Tuesday, February 19, 2013

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ጋርላንድ ቴክሳስ በfebrwary 16, 2013 የተጠራው ስብሰባ የቅዱስ ሜካኤል ደብርን በገለተልኛ ይቆይ ? ወይስ አባት ይኑረው? ግምገማ።

በየሐረርወርቅ ጋሻው(የኢትዮጵያወርቅ)

በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኑን ከፓለቲካ ነጻ ማውጣት አለብን ገለልተኛ ነኝ የሚሉት በውጪ አገር የሚኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናት በሙሉ በሲኖዶስ ስር መሆን ይጠበቅባቸዋል።



ብዙሰዎች ስለስብሰባው እየደወላችሁ ምንተወሰነ
የሚል ጥያቄኛ ሌላም ሃሳብ ይዛችሁ የምትደውሉት ብዙናችሁ። በተለመደው ከእኔ ሃቁን ለማወቅ ስለምትደውሉ አመሰግናለሁ። አንደኛ ለሁላችሁም የምመልስበት የስርልክ ሳዓት የለኝም። ሶስተኛ የቤተክርስቲያን አባልነታችሁን ከፈሉ ወይም አባል ሁኑ የተሰብሳቢነቱ እድል እንዲኖራችሁ። አራተኛ፡ ቤተክርስቲያኑ የቀዳው ቪዲዎ ስላለ በዛ ለመረዳት ስለምትችሉ የሚመለከተውን እንድታናግሩ አሳስባለሁ። አምስተኛ እኔ ከቤተክርስቲያኑ እርቀሻል እሁድ እሁድ ያለፈው ምርጫ ቦርድ ከተደረገ በሁዋላ በሚል የምትጠይቁኝ  ሁሉ: ስለኔ በቅዱስ ሜካኤል ደብር ቤተክርስቲያን ያለመታየትም ሚስጥር ስላልሆነ ይሄን ያህል ሰለተጨነቃችሁበት ባጭሩ ለመግለጽ ያሕል ፡ በሶስት የቦርድ አባላት ምርጫው በትክክሉ እንዳይሄድ ሻጥር ሰርተው ሰለደረስኩበት የዶክተር ግርማና የነርስ ጌታቸው ፊጣ ቦታውን መልቀቅ ለቤተክርስቲያኑ የሚያመጣውን ጉዳት ሰለማውቅ በማዘኔ ከእነዚህም ሰዎች ጋር ላለመጋጨት እራቅ ብሎ ተግባራቸው ግልጽ እስኪሆን ሌላ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በመሄድ ለመቆየት በማሰብ ነው። የተማረሰው፡ ከኮራብሽንና በሑለት ሰዎች ብቻ የሚመራ ቦርድ ቀርቶ ሁሉም የቦርድ አባል ድምጽ የሚስተናገድበት ያደረጉትን እነዚህን ሰዎች በመማራቸውና የተለመደውን የመንደር የሁዋላ ቀር አሰራር በማስቀረታቸው ትልቅ የድብቅ ዘመቻ አድርጎ ምእመናኑንና ቤተክርስቲያኑን በቦርድ ውስጥ ተቀምጠው መጉዳት ሕሌናዬ እንደ ብዙዎቹ አልተቀበለውም። እራቅ ማለቱን መርጬ ነው: ሆኖም ትቼዋለሁ ለቤተክርስቲያኑ ሰላምና ለምእመናኑ አንድነት ስል :: ስለ ፈጸሙትም ተንኮል እግዚአብሄር ይቅጣቸው። ለደወላችሁልኝ እቤቴም ድረስ እኔን ፍለጋ ለመጣችሁት ሁሉ አመሰግናለሁ። ሆኖም እኔ የግለሰቦች ተቃዋሚ ሳልሆን ህብረተሰባችንና ቤተክርስቲያናችንን አንድነታችንን የሚነድሉ ከራሳቸው ጥቅም ሌላ የማይታያቸው ቂመኞች ሰዎችን ተግባር ተቃዋሚ መሆኔን በግልጽ ላስቀምጥ እወዳለሁ። ይሔንን ስል በቤተክርስቲያንም ቦርድ ውስጥ ተቀምጠው ቤተክርስቲያኑን ከሚጎዱት ጋር የሚወግኑትን ለቤተክርስቲያኑ የሚጠቅሙትን ከቦር ውስጥ እንዲወጡ በአፍራሾች አይምሮ የሚመሩትንም ጭምር ማለት ነው። በስብሰባው ላይ እንደተናገርኩት አንድም የምጠላው ሰው የለም ህዝብን ለመከፋፈል በሚወስዱት እርምጃ አላከብራቸውም እንጂ።

