Wednesday, February 27, 2013

A History Gift to all Ethiopian People from Fikre Tolossa, Ph.D. "The mother and the great grrandmother of King David were Ethiopians"



በየሐረርወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያወርቅ)

ታሪኩን የማያውቅ እራሱን የማያውቅ እና የወደፊቱንም የማያውቅ ነው።
ይህ ውር እንደሚታወቀው፡ በአሜርካን አገር የጥቁሮች የታሪክ ወር በሚል በእያመቱ ይከበራል። ታዲያ በዚህ ብሎግ እና በፌስ ቡክ ስለ አፍሪካን አሜርክና ያወጣሁ ቢሆኑም የኢትዮጵያ ታሪክ ደግሞ የኢትዮጵያ እና የሕዝብዋ ወይም የራስዋ ብቻ ሳይሆን እንደሚታወቀው የመላው አፍሪአካ ተወላጆች በባርነትም ተስርቀው በአሜሪካን እና በካረቢያን፡ በኢንዶኔዢያ እና በሜክሲኮ እና በአለም ውስጥ የሚገኙት ሁሉ እና ቀጥሎም የአለም ስልጣኔ ከሆኑት አምስት አሃጉራት እና በስጡ ከሚገኙት አገሮች አንድዋ ስለሆነች ታሪክዋ የአለምም ጭምር ነው። ለዚህ ነው ከዚህ በታች ሲተረጎም የተደበቀው እና ያልተነገረው የጂውሽ ሕዝብ እና ኢትዮጵያውያን በሚል በእንግሊዘኛ የተጻፈውን አስገራሚ ታሪካዊ  መጽሃፍ በታሪክ አባትነታቸው በታወቁት በዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ የቀረበልንን የታሪክ ምግብ ለዚህ ወር ከሌሎች መጽሃፎች ሁሉ የመረጥኩት

     ብዙ ጊዜ እንደሚታወቀው አገራችንን ለመቆራረጥ በውጪ ጠላት በመደገፍ እራሱ የኢትዮጵያ ገበሬ እና ሕዝቡ ሰራዊቱ ጭምር በላቡ ያስተማራቸው ወንድሞቻችን የዚህ ጎሳ የዛ ጎሳ ነጻ አውጪ ነን ለነጻነትህ ቆሜአለሁ እያሉት በውጪ ጠላት ኢትዮጵያን ለመቆራረጥ እና አፍሪካን ለመቆጣጠር ከፋፍሉ ለሚደረገው ትልቅ መሳሪያ በመሆን ጠላት የሚጽፈውን የታሪክ ማጥፊያ መጽሃፍ ጸሃፊ በመምሰል ስማቸው የአንድነት መበተኛ መጸሃፍ ላይ ዶክተር እከሌ አቶ እከሌ ወዘተ በሚል እየተጻፈ ስኑን አየን። አሁንም እየጸፉ ነው። እነሱ በአሮፓ፡ በአሜሪካ፡ በካናዳ እና በተለያየ ቦታ በአረብ አገር ጭምር ኢትዮጵያን ለማፍረስ ተቀጣሪዎች በመሆናቸው ብዙ ገንዘብ ስለሚከፈላቸው እየተንደላቀቁ በአገር ቤትም መንግስት ይዘው በወገን ደም ሲበለጽጉ እና ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ሲያስተምሩ በፈረንጅ አገር፡  ታሪኩ እየተበወዘ እና እየተዋሸለት ግራ ያጋቡት  ኢትዮጵያዊ ግን የሃቅ እና የወገን ያልህ! እያለ ሃቀኛ የታሪክ አስተማሪ የወገን ፍቅር እረሃብ ሲያዛጋ ብዙ አመታት አስቆጠርዋል።
     ዛሬ ከላይ ጣል ያደረክዋት መንደርደሪያ ወይም አጭር መግቢያ ብዙ ለመጻፍ ሳይሆን የአገር ታሪካን ከርሳሞቹ አንቁዋሸው እና ዋሽተው ሲጽፉ ከላይ እንዳስቀመጥኩት በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያን እና ታሪክዋን ለሕዝብ የሚመግብ የሃቅ ታሪካችን ጸሃፊ እግዚአብሄር እንዳልነፈገን ለማሳየት እና ይሄም መጸሃፍ በሃስት ለተወናበደው ወጣት ሁሉ በእየአገሩ በኢዮጵያ፡ በሌላውም የአፍሪካ አገሮች፡ በአረብ አገሮች፡ በአውሮፓ፡ በአሚሪካን እና በካናዳ በጃፓን ኢዮጵያዊ ወጣት ባለበት ሁሉ ቤተሰብም እራሱን አስተምሮ ስለአኩሪ ታሪኩ ለልጆቹም የሚያስተምርበት የታሪክ ማህደር በጣም ከብዙ መጸሃፎች የተለየ ታሪክ ያዘለ ስለሆነ እና ከዚህም የበለጠ የታሪካችን ጠላቶች ለሆኑ መቁዋቁዋሚያ ትልቅ የታሪክ ምስክር መድሃኒት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ብዙ ሰዎች በሬዲዮ በፓልቶክ እና በቴሌቪዢን በኢንተርኔት ላይ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት እና ታሪክ የሚናገሩ የሚያናግሩ ይሄንን መጸሃፍ ሊኖራቸው ይገባል ብዬ አምናለሁ። 

     መጸሃፉ የኢትዮጵያን እና  የሕዝብዋን ታሪክ ከእግዚአብሄር ጋር በተያያዘ ከአብረሃም እና ከመልከጻዲቅ ማለትም ሞርመኖች አሜሪካን አገር እንደ አራያቸው አድርገው የሚያምኑበት የሚከተሉት እና ልጁን ኢትዮጵን ሳይቀር የሚገልጽም ይገኝበታል። በተጨማሪም የንጉስ ዳዊት እናት እና የሴት ቅድሚያአያት ኢትዮጵያውያን ናቸው በሚልም ተቀምጥዋል።

መጸሃፉ ገጹ ሃምሳ ሁለት ሲሆን ሌሎቹ ጸሃፊዎች ቢጽፉት ከአራት መቶ ገጽ የሚያንስ አይሆንም። ትልቅ መጸሃፍ የሚወጣው ነው ማለ ይቻላል ነግር ግን ዶክተሩ ከላይ እንዳስቀመጥኩት ወደ ሁዋላ ሳይሆን ወደ ፊት የሚያስቡ በመሆናቸው ቁምነገሩን እንጂ ተከታዮች አላስፈላጊ የተለመደ ሃተታ አላስቀመጡም። መጽሃፍዋ በሴት ቦርሳ ውስጥ ተይዛ በማንኛውም ጊዜ የምትነበብ ነች። ለወንዱም በኪሱ ሊይዘው የሚችል መጸሃፍ ነው። እንግዲህ ይሄንን ያህል ከገልጸኩላችሁ በሁዋላ የበኩሌን እዚህ ላይ እየደመደምኩኝ ከዚህ በታች ባለው ኢሜል ማለት መጽሃፉ ላይ ባገኘሁት በመጻፍ ዶክተር ፍቅሬን በቀጥታ በኤሜል በማግኝት መጽሃፉን ልታገኙ ትችላላችሁ። ftolossa@aol.com
     ስለ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ እና ለኢትዮጵያ እና ለሕዝቡ እስካሁን ላደረጉት አስተዋጽዎ በቅርብ በዚሁ ብሎግ ስለምጽፍ ተከታተሉ።