Monday, March 25, 2013

በዳላስ ቴክሳስ የስዴቱ ሲኖዶስ ተመረጠ!!!

በየሐረርወርቅ ጋሻው
ከቦታው በመገኘት የቀረበ ዘገባ።

በትናንትናው እለት እሁድ  February 24, 2013. በቅዱስ ሚካኤል ደብር ፡ ሶስት አማራጭ ለምርጫ በቀረበው መሰረት ማለትም "በአገር ቤቱ ሲኖዶስ? በሴዴቱ ሲኖዶስ? በገለልተኛነት?" በሚል የቀረበውን ጥያቄ ባያሌ ድምጽ በአገር ቤት ሲኖዶስና በገለልተኛነት የሚለውን ውድቅ አድርጎ የስዴቱን ሲኖዶስ መርጥዋል።  የቅዱስ ሚካኤል ደብር የመጀመሪያውና ትልቁ አብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሚገለገልበት ደብር ነው።

ስለ ቅዱስ ሚካኤል ደብር አመሰራረትና አቡነ ይስሃቅን የመሰለ አባት እንደነበረው ከዛም ገለልተኛ ወደ ሚለው ብሎም ዛሬ ወደ ደረስንበት ትክክለኛ ውሳኔ መድረስ መጀመሪያ ስላለው የቅዱስ ሚካኤል ደብር ታሪክና በትናንትናውም የተደረገውን ምርጫ አስመልክቶ የመንጃ ፍቃድ ካላሳያችሁ በሚል የወያኔ ተወካይዋና ቤተሰብ እንዳቅምቲ በቦታው ስላስቀመጥዋት ተዳፍራን  ስለሞገተችንና የተመለሱም እህቶቻችን ከምርጫው ሰልፍ ላይ እንደነበሩ ጭምር ሰሞኑን እስካቀርብ ድረስ እውንትና ትክክለኛ የመጽሃፍ ቅዱስ አመራርን መከተል እግዚአብሄርን መከትል ስለሆነ፡ እውነትም እግዚአብሄር ስለሆነ እውነት ሁላችንም እንድንተነፍስና ውነትን እንድንኖር አምላክ ይርዳን። ተከታተሉ። 
 


ከወር በፊት የወጣውን የመጀመሪያውን ስብሰባ በፊውብርዋሪ አስራ ስድስት ሁለት ሺሶስት በዚሁ ብሎግ ከዚህ በታች የሚታየውን በማንበብ ከላይ ባጭሩ የመዘገብኩትን የትናንቱን የምርጫ ውጤት ሊያብራራላችሁ ስለሚችል እንድትመለከቱት በትኩረት በትህትና አሳስባለሁ። ፎንቱን ትልልቅ ይደረግልን ማንበብ ችግር አለን ያላችሁኝም ምንም እንክዋን ካላችሁበት ኮምፑተር እራሳችሁ አጉልታችሁ ልታነቡት የሚያስችል ቢሆንም ቴክኒዎሎጅው ፡ ችግራችሁን ስለተገነዘብኩኝ በጠየቃችሁኝ መሰረት ጥያቄያችሁን ተቀብዬና አክብሬ ፊደሎቹን ትልልቅ አድርጌ ጽፌአለሁ እንደምታዩት። አመሰግናለሁ።


Tuesday, February 19, 2013
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ጋርላንድ ቴክሳስ በfebrwary 16, 2013 የተጠራው ስብሰባ የቅዱስ ሜካኤል ደብርን በገለተልኛ ይቆይ ? ወይስ አባት ይኑረው? ግምገማ።
በየሐረርወርቅ ጋሻው(የኢትዮጵያወርቅ)

በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኑን ከፓለቲካ ነጻ ማውጣት አለብን ገለልተኛ ነኝ የሚሉት በውጪ አገር የሚኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናት በሙሉ በሲኖዶስ ስር መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ብዙሰዎች ስለስብሰባው እየደወላችሁ ምንተወሰነ
የሚል ጥያቄኛ ሌላም ሃሳብ ይዛችሁ የምትደውሉት ብዙናችሁ። በተለመደው ከእኔ ሃቁን ለማወቅ ስለምትደውሉ አመሰግናለሁ። ሁለተኛ ለሁላችሁም የምመልስበት የስልክ ሳዓት የለኝም። ሶስተኛ የቤተክርስቲያን አባልነታችሁን ከፈሉ ወይም አባል ሁኑ የተሰብሳቢነቱ እድል እንዲኖራችሁ። አራተኛ፡ ቤተክርስቲያኑ የቀዳው ቪዲዎ ስላለ በዛ ለመረዳት ስለምትችሉ የሚመለከተውን እንድታናግሩ አሳስባለሁ። አምስተኛ እኔ ከቤተክርስቲያኑ እርቀሻል እሁድ እሁድ ያለፈው ምርጫ ቦርድ ከተደረገ በሁዋላ በሚል የምትጠይቁኝ ሁሉ: ስለኔ በቅዱስ ሜካኤል ደብር ቤተክርስቲያን ያለመታየትም ሚስጥር ስላልሆነ ይሄን ያህል ሰለተጨነቃችሁበት ባጭሩ ለመግለጽ ያሕል ፡ በሶስት የቦርድ አባላት ምርጫው በትክክሉ እንዳይሄድ ሻጥር ሰርተው ሰለደረስኩበት የዶክተር ግርማና የነርስ ጌታቸው ፊጣ ቦታውን መልቀቅ ለቤተክርስቲያኑ የሚያመጣውን ጉዳት ሰለማውቅ በማዘኔ ከእነዚህም ሰዎች ጋር ላለመጋጨት እራቅ ብሎ ተግባራቸው ግልጽ እስኪሆን ሌላ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በመሄድ ለመቆየት በማሰብ ነው። የተማረሰው፡ ከኮራብሽንና በሑለት ሰዎች ብቻ የሚመራ ቦርድ ቀርቶ ሁሉም የቦርድ አባል ድምጽ የሚስተናገድበት ያደረጉትን እነዚህን ሰዎች በመማራቸውና የተለመደውን የመንደር የሁዋላ ቀር አሰራር በማስቀረታቸው ትልቅ የድብቅ ዘመቻ አድርጎ ምእመናኑንና ቤተክርስቲያኑን በቦርድ ውስጥ ተቀምጠው መጉዳት ሕሌናዬ እንደ ብዙዎቹ አልተቀበለውም። እራቅ ማለቱን መርጬ ነው: ሆኖም ትቼዋለሁ ለቤተክርስቲያኑ ሰላምና ለምእመናኑ አንድነት ስል :: ስለ ፈጸሙትም ተንኮል እግዚአብሄር ይቅጣቸው። ለደወላችሁልኝ እቤቴም ድረስ እኔን ፍለጋ ለመጣችሁት ሁሉ አመሰግናለሁ። ሆኖም እኔ የግለሰቦች ተቃዋሚ ሳልሆን ህብረተሰባችንና ቤተክርስቲያናችንን አንድነታችንን የሚነድሉ ከራሳቸው ጥቅም ሌላ የማይታያቸው ቂመኞች ሰዎችን ተግባር ተቃዋሚ መሆኔን በግልጽ ላስቀምጥ እወዳለሁ። ይሔንን ስል በቤተክርስቲያንም ቦርድ ውስጥ ተቀምጠው ቤተክርስቲያኑን ከሚጎዱት ጋር የሚወግኑትን ለቤተክርስቲያኑ የሚጠቅሙትን ከቦር ውስጥ እንዲወጡ በአፍራሾች አይምሮ የሚመሩትንም ጭምር ማለት ነው። በስብሰባው ላይ እንደተናገርኩት አንድም የምጠላው ሰው የለም ህዝብን ለመከፋፈል በሚወስዱት እርምጃ አላከብራቸውም እንጂ።

በመጀመሪያ ብዙ ክርስቲያን የሚጠይቀውን ሲኖዶስ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ባጭሩ ለማስቀመጥ እወዳለሁ ይሄውም ከዚህ ቀደም በዚሁ ብሎግ በሰፊው ይጠቅማችሁዋል ብዬ የጻፍኩትን ማየት ስለምትችሉ።

