Sunday, June 19, 2011

"ውነተኛነትና ውነትን መናገር የሚገኘው ከመንፈስ ቅዱስ ነው" መምህር ልኡል ቃል በቅዱስ ሚካኤል ደብር ካስተማሩት።

 ከነበሩት ስድስት አር እስቶች በጥቂት ቃል ሁሉንም የአለምን ችግር መፍቻው ስለሆነው ነበር "መንፈስ ቅዱስ ወደ አለም የመጣው ወደ ውነት ሰዎች ለማድረስ ነው (ለመምራት)" ሃቅ ነው መንፈስ ቅዱስ በልቡ የያዘ ሰው እግዚአብሄርን ያውቃል። እግዚአብሄርን የሚያውቅ መንፈስ ቅዱስ በሰውነቱ ውስጥ ትኖራለች። የአለም ፍጡር የተባለ ሁሉ ውሸታም ቢሆን አንድ ሰው በፈጣሪ ተእዛዝ ብቻ ከተመራ በቁጥር ከሚበዙት ምናምንቴዎች የበለጠ የሚሆነው እሱ ብቻ ነው ይሄውም በአለምና በውነተኛው ንጉስ በክርስቶስ ፊት።ዕውነትን እንውደድ።ዕውነት እንሁን! እውነት አትመመን! እውነት በጣም ጣፋጭና የማትሰለች ምሕረት ነች። እውነት የምታመው መንገድዋን ስተን ስንጉዋዝ ብቻ ነው።


በቅዱስ ሚካኤል ደብር እየተደረገ ያለው ለወጣቱ ትውልድ የተለያየ እንክብካቤና ሳይጠይቁ በባእድ አገር ተወልድው ግራ ለተጋቡት ልጆቻችን ጠንካራ ምንም የማይጥስው የክርስትናን መንፈስ በመመገብ እየተደረገ ስላለው ጥረት ላየው ወጣቶቹ የትምሕርት ቤታቸውን የምረቃ ልብስ እንደለበሱ ስማቸው እየተጠራ ማንነታቸው ተከብሮና ታውቆ በቤተሰባቸው ሳይሆን በራሳቸው ጥረት ባሳዩት ትልቅ የማያልቅ ስጦታ ቄሳ ውስቱ ፊት እየተጠሩ መጸሃፍ ቅዱስ በያንዳንዳቸው ስም ተጽፎ የተዘጋጀላቸውን ሲሸለሙ ዛሬ ጠዋት አብዛኛው ምእመናን እንባችን ለምን እንደሆነ ባይገባንም ያነባን ብዙ ነበርን።  በተለይ ለልደትና ለትምህርት እድገት ስጦታ የክርስቶስን ታሪክና የጥቁሮች የአለም ስልጣኔ ስለአበረከትነው ለምሳሌ የመኪናዎች መሪ የትራፊክ መብራት፡ የምናብራው መብራት፡ ባቡር ሲመጣ የቁሙ መዝግ ያንና የጨረቃ መንኩራክር ጎማን ስለሰራበኢትዮጵያ ምድር ቢሆን ይህ በሰው አገር በአንድ ጎን የምንኖረው አንዋንዋር የአገር ፍቅር ናፍቆትና የቀዬአችን ትዝታ "አገሬ ዘመድ መሃል ብሆን ኖሮ ይችቀን እንዴት በደመቀች ከቤተክርስቲያን ሲወጣ ልጄ" ከሚለው አስተሳሰብ ይምስላል ሆኖም የደስታ እንጂ የሃዘን ለቅሶ ባለመሆኑ ደስ ሊለን ይገባል።

አሜን!!!

 

Saturday, June 18, 2011

የቅዱስ ሚካኤል ደብር ከዋክብትና ጨረቃ ሆኖ አመሸ።

በዳላስ ፎርት ወርዝ ተወዳዳሪ የሌለው ትልቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ጨረቃ ሆኖ አመሸ!!!

የአለም ፈጣሪ የእውነት ሕይወት ውነት የሆንከው ፈጣሪያችን ንጉሳችን፡ አባታችን፡ ዳኛችን፡ ምስክራችን፡ መሪያችን በውነት አወራ ጎዳና ዛሬ ምሽቱን በሙሉ ስብስበህን ስናመሰግንህና ስምህን እየጠራን ከደግነትህ ጋር በእልልታ እንድናመሽ የፈቀድክልን አምላክ አሁንም ጨረቃ ይምሰል ያንተስም የሚወደስበት ስብስብ ደጉ አባታችን።

ይሄንን ብሎግ የምታነቡ ብዙናችሁ ከብዙ አቅጣጫ። ዛሬ ምሽቱ በዳላስ በጣም የሚያስገርምና የማያልቅ ምግብ በሕብረት ከቅዱስ ሚካኤል ደብር የበላንብት ነው።
ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ካየንውና እንዳየንው እናቅርብላችሁ። ውነት እንዳለ ስትቀርብ ለጸሃፊም አታስቸግርም ምክኒያቱም ውነት ውነት ነችና።