በመጀመሪያ ብዙ ክርስቲያን የሚጠይቀውን ሲኖዶስ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ባጭሩ ለማስቀመጥ እወዳለሁ ይሄውም ከዚህ ቀደም በዚሁ ብሎግ በሰፊው ይጠቅማችሁዋል ብዬ የጻፍኩትን ማየት ስለምትችሉ።

ሲኖዶስ ማለት በቤተክህነት አጠቃቀም የጳጳሳት ጉባኤ ነው። የመጀመሪያው "ሲኖዶስ" የተጀመረው በእየሩሳሌም በሃምሳ ዓመተምሕረት ነው። በተጨማሪ ለቤተክርስቲያን መመሪያና መተዳደሪያ ይሆኑ ዘንድ ሕግጋትና ሥረዕታት የተፃፉበትና አራት ክፍል ያለው መጽሐፍ ሲኖዶስ ተብሎ ይጠራል። ይህም መጽሐፍ ሲኖዶስ ቤክርስቲያኖችን ከምትቀበላቸው ሰማኒያ አንዱ መጽሕፍት ውስጥ ይቆጠራል። የመጀመሪያው ሲኖዶስ ሊቀመንበር በመሆን የመራውም የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ወንድም በሚል የሚጠራው ቅድዱስ ያዕቆብ ነበር። ለሲኖዶስ መደረግ ምክኒያት የሆነም ነገር በሐዋ.ሥራም. አስራ አምስት ላይ እንደተገለጸው፡ ከአይሁድዳዊነትና ከመምለኬ ጣኦትነት ወደ ክስርትና የተለወጡ የአይሁድና የአህዛብ ወገኖች፡ በአንዳንድ ኦሪታዊ ሕግጋት ምክኒያት በፈጠሩት አለመግባባ ነበር። ስለዚህ፡ ሲኖዶስ የማይለወጥ የቤተክርስቲያናችን መመሪያ ነው። በሲኖዶስ የተወሰነን ወይም የጸደቀውን ነብሰ ገዳዮችና ወሮ በሎች ሊለውጡት አይችሉም። ም እመናንም ሊለውጡትና ምድራዊ ፍላጎታቸውን ድሎታቸውን ማርኪያ ለማድረግ እነደፈለጉት ሊያረጉ አይፈቀድላቸውም። ቤተክርስቲያን ሃቀኛዋ በግለሰቦች ወይም በሌላ አነጋገር በሞግዚት አትመራም በሃይማኖት አባትኛ አባቶች እንጂ።
ከላይ እንዳስቀመጥኩት በማይወበዘው የፓትሪያርክ አመራረጥና በሲኖዶስ በቀኖና ላይ መጀመሪያ በደርግ ጊዜ ሁለተናውን ፓትሪያርክ አስሮ ሌላ በመሾሙ ቅዱስ ሲኖዶስን ደፍርዋል። አሁንም በጠመንጃ አገር ይዞ በክክልል ሕዝብና አገርን የሚመራው የራሱን ሰው ፓትሪያርክ አድርጎ ነበር። አቡነ ጳውሎስ በድንገት በመሞታቸው ደግሞ ፓትሪያርኩን ብጹህ አቡነ መርቆሪዎስን በቦታቸው መልሶ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተክርስቲያንዋ መንግስት የተባለ እጅ እንዳይገባ እርቅ አባቶች እያደረጉ ባሉበት ሰዓት፡ የወያኔ መንግስትና ባለስልጣኖቹ የተጀመረውና እየሰመረ የመጣውን አቡነ መርቆሪዎስንንም ፓትሪያርክነታቸውን ያረጋገጠውን እረግጦ የራሱን ፓትሪያርክ ለማቁዋቁዋም እየተርዋርዋጠ ይገኛል በአሁኑ ጊዜ። ስለሆነም፡ ባስቸክዋይ የእርቁ አካል የሆኑት ድምጻቸው ሰለጠፉብን ይሰቀሉ የተባሉትም ቄሳውስት እርምጃ እንዳይወሰድባቸው በስብሃት ነጋና በግብረአበሮቹ ከዚህ በታች በስብሰባው ላይ ባለፈው ቅዳሜ ሃሳብ ለቤቱ እንደሰጠሁት እዚህም ላይ በመድገም የምእመናን ፊርማ በማሰባሰብ እርቁ ባስቸክዋይ እንዲቀጥል የወያን ጳጳስ ምርጫ በመቃወም በትክክለኛው የሃይማኖታችን ቀኖናና ሲኖዶስ ብቻ ያለ ፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ፓትሪያርኩ አቡነ መርቆሪዎስ በቦታቸው እዲመለሱና እግዚአብሔር ወደ ዘለዓለማዊ ቤታችን ለሁላችንም ወደ ሆነው ቤቱ እስቲጠራቸው ድረስ የቤተክርስቲያናችንን አባትነት እንዲቀጥሉ መተባበር ከሁላችንም ይቅብናል። የፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ስል ወያኔን ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚነኝ የሚለውም ጭምር እጁን ማውጣት አለበት። ወያኔም: ተቃዋሚውነን የሚሉትም ደጋፊዎቻቸውም እነሱ ባሉት ካልሆነ በሲኖዶስ በቀኖና የማያምኑ: ቤተክርስቲያንም የሚሄዱት:አላማቸውን ለማራመጃ ይረዳ ዘንድ ነው  ።