ሲኖዶስ ማለት በቤተክህነት አጠቃቀም የጳጳሳት ጉባኤ ነው። የመጀመሪያው "ሲኖዶስ" የተጀመረው በእየሩሳሌም በሃምሳ ዓመተምሕረት ነው። በተጨማሪ ለቤተክርስቲያን መመሪያና መተዳደሪያ ይሆኑ ዘንድ ሕግጋትና ሥረዕታት የተፃፉበትና አራት ክፍል ያለው መጽሐፍ ሲኖዶስ ተብሎ ይጠራል። ይህም መጽሐፍ ሲኖዶስ ቤክርስቲያኖችን ከምትቀበላቸው ሰማኒያ አንዱ መጽሕፍት ውስጥ ይቆጠራል። የመጀመሪያው ሲኖዶስ ሊቀመንበር በመሆን የመራውም የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ወንድም በሚል የሚጠራው ቅድዱስ ያዕቆብ ነበር። ለሲኖዶስ መደረግ ምክኒያት የሆነም ነገር በሐዋ.ሥራም. አስራ አምስት ላይ እንደተገለጸው፡ ከአይሁድዳዊነትና ከመምለኬ ጣኦትነት ወደ ክስርትና የተለወጡ የአይሁድና የአህዛብ ወገኖች፡ በአንዳንድ ኦሪታዊ ሕግጋት ምክኒያት በፈጠሩት አለመግባባ ነበር። ስለዚህ፡ ሲኖዶስ የማይለወጥ የቤተክርስቲያናችን መመሪያ ነው። በሲኖዶስ የተወሰነን ወይም የጸደቀውን ነብሰ ገዳዮችና ወሮ በሎች ሊለውጡት አይችሉም። ም እመናንም ሊለውጡትና ምድራዊ ፍላጎታቸውን ድሎታቸውን ማርኪያ ለማድረግ እነደፈለጉት ሊያረጉ አይፈቀድላቸውም። ቤተክርስቲያን ሃቀኛዋ በግለሰቦች ወይም በሌላ አነጋገር በሞግዚት አትመራም በሃይማኖት አባትኛ አባቶች እንጂ።
ከላይ እንዳስቀመጥኩት በማይወበዘው የፓትሪያርክ አመራረጥና በሲኖዶስ በቀኖና ላይ መጀመሪያ በደርግ ጊዜ ሁለተናውን ፓትሪያርክ አስሮ ሌላ በመሾሙ ቅዱስ ሲኖዶስን ደፍርዋል። አሁንም በጠመንጃ አገር ይዞ በክክልል ሕዝብና አገርን የሚመራው የራሱን ሰው ፓትሪያርክ አድርጎ ነበር። አቡነ ጳውሎስ በድንገት በመሞታቸው ደግሞ ፓትሪያርኩን ብጹህ አቡነ መርቆሪዎስን በቦታቸው መልሶ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተክርስቲያንዋ መንግስት የተባለ እጅ እንዳይገባ እርቅ አባቶች እያደረጉ ባሉበት ሰዓት፡ የወያኔ መንግስትና ባለስልጣኖቹ የተጀመረውና እየሰመረ የመጣውን አቡነ መርቆሪዎስንንም ፓትሪያርክነታቸውን ያረጋገጠውን እረግጦ የራሱን ፓትሪያርክ ለማቁዋቁዋም እየተርዋርዋጠ ይገኛል በአሁኑ ጊዜ። ስለሆነም፡ ባስቸክዋይ የእርቁ አካል የሆኑት ድምጻቸው ሰለጠፉብን ይሰቀሉ የተባሉትም ቄሳውስት እርምጃ እንዳይወሰድባቸው በስብሃት ነጋና በግብረአበሮቹ ከዚህ በታች በስብሰባው ላይ ባለፈው ቅዳሜ ሃሳብ ለቤቱ እንደሰጠሁት እዚህም ላይ በመድገም የምእመናን ፊርማ በማሰባሰብ እርቁ ባስቸክዋይ እንዲቀጥል የወያኔን ጳጳስ ምርጫ በመቃወም በትክክለኛው የሃይማኖታችን ቀኖናና ሲኖዶስ ብቻ ያለ ፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ፓትሪያርኩ አቡነ መርቆሪዎስ በቦታቸው እዲመለሱና እግዚአብሔር ወደ ዘለዓለማዊ ቤታችን ለሁላችንም ወደ ሆነው ቤቱ እስቲጠራቸው ድረስ የቤተክርስቲያናችንን አባትነት እንዲቀጥሉ መተባበር ከሁላችንም ይጠበቅብናል። የፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ስል ወያኔን ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚነኝ የሚለውም ጭምር እጁን ማውጣት አለበት። ወያኔም: ተቃዋሚውነን የሚሉትም ደጋፊዎቻቸውም እነሱ ባሉት ካልሆነ በሲኖዶስ በቀኖና የማያምኑ: ቤተክርስቲያንም የሚሄዱት:አላማቸውን ለማራመጃ ይረዳ ዘንድ ነው ።

