አስቸክዋይ ማሳሰቢያ ለዳላስ ፎርት ወርዝ ንዋሪዎች በሙሉ።
የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህበር የህንጻ ኮሚቲ በሚል ሌላ እያለ በላዩ ላይ ለምን አዲስ ኮሚቲ የትግሬነጻ አውጭ ቅጥረኞች ኒያላ ኢንሹራንስ በሚል ስም በድብቅ ሲሰሩ የተያዙት አሁን ደግሞ ለኢንቪስትመንት የሚጠቅማቸውን መንገድ ስላገኙ ለዛ ለማዋል እየተርዋርዋቱ ስለሆነ በዝርዝር ጉዳዩን ስለማቀርብ ይሄንንብሎግ ተከታተሉ። ያው የምታውቁዋቸው ሲሆን እኔ ባቁዋቁውምክት ይህንጻ ኮሚት ስም እኔ ሳላውቅ ብዙ ገንዘብ ከጽዋ ማህበር ሳይቀር ገንዘብ ላለፈ ስድስት አመት የሰበሰቡትን ጠፈራ ወርቅ፤ በትሩና ኪዳኔ አለማየሁን እንደሰጣችሁዋቸው ግንዘባችሁን ባስቸክዋይ እንዲመልሱና እነሱም የወሰዱት ከጽዋ ማህበር አንድሺ ዶላር በትሩ የሰበሰበውንም ጭምር ለሕዝቡ እንዲመልሱ እያሳሰብኩኝ ሕዝቡም ገንዘባችሁን ጠይቃችሁ እንድተረከቡ በድጋሚ አሳስባለህ። አቶ ሴፉ ይገዙንና አቶ መላኩን መላኩ ስል መላኩ ታደሰ ማለቴ አይደልም፤ በዚህ አጋጣሚ የማሳስባቸውና እንዲያውቁ የምጥይቃቸው፤ እነዚህ ሁለት ሰዎችም እንዲረዱ የምፈልገው ያልተነገራቸው የሕንጻ ፕሮጄክቱ ኮሚቲ እንዳለና፡ እነ በትሩ፤ ኪዳኔ አለማየሁ፤ ተፈራ ወርቅ፤ ዘውገ ቃኘው፤ ለወያኔተቀጣሪ በተጨባጭ መሆናቸውንና የቅዱስ ሚካኤልን ቤተክርስቲያን ሊወርሱትነው በሚል ውነቱን ለሕዝብ በማስቅረቤ በመብገናቸው፤ የነሱ ያልሆነውን ፕሮጄክትና ሃሳብ ካለው የህንጻና ከነበሩበት ዘርፈው የተቁዋቁዋም ኮሚቴ ውስጥ መግባታቸውን እንዲገነዘቡ ነው። እኔ ሕዝብ ሰብስቤ የተመሰረተው ኮሚቲ ውስጥ ይልማ ፈለቀ ፕሬዘደንት፤ እታለማሁ ፍቅሬ ምክትል ፤ ዘውገ ቃኘው ህዝብ ግንኙነት፤ ቲና ሕዝብ ግንኙነትና ተፈራ ወርቅ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ተወካይና ሌልችቹም ይገኙበታል። በዝርዝሩ አስክንገናኝ ለህንፃ ስራ ገንዘባችሁን ለፍታችሁ የምታመጡትን የእነ በትሩና ግብረአበሮቹ ብሎም የኒያላ ኢንሹራንስ (የጋሻ) ኢንቭስትመንት ሞርጌጅ መክፈያ አትሁኑ። በትክክሉ ኮሚቲው ዘራፊዎችና የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች የሌሉበት በቅርብ እንደገና ስራላይ እስቲውል ተባበሩኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም አስከባሪ የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው።
በየሐረርወርቅ (የኢትዮጵያ ወርቅ) ጋሻው።
