Sunday, October 31, 2010

ሕዝቡ አንቅሮ የተፋቸው በአሁን ጊዜ፤ አይናቸውን አንይ እያለ እሮሮ የሚያሰማው ዋሽተውት ያደሙት፤ በዳላስ ፎርት ውርዝ በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ መሃልና በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በተከሰተው ጸብ፤ የብጥብጡ ጠንሳሾች፤ ጠማቂዎችና ተጠያቂዎች ድብቅ የትግሬ ነጻ አውጪ በደሞዝ ተቀጣሪ ትግል አደብዛዦችበኒያላ ኢንሹርንስ ስምና በአይን ባንክ በሚል በሲያትል፤ በአትላንታ፤ በፍሎሪዳ ወዘተ የሚንቀሳቀሱት፤ አቶ በትሩ ገብረግዚአብሄር፤ አቶ ኪዳኔ አለማየህና በእድሚ በሰባ ውስጥ ያሉና ታናሻቸው ትልቁ የኒያላ ኢንሹራንስ ቀንድ የሆነው፤ ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አሰፋ ብቻ ናችው፨

የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በጋርላንድ ቴክሳስና ችግሮቹ ቁጥር ሶስት፡፡

በብሎግ ስማቸውን በግልጽ አስቀምጠው ላመኑበት ወይም ሕብረተሰባቸው ማወቅ አለበት ብለው ለሚያነሱት ጉዳይ ፤ በግልጽ የሚያቀርቡበት የመወያያና ሰላማዊ ሃሳብ ማስፈራሪያና ዛቻ ሊኖርበት የማይገባ ወደ ሑዋላ የማይከፈት መስኮት ነው። በሌላ በኩል ፤ የሃይማኖት ተቁዋማትን አስመልክቶም ሆነ ፖለቲክን ጭምር የሚጽፍ ሰው ወይም ሰዎች፤ ለሰላምም ይሁን ለጸብ ወይም ውሸት ለሚጽፉት ሳይቀር ጸሐፊዎቹ ወይም ጸሐፊው ስለጻፈው የጸበም ይሁን የሰላም ጋባዥ ነው አንባቢውን። ስለሆነም፤ ብሎግም እራሱን እየደበቀ እራሱ ያደረገውን ድርጊት ሌላ ሰዎች እንዳደረጉትና እንዳቀረቡለት አድርጎ መጻፍ የሚያሳየው ይዞት የተነሳው አላማና የሚጽፈውም ውነታ ስለሌለው ለተነሳበት ጸብ ብቻ የሚጠቅመውን ሁሉ እንደፈለገው በሚያስደስተው ሁኔታ ብቻ ጽፎ በማስነበብ፤ የሚፈልገው ዛፍና ፍሬው ወደ እሱና አበሮቹ ካልወደቁ አይኔን ግምባር ያድርገው ለማለት ብቻ ነው። በግልጽ የሚጽፍን የሚኮንን ውሸታምና ፈሪ በራሱ አይምሮና ጣቶቹን የሚጠራጠር ብቻ ነው።

በየሐረርውርቅ (የኢትዮጵያወርቅ)ጋሻው።
የዲፌደብልዩ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ብሎግ አዘጋጅና አቅራቢ።
ዳላስ ቴክሳስ አሜሪካ።

ወደ ዋናው አረስት ከመግባቴ በፊት ለአንባቢያን ማሳሰብ የምፈልገው፤ እኔ በግሌ ከማንኛውም (ዋም) ኢትዮጵያዊ ጋር ጽብ ወይም ግጭት የለኝም፤ የግል ኑሮዬን ወይም ውሎዬን ስራዬን ብሎም አዋዋሊን በሚመለክት። ነገር ግን ባአገሬና በሕዝብዋ በአንድ ሰንደቅ አላማዋ የሚነግድ የሚከፋፍል የሚያላግጥ አሽዋፊ ፓለቲኪኛ ሲመጣ በኢትዮጵያ አንድነት አልደራደርም። እነዚህ ጥቂት ወንድሞቼ ሕሌናቸውን ለግል ጥቅም የሸጡ የለወጡ የትግሬ ነጻ አውጪ ካምፕ ገብተው የኢትዮጵያነን ከሚሉት ጋር የማልስማማው በአገሬ አንድነት በሕዝብዋ ክብርና በአንድ አረንግዋዴ ፤ቢጫ ፤ቀይ ባንድራዋ ልዋጭ፤ ልዋጭ በአሜሪካን ዶላርና በኢትይጵያ ውስጥ በቤት መስሪያ መሬት ቁማር ትግሉን ቁማር ስለሚጫወቱ ብቻ መሆኑን በትህትና አሳስባለሁ። በድጋሚ፤ በአገሬና በሕዝብዋ አንድነት ባንድ ሰንደቅ አላማ ከማንም ጋር አልደራደርም ። ስልጣና ገንዘብም ሊማርኩኝ በብዙ መልኩ እየተተኮሱብኝ እሩምታው ቢሰማም ፤ ሊማርኩኝ አልቻሉም፤ ከኢትዮጵያዊነት የአንድነት ካምፕም ሊያነቃንቁኝና ሊማርክኙም አልቻሉም። እኔ ተው የምላቸው ሲጠየቁ በከተማው ለምሳሌ ዘውገ ቃኘው በኑሮዬ መጣችብኝ ከኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህበርር ሬዲዮ ዝግጅት ይነሳ በማለቴ። ወንዱ እንደምን ሴትዋ እንደወንድ እንዳልል ላገሩ ቅድሚያ ስጥቶ እራሱን የሚጎዳ አንድም ወንድ ገና አላየሁም ዳልላስ ውስጥ በተገኘው አብሮ የሚዋጥና የሚውጥ እንጂ። እኔ ደግሞ የጋራችን የሆነችውን በኢትዮጵያንና በሕዝቡ አንድነት መጡብኝ ነው መልሴ። ሕዝብ ሆይ እነሱ ለኪሳቸው እኔ ላገር አንድንትን ክብር ለሕዝብዋ አንድነትና ስለም ስለሆነ ትክክለኛውን ፍርድ ለሕዝቡ እተዋለሁ። ሆኖም የኔን ጥናት ይስጣችሁ የሌላችሁ እላለሁ።

የቅዱስ ሚካኤል ደብረና በጠቅላላው በዳላስ ፎርት ወርዝ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ በአንድነት፤ በመከባብር፤ በፍቅርና አንተ ትብስ አንቺ ትብሺ ተባበልን የኖርነውን አንድንታችንን የበጠበጡትና በቅዱስ ሚካኤል ደብርና በኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህበርና በሬዲዮ ስርጭቱ ጭምር አዛዥ ተደርገው የሕዝብ አናት ላይ ተንፈራጠው አልውርድ ብለው ችግር የፈጠሩብን ስማቸው ከዚህ በታች ያሉት ግለሰቦች ሲሆኑ ላለው የቤተክርስቲያን ክስም ይሁን የመረዳጃ ማህበሩን ሕገ ወጥ ስራ መጠቀሚያ ማድረግ ሌብነት በመረዳጃ ማህበሩ ስም መስፋፋት በሕብረተሰባችን ዋና ተጠያቂዎቹ ናቸው። እነዚህም ሻለቃ ተፈራ ውርቅ አሰፋ፤ አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሄር፤ አቶ ኪዳኔ አለማየሁ፤ ሲሆኑ በፍጹም ከእነዚህ ጋር ይተባበራል ብዬ ያልገመትኩት አቶ መላአኩ ታደሰም የነሱን ስራ አይን ባንክና ሌላውንም አስመክቶ በመተባበሩ ያንን አስመልክቶ መጠየቁ አይቀርም ሆኖም አቶ መላኩ ታደስን ከላይ ካስቀመትክዋቸው ሶስት ሰዎች እኩል በቀላል ሚዛን አልመዝነውም ትልቅ ስህተት ግን ስርትዋል። ሶስቱን የሕብረተሰባችንን በማንኛውም ሃላፊነት በሚጠይቅ እንደመረዳጃ ማህበርና ቤተክርስቲያን አካባቢ ብሎም የአገር ጉዳይ ወያኔን ለመቃወም በሚደረገው ትግል ውስጥ ክመጡ ጀምሮ ብዙ አኮላሹዋችሁ ወንዶቹን ከናካቴው እነሱ ይጎትቱዋችሁ ጀመር በየስብሰባው እናንተ እነሱን ዳር እንደማውጣት ወንድሞቼ። አንድነታችንን አክብረን ማስከበረ ክልብ በማያወላውል ተግባር ላገራችን አንድነትና ለሕዝቡ አንድነት ክብር የቆምን ብቻ ስለሆኑ ከበ1996 በፉት የነበረውን ፍቅራችንን መልሰን ባስቸክዋይ ካልገነባን ፤ ለራሳችንም ላገራችንም ለሕዝብዋም የጉዳትና የመከፋፈልን ካባ የለበስች ኢትዮጵያን ላዲሱ ትውልድ ጥለንለት እንደምናልፍ ማመን ይገባናል።


Dallas, Texas Ethiopian Community በ1996 በነጮች አቆጣጠር ነበር አይን ውስጥ የገባው ጥናቱ ወያኒና ሻቢያ ኢትዮጵያን ልክ እንደተቆጣጠርዋት፤ የወያኔ ጠላት ነን የሚሉን በእያፓ በኩል ብቅ ሲሉ፤ ውነት ሁላችንም መስሎን እያፓ ያመጣውን ደገፍን እጃችንን ዘርግተን ተቀበልናቸው። ከዛም መረዳጃ ማህበሩን ተረከቡን። እነዚህም ግለሰቦች ወደ ዳላስ የመጡበት መክንያት የሕዝቡ ብዛት ለኖሩበት የወረቀት ማጭበርበር በጣም ያልተበላ የሲራልዮን አልማዝ እድ ሆነው ስላገኙት ከኦክላሆማ፤ ከመንፊስ ቴኒሴን ከማያሚ ፍሎሪዳ አባልተን እንብላቸው በሚል የመጡ ሲሆኑ እየመሩም መሃላችን ያስገብዋቸው፤ በማስገባት የፓለቲካ ስልጣን ጥማቸውን ለማርካትና የሚወክሉት ፓርቲ ቦርድ አባላትን ያባዙ መስልዋቸው ሕዝቡን አሳምንው እንዲክተላቸው ማድረግ ያልቻሉት እን አቶ ፍቅረማሪያም ደረስና አቶ መንግስቱ ሙሴ ሲሆኑ ሌላው ትልቁ ተባባሪ አቶ ዘውገ ቃኘው በተነገረው ሰዎቹ የሌላቸውን ሹመት እየካበ ከግል ጥቅሙ አንጻር አጋር ጠቃሚ ሆነው ስላገኛቸው ተመሳሳይ ሰዎች በተግባር በማግኘቱ እያዳናቀ ለህዝብ ጆሮ በማስገባቱ የብዙ ኢትዮጵያውያን ኪስ ባዶ እንዲሆን ሚና ተጫውትዋል አድርግዋል። እነዚህን ሶስት ገለሰቦች በከተማው ብዙ የኖሩ በመሆናቸው የከተማው ሕዝብ ሊመክራቸው ይገባል። ጥፋታቸውንም አምነውበት ይቅርታ መጠየቅ ይገባቸዋል። የፍቅረማሪያምና የመንግስቱ ጉዳይ የፓለቲካ ፓርቲ ለማጠናክር መሆኑ ግልጽ ነው ሆኖም ህላችንንም ጉዱን።