የወያኔ መንግስት፡ ከላይ ያስቀመጥኩዋቸውን የሰላም መፍትሄ በቅርብ ቀን አልቀበልም ካለና የራሱን ፓትሪያርክ የሚሰይም ከሆነ፡ ሰያሚውም ተሰያሚውም አንድ ሕገወጥ መሆናቸውን ተቀብለን ፡ ወያኔ ሊገድልአቸው ሲል ካገር ወጥተው በመከራ ላይ የሚኖሩትን ብጹህ አቡነ መርቆሪዎስን አባትነት አክብረን ቤተክርስቲያንዋ በህግዋ መሰረት ሲኖዶስና ፓትሪያርክ መምረጥ እስክትጀምር በዚህ መልክ አባት ይዘን በሚመራው ቤተክርስቲያን መቀተል ይኖርብናል ብዬ አምናለሁ። ይሄ አባባሌና የማያወላውል ውሳኔዬ የማያስደስተው ካለ የክርስትና ሃይማኖት መመሪያን ማለትም አለም አቀፍ "ሲኖዶስ" እራሱ ክርስቶስ የፈጠራት ቤተክርስቲያንን መመሪያ ሳያውቅ የሚዋዢቅ በመሆኑ ያለማወቁ ችግር የሱ ወይም የስዋ ብሎም የነሱ እንጂ የእኔ አይሆንም። በሃይማኖቴ ሲመጣ በስብስብ ምክር የምወስነው ሳይሆን በመጸሃፍ ቅዱሱ በእግዚአብሄር ትእዛዝ ብቻ የምመራ ማንምም ሊያወናብደኝ የማይችል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሕግ ብቻ የምከተል መሆኔንም መግለጽ እወዳለሁ።
መልክት። አሁን በቅዱስ ሜካኤል ደብርን በግለለተኛ ይቆይ የሚሉትን ለመቁዋቁዋም የምትርዋርዋጡት ገና እናንተ ተኝታችሁ አይምሮ አችሁ ላይ "የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ለማስረከብ ለትግራይ ነጻ አውጪ አጥሩ ላይ ተንጠልጥለው የቦርድ መቀመጫውን ወንበር እያመረጡ ስለሆነ ቤተክርስቲያኑን እናድን" በሚል ለምእመናኑ በሙሉ በበራሪ ወረቀት ጭምር ማሳሰቢያ ስበትን ለቦርዱም በጊዜው ለነበረው ባቀረብኩበት ጊዜ የኔተቃዋሚ የነበራችሁ ፍርድ በሃሰት ከነሱጋር ሆናችሁ በሃሰት ህብረተሰቡን በማሸበር ጭምር የሬዲዮን ስርጭት አዘጋች በሚል ጭምር ውነቱ በህብረተሰቡ እንዳይታወቅ ያደረጋችሁ እኔ በስብሰባው ላይ የሰጠሁት የተባረክ ሃሳብ ስላላስደሰታችሁ ቅር እንዳላችሁ የነገራችሁኝ ነበራችሁ ሆኖም አወላዋይ ልባችሁን አንድ እንዲያረግላችሁ እግዚአብሄርን ለምኑት። ችግሩ የቤተክርሲያኑ እናንተና የድብቅ የወያኔ ተቀጣሪዎቹ ስለሆናችሁ። ቀደም ሲል እግዚአብሔርን የካዳችሁም ትገኙበታላችሁ። ይሄንን ስል ምን ማለቴ ነው::
ጠቅላላው ምእመንን ላስታውስ የሚፈልገው ከላይ ያስቀመጥኩዋቸው ሃቆች ዛሬ በእውን ፊት ለፊት ወጥተው ሰላም ቤተክርስቲያኑን ከመንሳታችው በፊት አስፈላጊው ጥንቃቄ ቢደረግ ኖሮ ዛሬ ይሄ ሁሉ እላይ እታች ባልተደቀነብን ነበር። እና መረሳትም የሌለበት የመረዳጃ ማሕበሩ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዳላስ ፎርት ወርዝ ንዋሪ መገልገያ የሆነውን የሬዲዮን ስርጭቱን ጭምር እና የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራልን እናድን ብዬ ሳቀርብ ከናካቴው አብሮዋቸው የነበሩት ጆሮ ዳባ ብለው፡ ዛሬ ተኩላዎቹን ከላይ እንዳስቀመጥኩት እየሰፈጸሙ ያሉት ከፋፋይ ተግባርን አብረዋቸው በመሃላችን ያሳደጉ እና ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ ሰላም ክርስቲያኑን በአምላክ የምናምነውን አላስቀምጥ ማለት ትልቅ አስተዋጽዎ አድርገዋል። በዛላይ የፓለቲካ ፓርቲ አባል ነን ተወካይ ነን ተቃዋሚንን በሚል ከልብና በእውነት ስለ አገራችን እና ሕዝቡ አንድነትና መብት የምንታገለውን ሁሉ እንቅፋት በመሆን የሚታወቁ : አንድም በተጨባጭ የረባ ስራ ሰርተው ውጤት ያላስመዘገቡና ቢጠየቁም ታጋይ ነን፡ ታግለናል ከሚል የአፍ ቃላት ወሬ በስተቀር በተግባር የሚተረጎም ያልሰሩ ሊሰሩም ገና በዚህ በቆየው እድሜያቸው እንክዋን ለወጣቱ ትውልድ ምን እንተውለት ጥሩ ነገር ብለው የማያስቡ ለራሳቸው ብቻ የሚያስቡ ሰዎች ናቸው።
አንደኛ፡ በስብሰባው ላይ ከተገኙት የቤትክርስቲያኑ አባላት የነበራቸው ተሳትፎ ይበል የሚያስብል ቢሆንም፡ በማር የተጠቀለለ መርዝ በውስጥ እንዳለበት ለመገንዘብ ለማንኛችንም ምእመን ነብይ መሆንን አልጠየቀንም ነበር። እነሆ የሚያስደነቀው በአፈ ቀላጤነት በማር የተሸፈነ መርዛቸውን እንድንቀበልላቸው እና ለቀጣዩ አላማቸው ማስፈጸሚያ ይረዳናል ብለው ቀድመው ይዘውት የነበረውን አቁዋም ወይም ወያኔነታቸውን ይዘው ሕዝብ ፊት መቅረብ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በፍጹም የማይፈቅድላቸው መሆኑን ሲገነዘቡ፡ ስልታቸውን በመቀየር በይፋ ከመቅረብ እና አቁዋማቸውን ከመግለጽ ይልቅ ከእነሱ አቁዋም ውጪ ያለውን ምእመናን ለማማለል (ለማታልል)እና የሚቀጥለውን የቦርድ ምርጫ በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማዋል እና እዛም ውስጥ ሰግስገው ሰርገው ለመግባት የሚያስችላቸውን የመራጭ ድምጽ ለማግኘት ሲሉ ብቻ አሁን የያዙትን ገለልተኛ የሚለውን አቁዋም እያራመዱ ይገኛሉ። ስለዚህ አሁን ለምእመናኑ ማሳሰብ የምፈልገው እነዚህ ሰዎች ወደ ስልጣን መጥተው ከተቆጣጠሩ በሁዋላ የሚፈቅዱትን የሚፈልጉትን ሁሉ ለማስፈጸም እንዲረዳቸው አንደኛ ፡ ቀደም ብለው በመረዳጃው ማህበር ስም ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በሚል ስም እራሳቸውን ሕዝብ ሳይምርጣቸው በስልሳ ሰው ድምጽ ብቻ አርባ አምስት ሺ የሚደርስ በዳላስ ንዋሪውን ኢትዮጵያዊ ከመጤፍ ባለመቁጠር በተለመደው እነዚሁ ጋንግስተሮች ናቸው ቦርድ ኦፍ ትረስቲ ብለው እራሳቸውን ሰይመው ሾመው ተመቻችተው ያሉት።