አይምሮዬን ልቤን በአንድ አምላክ ስም በማስተባበር ከዚህ በታች ያለውን እውነታ የበኩሌን የማውቀውን በግልጽ በተለመደው ሳቀርብላችሁ ብዙዎቻችሁ በጠየቃችሁኝ መሰረት ነው። ይሄውም፤ የመረዳጃ ማህበሩ ጉዳይ ለተቸገረው ወገን መገልገያነቱ በመቆሙና ቤሌላ በኩል ደግሞ የቅዱስ ሚካኤል ደብርን አስመልክቶ ከአመት በላይ ያስቆጠረው መካሰስ ጨምሮ ፤ ግራ ገባን የትኛውን ውይም የትኛዋን ለማመን፤ በጉዳዩም ያገባናል ብለን ለመግባት እንክዋን ሁሉም የራሱን ፍላጎትና ጥላቻ የተሞላበት ከማውራት ሌላ፤ በተጨባጭ ትክክለኛውን የሚነግረን በማጣታችን የስድብና የመንደር ወሬ ከማንበብና ከመስማት ሌላ ፤ ቁም ነገሩን ልንረዳ አልቻልንም ውይም ችግሩን በትክክል ባላችሁት መሰረት ነው። ታዲያ እኔም ጊዜዬን ወስጄ ካለችኝ ጊዜ ሃቁን ሳቀርብ፤ ስምታችሁ ለመነጋገሪያ በተለመደው እንድታደርጉት ሳይሆን፤ ከምጽፈው በመነሳት ውነታውን ይዛችሁ አመዛዝናችሁ ችግር የሚፈጥሩ ቁጭ ብለው በመነጋገር የማያምኑ እና ቁጭ ብለው ፊት ለፊት ከተነጋገሩ፤ ይዘውት የተነሱት አላማ ስለሚከሽፍባቸው ውሸቱን ውነት እያስመሰሉና ውነቱንም ሃሰት አድርገው እያቀረቡ ለግል ጥቅማቸው ብቻ በማሰብ ፤ እየበጠበጡን ያሉትን ጠርታችሁ በስብሰባ ለማናገርና እምቢም ካሉ ፤ በግልጽ ችግሩን መርመራችሁ ያገኛችሁትን ሃቅ ላልሰማው በማቅረብ ፤ ሰላማችሁን እንድታገኙ በሕብረት መስራትና ማድረግ ደግሞ ከናትንተ ይጠባቃል ይሄውም ከሁላችሁም ከሴቱም ከወንዱም ማለት ነው።
ለመግቢያ ለዛሬ ቲኒሽ የተረበሸውንና የተወናበደውን መንፈሣችሁን ወደ አንድ አቅጣጫና ማመዛዘኛ አስተሳሰብ፤ እንዲወስዳችሁ ወደ ፊት በሰፊው የምመለስበትን ቢሆንም፤ ባጭሩ እያደረኩኝ አቀርባለሁ ለዛሬ። ነገር ግን ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት የDallaseotc ብሎግ የተባለው መጀመሪያ መፈጠሩን የነገሩኝ ገና እንደተጀመረ ስሞን ማለት ነው ፤ አቶ ተኮላ መኮንን ነበሩ ። ብሎጉም የማን እንደሆነ በትክክል ማንም ባያውቅም የወንዶች መሆኑነበር የተነገረኝ፤ የከሌነው የእነ እከሌ ነው በሚል። ቤተክርስቲያንም ሰዎች ስለዚሁ ብሎግ ባለቤቶች በይሁናል የሁለት ወንዶች መሆኑን ነበር ያወሱት። ባለብሎጉን ባላውቅም ለማወቅም አልጥርም፤ ማንም ይሁን ማንም፤ እነተፈራ ውርቅ ወይም ዘውገ ያወጁትን አግልሉልን የሐረርወርቅን የሚለውን የዘራፊዎችና የስግብግቦች እንደ ውሻ በለቼልሞት እሩጫ አብሮ የማይሮጥ በሃቅ ሰርቶ የሚኖር እንደኔው ይመስላል ባለብሎጉ። የኢትዮጵያን አንድነትን የሕዝብዋን ክብር የበላይ አድርገን፤ የምናስቀድመውን እንደእነ ፍቅረማሪያም ሊቀነጥስንና ሊያስቀነጥስን እንደሚደክመው አይነት ኢትዮጵያዊ ሳይሆን፤ የሚያከብርና እራሱንም የሚሰድቡትን ማጥፋት ሲችል ፤ ነገር ግን የሁሉንም አስተያየት ፍርዱን ለሕዝብ በሚል ዴሞክራሲ መጀመሪያ በግሪክ አገር እንደተፈጠረችው ነች የብሎጉ ባለቤት አቀራረብ። እነዘውገም መማር ነው ያለባቸው እንጂ ከዳላስ ብሎ ሊኮንኑት