አንድ ም እመን ወንድም ብዙ ጊዜ ጸብለ ጻዲቅ የሚያድለን "ቦታ አታገኙም ቀደም ብላችሁ ኑ እንዳታረፍዱ ቦታ አታገኙም" አለን። ሆኖም ሰአቱ ቀድመን ከነበርንበት ቦታ ብንነሳም ልክ በሰአቱ አልደረስንም ወደ እኩል ሰአት ገደማ ተሽከርካሪ ኤልብጄን አጣቦት ስንቀረፈፍ ከቆየን በሁዋላ ደረስን። በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ገረገራውን አልፈን ልንገባ ስንል አስተናጋጅ ሸሪፍ ቢጤ አየን ታዲያ ያወንድማችን ቦታ አትገኙም ቶሎ ኑያለንን ቃሉን እንደዋዛ ወስደንው ስለነበረ ያአስተሳሰባችን ተለዉጦ አይ ቦታ የለም ማለት ነው እያልን ገባን። ቦታ ወደ ሁዋላ ካሉት ወንበሮች ላይ አግኝተን ተቀመጥን። ብዙም ሳይቆይ ዝግጅቱ ተጀመረ። ድምጽዋ ከሰላ ድንጋይ አንጣት እየሱስ ሞፈር ውሃን አቁዋርጦ እንደምትሰማ ተጣሪ ወይም ሸንኮራ ውሃጋ ቆሞ ሞቆራ ወንዝ እንደሚስማ አዋጅ አስተጋቢ ላዳመጣት የፈጣሪን ስም እያነሳች ስታንቆረቁረው ድምጽዋን ላዳመጠው ጆሮ፡ በየትጋ ወደ ሰውነታችን እንደገባ መንፈስ ቅዱስ  ባናውቅም፡ ሕይወታችን በእግዚአብሄር ትንፋሽ ጠበል እንደተነከረች ነው የተሰማን ሰውነታችንን በሙሉ። ታዲያ በጣም የገረመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ወንበር ሁሉ አልቆ ወንበር በላይ በላይ ከውጪ በምግብ ክፍሉ በተከታታይ ሲግዋዝ ስናይ የሕዝቡ ብዛት ሲገርመን አይተን በቤተክርስቲያኑ የማናውቀው ነገር ሌላም አስገራሚ ነገር አየን። ይሄውም ቦታቸውን ላለማጣት ከፊታችን የነበሩ ሁለት ሴቶች ልጅም የያዙ ወንበራቸውን ይዘው ወደ ሁዋላ ሲሄዱ ቦታ ለመለወጥ እንጂ ወንብሩን እንዳይወሰድባቸው አስበው መሆኑን ፈጽሞ አላሰብንም። ብዙም ሳይቆዩ ሴቶቹ ወንበሮቹን ይዘው በመመለስ እነበሩበት ቦታ ላይ ሲቀመጡ ስናይ ምንያህል ሕዝቡ በአምላክ ስም የተደገሰውን የመንፈስ ቅዱስ ምግብ በእምነቱ ባንድነት ለመመገብ የተራበ እንደነበረ ነው የተገነዘብነው ከራሳችን ጭምር ማልት ነው። አዳራሹ ውስጥ ሆኖ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ብሎም ወደ ፊትም ወደ ሁውላም ለቃኘው የሃይማኖት አባቶች ከዋክብት ምእመናኑና ዘማሪዎቹ ጨረቃ ይመስሉ ነበር።

ይሕንን የመሰለ ከኢትዮጵያ ካትላንታ ከዋሽንግተን ዲሲና ዳላስም ያሉትን  ጭምር በማጣመር የሃይማኖት አባቶችና እናቶችን ብሎም ወጣት መዘምራንን ጭምር ያቀፈ የመንፈስ ቅዱስ እራት ደግሰ አዘጋጅተው ለመገቡን የቅዱስ ሚካኤል ደብር ቦርድ በበለጠ የዚህን አይነት የተባረከ ጥሩ ተግባር እንዲያዘጋጁልን ከእነቤተሰባቸው እድሜ ከጤና ጋር አምላክ ያብዛላቸው።

አሜን!

Monday, June 13, 2011

Yemenu Negga 2011 Ethiopian Day Hero?

ኢትዮጵያ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ እንደተባለው ሆነና ነው እንጂ
የዳላስ ኢትዮጵያውያን ባለውለታ ጀግናችን ሊባል የሚገባው በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ የጋራ መረዳጃ ማሕበር አባት ይመኑ ነጋ ነው። ይመኑ ምኑ ነው ለጋራ መረዳጃው? የሚለውንና የጋራ መረዳጃ ማሕበሩ እንዴትና መቼ ተፈጠረ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ከእነማስረጃው እሮብ እለት ይቀጥላል። ላለፈው ዘጠኝ አመት ይሄንኑ ሃሳብ ባቀርብም የሕዝብ ባለውለታ እንደጠላት የሕዝብ በዳይ እንደተቆርቁዋሪ ተደርጎ የሚቀርብበት አፎች ገቡብንና እስከዛሬ ከረምን።

የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው።

አምላክ ለይመኑ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር በረጅሙ ጨምርለት።
አሜን!