ሁለተኛ፡ የሕብረተሰቡ ይሆነውን የሕዝቡን የሆነውን የሬዲዮ ስርጭት በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ሕዝቡ እንዳይጠቀምበት እና ሃሳቡን እንዳይገልጽ እና እንዳይገናኝበት፡ እንዳይወያይበት ፕሮግራሙን በሚያስፈጽሙት ግብረአበሮቻቸው የሚፈልጉትን ብቻ እያስተናገዱበት እነዚህም ሰዎች በአሁኑ ሰአት በገለልተኛነት እራሳቸውን ያስቀመጡ ስለሆነ ለዚሁም ከዚህ በላይ ምንም አይነት ማስረጃ ከራሳቸው አንደበት ከወጣው የማንነታቸውን መሰረት ለማወቅ በቂ ስለሆነ ከዚህ ሌላ ማስረጃ አስፈላጊ አይደለም።

ሶስተኛው፡ አሁን በግልጽ በማያስቀምጡት የወያኔን በለሃምሳ ሁለት ገጽ መመሪያ መሰረት ለማስፈጸም ከመቼውም ይበልጥ የተጣለባቸውን እና የተቀበሉትን የወያኔን እንደራሴነት አደራ የተሙዋላ ለማድረግ እና ከወያኔ አለቃቸው የተዘጋጀላቸውን ምንዳ ለመቀበል እጃቸውን ከመዘርጋታቸው በፊት አሁን በእጃቸው በቁጥጥራቸው ስር ሊገባላቸው ያልቻለውን ቤተክርስቲያን በቀጣዩ የቦርድ ምርጫ ተመራጭ ሆነው በመግባት ጠቅላላ ያለንን ሕልውና በሙሉ በገዢው ፓርቲ ፍላጎት እና ውሳኔ በሚመራው ሲኖዶስ የአማራ እና የኦርቶዶክስን አከርካሪ ሰብሬአለሁ በሚል በይፋ በሚለፍፈው ወያኔ ስር ዓት አሳልፎ ሊሰጡን የተዘጋጁ የቀበሮ ባሕታውያን ስለሆኑ፡ የቤተክርስቲያኑ አባላት እራሱን እና ቤተክርስቲያኑን ለማዳን ከነዚህ ተኩላዎች ፡ ከፍተኛ ሃላፊነት ከምንግዜውም የበለጠ እንዳለበት ማስገንዘብ እወዳለሁ። በመጨረሻም እኔ በግለሰቦች በእየቦና ቤቱ በሚወራ የስርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ሰው ሳልሆን ቀደም ብሎ በማሰብ የምናገርና ሃሳቤን ከገለጽኩኝ በሁዋላ የማርም የምቀለብስ ሳልሆን ፡ የማምንበትን በቅድሜያ አስቤ የምናገር መሆኔንም፡ በቤተክርስቲያኑ ስብሰባ ላይ የሰጠሑት ከላይ ያስቀመጥኩት ያላስደሰታቸው ችኩሎች ላስጨብጥ እወዳለሁ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ብሎም በልጆቹ ተጠብቃ ለዘለዓለም ትኖራለች!
የኢትዮጵያንና የሕዝብዋን አንድነት በአንድ ሰንደቅ አላማ ስር እግዚአብሄር ለዘላለም ይጠብቅልን።