የቤተክርስቲያን ክስ ትክክል ነው ብዬ ባላምንም እላይ ያካሰሱት ብዬ ሳልፍው፤ የቅዱስ ሚካኤል ቢተክርስቲያን በሁዋላ ደብር ወይም ካቴድራል ቦርድ ቀደም ሲል የሰራው ግፍ በእኔላይ ቢሚዘን ምናልብት ባቶ ተስፋዪ ተክሌላይ ከደረሰው በስተቀር ተወዳዳሪ እንክዋን አይገኝለትም በከተማው የለውምም። ገና ቢተክርስቲያኑ ህ ብሎ ሲጀመር የነበረውን መዝገብ አውጥተው ጥለው ሁሉ ነበር ነገር ግን ማህደሩላይ ስሜ መጻፉን ከውስጥ ባለማየታቸው ባዶውን ልገኝ ችልዋል ማን ለምን ያንን እንዳደረገም ታውቅዋል። በሃሰት የቤተክርስቲያኑ ሊቀመንበር መሰከረባት ብላችሁ ስንታችሁ ነበራችሁ ያዘናችሁት እኮ። ይሄውም የሃይማኖት አባቶች አይደፈሩ ፤ፓሊስ አይጠራባቸው እንደወንጀለኛ፤ ለወፍ ጎጆው እንደሆነ ሁሉ ቤቱ ዞሮ መግቢያው ለሃይምኖት አባቶች ድግሞ ቢተክርስቲያን ቤታቸው ስለሆነ ቁልፍ መለወጣችሁ በሃሳብ እንደማሳምን የሚለው ዳላስ እያመጥዋቸው ባሰቃይዋቸው ቁጥር ለአባቶች በመቆሜ ማለት ነው ይሂም ለግሌ አይደልም። የዛሬ አስራ ዘጠኝ አመት ቤተክርስቲያኑ እንዲገዛ ያስተባበሩት አባ ፍቅረማሪያም ዛሬ አቡነ ዳኔል ላይ በደረሰውና ከዛም በፊት መጥተው መንገድ ላይ በተጣሉት መነኩሲ መክኒያት ለምን ግፍ ይሰራል በማለቴ ማለት ነው። ታዲያ ፍርድ ቤት አልሄድኩኝም። ሞኝ ነኝ ማለት አይደለም ወይም ማንንም ፈርቼም አይደለም ቤተክህነትን አክብሬ እንጂ። የእግዚአብሄር ቢት የሁሉም ክርስቲያን ስለሆነ የግሌ አድርጌ ስለማልቆጥረው እንደ ግሌ ጉዳይ ውስጄ መክሰሱን አላምንበትም። በጸሎት ግን የማይቀለበስ ፍርድ አግኝቻለሁ። ፍርድ ቤት የቤተክርስቲያንን ችግር ለመፍታት የሚቻልበት ቢሆን ኖሮ ትክክለኛ መንገድ ቢሆን ኖሮ፤ የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ አቡነ ሞርቀሪዎስ ክስ ያቀርቡ ነበር ብዬ አምናለሁ። መክኒያቱም መብቱን የተቀማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ማንም የለም እንደሳቸው ባስተዳደር በደል ማለት ነው። የሰው ልጅ ሲከፋ ቤተክርስቲያን ይሄዳል። ሰዎች ሲያስከፉትም ለእግዚአብሄር መንገሩ ትልቅ ዘለአለማዊ ዘላቂ ፍርድ ይፈረድለታል ሃቅ ካለው። የሰው ልጆች መብት ተከራካሪዎችን እንክዋን ብናይ ፍርድ ቤት አይደለም ትግሉ። እኔም የሰው ልጆች መብት ታገይ ብሆንም ቤተክርስቲያንን አስመልክቶ በውስጡ ኤትየስቶችና ጥያቄ የምንጠይቀውን ከቤተክርስቲያኑ ለማጥፋት ብዙ ቢሞክሩም ካጠገባቸው እራቅ ከማለት ሌላ ለጥቂት ጊዜ አብሬ ጊዜዬን አላተፋም። ይሂንን ስል ብዙዎቻችሁ ለምን አትከሻቸውም በሃሰት ሲመሰከረብሽ ስትወነጀዬ ያላችሁ ብዙ በመሆናችሁ ነው። ሃይማኖቴን በኒኩ ወይም ቤተክርስቲያኑን የማደርገውን አውቅ ነበር ። አሁንም ችግሮች ከመጡ በሃይማኖቴ ላይ የማደርገውን መፍትሄ አውቃለሁ። ለመሳሌ ፓሊስ ቅዱስ ሚካኤል በር ላይ ሲቆም መጀመሪያ በግንባር ቦርዱን ገብቼ በግልጽ ደብዳቤ በማቅረብ አምላክ ቤት ፓሊስ ለምን ይቆማል አቁሙ ብዬያለሁ፤ ይህ ክስ ከመምጣቱ በፊት ነው።

