Sunday, June 19, 2011

"ውነተኛነትና ውነትን መናገር የሚገኘው ከመንፈስ ቅዱስ ነው" መምህር ልኡል ቃል በቅዱስ ሚካኤል ደብር ካስተማሩት።

 ከነበሩት ስድስት አር እስቶች በጥቂት ቃል ሁሉንም የአለምን ችግር መፍቻው ስለሆነው ነበር "መንፈስ ቅዱስ ወደ አለም የመጣው ወደ ውነት ሰዎች ለማድረስ ነው (ለመምራት)" ሃቅ ነው መንፈስ ቅዱስ በልቡ የያዘ ሰው እግዚአብሄርን ያውቃል። እግዚአብሄርን የሚያውቅ መንፈስ ቅዱስ በሰውነቱ ውስጥ ትኖራለች። የአለም ፍጡር የተባለ ሁሉ ውሸታም ቢሆን አንድ ሰው በፈጣሪ ተእዛዝ ብቻ ከተመራ በቁጥር ከሚበዙት ምናምንቴዎች የበለጠ የሚሆነው እሱ ብቻ ነው ይሄውም በአለምና በውነተኛው ንጉስ በክርስቶስ ፊት።ዕውነትን እንውደድ።ዕውነት እንሁን! እውነት አትመመን! እውነት በጣም ጣፋጭና የማትሰለች ምሕረት ነች። እውነት የምታመው መንገድዋን ስተን ስንጉዋዝ ብቻ ነው።


በቅዱስ ሚካኤል ደብር እየተደረገ ያለው ለወጣቱ ትውልድ የተለያየ እንክብካቤና ሳይጠይቁ በባእድ አገር ተወልድው ግራ ለተጋቡት ልጆቻችን ጠንካራ ምንም የማይጥስው የክርስትናን መንፈስ በመመገብ እየተደረገ ስላለው ጥረት ላየው ወጣቶቹ የትምሕርት ቤታቸውን የምረቃ ልብስ እንደለበሱ ስማቸው እየተጠራ ማንነታቸው ተከብሮና ታውቆ በቤተሰባቸው ሳይሆን በራሳቸው ጥረት ባሳዩት ትልቅ የማያልቅ ስጦታ ቄሳ ውስቱ ፊት እየተጠሩ መጸሃፍ ቅዱስ በያንዳንዳቸው ስም ተጽፎ የተዘጋጀላቸውን ሲሸለሙ ዛሬ ጠዋት አብዛኛው ምእመናን እንባችን ለምን እንደሆነ ባይገባንም ያነባን ብዙ ነበርን።  በተለይ ለልደትና ለትምህርት እድገት ስጦታ የክርስቶስን ታሪክና የጥቁሮች የአለም ስልጣኔ ስለአበረከትነው ለምሳሌ የመኪናዎች መሪ የትራፊክ መብራት፡ የምናብራው መብራት፡ ባቡር ሲመጣ የቁሙ መዝግ ያንና የጨረቃ መንኩራክር ጎማን ስለሰራበኢትዮጵያ ምድር ቢሆን ይህ በሰው አገር በአንድ ጎን የምንኖረው አንዋንዋር የአገር ፍቅር ናፍቆትና የቀዬአችን ትዝታ "አገሬ ዘመድ መሃል ብሆን ኖሮ ይችቀን እንዴት በደመቀች ከቤተክርስቲያን ሲወጣ ልጄ" ከሚለው አስተሳሰብ ይምስላል ሆኖም የደስታ እንጂ የሃዘን ለቅሶ ባለመሆኑ ደስ ሊለን ይገባል።

አሜን!!!