የወያኔ መንግስት፡ ከላይ ያስቀመጥኩዋቸውን የሰላም መፍትሄ በቅርብ ቀን አልቀበልም ካለና የራሱን ፓትሪያርክ የሚሰይም ከሆነ፡ ሰያሚውም ተሰያሚውም አንድ ሕገወጥ መሆናቸውን ተቀብለን ፡ ወያኔ ሊገድልአቸው ሲል ካገር ወጥተው በመከራ ላይ የሚኖሩትን ብጹህ አቡነ መርቆሪዎስን አባትነት አክብረን ቤተክርስቲያንዋ በህግዋ መሰረት ሲኖዶስና ፓትሪያርክ መምረጥ እስክትጀምር በዚህ መልክ አባት ይዘን በሚመራው ቤተክርስቲያን መቀተል ይኖርብናል ብዬ አምናለሁ። ይሄ አባባሌና የማያወላውል ውሳኔዬ የማያስደስተው ካለ የክርስትና ሃይማኖት መመሪያን ማለትም አለም አቀፍ "ሲኖዶስ" እራሱ ክርስቶስ የፈጠራት ቤተክርስቲያንን መመሪያ ሳያውቅ የሚዋዢቅ በመሆኑ ያለማወቁ ችግር የሱ ወይም የስዋ ብሎም የነሱ እንጂ የእኔ አይሆንም። በሃይማኖቴ ሲመጣ በስብስብ ምክር የምወስነው ሳይሆን በመጸሃፍ ቅዱሱ በእግዚአብሄር ትእዛዝ ብቻ የምመራ ማንምም ሊያወናብደኝ የማይችል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሕግ ብቻ የምከተል መሆኔንም መግለጽ እወዳለሁ።
መልክት። አሁን በቅዱስ ሜካኤል ደብርን በግለለተኛ ይቆይ የሚሉትን ለመቁዋቁዋም የምትርዋርዋጡት ገና እናንተ ተኝታችሁ አይምሮ አችሁ ላይ "የቅዱስ ሚካኤልን ደብር ለማስረከብ ለትግራይ ነጻ አውጪ አጥሩ ላይ ተንጠልጥለው የቦርድ መቀመጫውን ወንበር እያመረጡ ስለሆነ ቤተክርስቲያኑን እናድን" በሚል ለምእመናኑ በሙሉ በበራሪ ወረቀት ጭምር ማሳሰቢያ ስበትን ለቦርዱም በጊዜው ለነበረው ባቀረብኩበት ጊዜ የኔተቃዋሚ የነበራችሁ ፍርድ በሃሰት ከነሱጋር ሆናችሁ በሃሰት ህብረተሰቡን በማሸበር ጭምር የሬዲዮን ስርጭት አዘጋች በሚል ጭምር ውነቱ በህብረተሰቡ እንዳይታወቅ ያደረጋችሁ እኔ በስብሰባው ላይ የሰጠሁት የተባረክ ሃሳብ ስላላስደሰታችሁ ቅር እንዳላችሁ የነገራችሁኝ ነበራችሁ ሆኖም አወላዋይ ልባችሁን አንድ እንዲያረግላችሁ እግዚአብሄርን ለምኑት። ችግሩ የቤተክርሲያኑ እናንተና የድብቅ የወያኔ ተቀጣሪዎቹ ስለሆናችሁ። ቀደም ሲል እግዚአብሔርን የካዳችሁም ትገኙበታላችሁ። ይሄንን ስል ምን ማለቴ ነው::
ጠቅላላው ምእመንን ላስታውስ የሚፈልገው ከላይ ያስቀመጥኩዋቸው ሃቆች ዛሬ በእውን ፊት ለፊት ወጥተው ሰላም ቤተክርስቲያኑን ከመንሳታችው በፊት አስፈላጊው ጥንቃቄ ቢደረግ ኖሮ ዛሬ ይሄ ሁሉ እላይ እታች ባልተደቀነብን ነበር። እና መረሳትም የሌለበት የመረዳጃ ማሕበሩ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዳላስ ፎርት ወርዝ ንዋሪ መገልገያ የሆነውን የሬዲዮን ስርጭቱን ጭምር እና የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራልን እናድን ብዬ ሳቀርብ ከናካቴው አብሮዋቸው የነበሩት ጆሮ ዳባ ብለው፡ ዛሬ ተኩላዎቹን ከላይ እንዳስቀመጥኩት እየሰፈጸሙ ያሉት ከፋፋይ ተግባርን አብረዋቸው በመሃላችን ያሳደጉ እና ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ ሰላም ክርስቲያኑን በአምላክ የምናምነውን አላስቀምጥ ማለት ትልቅ አስተዋጽዎ አድርገዋል። በዛላይ የፓለቲካ ፓርቲ አባል ነን ተወካይ ነን ተቃዋሚንን በሚል ከልብና በእውነት ስለ አገራችን እና ሕዝቡ አንድነትና መብት የምንታገለውን ሁሉ እንቅፋት በመሆን የሚታወቁ : አንድም በተጨባጭ የረባ ስራ ሰርተው ውጤት ያላስመዘገቡና ቢጠየቁም ታጋይ ነን፡ ታግለናል ከሚል የአፍ ቃላት ወሬ በስተቀር በተግባር የሚተረጎም ያልሰሩ ሊሰሩም ገና በዚህ በቆየው እድሜያቸው እንክዋን ለወጣቱ ትውልድ ምን እንተውለት ጥሩ ነገር ብለው የማያስቡ ለራሳቸው ብቻ የሚያስቡ ሰዎች ናቸው።
አንደኛ፡ በስብሰባው ላይ ከተገኙት የቤትክርስቲያኑ አባላት የነበራቸው ተሳትፎ ይበል የሚያስብል ቢሆንም፡ በማር የተጠቀለለ መርዝ በውስጥ እንዳለበት ለመገንዘብ ለማንኛችንም ምእመን ነብይ መሆንን አልጠየቀንም ነበር። እነሆ የሚያስደነቀው በአፈ ቀላጤነት በማር የተሸፈነ መርዛቸውን እንድንቀበልላቸው እና ለቀጣዩ አላማቸው ማስፈጸሚያ ይረዳናል ብለው ቀድመው ይዘውት የነበረውን አቁዋም ወይም ወያኔነታቸውን ይዘው ሕዝብ ፊት መቅረብ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በፍጹም የማይፈቅድላቸው መሆኑን ሲገነዘቡ፡ ስልታቸውን በመቀየር በይፋ ከመቅረብ እና አቁዋማቸውን ከመግለጽ ይልቅ ከእነሱ አቁዋም ውጪ ያለውን ምእመናን ለማማለል (ለማታልል)እና የሚቀጥለውን የቦርድ ምርጫ በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማዋል እና እዛም ውስጥ ሰግስገው ሰርገው ለመግባት የሚያስችላቸውን የመራጭ ድምጽ ለማግኘት ሲሉ ብቻ አሁን የያዙትን ገለልተኛ የሚለውን አቁዋም እያራመዱ ይገኛሉ። ስለዚህ አሁን ለምእመናኑ ማሳሰብ የምፈልገው እነዚህ ሰዎች ወደ ስልጣን መጥተው ከተቆጣጠሩ በሁዋላ የሚፈቅዱትን የሚፈልጉትን ሁሉ ለማስፈጸም እንዲረዳቸው አንደኛ ፡ ቀደም ብለው በመረዳጃው ማህበር ስም ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በሚል ስም እራሳቸውን ሕዝብ ሳይምርጣቸው በስልሳ ሰው ድምጽ ብቻ አርባ አምስት ሺ የሚደርስ በዳላስ ንዋሪውን ኢትዮጵያዊ ከመጤፍ ባለመቁጠር በተለመደው እነዚሁ ጋንግስተሮች ናቸው ቦርድ ኦፍ ትረስቲ ብለው እራሳቸውን ሰይመው ሾመው ተመቻችተው ያሉት።