አንዳንድ ሰዎች ከይልማ ፈለቀ ጋር ያለው ችግር ምንድንው ብላችሁዋል። ይልማ ፈለቀና ተፈራ ወርቅ የክርስቲ ተፈራን የአስራ አምስት አመት ልጅዋን በመጣ በወሩ እስዋ ሰው በቦክስ መተሻል ተብላ ልጁም እናትህን አግዘሃል ተብሎ ታስሮ ሲፈታ ፤እናቱ ግን በስር ቢት ከርማ ስለነበረ ለስዋ ሳይነግርዋት የአሜርካን መንግስት ሳያባርረው ልጁን ይውጣ ሳይል፤አንድም ደብዳቤ ከኢሚግሬሽን ችግር ሳይፈጠር በራሳቸው ፍቃድ ይልማና ተፈራ ወርቅ ልጁም እናቱም ናፍቆታቸውን አስር አመት ሲያልሙ የነበረውን አብሮ ለመኖር ሕልም ቀጭተው ልጁን ዲፓርት አደረጉት ወደ አዲስ አበባ። በዛ ላይ እስዋ እንደነገረችኝ መኪናዋን በማን ፊርማ ልትሸጥ እንደቻለች መልስ ከመረዳጃ ማህበሩ ማጣትዋ ሲሆን ለማንኛውም መኪናዬን ሽጡ ብላ አልፈቀደችም የፈረመችውም አልነበረም። ምነው ለዚህ አይነት ችግር የምንሆና ብዙም ለወገን የደረስን በከተማው እያለን ምናለ ቢነግሩን ማን ፈቀደላቸው የሰው ልጅ በድብቅ ብዙ ሰው ሳይሰማ አስቀምጥልን ብለው አንዱን ወጣት ከዛም ገንዘቡ ሲባዛ ልጁን ለመላክ? ለመሆን አቶ ሃብቴ የሰጠውስ አራት መቶ ሃብሳ ዶላር ግፋ ብኢል ሌላ አራት መቶ ቢያስጨምር ነው እኛ የማናውቀቅ የአይር መጉዋጉዋዣ ጂት መጥቶ ይሆን ብዞ ገንዘብ የሚያስከፍል ለአንዴ መሄጃ ስምንት መቶ መስሎኝ ነበር ያኔ። ይልማ ፈለቀም የሞቀ መረዳጃ ማህበር ውስጥ ገብቶ ተፈራ ወርቅም እንዲሁ ተጠቃሚ ቢሆኑም ቅሉ፤ የመጣውን ሁሉ ኢትዮጵያውያዊ ተቸገርኩኝ ሲል ሂድ ከዚህ ብሎ በግልምጫ ከማባረርና ከመሆነን፤ ምናለ ለሕዝቡ ስለተቸገረው ኢትዮጵያዊ እንደረዳው ቢነግሩን? እነዚህ ግለሰቦች፤በዳላስ በከተማችን በሕብረተሰባችን ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ጭካኔ በሰው ልጅ ስም ገንዘብ ስብስቦው የሰው ልጅ ማባረር የራሳቸውን ልጆች እያሳደጉና ዘምድ እያስመጡ ያፈጸሙት ግፍ ገና በምድርም በሰማይም እግዚአብሄር ይጠይቃቸዋል የፈርድባቸዋልም አሁንም እየታየ ነው። አንድ ቀን እንደነሱ በኤርፕሌን በራ የመጣች ነች ወደ አሜሪካን ነገር ግን ቀን የጣላትና የነሱን እጅ አየች የክፉ ኢትዮጵያውያንን ጥቂት ወንዶች። በልጅዋ ስም ብዙ ገንዘብ ተዋጥትዋል ለምሳሌ አቶ ሃብቴ ብቻውን አራት መቶ ሃምሳ ዶላር ስጥቶዋል ይታያችሁ ይሄ ሁሉ ለአንድ ጊዜ ወደ አገር ቤት መሄጃ መሆኑ ነው። እንክዋን አራት መቶ ሃምሳ ዶላር በዚህ ላይ ልጁን ወስደው በግሮሰሪው ውስጥ የሰራ የነበረ ጥሩ ወጣት ልጅ መኖሪያ አፓርትመንት አስቀምጥ ብለው ልጁን ሊንረዳ የምንችል ኢትዮጵያውያን እንዳናውቅ አድርገው ትልቅ ካርጎ እቃ ወይም ጄት በጄት ውስጥ አሳፍረው ይልኩ ይመስል በሰበሰቡት ገነዝብ ውስጥ ትኬት ገዝተው ልጁን አባረሩት ካሜሪካን ምድር። ክርስቲ ተፈራም ከስር ቤት ስትፈታ መጀመሪያ የራባትን ያላየችውን ልጅዋን ለማየት ነበር የጁቭናል ዲፓርትመንትን የጠየቅቸው። ይሂንን ስተረዳ በሞራል ውድቀትና በብስጪት እነዚህን ሰዎች ብዙ ነገር ለማድረግ ብትፈልግም ከዚህ ቀደም ማታ ማታ እሁድ ይተላለፍ በነበረው የአማርኛ ስርጪት፡ እየመከርኩኝ ልጅዋን ተመልሱ እንዲመጣላት ላስመጣላት እንደምችል ገልጬ ኑሮዋን ለማስተካከል ደፋ ቀና ስትል የይልማና የተፈራ ወርቅ ብሎም በትሩና ዘውገ ያደረሱባት ግፍ ለሞት አድርስዋት በአርባ ሁለት አምትዋ ከዚህ አለምና ክለጆችዋ በሞት ተለይታለች። እነዚህ ግልሰቦች ግን አሁንም ሕዝቡን በቅዱስ ሚካኤል በጊዮርጊስ ቢተክርስቲያኖች ሳይቀር እያደሙት ይገኛሉ። በመጨረሻም ወንድምዋ መጥቶ እራቅ ያለ ቦታ በርካሽ አግኝቶ የቀብርዋ ስነስራት ተፈጽምዋል። ከጁቭናል ዲፓርትመንት ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ሳጣራ የአሜሪካን መንግስት ይውጣ ከአሜሪካን ብሎ ልጁን ፈጽሞ እንዳላለና ምንም ማስረጃ ልጁን ካገር አስወጡ የሚል ከኢሚግሬሼንም ለይልማ ፈለቀም ይሁን ለተፈራ ወርቅ ወይም ክርስቲ ተፈራ ለምታውቃት አንዲት ሴት ጭምር ተዛዝ ወይም ጥያቄው አልቀረበም በፍጹም። በልጁ ላይ፤ ደህና ሲማር ከነበረበትና እናቱም እስክትለቀቅ አቅም አዳም የደረሰ ባለመህኑ የአሜሪካን መንግስት በሲስተሙ መሰረት፤ ትምህርት ቤት በጁቭናል ሲያስተምረው ስለነበረ እንዳይቀጥል ልጁን እናቱ ሳታውቅ አለ በከተማው ብላ እያሰበች ፍቃድ ሳይጠይቅዋት፤ ሌላው ቢቀር ምን እናድርገው ሳይልዋት፤ ልጅዋን በመከራ ወደ አሜሪካን አገር የገባላትን በፍቅዳቸው ተፈራ ወርቅና ይልማ ዘሪሁን ልጁ በመጣ በሁለት ወሩ ዲፓርት አደረጉባት። በመረዳጃ ማህበሩ ውስጥ በመቀመጣቸው ይልማ ፈለቀ ቦታውን በጊዜው ለቅቄአለሁ ያለውና ሳይመረጥ ከላይ እንዳልኩት በመረዳጃ ቦርድ ውስጥ ተነጥፎ የነበርው ተፈራ ወርቅ አሁንም በመረዳጃ መህበሩ በስተጀርባው የተንጠለጠለው በይልማ አዛይነት ጊዜ አልፈጀበትም በጎ መስራት ለወገን መራራት ማድረግ የማይችለው ውስጥ በመግባቱ አላማው ሌላ ስለሆነ በማህበሩ የተተከለበት፤ ወገኖቻችን ያለምንም የግል ጥቅም ምንም ይሁን፡ ችግሩ ወይም ክብደቱ ልንረዳ የምንወደው ብሎም ለምንችለው ኢትዮጵያውያን ሊነግረን/ሊነግሩን ሲችሉ ተባብረው ከይልማ ፈለቀ ጋር ልጁን በፍቃዳቸው ዲፓርት ለማድረግ/አደረጉት። ይታያችሁ አንድ ቀን እንክዋን ክርስቲ ተፈራን የታሰረችበት ሄደው አይተዋት አይውቁም። እራሳቸውን እንደ አሚሪካን መንግስት ቆጥረው ዲፓርት አድርገውባታል ወደ አዲስ አበባ። ካልቻሉ ለሕብረተሰቡ ያስታውቁ ነው ጥያቄዪ እኔ ። የራሳቸውን ልጆች እያሳደጉ የሌላ ኢትዮጵያዊት ልጅ ግን ገንዘብ አምጡ ብለው ሕዝቡን ሞክረንለት እዚህ እንዲቆይ አልተቻለም በሚል በሃሰት፤ እደግመዋለሁ ልክ ትልቅ በካርጎ እቃ ወይም ጄት በጄት ውስጥ ያሳፍሩ ይመሰል መኪናዋም እቃዋም ያለእስዋ ፊርማ ተሸጥዋል ይሄ በሕይወት እያለች እነሱው ፊት እኔ ባቁዋቁዋምኩላት "የክርስቲ ተፈራ እርዳት ኮሚቲ" ስብሰባላይ አቶ ሃኪም መሃመድ ሚስ ሶፌ ጂ፤ ተፈራ ወርቅ አሰፋ፤ ይልማ ፈለቀና የኮሚቲው ተቆጣጣሪ ያደረክዋት እራስዋ ክርስቲ ተፈራ የተናገረቸው መለት ነው። ይሄ ግፍ ተሰርቶባት ሲገርማት ከእስር ቤት ስትወጣ ልጄን ለማን ብላችሁ ላካችሁት? መኪናዬስ? ብላ በመጠየቅዋ፤ በ 2006 በኢትዮጵያ ቀን በአለ ላይ፤ ማለትም ይልማ ፈለቀ አዘጋጅ ኮሚቲው ሰብሳቢና ተፈራ ወርቅ የመረዳጃ ማሕበሩ ፈላጭ ቖራጭ ወይዘሮ ክርስቲ ተፈራ ሶስት ደቂቃ ለሕዝብ ችግሪን የማሰማበት ስጡኝ ቲኒሽ ለምበላውኛ ለቤት ክራይ የሚረዳኝ ስጡኝ ብዪ ልጥይቅ ስትል ከለከልዋት። ነገር ግን የአይን ባንክና የኒያላ ኢንሹራንስ (ግሻ ኢንሹራንስ)የዘውገ ቃኘው የቤት እሸጣለሁና የበትሩ ኒያላ ኢንሹራንስ (ጋሻ)ዌል ፋርጎ የሚለው በሕዝቡ መረዳጃ ማሕበር ገንዘብ በቀን አራት ሺዶላር ከፈልን የሚሉበትን አዳራሽ አሸብርቆት ነበር። በብስጭት አሳምመዋት ባለችበት ሰአት በሞትና በሕይወት መሃል በምትሰቃይበት ግዜ ይልማ ፈለቀም ተፈራ ወርቅም ሲጀመር ጀምሮ የሚሰሩበት የወያኔና የኢንቬስተሮቹ አንዱ መድረክ ሬዲዮ ላይም ሕዝብም ያደረሱባትን በደል ለመናገር ድምጽዋን እንዳይሰማ አፍነዋት የተጨቖኘችው ክርስቲን ተፈራ ስትናገር፤ ተፈራ ወርቅ አሰፋ፤ በትሩ ዘውገ ቃኘው፤ ይልማ ፈለቀ በቁሜ ገደሉኝ በደሌን በ....ስልወጣ! እንዳለቸው ወዴያው በእውነት ሞታ ተቀበረች በአርባ ሁለት አመትዋ።
ይልማ ፈለቀ የተቸገሩ ኢትዮጵያውያንን ጉድይ ማስፈጸሙ ጥቅም ያለው ባለመሆኑ፤ ለወገን የምንገበግበውም እንዳንረዳቸው ጉዳያቸውን ችግራቸውን አፍኖ ለሕዝብ ባለማሰምት ታዋቂ ሆንዋል። የክርስቲ ተፈራ ጉዳይ አንዱ ብቻ ሲሆን ይልማ ፈለቀ ቤተክርስቲያኑንም አስመልክቶ ወይም የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበሩኝ የጠሙዋላው ውስጥ ጥልቅ አለእንጂ ምንም አተዋጽኦ ያደረገ አይደለም። የዛሬ ሶስት አመት በጹሑፍ እንደበተንኩት የጋራ መረዳጃ ማሕበሩንና የሬዲዮ ስርጭቱን በጋሻ ኢንሹራ ማለትም ኒያላ ከዛም እድር በሚል ስም እርስ በእርስ መረዳዳቱን አጥፍቶ በእድር በሚል የትግሬ ነጻ አውጪ ፕሮግራም ሊተኩት ሲሉ፤ በመንቃቴና ለሕዝብ ይፋ በማድረጌ መክኒያት ስላስተላለፉት ስለምመለስበት በዛልይ አቀርበዋለሁ። ለዛሬ ግን ወደ ጀመርኩበት ልመለስና፤ የተቸገሩትም አንገታቸውን ደፍተው ኢትዮጵያዊ አያሳየኝ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ የሚባልም አልስማ የሚለው እሮሮ ከላይ ባለው መክንያት ስንቱ ነው። ቀጠሮም በመረዳጃ ማሕበሩ ጉዳይ ጠይቄ በቅርብ አቀርበዋለሁ አመት ሆነው የጋራ መረዳጃው ፕሬዘደንት የተባለው የሚመከተው የገንዘብም ጥያቄም ስላለ ስለ ክርስቲ ተፈራም ስብሰባው እንዳይደረግና ግብረአበሮቹ ያስተላለፉትን በሃሰት የተሞላ በመረዳጃ ማሕበሩ እንዳትደርስብን ልሕዝቡ ያቀረበችውኝ ተሳስቼ ነው ብላ ይቅርታ ካልጠየቀችን የሚለውን በመደገፍና እንደ ፍርድ ቤት ሕግ ፍርድ ወስዶት ማለት ነው። በሬዲዮም እንናገር እድል ይሰጠኝ ሲል ሕብረተሰቡ እነይልማ ፈለቀ እነዘውገ ለራሳቸው ጥቅም ካልሆነ ሕዝቡ በስሙ የሚከፈልበትን የሬዲዮ ስርጭት ጠጠቃሚ እንዳይሆን ከልክለውት እሮሮዋቸውን የሚያሰሙ ስንቶቹ ናቸው ። በጣም የሚያስደንቅ ነገር ግን በዳላስ ባንክ ሊከፍት ነው በኤሌትሪክ የሚሄድ ባስ ባኢትዮጵያ የከፈተ በዳላስም ላሜርካን ሕዝብ ሊከፍት ነው በሚ ገንዘብ አምጡ አክሲሆን ገቡ የኢትዮጵያ ባንክ ልንከፍት ነው ብለው ገለሰቡን በዚሁ ሕዝቡን ለማጭበርበሪያ ወጥቶ ሕዝቡ ገንዘብ እንዲሰጥና አቶ ጠቅላይ መለስ ዜናዊ ባሉት መሰረት በሚል ገንዘብ ጠይቅ ስብሰባ ጠርተንልሃል ሲሉት እምቢ ያላቸውን ሻለቃ ውይም ኢንጂነሬ ገታቸው እሼቱን የቅዱስ ሚካኤል ደብር እጃችን ላይ ነው ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ የኛው ነው እያሉ በመጨረሻም ይልማ ፈለቀ ይሄንን ችግር የሌለውን ግለሰብ ያላወቁ አለቁ አሉ፤ ውነት ባንክ ሊከፍት መስልዋቸው በትሩም ፤ ኪዳኔ አለማየሁም ተፈራ ወርቅም በተለይ ይልማ ፈለቀ እቤቱ ለኢንጂነር ጌታቸው ማንም ሳይሰማ ግብዣ ያደረገለት ሰው ነው። የደግንት ቢሆንማ ጥሩ ነብር ምን ለአሜሪካን ምግብ ችግር የለም። ቁምነገሩ ለዚህ ነው የግል ጥቅም ላይ ብቻ ነው የጋራ መረዳጃ ማህበሩን የሚጠቀሙት የምላችሁ በሃቅ። በኢንጂኔር ጊታቸው እሼቱ ላይ የሚፈልጉት ስላልሆነ እነ በትሩ ያስቀመጡት ስም በጣም ከባድ በመሆኑ ባለቤቱ ኢንጅነር ጌታቸው የገለጸውን ማቅረብ ይችላል። ሆኖም አህን እነዚህን ግለሰቦች በሙሉ የዛሬ ሶስት አመት ከሁዋላቸው በላት! በላት! እኝበላት! እናቁማት! በሚል ለግል ጥቅም ወያኔ ያሰለፋቸው በስም ኢትዮጵያውያን በተግባር ግን የአሜሪካን ዶላሮች የሆኑ ወንዶች በወያኔ ጭፍሮች እየታጀቡ ምስያቸውን ሰብስበው እኔ ላይ እንደዋሹት እርስ በእርሳቸው በአሁኑ ወቅት ፤ አንዱ ላንዱ መደበቂያ ሊሆን በማይችልበት ሁኒያታ በመገፋፈጥ የእራሳቸውን ምንና ማንነት ፤ ገበናቸውኝ በግልም በጥንድም እያስመሰከሩ በመሆኑ ሕዝቡን በማታለላቸው በአጭበርባሪነት ሚዛንና ፍርድ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ። ሕዝብረተሰቡም እነዚህን ጥቂት ውርውሮች ወንዶች ስላወቃችሁዋቸው ፤ ምስክሮቹም በራሳቸው እነሱው በመሆናቸው ፤ውሸታቸው ሁሉ በመረጋገጫ በመያዙ፤ የሃሰት መስካሪነታቸው በቁርጥ የኢትዮጵያ ልጆች ላይ ሃጢያት መቖለሉ ዘዴያቸው አልፎበት አልሰራ ስላለ፤ ዳላስ የእርስበርስ ግጭታቸውን የዳላስ ኢትዮጵያን በሙሉ በማስመሰል በየስልክ ኮንፍራንስ ውስት፤ ሲያስተጋቡት ተገኝተዋል። ይህንንም ተግባር ሕዝብ ልብ በል።

ከላይ የተጻፈውን ሁሉ ካነበባችሁ በመጨረሻም የእኔን ችግር ፤ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን የምንረዳ በጣም ደስ እያለንና በጣም ከውስጣችን ለወገን የምንቆረቆር በዚሁም ለተቸገረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንደችግሩ ፈጥኖ በመድረስ ቀኝ እጁ በመሆን የምንታወቅ ሰዎች ሕዝቡን አስተባብረን ጭምር ወገናችንን ልንረዳ ስንችል እነዚህ ለግል ጥቅም የሰከሩ ጥቂት ግለሰቦች የመረዳጃ ማህበሩን ብለው ቤተክርስቲያኑ ከሁዋላ ይዘው የሶሻል ኮሚቴ በሚል ስም ኢትዮጵያዊው እንዳይረዳ ለምን የችግ ራስ ዳሽን ወይም ኪሊማንጃሮ ይሆኑበታል ነው። እንርዳ ወገን ነው የምለው። ወንጀል ተደርጎም የቀረበብኝ ይሄው ነው ለምን ኢትዮጵያውያንን በነጻ ጉዳያቸውን ተፈጽማለች ታስፈጽማለች ነው።


በሚቀጥለው እስክንገናኝ አምላክ አገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን ከከፋፋዩ የትግሬ ነጻ አውጪ እጂ ነጻ ያድርግልን። የከርሞ ሰው ይበለን ሁላችንንም።

Saturday, October 23, 2010

www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com በዳላስ ፎርት ወርዝ የኢትዮጵያ ሕብረተስብ ስም በሕዝቡ ጥያቂ የተከፈተ ሲሆን አገልግሎቱ በግልጽ ለሕብረተሰቡ እንጂ ለግልሰቦች ወይም ለግልጥቅም አይደልም።