የሕሌና ችሎታም ብቃትም የላቸውም። በእርግጥ አስተያየት ሰጪዎች በዳላስ ብሎግ ላይ ለምትጽፉት ባለብሎጉ የማይመለከተው ቢሆንም፤ ባለው ውዝግብ መክኒያት በዳላስ ብትናደዱ ፤ስለምትሰጡት አስተያየት ግን ትልቁን ቁምነገር ቤተክርስቲያንና አገርን ጉዳይ ማተኮሩን ትታችሁ የግለሰቡቹን የግል ጉዳይ መጻፉ አንባቢያችሁን ከዋናው ጉዳይ መስመሩንና ጌዜውን እንዲያባክን ያደርጋል። ጉዳይ ላይ ብቻ እናተኩር ስለ ክሱ ለምሳሌ፤ መቼነው ብጥብጥ በቅዱስ ሚካኤል ደብር የተጀመረው? ስረመሰረቱ ያለመግባባቱ ከየትመጣ? ለምን ክስተጀመረ? ማነው ተጠያቂው? ከሳሾቹስ ውነት አላቸው ወይስ በሃሰት እንደው በከንቱ ነው? ቤተክርስቲያኑና የኢትዮጵያ የጋራመረዳጃ ዛሬ የአንድግሩፕ የገንዘብ ምንጭ ይሆነው ብሎም እድሩና የኒያላ ኢንሹራንስ፤ የኢትዮጵያ ካውንስል የሚለውና የም እመናን ጉብኤ፤ የአፍሪካ ቀንድ ዴቭሎፕመንትና እኔ የጀመርኩትን የኮሚኒቲ ሴንተር ገንዘብ አምንጡ እያሉ ስላሉት፤ አይን እናበራለን በሚል የአይን ባንክ ክሊኒክ በሚል በአንድ የአጭበርባሪ ዛፍ ላይ በተለያየ አቅጣጫ በሰሜን በደቡብ፤ በም እራብና በምስራቅ ቅርንጫፎች በአሜሪካን ከተማዎች የተንጠለጠሉት ለምንና እንዴት በቅዱስ ሚካኤል ደብር በዳላስ ሊገባ ቻለ ለምን፤ የሚለው ላይ ብቻ እናተኩር። ብሎግ እንዴት እንደሚሰራና መረጃዎችን እንዴት ያለማግኘት ወይንም ማግኘት እንደሚቻል በሌላ ጊዜ እመጣበታለሁ። ለዛሬ ግን Dallaseotc የሐረርወርቅ ብሎግ ነው ብለው ደግሞ ወደ እኔ ያመጡትን ያሃሰት ደም በመላው ሰውነታቸው የሚሰራጭባቸው ተፈራ ወርቅና ፍቅረማሪያም (ሌሎቹም አሉ የነሱን ስም ልተውና ዋናዎችን ለመጥቀስ ነው) ብሎግ ምን እንደሆነ እንዲማሩና እንዲያጠኑ እስተዛው የቤት ስራ በመስጠት ለዛሬ፤ ቀጥሎም፤ ጀግናው አቤ ጉበኛ ስለ ጀግናው አንድ ለኢትዮጵያ የነበሩት ስለ አጼ ቴዎድሮስ "አንድ ለናቱ" በሚል ስለ እነ ፍቅረማሪያምና ተፈራ ወርቅና ዘውገ አይነቶቹ ከንቱዎች በመጸሃፋቸው ካስቀመጡት ተውሼ ለዛሬ የነዚህ ውሸታሞች የስም ላጲሶች ጉዳይ በዚህ አጠቃልዬ ወደ ዋናው ቁም ነገር እገባለሁ ይሄውም።
"ሳያውቁኝ በወሬ በመነዳት፤ እያወቁኝ በምቀኝነት የሐሰት ወሬ የሚያወሩብኝን ሁሉ፤ ከተፈጥሮ ደካማነትና በስንፍናቸው ከሚጫወትባቸው ድንቁርና እግዚአብሔር እንድያድናቸው እመኝላቸዋለሑ።" አቤ ጉበኛ አንድ ለናቱ ከሚለው መጽሃፋቸው በገጽ አምስት ይመልከቱት።
በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ከተጀመረ ጀምሮ አንድም ጥሩ አስተዳዳሪና የሰላም የእውነተኛ ሰው ቦርድ ውስጥ ሰርቶ ወይም የቦርድ ሊቀመንበር ኖሮ አያውቅም በሚል ብዙዎቻችሁ የአፍ ልምድ ሆኖባችሁ ስትናገሩና አዳዲስም ለመጡት ይሄንኑ ስታካፍሉ እነሱም ከናንተ የሰሙትን በመቀበል ሲሞግቱኝ ብዙ ሰው አጋጥሞኛል። ሆኖም ከዚህ በታች ያሉትን ሰዎች ሳላነሳ ያለፍኩበት ጊዜ የለም ለነሱ ሳይሆን ለኛ የእነሱን ጥሩ ስራና ችሎታ በማስወስ የተሻለ ስራ መስራት እንድንችል። አሁንም በዚህ መልኩ ስለነሱ ላቀርብ አምላክ ስለፈቀደልኝ ምስጋናኤ ትልቅ ነው። ስለ ሰዎቹ ሳይሆን ስለውነት መመስከር ነው። ከዛም የነሱን የአመራር መንገድ ይዘን አሁን ካለንበት የጽብ ኩዋስ ጨዋታ ወጥነት ወደ ቤተክርስቲያን አይምሮውችንንና ሰውነታችንን እንደንመለስ ነው የኔ ልፋቴ። ብዙዎቻቸው በጣም እባክሽን ውነቱ ስለዚህ ከተማ ችግር አንቺ እጅ ስለሆነ ውነቱን ንገሪን ወይም ንገሪኝ የትኛውነው ውነቱን የያዘው የሚለው ጥያቄያችሁ የመጣው ወደ እኔ እያንዳዳችሁን ከቤተችሁ እየቀሰቀሰ የነካችሁ መክኒያት በመኖሩ ነው። ግን ምክሬ በግል እስኪመጣባችሁ አትጠብቁ በጋራ ስለሚያደማችሁ እንጂ።
ሰፋ አድርጌ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንዴት እንደተጀመረና እንደተገዛ ቦርድስ እንዴት ተዋቀረ ስለሚለውና ስለችግሮቹ ወደፊት አወሳዋለሁ አይቀሬ ነው። ነገር ግን ጥንስ ሱን ሃሳቡን ቤተክርስቲያን እነግዛ ብሎ እኔንም ሕዝቡን በስልክ ገንዘብ እንዲሰጥ እንዳነሳሳ እየደወልኩኝ ሌሎቹን ደግሞ በስብሰባ ጠርቶ በሁዋላ ቦርድ በሚል የተቀመጡት ማለት ነው በዚህ መልክ ነበር ባጭሩ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሊገዛ የቻለው። የተገዛውም የተሰበሰቡት በሰጡት ገንዘብ ሳይሆን በነጋዴውና በሕዝቡ ሲሆን እስላሞችም በጊዜ እነ ሃኪም መሃመድና ብሎም ዋርዳ ሳይቀሩ ገንዘብ መስጠታቸውም ሃቅ ነው። ወደፊት እንዳልኩት በሰፈው አቀርበዋለሁኝ ለብዙ ጊዜ ጽፌ ያስቀመጥኩት ስላለ ስለሚካኤል አጀማመርና በሕይወት እያሉ አቶ ታደሰ ግዛው እንደመዘግብ ጠርተውኝ ልጃቸው ቤት ያስመዘገቡኝም ጨምሬ።
ሚካኤልን ያለምንም እንከንና ሲያገለግሉ የነበሩት ሁለት ሰዎች ናቸው አንደኛ አቶ ምስክር ሁለተኛ አቶ ዳኜ። ጋሼ ምስክር (ቄስ ምስክር አሁን) በጣም የሚገርመው የፈለገው ነገር ቢሆን ፊታቸው ላይ ተጨባጭ ማስረጃ እንክዋን ካላዩ ለወለድዋቸው ልጆች እንክዋን የማያዳሉ በእግዚአብሄር መንገድ ብቻ በእውነት መንገድ የሚሄዱ ለግማሾቻችን አባት፤ ለግማሹ ወንድም ናቸው። እኔ በእድሜዬ ብዙ ሰዎች ሃቀኛ የሆኑ አይቻለሁ ጋሼ ምስክርና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሃይማኖት በየነ ግን ከልጆቻቸው ጋር በአገር ጉዳይም ይሁን ሚካኤልን አስመልክቶ በተለያየ ጊዜ በተደረገው ያለመግባባት በፍጹም ለስጋቸው አድልተው የማያውቁ ሃቀኛ ሰዎች ናቸው።
