Saturday, March 23, 2013

ከቅዱስ ሚካኤል ደብር ተቆርቁዋሪ አባላት ከማስረጃ ጋር የተላከ የመጀመሪያ የማንቂያ ደውል እነሆ።


ከቅዱስ ሚካኤል ደብር ተቆርቁዋሪ አባላት ከማስረጃ ጋር የተላከ የመጀመሪያ የማንቂያ ደውል እነሆ።

እንደሚታወቀው የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር በጋርለንድ ቴክሳስ፡ በእግዚአብሄር ሃይልና በምእመናኑ ብርታት ትናንት ከነበረበት ተነስቶ ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ መብቃቱ ይታወቃል። ይህ ቤተክርስቲያን በሐገር ቤት በኢትዮጵያ ያለውን የገዢ መደብ ጭምር ያማለለ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ተሰጥቶት ሐገር ቤት ላለው ጨቁዋኝ ገዢ መደብ መገልገያ እንዲሆን በእጅ መንሻነት ለመስጠትና በምላሹም ተስፋ ያደረጉበትን ጉርሻ ለመቀበል በዝግጅት ላይ ያሉትና ሙሉ ጊዜያቸውን በዚህ ጉዳይ የሚያጠፉ ከዚህም ቀደም በተግባር ጭምር ቤተክርስቲያኑን ወደ ክስ በመውሰድ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ወጪ እንዲያወጣ ያደረጉና ያስደረጉ፡ አሁንም አርፈው ለመቀመጥ የተሳናቸው፡ አካላትን ደጋግመን ፡ ደጋግመን በተለያየ መንገድ ብንገልጽም፡ ልቡናውን ከፍቶ ለማዳመጥ የቻለው ጥቂት ወገን ብቻ ከፍተኛ ትንንቅ እያደረገ ቤተክርስቲያኑን ሳያስደፍር እስካሁን ጠብቅዋል። ይህ እየሆነባቸው የተቸገሩ፡ የወያኔ ባላደራዎች፡ በአሁኑ ወቅት በሻለቃ ተፈራ ወርቅ አሰፋ የቀድሞው የእሴፓ አብዮታዊ ወታደራዊ ፓለቲካ አስተዳደር ቢሮ ካድሬ፡ የዛሬ የወያኔ ምርጥ ሹመኛ በዳላስ፡ ሊቀመንበርነት የሚመራውን "የተባበሩት የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የምፍትሄ ኮሚቲ" በሚል ተደራጅተው ከምንጊዜውም በበለጠ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው በቅንነትና በየዋህነት የሚያመልከውን ምእመን ወይም የቤተክርስቲያኑን አባላት፡ ይሁንታ ማግኘት ሳያስፈልጋቸው በማን አለብኝነት እራሳቸውን ሹመውና ተሹዋሹመው፡ ቀደም ሲል በህቡእ ይታገሉ የነበሩት ጭምር ወቅቱን እንደሞትና የሽረት ትግል በመቁጠር፡ እንደቀድሞው ተሸሽገው ከጀርባ ሳይሆን በፊት ሊፈት በግልጽ ከቁጥጥራቸው ውጪ በሆነ ጭንቀት የተነሳ፡ ከወያኔ የተሰጣቸውን አደራና ሃላፊነት ለመወጣት አሁን በስራ ላይ ያለውን የቤተክርስቲያኑን ቦርድ አስወግድው የራሳቸውን ጀሌዎች በውስጡ ለመሰግሰግ ተነገወዲያ እሁድ በሚደረገው ምርጫ ቀዳሚነት የነሱን ሃሳብ ተቀባይ በማድረግ፡ ቤተክርስቲያኑን ያለአባትና ያለ እርሰ ደብር ለማስቀረትና እንደ ከዚህ በፊቱ፡ ያለተቆጣጣሪ ያለከልካይ፡ ሲያዙና ሲናዝዙበት የነበረውን፡ የቅዱስ ሚካኤል ደብረ መሕረትን ሃብትና ንብረት በሙሉ፡ በወያኔ ቁጥጥር ስር ለማስገባት አባላቶቻቸውን በመቀስቀስና በማደራጀት ላይ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት፡ ለቤተክርስቲያኑ መእመናን በሙሉ በዚህ ብሎግ አማካኝነት ልንገልጽ የምንወደው ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ያለአባት የተመራበት ቀኖናም ሆነ ዘመን የለም። ይህንንም ስንል የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሁዋላ ደብር ሲገዛም ጀምሮ በአባት እንጂ ያለአባት እንዳልነበረም ልናስታውስት እንወዳለን ። ስለሆነም፡ አሁን የሃይማኖትን ሂደትና የፓለቲካን አሰራር እርስ በእርሱ እያጣረሱ፡ ሊሆን በማይችል መንገድ የገለልተኝነት መርህ በምን ወቅትና በምን ሁኔታ ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን የሚያውቅ ማንም የለም ብሎ በሚያምነው ጭፍን አስተሳሰባቸው፡ ሊያስፈጽሙት መሞከራቸው ሳያንስ፡ እኛን ያሳዘነን ለቤተክርስቲያኑ ምእመንና አባላት ያላቸው ከፍተኛ ንቀት ነው። ይሄንን ስንል በቂ መክኒያትና ማስረጃ በእጃችን ላይ ይዘንው። ማስረጃ ስንል የራሳቸውን ቃለ ጉባኤ በአምስት ገጽ የመዘገቡትን ከዚህ ደብዳቤያችን በታች እንድትመለከቱት እናሳሰባለን። የህ አምስት ገጽ ቃለ ጉባኤም እንደሚያስረዳው በግልጽ የስብሰባው የኮሚቲው ሊቀመንበርና ሰብሳቢ በዳልስ ቀደንኛው ወያኔ ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አሰፋን ነው።