የቅዱስ ሚካኤል ክቴድራል በጋርላንድ ቴክሳስና ችግሮቹ ቁጥር ሁለት እነሆ።

በየሐረር ወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው
ዳላስ ቴክሳስ፤ አሜሪካ።

        በመጀመሪያ ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ስለ ብሎግ ሕግና ስርአት ውነታ ባጭሩ ማስገንዘብ እወዳለሁ። ብሎግ ባጭሩ ሰዎች እራሳቸውን ማነነታቸውንና ትክክለኛ ስማቸውን ሳይደብቁ ሃሳባቸውን እንደልብ በነጻነት የሚጽፉበትና ሕዝቡም ወይም ሕብረተሰባቸው ሃሳቡን በነጻ የሁሉንም መብት አክብሮ ሃሳብ የሚሰጥበት ። ይሄም እኔ በይሆናል ወይም መሰለኝ በሚል የምለው ሳይሆን ባለብሎግ ድርጅቱ ያወጣው ሕግ ነው። ገብቶ መንበብ ይቻላል። እያስመሰሉ መጻፍና የሌላውን ጽሁፍ የራስ አድሮ ማቅረብና ማንነትን ደብቆ ሌላሰው በማስመሰል pretending to be someone else) መጻፍ  ሕገ ወጥ ተግባር መሆኑን የብሎግ ሕግና ስርአት ብሎግ ለሚከፍት ሁሉ ያስረዳል። ብሎግ የሚከፍተውም ማንኛውም ሰው ሕጉቹን ተቀብያለሁ የሚለውን ካላመለከተ መቀበሉን ካላረጋገጠ ባለብሎግ ሊሆንም አይችልም። የእኛ ወንድሞች ግን ፊት ለፊት ግቡ ሲባሉ በጐዋሮ ዙሪያ ዞረው ተሸፋፍነው ነው ብሎግ ላይ አዳምጡን የሚሉን። መጀመሪያ እራሳችሁን ለሕዝብ ስታስታውቁ ነው ለሕዝብ የምትቆሙ ተቆርቁዋሪዎች ልትሆኑ የምትችሉት። ክርስቶስ ስንት መከራ እንደደረሰበት እንክዋን ክርስቲያኑ ሌላውም የሚያውቀው ነው ስለዚህ ላመናችሁበት ፊትለፊት ወጥታችሁ ውነት ሰው ሆናችሁ ተገኙ መጀመሪያ። ከብሎግ ሕግ በከፊል የወሰድኩትን ሃቅን እነሆ፡፡ 

Blogger Content Policy

Impersonating others: Please don't mislead or confuse readers by pretending to be someone else or pretending to represent an organization when you don't. We're not saying you can't publish parody or satire - just avoid content that is likely to mislead readers about your true identity.
Blogger is a free service for communication, self-expression and freedom of speech. We believe Blogger increases the availability of information, encourages healthy debate, and makes possible new connections between people.
The boundaries we've defined are those that both comply with legal requirements and that serve to enhance the service as a whole.
Violence: Don't threaten other people on your blog. For example, don't post death threats against another person or group of people and don't post content encouraging your readers to take violent action against another person or group of people.)


     የቅዱስ ሚካኤል ደብረምሕረት ካቴድራል በጋላንድ ቴክሳስና ችግሮቹ ቁጥር ሁለት እነሆ።

ሰው ሰሚ ካጣ ወደ ሚሰማው ይሄዳል። በጊዜው ቦርዱ በቦርድ አሰራር ሳይሆን በጉልበት አስተሳሰብ ጡንቻ በመታገሉ ክሱ በያይነቱ ሊከሰት ችልዋል። በሃላፊነት የተቀመጡ ሰዎች አንድ ሰው ብቻ እንደፈለገው በሚሰጠው መልስ ሳይሆን በቦርድ ስብሰባ በመገኘት ተነጋግረው ለቤተክርስቲያኑ አባላት ምንም ይሁን ጥያቄው ማንም ይጠይቀው መልስ ለጥያቄ መሰጠት ነበረብት ያአልተደረገም ቀደም ሲል በቤተክርስቲያኑ ቦርድ። ትርፉ እንግዲህ አብሮ የኖረው በማያውቀውና ባላጣራው ጉዳይ ማጋጨት ሆንዋል እንደሚታየው። አንዳንድ ስር የለቅቁ ውሸቶችም እንደውነት ቀርበውም ነብር ቤተክርስቲያኑን ፕሮቴስታንት ሊወርሱት ነው በሚል ያአሁን ውነት ለመናገር አጣርቼ ሃሰት ሆን አግኝቼዋለሁ። ሌላውን ለግል ጉዳይ ለማሳመን መዋሸት የለበትም። በተለይ አንዳንድ እህቶቼ በዚህ አይነት ውሸት ብዙ ተርዋርጠዋል የተታለሉ ይመስላል። ጉዳዩ ፍርድ ቤት የሚይስኬድ አልነበርም በፍጹም። ባንድ የቦርድ ስብሰባ  የሚፍታ ነበር።


       ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያውያን በአንድ አምላክ ስም የከበረ የኢትዮጵያዊነት ስላምታ እንዴት ናችሁ ብዬ ሳቀርብ ከልቤ ነው። ለሰጣችሁኝ ማበረታቻ ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ። አንዱም ብሎግ አስተያየት ሰጥቶል ክሪቲክ ጥሩ ነው መጥፎ የሚሆነው ሃሰት ፈጥሮ ውነት አስመስሎ ማውራት ነው። አስተያየት እቀበላለሁ ጉዳዩ የዚህ ብሎግ ሕዝባዊ በመሆኑ ግላዊ ሳይሆን። ከዚህ በታች ያለውን በፍርድ ቤት ውስጥ እራሳችሁን አስቀምጣችሁ በኔ ቦታ አስቡት የትኛው አጠገብ ነው የምቀመጠው ብላችሁም አስቡት። መሃል ላይ መቀመጫ የለም ከከሳሽም አይደለሁም ችግሩንም ከፈጠሩት ከአንዳንድ የቦርድ አባላትም አይደለሁም አንዳቸውም የእኔ አጋዢነች የሚሉትን እምነታቸውን ልተባበር አልፈለኩም ስላልሆንኩም። ሆኖም ወደ አገኘሁት ሰው በጣም ተጠግቶኝ ሊቀመጥ ወደ ማይችልበት ባዶና ሰፊ መቀመጫ ተቀመጥኩኝ። የመጀመሪያ ጊዘ ያገኘሁት ቦታ በሚካኤል ካቴድራል ቦርድ በተቀመጡበት ነበር የተቀመጥኩት። ሁለተኛ ጊዜ ስሄድ ደግሞ ቦታው ተመቻችቶ ብቻዬን ያገኘሁት በከምለት በከሳሾቹ በኩል ስለነበር በከሳሾቹ በኩል ተቀመጥኩኝ። ነገሩ ለሁለቱም እኩል እራሴን ያካፈልኩኝ ይሚስል ነበር። ከፍርድ ቤቱም ስንወጣ ሁሉም ሰላም ብዬ በመሳምም ስላም የምላቸውን በተለመደው አቅፌ የኢትዮጵያዊነት ሰላምታዬን አቀርበኩኝ። የማላቃቸውንም ክሳሽና ሌላውንም በመተዋወቅ ሰላምታዬን ከልብ አቀረብኩኝ እንግዲህ ይሄ መንደርደሪያ ሲሆን የፍርድ ቤቱን ወይም የችሎቱን ሲኒማ እነሆ ። በነገራችን በሁለቱ ወንዶችና ባንዲት ሴት ክስ ቀረበ ስለተባለው የማውቀው ነገር ምንም የለም።


     ፍርድ ቤት የመጀመሪያው ክስን አስመልክቶ ዳኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀርብለት ያለውን  ላካፍላችሁ ባጭሩ። ዳኛው ለተካሰሱት እንደዳኛ ሳይሆን መካሪና እንደውም የኢትዮጵያን ሕብረተሰብ በጣም ያውቅ ይመሰል እነእንትናና እነእንትና እንዴት ምን ሲደረግ ለዚህ ለማይረባ ጥያቄ ፍርድ ቤት ወረዳችሁ አይነት ነበር ያለው በተቆጣ መልኩ ስራ ፈቶች ስንት ነገር እያለ ከባድ ይሄንን መፍታት አቅትዋችሁ ወደ ፍርድ ቤት የሚያስመጣ ስንት ትልልቅ ጉዳይ እያለ እናንተ የደላው ሙቅ ያኝካል እንደተባለው ሁለት ጠበቃ ይዛችሁ ፍርድ ቢት ትዳረሳላችሁ አታፍሩም? በሉ ከዚህ ሄዱ ጉዳያችሁን እዚያው ጨርሱ ከፊቴ ሄዱልኝ የሚል አይነት አነጋገር ነበረው በቀጥታ ያጥሩ ዳኛ ስላም ለሁሉም ሰው የሚመኝና ጊዜውን ለማይረባ ጉዳይ ያጠፉበት የተናገረው።

     ዳላስ መሃል ከተማ ፍርድ ቤት ሄድኩኝ። ትመጣለች ብሎ የጠበቀ ከቅዱስ ሚካኤል ደብርም ቦርድ ይሁን የቅዱስ ሚካኤልን ቦርድ ከከሰሱትም አልነበረም። ከሁለቱም ጋር በፈጸሙት ተግባር የማልስማማበት አለኝ። ታዲያ ዳኛ ገብቶ የሌላ ተካሳሾች ጉዳይ እየሰማ ነበር ትልቅ የወርካ በር ድምጽ የሌለው ከፍቼ የገባሁት። አንድ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ነው አግድም መቀመቻዎች ያሉት። በኔ ቦታ ሁኑና አስቡት ያለችን በሰከንድ የሚትቆጠር ጊዜ ነች ዳኛው እያዳመጠ ስለሆነ የኔ ውር ወር ማለት ችግር ሊያመጣ ይችላል ጣልቃ በመግባቴ ፍርድ ላይ እያለ። ወዴት ነው የምቀመጠው ብዬ አሰብኩኝ። ቀኝ ሳይ አቶ ተኮላና አቶ ጸሃይ ጽድቅና ወይዘሮ ጥሩ አይርን ጨምሮ ከዚህ ቀደም ማላውቃቸው ሁለት ሰዎችም አብረዋቸው ተቀምጠዋል፤ ፊታቸውን ዞር አድርገው ሲያዩኝ ሳቄ መጣ መክኒያቱም ከማውቃቸው ጋር ሁሌም ስለምስቅ። ክሱን አክብጄ ማየት አቃተኝ ለደቂቃ። በቀኝ ደግሞ ዞር ስል የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ እዬልና እነ ዶክተር ግርማ ብሎም አቶ አበራ የተባሉት ፊት ቁጭ በማለታቸው መግባቴን አላዩኝ። እንዳልኩት በሩ ሲከፈት ዝም ያለ ሰላማዊና አርፍዶ ሊሚመጣ ባለጉዳይ አውቀው የተሰራ ይመስላል እግዜር ይሰጠው በሩ ለሁሉም እረድቶኛል ዝም በማለቱ። ከቦርዱ በኩል ከሁዋላ የተቀመጡት ወይዘሮ ፈትለወርቅና አቶ ዮሴፍ የአቶ ዮሴፍ ባለቤት ወይዘሮ እመቤት ነበሩ ሲሆኑ ዮሴፍና ፈትለቀርቅ በተለይ ሳቅታ የተሞላበት እንክዋን ደህና መጣሽ አይነት ፊትዋላይ አነበብኩኝ። በመጨረሻም አዳምጥ ጀመር። ግራ እና ቀኝ እያየሁኝ የሁለቱንም ወገን የሰውነት ንግግርና የፊታቸውን ድምጽ የሌለው ንገግር አይጀመረ በደንብ ተደላድዬ። ነገሩ ገረመኝ እልህና ያለመከባበር ምንያህል እሳት እንደሆነ። ለነገሩ ፍርድ ቤት ሰውከስሼ ባላውቅም ብዙ ጊዜ የሄድኩበት በመሆኑ በሰውልጅ መብት ተከራካሪነቴ በልጅነቴም የአውራጃ ፍርድ ቤት ሱስ ነበረብኝ በትምህርት ሰአት ከተስፋ ኮከብ ጥፈኛና ደጃች በቀለ ወያ ትምህርት ቤት ሌላው ወደ ምግብ ሲሄድ እኔ ወሬና ብዙ ቲያትር ወደ ማይበት አውራጃ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት በመሄድ እታወቅ ነበር ዳሩ ግን አንድ ቀን ያጠኑኝ ዳኛ የማን ልጅ ነሽ ለምን እዚህ ትመጫለሽ ሁልቀን ብለው እስካባረሩኝ ጊዜ ደረስ ማለት ነው። ታዲያ ያልማድ ብዙ እረድቶኛል ፍርድ ቤት ጋር ተለማምጃለሁ ፓሪስም እንዲሁ። ይሄንን ስታነቡ እየተዝናናችሁ ታተኩሩበት ዘንድ ነው በዚህ መልክ የማቀርብላችሁ። በመጨረሻም የመጀመሪያው ባለጉዳዩች ጉዳይ አለቀና የኛዎቹ ጠበቃዎቻቸው ማለት ከሳሽ ኢትዮጵያዊ ኦርቶዲክስ ተዋህዶ አማኝና የኢትዮጵያ ኦርቶዲክስ እዋህዶ ቤተክርስቲያን ቦርድ ተከሳሾች። አሁን ክሱ ውነት መሆኑን ልቤ ተቀበለው በጣም ማዘንም ጀመርኩኝ ልገልጸው ከሚገባው በላይ።  በበኩሌ ሁለትትቱ ወገኖች የያዛቸው አባዜ እያሳመማቸው በመሆኑ አዝኜላቸው ወደ እግዚአብሄር ጽለይኩላቸው።