ጋሼ ምስክር ፤ የቅዱስ ሚካኤልን በምክትል ሊቀመንበርነት ሲያገለግሉ በነበረበት ወቅት ነብሱን ይማረውና ከሻለቃ ክፍሌ ጋር ሲሰሩ በመከባበርና፤ በትክክልኛ ብቻ በሆነው የስራ ልምዳቸው እንደነበር ሁላችንም ውነት የምንመሰክረው የምናውቀው ነው። ሻለቃ ክፍሌ ወደ ኢትዮጵያም በገባበት ሰሞን ቤተክርስቲያኑን በሚገባ ጠብቀውና ሕዝቡን አንድ አድርገው ሰላም በሰፈነበትና ቦርዱ ውስጥ እንክዋን ያሉት ሰዎች እነማን ናቸው ብሎ ሰው ስለምንም ችግር የማያስብበት ጊዜ ነበር የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የነበረው እርጭ ያለ ውነትም የክርቲያኖች ቤት። ሻለቃ ክፍሌ ሲመለስ ነበር ሕዝብ እንክዋን ኢትዮጵያ ገብቶ መመለሱን ያወቁት እስከዚህ ነበር የጨዋ አመራርና አስተዳደር የሚችሉ ትምህርቱም እውቀቱም ስለቤተክርስቲያን ያላቸው ሰዎች ጥቅም። ሻለቃ ክፍሌ እኔ የሰምንት አመት ገደማ ሆኜ ከሚያውቁኝ ወጣት መኮንኖች አንዱ እሱ ነበር። እንደ አባቴ ነበር የማየው እሱም ልጄ ነበር የሚለኝ። ስለ አቶ ምስክር ያለውን ክብርና አድናቆት የገለጸለኝን በቀጥልበት ብዙ ጊዜ ይፈጃልና ጋሼ ምስክር ምንም እንከን የሌለባቸው አስተዳደር ችሎታቸው ከማንም የማይመጣጠን ነበር። ስለ ሻለቃ ክፍሌ ለብቻው በቅርብ እጽፋለሁ ጎበዝ የአስተዳዳር ችሎታ የነበረው ነበር ክስር አት ማስጠበቅ ጋር አጣምሮ።
ሌላው አቶ ዳኜው ላቀው የተባሉት ሲሆኑ እኝህ ሰውማ ግማሾቻችን ከቦርዱ ሲወጡ ነው የሚካኤል ቤተክርስቲያን ቦርድ ሊቀመንበር መሆናቸውን የሰማነው። የነበረውን ሰላም አጠናክረው ሁሉንም በአምላክ ፍቅር ስም አቅፈው ከሁሉም ጋር በሰላም ሃላፊነታቸውን ሳያጉዋድሉ ሁሉንም እንደ ጸባዩ ይዘው አገልግለው ቦታውን በግድ ሳይሆን በወድ የለቁቁ ናቸው ልክ እንደጋሼ ምስክር። እኝህም ሰው የብዙ አመት የአስተዳደር ችሎታ ያላቸውና የሚቀርባቸው በጆሮዋቸው እየመጣ መከፋፈል እንዲፈጠር ሲሞክር እንክዋን እንዳልሰማ አይተው ተው ወይም ተይ ብለው የሚያልፉ ለመሆናቸው ብዙ ሰዎች የሚያወሱት ነው። ዳኜ ደጉ ጥሩ ሰው የሚል ስም አትርፈዋል በዳላስ ፎርት ወርዝ።
የቤተክርስቲያኑ ክስ ሲጀምር ወደ ሰላሳ የሚሆኑ ሰዎች የቤተክርስቲያኑ አባላት በማነጋገር ክሱ ቆሞ በሰላም ያለውን ችግር አዳምጠን መታረም ያለበት እንዲታረምና ወደፊትም የቦርድ አባላት ምእመናንና አባላቱን በስልጣናቸው በመጠቀም እንዳይበድሉ በምተረዋርዋጥኩበት ጊዜ ብዙ ሰዎች እስቲ አቶ ዳኜን አነጋግሪ ውነቱን ሊነግርሹሽ የሚችሉት እሳቸው ብቻ ናቸው፤ በሚል ወደ ሳቸው መሩኝ። ውነትም በትክክሉ ስላለው ችግር እሳቸው ያስረዱኝን በድጋሚ ፍርድ ቤትም ሄጄ ሰማሁት። ስለፍርድ ቤት ከዳኛ የሰማሁትን በሚቀጥለው እንደማቀርብ ቃል እየገባሁ አቶ ዳኜንና ጋሼ ምስክርን የመሰሉ በችሎታና በልብ ጥሩ ነት የታደሉ በመሃላችን ፍርድ ቤት መዳረሳችን የሚያስገርም ነው።