ሁለተኛ፡ የሕብረተሰቡ ይሆነውን የሕዝቡን የሆነውን የሬዲዮ ስርጭት በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ሕዝቡ እንዳይጠቀምበት እና ሃሳቡን እንዳይገልጽ እና እንዳይገናኝበት፡ እንዳይወያይበት ፕሮግራሙን በሚያስፈጽሙት ግብረአበሮቻቸው የሚፈልጉትን ብቻ እያስተናገዱበት እነዚህም ሰዎች በአሁኑ ሰአት በገለልተኛነት እራሳቸውን ያስቀመጡ ስለሆነ ለዚሁም ከዚህ በላይ ምንም አይነት ማስረጃ ከራሳቸው አንደበት ከወጣው የማንነታቸውን መሰረት ለማወቅ በቂ ስለሆነ ከዚህ ሌላ ማስረጃ አስፈላጊ አይደለም።

ሶስተኛው፡ አሁን በግልጽ በማያስቀምጡት የወያኔን በለሃምሳ ሁለት ገጽ መመሪያ መሰረት ለማስፈጸም ከመቼውም ይበልጥ የተጣለባቸውን እና የተቀበሉትን የወያኔን እንደራሴነት አደራ የተሙዋላ ለማድረግ እና ከወያኔ አለቃቸው የተዘጋጀላቸውን ምንዳ ለመቀበል እጃቸውን ከመዘርጋታቸው በፊት አሁን በእጃቸው በቁጥጥራቸው ስር ሊገባላቸው ያልቻለውን ቤተክርስቲያን በቀጣዩ የቦርድ ምርጫ ተመራጭ ሆነው በመግባት ጠቅላላ ያለንን ሕልውና በሙሉ በገዢው ፓርቲ ፍላጎት እና ውሳኔ በሚመራው ሲኖዶስ የአማራ እና የኦርቶዶክስን አከርካሪ ሰብሬአለሁ በሚል በይፋ በሚለፍፈው ወያኔ ስር ዓት አሳልፎ ሊሰጡን የተዘጋጁ የቀበሮ ባሕታውያን ስለሆኑ፡ የቤተክርስቲያኑ አባላት እራሱን እና ቤተክርስቲያኑን ለማዳን ከነዚህ ተኩላዎች ፡ ከፍተኛ ሃላፊነት ከምንግዜውም የበለጠ እንዳለበት ማስገንዘብ እወዳለሁ። በመጨረሻም እኔ በግለሰቦች በእየቦና ቤቱ በሚወራ የስርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ሰው ሳልሆን ቀደም ብሎ በማሰብ የምናገርና ሃሳቤን ከገለጽኩኝ በሁዋላ የማርም የምቀለብስ ሳልሆን ፡ የማምንበትን በቅድሜያ አስቤ የምናገር መሆኔንም፡ በቤተክርስቲያኑ ስብሰባ ላይ የሰጠሑት ከላይ ያስቀመጥኩት ያላስደሰታቸው ችኩሎች ላስጨብጥ እወዳለሁ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ብሎም በልጆቹ ተጠብቃ ለዘለዓለም ትኖራለች!
የኢትዮጵያንና የሕዝብዋን አንድነት በአንድ ሰንደቅ አላማ ስር እግዚአብሄር ለዘላለም ይጠብቅልን።