ዳኛው ወዳለው ልሂድ::
     በእድሜ ገና በመጨረሻው አርባዎች ውስጥ ያለ የሚመስለው ፈረንጅ  ዳኛ ጠበቃዎቹን በስም ጠራ በተለይ የቤተክርስትያኑን ጠበቃ በጣም እንደሚያውቀው ባነጋገሩ ማወቅ ቀላል ነው የዳላስ ዳኛና ጠበቃዎችን ጸባይና ልምድ ለሚያውቀው ለእንደ እኔ አይነት የመብት ተከራካሪ ጊዜ አልፈጀብኝም ስራዳው። ዳኛው የቤተክርስቲያኑ ጠበቃ ስሙን ጠርቶ ምነው ይሄ ጉዳይ አሁን ፍርድ ቤት የሚያመጣ እንዳልሆነ እያወቅህ ለምን እዚህ ተዳረሰ? ይሄ ጉዳይ በሁለት ወንድማማቾች መሃል የተፈጠረ ችግር ነው በመነጋገር የሚፈታ ነው። ፍርድ ቤት ፈጽሞ የሚያመጣ ጉዳይ አይደለም። እኔ የምፈርደው ለሁለታችሁም ለከሳሾችም ለተከሳሾችም የሚጎዳ ይሆናል። ስለዚህ በከሳሽና በተከሳጭ መሃል ገብቶ ጉዳዩን አይቶ አስታራቂ ሃሳብ የሚያመጣ አንድ ሚዲዬተር ፈልጉ አለና ስም ጠርቶ እከሌ ለዚህ ጉዳይ ጥሩ ይመስለኛል በሚል እንደዳኛ ሳይሆን አንድ ሰላማዊ የሃይማኖት አባት የተጣሉ ሰዎችን አንተም ተው አንተም ተው ብሎ እንደሚያስታርቅ ማለት ነው በትክክሉ ለማስቀመጥ። ከናካቴው ዳኛው እኔም ቤተክርስቲያን አለኝ እኮ ይገባናል ስለቤተክርስቲያና ስለእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች በሚል በመደጋገም ይሄ በፍጹም ፍርድ ቤት የሚያስመጣ ጉዳይ አልነበረም ጠበቃ እክሌ አንተም ታውቀዋለህ በሚል ለቤተክርስቲያኑ ጠበቃ ሃሳቡን ሰጠ ። ቀጥሎም፤ ሆኖም ጉዳያችሁን ወደ እኔ ችሎት ማምጣታችሁ ትክክለኛ እርምጃ ነው የወሰዳችሁት አላቸው ከሳሾቹን። ይሄውም በቦታው ሆኖ ለተረዳው ሕጉን በእራሳችሁ እጂ እንክዋን ያልወሰዳችሁ ለማለት ነው። በመጨረሻም ጎበዝ ሚዲየተር የሆነ ጠበቃዎቹም ዳኛውም በሚያውቀው ጉዳዩ እንዲታይ እና ውጤቱን በሚቀጥለው አቅርቡልኝ ብሎ ችሎቱን ዘጋና አሰናበተን።

      ከሳሾቹም ይሁኑ ተከሳሾቹ፡ የቅዱስ ሚካኤል ደብርን አስመልክቶ ከሁለቱም ወገን ስለሚከሰተው ጎጂ ውጤት ፈጽሞ ዞር ብለው ሊያዩት እንዳልቻሉና በእልህ ሁሉም የአሳይሃለሁ ወይም የአሳይሻለው የእናሳያችሁዋለን አይነት የሴጣን ፈረስ ሲጋልቡ ነበር ፊታቸው ላይ የሚታየው ። ማሸነፍ እንጂ እንሸነፋለን የሚለውን መጥራት አልቻሉም። ከፍርድ ቤቱ ወጥተው ጥግ ፤ ጥግ ይዘው ከጠበቆቻቸው ጋር ብቻ ለብቻ ሲነጋገሩ ላያቸው ምን ያህል የሰው ልጅ ከንቱና የራሱን ፍላጎት ብቻ ለማሙዋላት ሲል ሃይማኖቱን ማለትም አምላክን እንደሚረግጥም ነው የተረዳሁት ። በዚህ መሃል እኔም ወደ ዳኛው ችሎት ከመሄዱ በፊት ተቻኩዬ ጥልቅ አልኩኛና ተመልሼ አንድ ጥያቄ ጠየኩት ዳኛውን። ኮቱን እየለበሰ ቸኩል ባለው ጨዋና ጥሩ ልብና አንደጋገሩ የአንድ ደቂቃ ሃሳቤን አዳምጦ መልስ እንደዚህ ሲል ገለጸለኝ ይሄውም ፤ ሌሎች የቤተክርስቲያኑ አባላት በጉዳዩ ያገባኛል ብለን በሚቀጥለው ቀጠሮ ለማድረግ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ? በሚል ላቀረብኩት ጥያቄ ፔቲሽን ወይም ያገባናል የሚል ደብዳቤ ጽፌ ለሱ ጽሕፈት ቤት ባቀርብ እስራላይ ሊውል እንደሚችል አስረድቶኝ ተለያየን።

      ሁለተኛው ቀጠሮ ደረሰ ያው የበፊቱ ፍርድ ቤት ችሎት ነበር ክሱ የሚሰማው (ዲፓዚሽን) በቦታው ተገኘሁ።   በተለመደው ሕግ መቼም ልቡ ያበጠበትንምና አዋቂነኝ የሚለውን ሁሉ ለተወሰነ ስከንድ ከመቀመጫው ብድግ ያደርገዋልና እሳት ወይም እሾክ እንደወጋው ሰው ሁላችንም ብድግ በሉ ተባልን ተነስተንም ተቀመጥን። ባጭሩ ልግለስ የዝህን ቀን የዳኛ ውሳኔ። የቤተክርስቲያኑ ቦርድ ዋና ጠበቃን ዳኛው በጠየቀው መሰረት መልስ ሲሰጥ ከሳሾቹ የሚጠይቁት የቤተክርስቲያኑን አባላት ስምና አድራሻ የስልክ ቁጥር ጭምር ነው እና መስጠት እንደማይፈልጉ ደንበኞቹ ተናገረ። ቢትሰጥዋቸው ችግሩ ምንድነው? ሲለው ቤተክርስቲያን የገንዘብ መዋጮ ሊጠይቁበት ነው በሚል መለሰለት። ዳኛው እንክዋን የስም ዝርዝር ለምን ቤተክርስቲያን አይገዙም እግቢያችሁ ውስጥ ገንዘብ እስካልጠየቅ ድረስ መብታቸው ነው በሚል ደምድሞ የከሳሽ ጠበቅን ለምን አስፈለገ የአባላት ስምዝርዝር እና አድራሻ? አለው። የአባላትን ስም ዝርዝር የደበቁበትን መክንያት ገልጾ ቁጥራቸውን ለማወቅ እንደሆነና በቅርቡ የተቀየረው ባይሎው የቤተክርስቲያን መተዳደሪያ በአባላት ድምጽ ነው ያሉት ሃሰት ስለሆነ ማረጋገጥ እንፈልጋለን በሚል ለተጠየቀው መልስ ሰጠ። በመጨረሻም ዳኛው ባለፈው የሰጠው ት እዛዝ መሰረት አስማሚ ወይም ሕጋዊ ሽማግሌጋ ሄደው ባለመስማማታቸውን ሲረዳ ፡ እኔ ፍርድ ከሰጠሁኝ ሁለቱም ወገን ይጎዳል እንጂ አንዳቸውም አይጠቀሙም አሁንም ጊዜ ውሰዱና ባልክዋችሁ መመሪያ መሰረት ተስማምታችህ መልስ ይዛችሁ ኑ። ለዛሬ ደግሞ የምወስነው የሚካኤል ቦርድ ለሁለቱ ከሳሾች የቤተክርስቲያኑን አባላት በሙሉ ስምዝርዝር ያለስልክና አድራሻ እንድትሰጡ በሚል ደምድሞ የቀኑ የፍርድ ቤት ጉዳይ በጠዋቱ ተደምድሞ እኔም ወድ ስራዬ ሄድኩኝ።

     ለማጠቃለል ስለመጀመሪያው ክስ ጉዳይ አንደኛ ስለቤተክርስቲያኑ ያገባናል የምትሉ ሁሉ ቤተክርስቲያን ውስጥ እሁድ እሁድ ከመገለማመጥና ምን አለ ፍርድ ቤቱ? በሚል በስመአበሎ ከመስማት ተባራሪ ሁለተኛ እጅ ወይም አራተኛ ጆሮ በፍርድ ቢት በመገኘት ድጋፍ ለማንኛውም ለመስጠት ሳይሆን ውነቱን ስለክሱ በተረዳችሁ ነበር። ከሳሾችንም ቦርዱንም ላይ ፈራጅም ከመሆን የውነተኛ ዳኛን ብታዳምጡ ዛሬ ነገር አልቆ ነበር።

        ያኔም ነገርክዋችሁ አሁንም እደግመዋለሁ። የዚህ ሁሉ ትልቅ ችግሮች ቤተክርስቲያኑን ለመውረስ አሁንም ትልቅ ጥረት እያደረጉ ያሉት ፡
አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሄርን፤ አቶ ኪዳኒ አለማይህን፤ ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አሰፋን እና ከሁዋላ ያሉት ተሳቢዎች ናቸው። ይሄንን ለማቆም የሚቻለው አሁንም በመቀጠል በኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህበር ቦርድ ውስጥ የራሳቸውን ሰዎች እያዘጋጁ ነው ለምርጫ። ከሚለቁትም ውስጥ የነሱው ሰዎች ሲሆኑ ምትካቸው ተዘጋጅቶ አልቅዋል። በቤተክርስቲያኑም ቦርድ የራሳቸውን ሰዎች አስገብተዋል። ሌሎችም ሊጨምሩ ነው።


እድሩ ከመረዳጃ ማህበሩ ጋር የተገናኘ ነገር የለውም። ለምሳሌ ገንዘብ የለንም ቢሉዋችሁ እድር የገባችሁት የኢትዮጵያን የጋራ መረዳጃ ማህበር የመጠየቅ መብት የላችሁም ። መክንያቱም እድሩና መረዳጃው የሚገናኙበት በእድሩ ማመልከቻ ላይ MAAEC በሚለው አጥራር ሕዝቡን ለማሳመኛ በሚጠቀሙበት ማጭበርበሪያ ዘዴ ብቻ ነው። ሌላው አርባ ዶላር እንሰጣለን በነብስ ወከፍ የተባለው ተስጥቶም አያውቅም ማስረጃው አለ። በጥቅም የሚቃረጡት የኢትዮጵያን የጋራ መረዳጃ ማህበር አንዳንድ አባላትም ቢሆኑ ሕግ ይጠይቃቸዋል በግል ሃላፊነት።