ባጭሩ አቶ እዮልን አስመልክቶ ከቤተክርስቲያኑ ገንዘብ ወስድዋል ብዬ አላምንም ጠርጥሬውም አላውቅም። እኔ ከእዮኤል ጋር የነበረን ችግር ወይም ጥያቄ ፤ ስልጣኑን ተጠቅሞ ቤተክርስቲያኑንና አባላትን ጎድትዋል ነው። ነገር ግን እዮኤል ገንዘብ መውሰዱን የሐረርወርቅም ታውቃለች፤ ማስረጃም አላት የተባለው የፈጠራ ወሬ ነው። በዚህ አጋጣሚ ማለት የምፈልገው ግን እዮኤል ደግ ሰውና የዋህ መሆኑን ነው። እነ በትሩ፤ ኪዳኔ አለማየሁና አጃቢዎቻቸው ተጠቅምውበታል ስላመናቸው። ሰው ለመጉዳት አስቦ በተንኮል፤ ነገር በጥብጦ ሕዝብን ወይም ግለሰብን የሚጎዳ ስራ አይሰራም እዮኤል እልህ አለው እንዳብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወንድ ሳያስብ ይናገራል ከቦርድ አባላት ጋር ሳይማከር ውሳኔ የራሱን ይሰጣል፤ ቃሉን አይጥብቅም። ነገር ግን አጭበርባሪዎችን ለይቶ ማየት ባለመፈለጉና ባለመቻሉ፤ የለፋበትን ቤተክርስቲያንና አስተዳደር እንደተሰጠው በምርጫ የተረከበውን ሳያስረክብ ለመረጠው ሕዝብ መውጣት ችልዋል። ይሄንን ስል ብዙ ሰዎች "በሃሰት ምሰክሮበሽ?" የምትሉ ብዙ መሆናችሁን አውቃለሁ። ግን ዛሬ የማወራው እኔ ላይ ስለተደረገው ሳይሆን፤ ሌሎች ጥሩ ስለሰሩት ስለሆነ የኔ በመጨረሻ ይቀርባል አይስቸኩልም ። መክኒያቱም ውነትን ተከተዬ ለሕዝቡ ክብርና ጥቅም መቆሜን ብዙሃኑ የተረዳ በመሆኑ፤ ሲጀመርም ስለእኔ ብዬ ሳይሆን ያሁሉ ውርጂብኝና አድማ በካንጋሩ ዳኞችና የካንጋሩ ወረዳ ፍርድ ቤት ከረጂ ምግብ ቤትና ላክንታኢን የካንጋሩ አውራጃ ፍርድ ቤት የደረሰብኝ፤ ያአያሳስብኝም። ስለእኔ ብዬም ሳይሆን ተፈራ ወርቅና ዘውገ ቃኘው በሕዝብ ስም ከተቀመጡበት ይልቀቁ በማለቴ እንጂ። ሳልናገር የማላልፈው አንድ ቁምነገር ቢኖ፤ የእዮኤል ባለቤት በጣም የምትመሰገን ነች። ከኢዮኤል ጋር የተጋጨውን ሁሉ እንክዋን ልታኮርፍና ፊትልትነሳ ፤ በክርስቲያንና እንደስምዋ እንደ ኢትዮጵያ ሁላችንን በፍቅር አቅፋ የኖረች ነች። መደረብ ሲያልፍም አይነካት ማስታረቅ እንጂ። አንድ ቀን የሰላም አርአያ ተብላ ሽልማት በቅዱስ ሚካኤል ደብር እንደምትመረቅ ተስፋአለኝ።
ቀጥዬም ማለት የምፈልገው ሌላው ትሁትና የአስተዳደርና የቦርድ አመራር ሃላፊነትን ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ወንድም ዮሴፍ እረታ ሲሆን፤ ይሄውም ከተጨባጭ የስራው ውጤት አንዱን ብጠቅስ፤ አቶ እዮኤል ነጋ በሃሰት በኔላይ ማለትም በዳላስ ፎርት ወርዝ ብቸኛዋ የኢትዮጵያ አንድነትንና የሕዝብዋን ክብር አንድ ሰንደቅ አላማዋን በማስከበር ለገንዘብ ፍንክች የማልል፤ የአገሬን ጉዳይ በትግሬ ነጻአውጭ የማለውጥ፤ ቆራጥ የኢትዮጵያ አንበሳን፤ የትግሬ ነጻአውጪና ጥገኞቹ ከበውኝ ለምን የወያኔ ጭፍረኞችና ደሞዝተኞች መሆናችንን ለሕዝብ ገለጻ አደረገች በሚል በመነሳት፤ ከሕዝቡ ትገለልልን በሚል ተነስተው፤ እነሱው ከሳሽ እነሱው ጠበቃ፤ እነሱው ዳኛ ፤ እነሱው ምስክር፤ ሸንና አስተባባሪ ሆነው ፍርድ በፈረዱብኝ ጊዜ በተደረገው ሕሌናቸውንና አገራቸውን ሕዝብዋን ለገንዘብ የሸጡ የሆዳሞች አንድነት ውስጥ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቦርድ፤ ሊቀመንበሩን እኔን ከሆዳሞቹጋር በመተባበር እንዲያወግዘኝ ልኮልናል በሚል በትሩ ገብረእግዚአብሄር፤ተፈራ ወርቅ የተባለው፤ ዘውገ ቃኘው፤ ኪዳኔ አለማየሁ እንዳሉት፤ ሃቁን በሶስት ቀን ውስጥ የቤተክርስቲያኑ ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ እንዲያስታውቀኝ በሚል በደብዳቤ ለቦርዱ በጠየኩት መሰረት፤ ልክ በጠየኩት መሰረት፤ በሶስት ቀን ውስጥ ፈጽሞ ቤተክርስቲያኑም ቦርዱም አንድም ሰው በተባለው ቦታና ቀን እንዳላክ ገልጾ ፤ ቤተክርስቲያኔም ቦርዱም በሙሉ ለኔ ጥሩምኞታቸውንና የክርስቲያንነት ድጋፋቸውን በአቶ ዮሴፍ ፊርማ የተረጋገጠ ደብዳቤ እንዲደርሰኝ እድርግዋል። ይሄም የሚያሳየው የራሱን ሃላፊነትና የቤተክርስቲያኑን አስተዳደር ጠንቅቆ ማወቁን ነው። አቶ ዮሴፍ፤ የቅዱስ ሚካኤል ቦርድ የላከው ማንም እንደሌለ ባስቸክዋይ ባድራሻዬ በመላኩ ለቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳደር የቦርድ ሊቀመንበርነት ቦታ በሃላፊነት የሰጡት ሰዎች ሁሉ ሊመሰገኑ ይገባል በዚህ አጋጣሚ።
ሌላው ትሁትና የሁሉንም እሮሮ አዳማጭ የነበረው ቦርድ ውስጥ ሲሰራ አቶ ልኡልሰገድ ነው። ወንድም ልኡልሰገድ የተጠየቀውን ያለበትን ሃላፊነት በስነስርአቱ የተወጣና ሁላችንንም ያለምንም ማዳላትና ማቅረብ ወይም ማራቅ በክርስቲያንነታችና በኢትዮጵያውያንነታችን የወንድምነት ፍቅር የሚያሳየን የነበር ነው በቦርድ ውስጥ። እንዴት ወደ ማህበረ ቅዱሳን በሚባል የሚጠሩት ከሚካኤል ይውጡና የጥቅም ግጭት ያመጣሉ የሚለውን ማመልከቻ ካቀረቡት ዶክተር ሰለሞንና አቶ መላኩ ታደሰ ጋር ሊጣመረ እንደቻለና ንትርክ ውስጥ ሊገባ እንደቻለ ባላውቅም፤ ቤተክርስቲይኑን ንትርክ ውስጥና ከዛም ወደ ፍርድ ቤት ለክስ ግለሰቦችን አዳረሰ ወይም መክኒያት ነው ለተባለው ማመልከቻ ካቀረቡት አንዱ ነው፤ ይሄም ሌላው በቅርብ የማብራራላችሁ ጉዳይ ነው።
