይነት የሴጣን ፈረስ ሲጋልቡ ነበር ፊታቸው ላይ የሚታየው ። ማሸነፍ እንጂ እንሸነፋለን የሚለውን መጥራት አልቻሉም። ከፍርድ ቤቱ ወጥተው ጥግ ፤ ጥግ ይዘው ከጠበቆቻቸው ጋር ብቻ ለብቻ ሲነጋገሩ ላያቸው ምን ያህል የሰው ልጅ ከንቱና የራሱን ፍላጎት ብቻ ለማሙዋላት ሲል ሃይማኖቱን ማለትም አምላክን እንደሚረግጥም ነው የተረዳሁት ። በዚህ መሃል እኔም ወደ ዳኛው ችሎት ከመሄዱ በፊት ተቻኩዬ ጥልቅ አልኩኛና ተመልሼ አንድ ጥያቄ ጠየኩት ዳኛውን። ኮቱን እየለበሰ ቸኩል ባለው ጨዋና ጥሩ ልብና አንደጋገሩ የአንድ ደቂቃ ሃሳቤን አዳምጦ መልስ እንደዚህ ሲል ገለጸለኝ ይሄውም ፤ ሌሎች የቤተክርስቲያኑ አባላት በጉዳዩ ያገባኛል ብለን በሚቀጥለው ቀጠሮ ለማድረግ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ? በሚል ላቀረብኩት ጥያቄ ፔቲሽን ወይም ያገባናል የሚል ደብዳቤ ጽፌ ለሱ ጽሕፈት ቤት ባቀርብ እስራላይ ሊውል እንደሚችል አስረድቶኝ ተለያየን።

      ሁለተኛው ቀጠሮ ደረሰ ያው የበፊቱ ፍርድ ቤት ችሎት ነበር ክሱ የሚሰማው (ዲፓዚሽን) በቦታው ተገኘሁ።   በተለመደው ሕግ መቼም ልቡ ያበጠበትንምና አዋቂነኝ የሚለውን ሁሉ ለተወሰነ ስከንድ ከመቀመጫው ብድግ ያደርገዋልና እሳት ወይም እሾክ እንደወጋው ሰው ሁላችንም ብድግ በሉ ተባልን ተነስተንም ተቀመጥን። ባጭሩ ልግለስ የዝህን ቀን የዳኛ ውሳኔ። የቤተክርስቲያኑ ቦርድ ዋና ጠበቃን ዳኛው በጠየቀው መሰረት መልስ ሲሰጥ ከሳሾቹ የሚጠይቁት የቤተክርስቲያኑን አባላት ስምና አድራሻ የስልክ ቁጥር ጭምር ነው እና መስጠት እንደማይፈልጉ ደንበኞቹ ተናገረ። ቢትሰጥዋቸው ችግሩ ምንድነው? ሲለው ቤተክርስቲያን የገንዘብ መዋጮ ሊጠይቁበት ነው በሚል መለሰለት። ዳኛው እንክዋን የስም ዝርዝር ለምን ቤተክርስቲያን አይገዙም እግቢያችሁ ውስጥ ገንዘብ እስካልጠየቅ ድረስ መብታቸው ነው በሚል ደምድሞ የከሳሽ ጠበቅን ለምን አስፈለገ የአባላት ስምዝርዝር እና አድራሻ? አለው። የአባላትን ስም ዝርዝር የደበቁበትን መክንያት ገልጾ ቁጥራቸውን ለማወቅ እንደሆነና በቅርቡ የተቀየረው ባይሎው የቤተክርስቲያን መተዳደሪያ በአባላት ድምጽ ነው ያሉት ሃሰት ስለሆነ ማረጋገጥ እንፈልጋለን በሚል ለተጠየቀው መልስ ሰጠ። በመጨረሻም ዳኛው ባለፈው የሰጠው ት እዛዝ መሰረት አስማሚ ወይም ሕጋዊ ሽማግሌጋ ሄደው ባለመስማማታቸውን ሲረዳ ፡ እኔ ፍርድ ከሰጠሁኝ ሁለቱም ወገን ይጎዳል እንጂ አንዳቸውም አይጠቀሙም አሁንም ጊዜ ውሰዱና ባልክዋችሁ መመሪያ መሰረት ተስማምታችህ መልስ ይዛችሁ ኑ። ለዛሬ ደግሞ የምወስነው የሚካኤል ቦርድ ለሁለቱ ከሳሾች የቤተክርስቲያኑን አባላት በሙሉ ስምዝርዝር ያለስልክና አድራሻ እንድትሰጡ በሚል ደምድሞ የቀኑ የፍርድ ቤት ጉዳይ በጠዋቱ ተደምድሞ እኔም ወድ ስራዬ ሄድኩኝ።

     ለማጠቃለል ስለመጀመሪያው ክስ ጉዳይ አንደኛ ስለቤተክርስቲያኑ ያገባናል የምትሉ ሁሉ ቤተክርስቲያን ውስጥ እሁድ እሁድ ከመገለማመጥና ምን አለ ፍርድ ቤቱ? በሚል በስመአበሎ ከመስማት ተባራሪ ሁለተኛ እጅ ወይም አራተኛ ጆሮ በፍርድ ቢት በመገኘት ድጋፍ ለማንኛውም ለመስጠት ሳይሆን ውነቱን ስለክሱ በተረዳችሁ ነበር። ከሳሾችንም ቦርዱንም ላይ ፈራጅም ከመሆን የውነተኛ ዳኛን ብታዳምጡ ዛሬ ነገር አልቆ ነበር።

        ያኔም ነገርክዋችሁ አሁንም እደግመዋለሁ። የዚህ ሁሉ ትልቅ ችግሮች ቤተክርስቲያኑን ለመውረስ አሁንም ትልቅ ጥረት እያደረጉ ያሉት ፡
አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሄርን፤ አቶ ኪዳኒ አለማይህን፤ ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አሰፋን እና ከሁዋላ ያሉት ተሳቢዎች ናቸው። ይሄንን ለማቆም የሚቻለው አሁንም በመቀጠል በኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህበር ቦርድ ውስጥ የራሳቸውን ሰዎች እያዘጋጁ ነው ለምርጫ። ከሚለቁትም ውስጥ የነሱው ሰዎች ሲሆኑ ምትካቸው ተዘጋጅቶ አልቅዋል። በቤተክርስቲያኑም ቦርድ የራሳቸውን ሰዎች አስገብተዋል። ሌሎችም ሊጨምሩ ነው።


እድሩ ከመረዳጃ ማህበሩ ጋር የተገናኘ ነገር የለውም። ለምሳሌ ገንዘብ የለንም ቢሉዋችሁ እድር የገባችሁት የኢትዮጵያን የጋራ መረዳጃ ማህበር የመጠየቅ መብት የላችሁም ። መክንያቱም እድሩና መረዳጃው የሚገናኙበት በእድሩ ማመልከቻ ላይ MAAEC በሚለው አጥራር ሕዝቡን ለማሳመኛ በሚጠቀሙበት ማጭበርበሪያ ዘዴ ብቻ ነው። ሌላው አርባ ዶላር እንሰጣለን በነብስ ወከፍ የተባለው ተስጥቶም አያውቅም ማስረጃው አለ። በጥቅም የሚቃረጡት የኢትዮጵያን የጋራ መረዳጃ ማህበር አንዳንድ አባላትም ቢሆኑ ሕግ ይጠይቃቸዋል በግል ሃላፊነት።

አስጀምረህ ላስጨረስከኝ አምላክ ምስጋና ይግባህ።