አስጀምረህ ላስጨረስከኝ አምላክ ምስጋና ይግባህ።

Friday, October 22, 2010

Ethiopian National Government In Exile Supports "Ethiopians to remember martyrs of the 2005 Election Massacre"

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የስዴት መንግስት የተሰጠ የድጋፍ መግለጫ።


October 22, 2010
ዳላስ ፤ቲክሳስ፤ አሜሪካ።

ከአምስት አመት በፊት የትግሬ ነጻ አውጪ መሪ ለገሰ ዜናዊ በአጋዚያን ጠባቂዎቹ ያስረሸናቸውን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችዋን ውለታና የከፈሉትን ምስዋእትነት ለማስታወስ ዋሽንግተን ዲሲና በአለም ዙሪያ በሚደረገው የሰማእታት ቀን አከባበር ፤  በዳላስ ፎርት ወርዝ ንዋሪና ይሄን መልክታችንን ለምታገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የዜግነት ግዴታችሁን ብሎም የሄሌና ለመወጣት ከዚህ በታች ከዋሽንገተን ዲሲ የወጣውን ጋዜጣዊ መግለጫ በመመልክት ፤ በምታገኙት የስልክ ቁጥርና የኢሜል አድራሸ በመጠቀም የስማእታት ቀን የሕብረት አዘጋጅ ስብስብ አካል ውስጥ በመቀላቀል የበኩላችሁን እንደትተባበሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የስዴት መንግስት ያሳስባል (http://www.ethiopiannationalgovernmentinexile.org/) ::

ከዚህ በታች ያለውን መግለጫ ያወጣው Ethiopians to remember martyrs of the 2005 Election Massacre  አዘጋጅና አስተባባሪ ስብስብ ከዋሽንግተን ዲሲ ነው።

Ethiopians to remember martyrs of the 2005 Election Massacre
Press Release | October 21, 2010

Ethiopians from various cities in the U.S., Canada, Europe and Australia held a conference on Saturday to discuss and coordinate plans for the upcoming 5th anniversary of the 2005 Ethiopian Election Massacre.
As we approach the Month of November, the Global Task Force calls on all Ethiopia Democratic forces -- political, civic, human rights, media groups, and others concerned groups -- in each city and locality throughout US, Europe, Africa, Oceania, and others to come and work together in remembering the martyrs of 2005 election and the thousands of Ethiopians who perished in the hands of Meles Zenawi regime while struggling for freedom, justice, and democracy to prevail in Ethiopia.
To participate in Sunday's teleconference please register by sending email with full name and phone number to tamagn@gmail.com or call 202 656 5117.
For further info: tamagn@gmail.com

Friday, October 15, 2010

የቅዱስ ሚካኤል ደብረምሕረት ካቴድራል በጋርላንድ ቴክሳስና ችግሮቹ ቁጥር አንድ። በየሳምንቱ አርብ ማታ ቀጣዮቹ ጽሁፎች ይወጣሉ።

           አስቸክዋይ ማሳሰቢያ ለዳላስ ፎርት ወርዝ ንዋሪዎች በሙሉ።

የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህበር የህንጻ ኮሚቲ በሚል ሌላ እያለ በላዩ ላይ ለምን አዲስ ኮሚቲ የትግሬነጻ አውጭ ቅጥረኞች ኒያላ ኢንሹራንስ በሚል ስም በድብቅ ሲሰሩ የተያዙት አሁን ደግሞ ለኢንቪስትመንት የሚጠቅማቸውን መንገድ ስላገኙ ለዛ ለማዋል እየተርዋርዋቱ ስለሆነ በዝርዝር ጉዳዩን ስለማቀርብ ይሄንንብሎግ ተከታተሉ። ያው የምታውቁዋቸው ሲሆን እኔ ባቁዋቁውምክት ይህንጻ ኮሚት ስም እኔ ሳላውቅ ብዙ ገንዘብ ከጽዋ ማህበር ሳይቀር ገንዘብ ላለፈ ስድስት አመት የሰበሰቡትን ጠፈራ ወርቅ፤ በትሩና ኪዳኔ አለማየሁን እንደሰጣችሁዋቸው ግንዘባችሁን ባስቸክዋይ እንዲመልሱና እነሱም የወሰዱት ከጽዋ ማህበር አንድሺ ዶላር በትሩ የሰበሰበውንም ጭምር ለሕዝቡ እንዲመልሱ እያሳሰብኩኝ ሕዝቡም ገንዘባችሁን ጠይቃችሁ እንድተረከቡ በድጋሚ አሳስባለህ። አቶ ሴፉ ይገዙንና አቶ መላኩን መላኩ ስል መላኩ ታደሰ ማለቴ አይደልም፤ በዚህ አጋጣሚ የማሳስባቸውና እንዲያውቁ የምጥይቃቸው፤ እነዚህ ሁለት ሰዎችም እንዲረዱ የምፈልገው ያልተነገራቸው የሕንጻ ፕሮጄክቱ ኮሚቲ እንዳለና፡  እነ በትሩ፤ ኪዳኔ አለማየሁ፤ ተፈራ ወርቅ፤ ዘውገ ቃኘው፤  ለወያኔተቀጣሪ በተጨባጭ መሆናቸውንና የቅዱስ ሚካኤልን ቤተክርስቲያን ሊወርሱትነው በሚል ውነቱን ለሕዝብ በማስቅረቤ በመብገናቸው፤ የነሱ ያልሆነውን ፕሮጄክትና ሃሳብ ካለው የህንጻና ከነበሩበት ዘርፈው የተቁዋቁዋም ኮሚቴ ውስጥ መግባታቸውን እንዲገነዘቡ ነው። እኔ ሕዝብ ሰብስቤ የተመሰረተው ኮሚቲ ውስጥ ይልማ ፈለቀ ፕሬዘደንት፤ እታለማሁ ፍቅሬ ምክትል ፤ ዘውገ ቃኘው ህዝብ ግንኙነት፤ ቲና ሕዝብ ግንኙነትና ተፈራ ወርቅ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ተወካይና ሌልችቹም  ይገኙበታል። በዝርዝሩ አስክንገናኝ ለህንፃ ስራ ገንዘባችሁን ለፍታችሁ የምታመጡትን የእነ በትሩና ግብረአበሮቹ ብሎም የኒያላ ኢንሹራንስ (የጋሻ) ኢንቭስትመንት ሞርጌጅ መክፈያ አትሁኑ። በትክክሉ ኮሚቲው ዘራፊዎችና የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች የሌሉበት በቅርብ እንደገና ስራላይ እስቲውል ተባበሩኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም አስከባሪ የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው።



በየሐረርወርቅ (የኢትዮጵያ ወርቅ) ጋሻው።

           አይምሮዬን ልቤን በአንድ አምላክ ስም በማስተባበር ከዚህ በታች ያለውን እውነታ የበኩሌን የማውቀውን በግልጽ በተለመደው ሳቀርብላችሁ ብዙዎቻችሁ በጠየቃችሁኝ መሰረት ነው። ይሄውም፤ የመረዳጃ ማህበሩ ጉዳይ ለተቸገረው ወገን መገልገያነቱ በመቆሙና ቤሌላ በኩል ደግሞ የቅዱስ ሚካኤል ደብርን አስመልክቶ ከአመት በላይ ያስቆጠረው መካሰስ ጨምሮ ፤ ግራ ገባን የትኛውን ውይም የትኛዋን ለማመን፤ በጉዳዩም ያገባናል ብለን ለመግባት እንክዋን ሁሉም የራሱን ፍላጎትና ጥላቻ የተሞላበት ከማውራት ሌላ፤ በተጨባጭ ትክክለኛውን የሚነግረን በማጣታችን የስድብና የመንደር ወሬ ከማንበብና ከመስማት ሌላ ፤ ቁም ነገሩን ልንረዳ አልቻልንም ውይም ችግሩን በትክክል ባላችሁት መሰረት ነው። ታዲያ እኔም ጊዜዬን ወስጄ ካለችኝ ጊዜ ሃቁን ሳቀርብ፤ ስምታችሁ ለመነጋገሪያ በተለመደው እንድታደርጉት ሳይሆን፤ ከምጽፈው በመነሳት ውነታውን ይዛችሁ አመዛዝናችሁ  ችግር የሚፈጥሩ ቁጭ ብለው በመነጋገር የማያምኑ እና ቁጭ ብለው ፊት ለፊት ከተነጋገሩ፤ ይዘውት የተነሱት አላማ ስለሚከሽፍባቸው ውሸቱን ውነት እያስመሰሉና ውነቱንም ሃሰት አድርገው እያቀረቡ ለግል ጥቅማቸው ብቻ በማሰብ ፤ እየበጠበጡን ያሉትን ጠርታችሁ በስብሰባ ለማናገርና እምቢም ካሉ ፤ በግልጽ ችግሩን መርመራችሁ ያገኛችሁትን ሃቅ ላልሰማው በማቅረብ ፤ ሰላማችሁን እንድታገኙ በሕብረት መስራትና ማድረግ ደግሞ ከናትንተ ይጠባቃል ይሄውም  ከሁላችሁም ከሴቱም ከወንዱም ማለት ነው።


         ለመግቢያ ለዛሬ ቲኒሽ የተረበሸውንና የተወናበደውን መንፈሣችሁን ወደ አንድ አቅጣጫና ማመዛዘኛ አስተሳሰብ፤ እንዲወስዳችሁ ወደ ፊት በሰፊው የምመለስበትን ቢሆንም፤ ባጭሩ እያደረኩኝ አቀርባለሁ ለዛሬ። ነገር ግን ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት  የDallaseotc ብሎግ የተባለው መጀመሪያ መፈጠሩን የነገሩኝ ገና እንደተጀመረ ስሞን ማለት ነው ፤ አቶ ተኮላ መኮንን ነበሩ ። ብሎጉም የማን እንደሆነ በትክክል ማንም ባያውቅም የወንዶች መሆኑነበር የተነገረኝ፤ የከሌነው የእነ እከሌ ነው በሚል።  ቤተክርስቲያንም  ሰዎች ስለዚሁ ብሎግ ባለቤቶች በይሁናል የሁለት ወንዶች መሆኑን ነበር ያወሱት። ባለብሎጉን ባላውቅም ለማወቅም አልጥርም፤ ማንም ይሁን ማንም፤ እነተፈራ ውርቅ ወይም ዘውገ ያወጁትን አግልሉልን የሐረርወርቅን የሚለውን የዘራፊዎችና የስግብግቦች እንደ ውሻ በለቼልሞት እሩጫ አብሮ የማይሮጥ በሃቅ ሰርቶ የሚኖር እንደኔው ይመስላል ባለብሎጉ።  የኢትዮጵያን አንድነትን የሕዝብዋን ክብር የበላይ አድርገን፤ የምናስቀድመውን እንደእነ ፍቅረማሪያም ሊቀነጥስንና ሊያስቀነጥስን እንደሚደክመው አይነት ኢትዮጵያዊ ሳይሆን፤ የሚያከብርና እራሱንም የሚሰድቡትን ማጥፋት ሲችል ፤ ነገር ግን የሁሉንም አስተያየት ፍርዱን ለሕዝብ በሚል ዴሞክራሲ መጀመሪያ በግሪክ አገር እንደተፈጠረችው ነች የብሎጉ ባለቤት አቀራረብ። እነዘውገም መማር ነው ያለባቸው እንጂ ከዳላስ ብሎ ሊኮንኑት የሕሌና ችሎታም ብቃትም የላቸውም። በእርግጥ አስተያየት ሰጪዎች በዳላስ ብሎግ ላይ ለምትጽፉት ባለብሎጉ የማይመለከተው ቢሆንም፤ ባለው ውዝግብ መክኒያት በዳላስ ብትናደዱ ፤ስለምትሰጡት አስተያየት ግን  ትልቁን ቁምነገር ቤተክርስቲያንና አገርን ጉዳይ ማተኮሩን ትታችሁ የግለሰቡቹን የግል ጉዳይ መጻፉ አንባቢያችሁን ከዋናው ጉዳይ መስመሩንና ጌዜውን እንዲያባክን ያደርጋል። ጉዳይ ላይ ብቻ እናተኩር ስለ ክሱ ለምሳሌ፤ መቼነው ብጥብጥ በቅዱስ ሚካኤል ደብር የተጀመረው? ስረመሰረቱ ያለመግባባቱ ከየትመጣ? ለምን ክስተጀመረ? ማነው ተጠያቂው? ከሳሾቹስ ውነት አላቸው ወይስ በሃሰት እንደው በከንቱ ነው? ቤተክርስቲያኑና የኢትዮጵያ የጋራመረዳጃ ዛሬ የአንድግሩፕ የገንዘብ ምንጭ ይሆነው ብሎም እድሩና የኒያላ ኢንሹራንስ፤ የኢትዮጵያ ካውንስል የሚለውና የም እመናን ጉብኤ፤ የአፍሪካ ቀንድ ዴቭሎፕመንትና እኔ የጀመርኩትን የኮሚኒቲ ሴንተር ገንዘብ አምንጡ እያሉ ስላሉት፤ አይን እናበራለን በሚል የአይን ባንክ ክሊኒክ በሚል በአንድ የአጭበርባሪ ዛፍ ላይ በተለያየ አቅጣጫ በሰሜን በደቡብ፤ በም እራብና በምስራቅ ቅርንጫፎች በአሜሪካን ከተማዎች የተንጠለጠሉት ለምንና እንዴት በቅዱስ ሚካኤል ደብር በዳላስ ሊገባ ቻለ ለምን፤ የሚለው ላይ ብቻ እናተኩር። ብሎግ እንዴት እንደሚሰራና መረጃዎችን እንዴት ያለማግኘት ወይንም ማግኘት እንደሚቻል በሌላ ጊዜ እመጣበታለሁ። ለዛሬ ግን  Dallaseotc የሐረርወርቅ ብሎግ ነው ብለው ደግሞ ወደ እኔ ያመጡትን ያሃሰት ደም በመላው ሰውነታቸው የሚሰራጭባቸው ተፈራ ወርቅና ፍቅረማሪያም (ሌሎቹም አሉ የነሱን ስም ልተውና ዋናዎችን ለመጥቀስ ነው) ብሎግ ምን እንደሆነ እንዲማሩና እንዲያጠኑ እስተዛው የቤት ስራ በመስጠት ለዛሬ፤ ቀጥሎም፤  ጀግናው አቤ ጉበኛ ስለ ጀግናው አንድ ለኢትዮጵያ የነበሩት ስለ አጼ ቴዎድሮስ "አንድ ለናቱ" በሚል ስለ እነ ፍቅረማሪያምና ተፈራ ወርቅና ዘውገ አይነቶቹ ከንቱዎች በመጸሃፋቸው ካስቀመጡት ተውሼ ለዛሬ የነዚህ ውሸታሞች የስም ላጲሶች ጉዳይ በዚህ አጠቃልዬ ወደ ዋናው ቁም ነገር እገባለሁ ይሄውም።
"ሳያውቁኝ በወሬ በመነዳት፤ እያወቁኝ በምቀኝነት የሐሰት ወሬ የሚያወሩብኝን ሁሉ፤ ከተፈጥሮ ደካማነትና በስንፍናቸው ከሚጫወትባቸው ድንቁርና እግዚአብሔር እንድያድናቸው እመኝላቸዋለሑ።" አቤ ጉበኛ አንድ ለናቱ ከሚለው መጽሃፋቸው በገጽ አምስት ይመልከቱት።


       በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ከተጀመረ ጀምሮ አንድም ጥሩ አስተዳዳሪና የሰላም የእውነተኛ ሰው ቦርድ ውስጥ ሰርቶ ወይም የቦርድ ሊቀመንበር ኖሮ አያውቅም በሚል ብዙዎቻችሁ የአፍ ልምድ ሆኖባችሁ ስትናገሩና አዳዲስም ለመጡት ይሄንኑ ስታካፍሉ እነሱም ከናንተ የሰሙትን በመቀበል ሲሞግቱኝ ብዙ ሰው አጋጥሞኛል። ሆኖም ከዚህ በታች ያሉትን ሰዎች ሳላነሳ ያለፍኩበት ጊዜ የለም ለነሱ ሳይሆን ለኛ የእነሱን ጥሩ ስራና ችሎታ በማስወስ የተሻለ ስራ መስራት እንድንችል። አሁንም በዚህ መልኩ ስለነሱ ላቀርብ አምላክ ስለፈቀደልኝ ምስጋናኤ ትልቅ ነው። ስለ ሰዎቹ ሳይሆን ስለውነት መመስከር ነው። ከዛም የነሱን የአመራር መንገድ ይዘን አሁን ካለንበት የጽብ ኩዋስ ጨዋታ ወጥነት ወደ ቤተክርስቲያን አይምሮውችንንና ሰውነታችንን እንደንመለስ ነው የኔ ልፋቴ። ብዙዎቻቸው በጣም እባክሽን ውነቱ ስለዚህ ከተማ ችግር አንቺ እጅ ስለሆነ ውነቱን ንገሪን ወይም ንገሪኝ የትኛውነው ውነቱን የያዘው የሚለው ጥያቄያችሁ የመጣው ወደ እኔ እያንዳዳችሁን ከቤተችሁ እየቀሰቀሰ የነካችሁ መክኒያት በመኖሩ ነው። ግን ምክሬ በግል እስኪመጣባችሁ አትጠብቁ በጋራ ስለሚያደማችሁ እንጂ።


    ሰፋ አድርጌ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንዴት እንደተጀመረና እንደተገዛ ቦርድስ እንዴት ተዋቀረ ስለሚለውና ስለችግሮቹ ወደፊት አወሳዋለሁ አይቀሬ ነው።  ነገር ግን ጥንስ ሱን ሃሳቡን ቤተክርስቲያን እነግዛ ብሎ እኔንም ሕዝቡን በስልክ ገንዘብ እንዲሰጥ እንዳነሳሳ እየደወልኩኝ ሌሎቹን ደግሞ በስብሰባ ጠርቶ በሁዋላ ቦርድ በሚል የተቀመጡት ማለት ነው በዚህ መልክ ነበር ባጭሩ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሊገዛ የቻለው። የተገዛውም የተሰበሰቡት በሰጡት ገንዘብ ሳይሆን በነጋዴውና በሕዝቡ ሲሆን እስላሞችም በጊዜ እነ ሃኪም መሃመድና ብሎም ዋርዳ ሳይቀሩ ገንዘብ መስጠታቸውም ሃቅ ነው። ወደፊት እንዳልኩት በሰፈው አቀርበዋለሁኝ ለብዙ ጊዜ ጽፌ ያስቀመጥኩት ስላለ ስለሚካኤል አጀማመርና በሕይወት እያሉ አቶ ታደሰ ግዛው እንደመዘግብ ጠርተውኝ ልጃቸው ቤት ያስመዘገቡኝም ጨምሬ።


        ሚካኤልን ያለምንም እንከንና ሲያገለግሉ የነበሩት ሁለት ሰዎች ናቸው አንደኛ አቶ ምስክር ሁለተኛ አቶ ዳኜ። ጋሼ ምስክር (ቄስ ምስክር አሁን) በጣም የሚገርመው የፈለገው ነገር ቢሆን ፊታቸው ላይ ተጨባጭ ማስረጃ እንክዋን ካላዩ ለወለድዋቸው ልጆች እንክዋን የማያዳሉ በእግዚአብሄር መንገድ ብቻ በእውነት መንገድ የሚሄዱ ለግማሾቻችን አባት፤ ለግማሹ ወንድም ናቸው። እኔ በእድሜዬ ብዙ ሰዎች ሃቀኛ የሆኑ አይቻለሁ ጋሼ ምስክርና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሃይማኖት በየነ ግን ከልጆቻቸው ጋር በአገር ጉዳይም ይሁን ሚካኤልን አስመልክቶ በተለያየ ጊዜ በተደረገው ያለመግባባት በፍጹም ለስጋቸው አድልተው የማያውቁ ሃቀኛ ሰዎች ናቸው።
ጋሼ ምስክር ፤ የቅዱስ ሚካኤልን በምክትል ሊቀመንበርነት ሲያገለግሉ በነበረበት ወቅት ነብሱን ይማረውና ከሻለቃ ክፍሌ ጋር ሲሰሩ በመከባበርና፤ በትክክልኛ ብቻ በሆነው የስራ ልምዳቸው እንደነበር ሁላችንም ውነት የምንመሰክረው የምናውቀው ነው። ሻለቃ ክፍሌ ወደ ኢትዮጵያም በገባበት ሰሞን ቤተክርስቲያኑን በሚገባ ጠብቀውና ሕዝቡን አንድ አድርገው ሰላም በሰፈነበትና ቦርዱ ውስጥ እንክዋን ያሉት ሰዎች እነማን ናቸው ብሎ ሰው ስለምንም ችግር የማያስብበት ጊዜ ነበር የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የነበረው እርጭ ያለ ውነትም የክርቲያኖች ቤት። ሻለቃ ክፍሌ ሲመለስ ነበር ሕዝብ እንክዋን ኢትዮጵያ ገብቶ መመለሱን ያወቁት እስከዚህ ነበር የጨዋ አመራርና አስተዳደር የሚችሉ ትምህርቱም እውቀቱም ስለቤተክርስቲያን ያላቸው ሰዎች ጥቅም። ሻለቃ ክፍሌ እኔ የሰምንት አመት ገደማ ሆኜ ከሚያውቁኝ ወጣት መኮንኖች አንዱ እሱ ነበር። እንደ አባቴ ነበር የማየው እሱም ልጄ ነበር የሚለኝ። ስለ አቶ ምስክር ያለውን ክብርና አድናቆት የገለጸለኝን በቀጥልበት ብዙ ጊዜ ይፈጃልና ጋሼ ምስክር ምንም እንከን የሌለባቸው አስተዳደር ችሎታቸው ከማንም የማይመጣጠን ነበር። ስለ ሻለቃ ክፍሌ ለብቻው በቅርብ እጽፋለሁ ጎበዝ የአስተዳዳር ችሎታ የነበረው ነበር ክስር አት ማስጠበቅ ጋር አጣምሮ።

 
        ሌላው አቶ ዳኜው ላቀው  የተባሉት ሲሆኑ እኝህ ሰውማ ግማሾቻችን ከቦርዱ ሲወጡ ነው የሚካኤል ቤተክርስቲያን ቦርድ ሊቀመንበር መሆናቸውን የሰማነው። የነበረውን ሰላም አጠናክረው ሁሉንም በአምላክ ፍቅር ስም አቅፈው ከሁሉም ጋር በሰላም ሃላፊነታቸውን ሳያጉዋድሉ ሁሉንም እንደ ጸባዩ ይዘው አገልግለው ቦታውን በግድ ሳይሆን በወድ የለቁቁ ናቸው ልክ እንደጋሼ ምስክር። እኝህም ሰው የብዙ አመት የአስተዳደር ችሎታ ያላቸውና የሚቀርባቸው በጆሮዋቸው እየመጣ መከፋፈል እንዲፈጠር ሲሞክር እንክዋን እንዳልሰማ አይተው ተው ወይም ተይ ብለው የሚያልፉ ለመሆናቸው ብዙ ሰዎች የሚያወሱት ነው። ዳኜ ደጉ ጥሩ ሰው የሚል ስም አትርፈዋል በዳላስ ፎርት ወርዝ።


          የቤተክርስቲያኑ ክስ ሲጀምር ወደ ሰላሳ የሚሆኑ ሰዎች የቤተክርስቲያኑ አባላት በማነጋገር ክሱ ቆሞ በሰላም ያለውን ችግር አዳምጠን መታረም ያለበት እንዲታረምና ወደፊትም የቦርድ አባላት ምእመናንና አባላቱን በስልጣናቸው በመጠቀም እንዳይበድሉ በምተረዋርዋጥኩበት ጊዜ ብዙ ሰዎች እስቲ አቶ ዳኜን አነጋግሪ ውነቱን ሊነግርሹሽ የሚችሉት እሳቸው ብቻ ናቸው፤ በሚል ወደ ሳቸው መሩኝ። ውነትም በትክክሉ ስላለው ችግር እሳቸው ያስረዱኝን በድጋሚ ፍርድ ቤትም ሄጄ ሰማሁት። ስለፍርድ ቤት ከዳኛ የሰማሁትን በሚቀጥለው እንደማቀርብ ቃል እየገባሁ አቶ ዳኜንና ጋሼ ምስክርን የመሰሉ በችሎታና በልብ ጥሩ ነት የታደሉ በመሃላችን ፍርድ ቤት መዳረሳችን የሚያስገርም ነው።