አቶ ተኮላን ያወኩት ማንንም ሳይፈራ ምን ይሉኛል ትናንታ በሬዲዮ ከእነ በትሩ ፤ተፈራ ወርቅ ፤ ዘውገ ጋር ወግኜ ቀርቤ ሳላነግግራት፤ በሬዲዮ ስኮንናት የተፈረደባትንም ፍርድ አርቃቂነት ሃላፊነት ተቀብዬ የተነሳሁባትን ዛሬ እንዴት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሎ ስለሌሎች ሳይጨነቅ፤ በራሱ አይምሮ በመነሳሳት፡ ከዚህ በታች ያለውን ከተናገረ በሁዋላ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ስብሰባላይ በቄሶች ፊት ። ከዛ በሁዋላ፤ ስላለው የቤተክርስቲያን ችግር መፍትሄ ለመፈለግ ከማነጋግራቸው ወንድሞቼና እህቶቼ አንዱ ነበር። ችግሮችን ለማቆም በየጊዜው እየደወልኩኝ አነጋግረው ነበር። ይሄውም ተፈራ ወርቅ ስብስብ ብሎ በብዙዎቹ ቁንጮዋቸው ላይ ሳይቀመጥ በፊት ማለት ነው። ስለዚህም በሌላ ጊዜ አቀርባለሁ። በእርግጥ ተፈራ ውርቅን ጥልቁ የቤተክርስቲያኑን ብጥብጥ ጠማቂውን በኮሚቲ አናት ላይ ቁጢጥ ካደረጉት በሁላ፤ የእኔና የአቶ ተኮላ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ተቁዋርጥዋል። የዲፐሎማቲክ ግንኙነቱን ለመቀጠል እሞክራለሁ። በከተማችን ፤ አንዱም ወንድ ስለጥፋቱ እንክዋንስ ይቅርታ ሊጠይቅ ይቅርና እንደውም በራሱ ዘራፊነት በስው ብሶ አግልሉልኝ ከኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህብር የሚል ሲሆን ፤ አቶ ተኮላ ግን ከልቡ ከዚህ ቀጥሎ ባለው ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ፤ ሁላችንም ስህተት ካለን ይቅርታ ብንጠይቅ ቲንሽነት ሳይሆን ትልቅ ልባምና አይምሮም እንዳለን እንረዳለን። አቶ ተኮላ ያለው "ወይዘሮ የሐረርወርቅን በጣም አደንቃለሁ። ጠንካራ ጎንዋን ስጠኝ ለኔም ብዬ አምላክን እለምነዋለሁ፡ ነግር ግን የኔ ችግር ከወይዘሮ የሐረርወርቅ ጋር፤ ወረቀት እየጻፈች የምትበትነው ነው ሆኖም ይቅርታ ወይዘሮ የሐረርወርቅ፤ ብዙ ሰዎች ወይዘሮ የሐረርወርቅን አስቀይማሃል ስላሉኝ ይቅርታ እጠይቃለሁ" በሚል በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጣም ትምህርታቸው ልብ ውስጥ የሚገባው አባታችን ከቤተክርስቲያን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉት ፤ የተጣላውን ሁሉ አቶ እዮኤልንና ወይዘሮ ጥሩ አይርን ጭምር ባስታረቁበት ጊዜ ነበር። ታዲያ እኔም ይቅርታውን ከመቀበሌ በፊት ያልኩት ነበረኝ ያንን በቲያትር መልክ ወደ ፊት ለመዝናኛ በዚሁ ብሎግ አቀርባለሁ።
በመጨረሻም የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጥሩ የቦርድ አመራርና ሰላም ኖሮት አያውቅም የሚባለው እንግዲህ ከዚህ በላይ ባሰፈርኩት ውነታ ተሸንፍዋል።
አምላክ ሁላችሁንም ስለውነት ያቁማችሁ ከውነት ሌላ አፋችሁውስጥ ሃሰት አያናግራችሁ። ሃሰት የሚናገር በውስጡ እንደእሳተ ጎሞራ የሚተናነቀ ውሸት ሰላም እየነሳው ስለሆነ። ከዚህ በላይ የጻፍኩትን አስጀምረህ ያስጨረስከኝ አምላኬ ትልቅ ምስጋና ይግባህ። አሜን።