Saturday, June 18, 2011

የቅዱስ ሚካኤል ደብር ከዋክብትና ጨረቃ ሆኖ አመሸ።

በዳላስ ፎርት ወርዝ ተወዳዳሪ የሌለው ትልቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ጨረቃ ሆኖ አመሸ!!!

የአለም ፈጣሪ የእውነት ሕይወት ውነት የሆንከው ፈጣሪያችን ንጉሳችን፡ አባታችን፡ ዳኛችን፡ ምስክራችን፡ መሪያችን በውነት አወራ ጎዳና ዛሬ ምሽቱን በሙሉ ስብስበህን ስናመሰግንህና ስምህን እየጠራን ከደግነትህ ጋር በእልልታ እንድናመሽ የፈቀድክልን አምላክ አሁንም ጨረቃ ይምሰል ያንተስም የሚወደስበት ስብስብ ደጉ አባታችን።

ይሄንን ብሎግ የምታነቡ ብዙናችሁ ከብዙ አቅጣጫ። ዛሬ ምሽቱ በዳላስ በጣም የሚያስገርምና የማያልቅ ምግብ በሕብረት ከቅዱስ ሚካኤል ደብር የበላንብት ነው።
ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ካየንውና እንዳየንው እናቅርብላችሁ። ውነት እንዳለ ስትቀርብ ለጸሃፊም አታስቸግርም ምክኒያቱም ውነት ውነት ነችና።

አንድ ም እመን ወንድም ብዙ ጊዜ ጸብለ ጻዲቅ የሚያድለን "ቦታ አታገኙም ቀደም ብላችሁ ኑ እንዳታረፍዱ ቦታ አታገኙም" አለን። ሆኖም ሰአቱ ቀድመን ከነበርንበት ቦታ ብንነሳም ልክ በሰአቱ አልደረስንም ወደ እኩል ሰአት ገደማ ተሽከርካሪ ኤልብጄን አጣቦት ስንቀረፈፍ ከቆየን በሁዋላ ደረስን። በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ገረገራውን አልፈን ልንገባ ስንል አስተናጋጅ ሸሪፍ ቢጤ አየን ታዲያ ያወንድማችን ቦታ አትገኙም ቶሎ ኑያለንን ቃሉን እንደዋዛ ወስደንው ስለነበረ ያአስተሳሰባችን ተለዉጦ አይ ቦታ የለም ማለት ነው እያልን ገባን። ቦታ ወደ ሁዋላ ካሉት ወንበሮች ላይ አግኝተን ተቀመጥን። ብዙም ሳይቆይ ዝግጅቱ ተጀመረ። ድምጽዋ ከሰላ ድንጋይ አንጣት እየሱስ ሞፈር ውሃን አቁዋርጦ እንደምትሰማ ተጣሪ ወይም ሸንኮራ ውሃጋ ቆሞ ሞቆራ ወንዝ እንደሚስማ አዋጅ አስተጋቢ ላዳመጣት የፈጣሪን ስም እያነሳች ስታንቆረቁረው ድምጽዋን ላዳመጠው ጆሮ፡ በየትጋ ወደ ሰውነታችን እንደገባ መንፈስ ቅዱስ  ባናውቅም፡ ሕይወታችን በእግዚአብሄር ትንፋሽ ጠበል እንደተነከረች ነው የተሰማን ሰውነታችንን በሙሉ። ታዲያ በጣም የገረመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ወንበር ሁሉ አልቆ ወንበር በላይ በላይ ከውጪ በምግብ ክፍሉ በተከታታይ ሲግዋዝ ስናይ የሕዝቡ ብዛት ሲገርመን አይተን በቤተክርስቲያኑ የማናውቀው ነገር ሌላም አስገራሚ ነገር አየን። ይሄውም ቦታቸውን ላለማጣት ከፊታችን የነበሩ ሁለት ሴቶች ልጅም የያዙ ወንበራቸውን ይዘው ወደ ሁዋላ ሲሄዱ ቦታ ለመለወጥ እንጂ ወንብሩን እንዳይወሰድባቸው አስበው መሆኑን ፈጽሞ አላሰብንም። ብዙም ሳይቆዩ ሴቶቹ ወንበሮቹን ይዘው በመመለስ እነበሩበት ቦታ ላይ ሲቀመጡ ስናይ ምንያህል ሕዝቡ በአምላክ ስም የተደገሰውን የመንፈስ ቅዱስ ምግብ በእምነቱ ባንድነት ለመመገብ የተራበ እንደነበረ ነው የተገነዘብነው ከራሳችን ጭምር ማልት ነው። አዳራሹ ውስጥ ሆኖ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ብሎም ወደ ፊትም ወደ ሁውላም ለቃኘው የሃይማኖት አባቶች ከዋክብት ምእመናኑና ዘማሪዎቹ ጨረቃ ይመስሉ ነበር።

ይሕንን የመሰለ ከኢትዮጵያ ካትላንታ ከዋሽንግተን ዲሲና ዳላስም ያሉትን  ጭምር በማጣመር የሃይማኖት አባቶችና እናቶችን ብሎም ወጣት መዘምራንን ጭምር ያቀፈ የመንፈስ ቅዱስ እራት ደግሰ አዘጋጅተው ለመገቡን የቅዱስ ሚካኤል ደብር ቦርድ በበለጠ የዚህን አይነት የተባረከ ጥሩ ተግባር እንዲያዘጋጁልን ከእነቤተሰባቸው እድሜ ከጤና ጋር አምላክ ያብዛላቸው።

አሜን!