        ባጭሩ አቶ እዮልን አስመልክቶ ከቤተክርስቲያኑ ገንዘብ ወስድዋል ብዬ አላምንም ጠርጥሬውም አላውቅም። እኔ ከእዮኤል ጋር የነበረን ችግር ወይም ጥያቄ ፤ ስልጣኑን ተጠቅሞ ቤተክርስቲያኑንና አባላትን ጎድትዋል ነው። ነገር ግን እዮኤል ገንዘብ መውሰዱን የሐረርወርቅም ታውቃለች፤ ማስረጃም አላት የተባለው የፈጠራ ወሬ ነው። በዚህ አጋጣሚ ማለት የምፈልገው ግን እዮኤል ደግ ሰውና የዋህ መሆኑን ነው። እነ በትሩ፤ ኪዳኔ አለማየሁና አጃቢዎቻቸው ተጠቅምውበታል ስላመናቸው። ሰው ለመጉዳት አስቦ በተንኮል፤ ነገር በጥብጦ ሕዝብን ወይም ግለሰብን የሚጎዳ ስራ አይሰራም እዮኤል እልህ አለው እንዳብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወንድ ሳያስብ ይናገራል ከቦርድ አባላት ጋር ሳይማከር ውሳኔ የራሱን ይሰጣል፤ ቃሉን አይጥብቅም። ነገር ግን አጭበርባሪዎችን ለይቶ ማየት ባለመፈለጉና ባለመቻሉ፤ የለፋበትን ቤተክርስቲያንና አስተዳደር እንደተሰጠው በምርጫ የተረከበውን ሳያስረክብ ለመረጠው ሕዝብ መውጣት ችልዋል። ይሄንን ስል ብዙ ሰዎች "በሃሰት ምሰክሮበሽ?" የምትሉ ብዙ መሆናችሁን አውቃለሁ። ግን ዛሬ የማወራው እኔ ላይ ስለተደረገው ሳይሆን፤ ሌሎች ጥሩ ስለሰሩት ስለሆነ የኔ በመጨረሻ ይቀርባል አይስቸኩልም ። መክኒያቱም ውነትን ተከተዬ ለሕዝቡ ክብርና ጥቅም መቆሜን ብዙሃኑ የተረዳ በመሆኑ፤ ሲጀመርም ስለእኔ ብዬ ሳይሆን ያሁሉ ውርጂብኝና አድማ በካንጋሩ ዳኞችና የካንጋሩ ወረዳ ፍርድ ቤት ከረጂ ምግብ ቤትና ላክንታኢን የካንጋሩ አውራጃ ፍርድ ቤት የደረሰብኝ፤ ያአያሳስብኝም። ስለእኔ ብዬም ሳይሆን ተፈራ ወርቅና ዘውገ ቃኘው በሕዝብ ስም ከተቀመጡበት ይልቀቁ በማለቴ እንጂ። ሳልናገር የማላልፈው አንድ ቁምነገር ቢኖ፤ የእዮኤል ባለቤት በጣም የምትመሰገን ነች። ከኢዮኤል ጋር የተጋጨውን ሁሉ እንክዋን ልታኮርፍና ፊትልትነሳ ፤ በክርስቲያንና እንደስምዋ እንደ ኢትዮጵያ ሁላችንን በፍቅር አቅፋ የኖረች ነች። መደረብ ሲያልፍም አይነካት ማስታረቅ እንጂ። አንድ ቀን የሰላም አርአያ ተብላ ሽልማት በቅዱስ ሚካኤል ደብር እንደምትመረቅ ተስፋአለኝ።


         ቀጥዬም ማለት የምፈልገው ሌላው ትሁትና የአስተዳደርና የቦርድ አመራር ሃላፊነትን ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ወንድም ዮሴፍ እረታ ሲሆን፤ ይሄውም ከተጨባጭ የስራው ውጤት አንዱን ብጠቅስ፤ አቶ እዮኤል ነጋ በሃሰት በኔላይ ማለትም በዳላስ ፎርት ወርዝ ብቸኛዋ የኢትዮጵያ አንድነትንና የሕዝብዋን ክብር አንድ ሰንደቅ አላማዋን በማስከበር ለገንዘብ ፍንክች የማልል፤ የአገሬን ጉዳይ በትግሬ ነጻአውጭ የማለውጥ፤ ቆራጥ የኢትዮጵያ አንበሳን፤ የትግሬ ነጻአውጪና ጥገኞቹ ከበውኝ ለምን የወያኔ ጭፍረኞችና ደሞዝተኞች መሆናችንን ለሕዝብ ገለጻ አደረገች በሚል በመነሳት፤ ከሕዝቡ ትገለልልን በሚል ተነስተው፤ እነሱው ከሳሽ እነሱው ጠበቃ፤ እነሱው ዳኛ ፤ እነሱው ምስክር፤ ሸንና አስተባባሪ ሆነው  ፍርድ በፈረዱብኝ ጊዜ በተደረገው ሕሌናቸውንና አገራቸውን ሕዝብዋን ለገንዘብ የሸጡ የሆዳሞች አንድነት ውስጥ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቦርድ፤ ሊቀመንበሩን እኔን ከሆዳሞቹጋር በመተባበር እንዲያወግዘኝ ልኮልናል በሚል በትሩ ገብረእግዚአብሄር፤ተፈራ ወርቅ የተባለው፤ ዘውገ ቃኘው፤ ኪዳኔ አለማየሁ እንዳሉት፤ ሃቁን በሶስት ቀን ውስጥ የቤተክርስቲያኑ ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ እንዲያስታውቀኝ በሚል በደብዳቤ ለቦርዱ በጠየኩት መሰረት፤ ልክ በጠየኩት መሰረት፤ በሶስት ቀን ውስጥ ፈጽሞ ቤተክርስቲያኑም ቦርዱም አንድም ሰው በተባለው ቦታና ቀን እንዳላክ ገልጾ ፤ ቤተክርስቲያኔም ቦርዱም በሙሉ ለኔ ጥሩምኞታቸውንና የክርስቲያንነት ድጋፋቸውን በአቶ ዮሴፍ ፊርማ የተረጋገጠ ደብዳቤ እንዲደርሰኝ እድርግዋል። ይሄም የሚያሳየው የራሱን ሃላፊነትና የቤተክርስቲያኑን አስተዳደር ጠንቅቆ ማወቁን ነው።  አቶ ዮሴፍ፤ የቅዱስ ሚካኤል ቦርድ የላከው ማንም እንደሌለ ባስቸክዋይ ባድራሻዬ በመላኩ ለቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳደር የቦርድ ሊቀመንበርነት ቦታ በሃላፊነት የሰጡት ሰዎች ሁሉ ሊመሰገኑ ይገባል በዚህ አጋጣሚ።


         ሌላው ትሁትና የሁሉንም እሮሮ አዳማጭ የነበረው ቦርድ ውስጥ ሲሰራ አቶ ልኡልሰገድ ነው። ወንድም ልኡልሰገድ የተጠየቀውን ያለበትን ሃላፊነት በስነስርአቱ የተወጣና ሁላችንንም ያለምንም ማዳላትና ማቅረብ ወይም ማራቅ በክርስቲያንነታችና በኢትዮጵያውያንነታችን የወንድምነት ፍቅር የሚያሳየን የነበር ነው በቦርድ ውስጥ። እንዴት ወደ ማህበረ ቅዱሳን በሚባል የሚጠሩት ከሚካኤል ይውጡና የጥቅም ግጭት ያመጣሉ የሚለውን ማመልከቻ ካቀረቡት ዶክተር ሰለሞንና አቶ መላኩ ታደሰ ጋር ሊጣመረ እንደቻለና ንትርክ ውስጥ ሊገባ እንደቻለ ባላውቅም፤ ቤተክርስቲይኑን ንትርክ ውስጥና ከዛም ወደ ፍርድ ቤት ለክስ ግለሰቦችን አዳረሰ ወይም መክኒያት ነው ለተባለው ማመልከቻ ካቀረቡት አንዱ ነው፤ ይሄም ሌላው በቅርብ የማብራራላችሁ ጉዳይ ነው።


           አቶ ተኮላን ያወኩት ማንንም ሳይፈራ ምን ይሉኛል ትናንታ በሬዲዮ ከእነ በትሩ ፤ተፈራ ወርቅ ፤ ዘውገ ጋር ወግኜ ቀርቤ ሳላነግግራት፤ በሬዲዮ ስኮንናት የተፈረደባትንም ፍርድ አርቃቂነት ሃላፊነት ተቀብዬ የተነሳሁባትን ዛሬ እንዴት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሎ ስለሌሎች ሳይጨነቅ፤ በራሱ አይምሮ በመነሳሳት፡ ከዚህ በታች ያለውን ከተናገረ በሁዋላ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ስብሰባላይ በቄሶች ፊት ። ከዛ በሁዋላ፤ ስላለው የቤተክርስቲያን ችግር መፍትሄ ለመፈለግ ከማነጋግራቸው ወንድሞቼና እህቶቼ አንዱ ነበር። ችግሮችን ለማቆም በየጊዜው እየደወልኩኝ አነጋግረው ነበር። ይሄውም ተፈራ ወርቅ ስብስብ ብሎ በብዙዎቹ ቁንጮዋቸው ላይ ሳይቀመጥ በፊት ማለት ነው። ስለዚህም በሌላ ጊዜ አቀርባለሁ።  በእርግጥ ተፈራ ውርቅን ጥልቁ የቤተክርስቲያኑን ብጥብጥ ጠማቂውን በኮሚቲ አናት ላይ ቁጢጥ ካደረጉት በሁላ፤ የእኔና የአቶ ተኮላ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ተቁዋርጥዋል። የዲፐሎማቲክ ግንኙነቱን ለመቀጠል እሞክራለሁ።    በከተማችን ፤ አንዱም ወንድ ስለጥፋቱ እንክዋንስ ይቅርታ ሊጠይቅ ይቅርና እንደውም በራሱ ዘራፊነት በስው ብሶ አግልሉልኝ ከኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማህብር የሚል ሲሆን ፤ አቶ ተኮላ ግን ከልቡ ከዚህ ቀጥሎ ባለው ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ፤ ሁላችንም  ስህተት ካለን ይቅርታ ብንጠይቅ ቲንሽነት ሳይሆን ትልቅ ልባምና አይምሮም እንዳለን እንረዳለን። አቶ ተኮላ ያለው "ወይዘሮ የሐረርወርቅን በጣም አደንቃለሁ። ጠንካራ ጎንዋን ስጠኝ ለኔም ብዬ አምላክን እለምነዋለሁ፡ ነግር ግን የኔ ችግር ከወይዘሮ የሐረርወርቅ ጋር፤ ወረቀት እየጻፈች የምትበትነው ነው ሆኖም ይቅርታ ወይዘሮ የሐረርወርቅ፤ ብዙ ሰዎች ወይዘሮ የሐረርወርቅን አስቀይማሃል ስላሉኝ ይቅርታ እጠይቃለሁ" በሚል በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጣም ትምህርታቸው ልብ ውስጥ የሚገባው አባታችን ከቤተክርስቲያን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉት ፤ የተጣላውን ሁሉ አቶ እዮኤልንና ወይዘሮ ጥሩ አይርን ጭምር ባስታረቁበት ጊዜ ነበር። ታዲያ እኔም ይቅርታውን ከመቀበሌ በፊት ያልኩት ነበረኝ ያንን በቲያትር መልክ ወደ ፊት ለመዝናኛ በዚሁ ብሎግ አቀርባለሁ።


             በመጨረሻም የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጥሩ የቦርድ አመራርና ሰላም ኖሮት አያውቅም የሚባለው እንግዲህ ከዚህ በላይ ባሰፈርኩት ውነታ ተሸንፍዋል።

      አምላክ ሁላችሁንም ስለውነት ያቁማችሁ ከውነት ሌላ አፋችሁውስጥ ሃሰት አያናግራችሁ። ሃሰት የሚናገር በውስጡ እንደእሳተ ጎሞራ የሚተናነቀ ውሸት ሰላም እየነሳው ስለሆነ። ከዚህ በላይ የጻፍኩትን አስጀምረህ ያስጨረስከኝ አምላኬ ትልቅ ምስጋና ይግባህ። አሜን።