From a priest that thinks like me in regard to ETOC see the commentary below:

By: ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

፭ኛ፦ በሰላሙ ቡድን ላይ የወደቀው ታሪካዊ ግዴታ፦


"ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ"

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

nigatuasteraye@gmail.com

የካቲት ፳፻፭ ዓ..
ማሰሰቢያ፦ "ወለእመ ተራድአ በመኳንንተ ዝንቱ ዓለም፡ወተሠይመ ለቤተ ክርስቲያን እምሃቤሆሙ ይትመተር ወይሰደድ ውእቱኒ ወኩሎሙ እለ ተሳተፍዎ"(.. ፻፸፭) ማለትም፦ "በመንግስት ድጋፍ የተሰየመ ግለ ሰብ ጭንጋፍ ነው"። በቦታው እንዲቀመጥ የተባበሩት ሰዎችም ህይወት የሌለውን ህይወት ያለው በማስመሰል የተባበሩ ናቸውና ጭንጋፎች (ምቱራን) ናቸው።
"ይትመተር" ማለት፦ ይጨንገፍ ማለት ነው። "ይሰደድ" ማለት ደግሞ፤ ጭንጋፍ ሆኖ በተወለደ ህይወት አልባ ውራድ ላይ የሚፈጸመው ስርአት ይድረስበት ማለት ነው። ሊወለድ ነው እየተባለ የሚታወጅለት ይህን ግለ ሰብ፤ በመንበሩ ላይ አጽናው ብለን በቅዳሴያችን ልናወሳው ይቅርና፤ "አርህቅ እግዚኦ እምኔየ። ወእምነ ኩሉ ህዝብከ። ወእምዝንቱ መካን ቅዱስ ዘዚአከ"(.. ገጽ ፴ ቁ ፴፰) እያልን ከፍ ባለ ድምጻችን ከግላችን፤ ከማህበራችንና ከተቀደሰው መንበራችን እንዲርቅ የምናውጅበት ምቱር ፓትርያርክ ነው። መመሪያችን "ወእለ ሴሙ ላዕሆሙ መገብተ ከሐድያነ ንኮንኖሙ በግዘት በኩሉ መዋዕል"(.. ፻፩፡ ፳፫) እንዲል ይወገድ የሚለው ምቱሩን (ጭንጋፉን) ብቻ ሳይሆን ሿሚዎችንና የተስማሙትን ሁሉ ነው።
መግቢያ

"እመኒ ሞአ በጉሁሉት ምቱር ውእቱ" (.. . ቁጥ. ፻፸፮)
"በሸፍጥ ምርጫ በመንበር ላይ የሚቀመጥ ምቱር" ማለትም ህይወት የሌለው ጭንጋፍነው። በባህላችን የአዕምሮ መታወክ ካልገጠመን በቀር፤ ውራድ ወይም ጭንጋፍ ሆኖ የተወለደውን ሰውም ሆነ እንስሳ ለማሳደግ ከናቱ ማህጸን ተቀብሎ የሚያቅፍ የለም።
ህዝብ ሳይመርጠው፥ እግዚአብሄር ሳይጠራው ወደ ፓትርያርክነት የሚመጣ እንደ ውርጃ ይቆጠራል። እንዳይከሰት ጥንቃቄ ይደረግ ዘንድ መጽሐፋችን መመሪያ ይሰጣል። በዘመናችንም የውስጥና የውጭ ሲኖዶሶች በሰየሙት ዛሬ የሞት ስቅላት አቶ ስብሀት ነጋ በፈረዱበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ (የሰላሙ ቡድን) አማካይነት ተጨንግፎ ከሚወለድ ፓትርያርክ እንድናለን ብለን ተስፋ አድርገን ነበር። 2
ነገር ግን የወያኔ መንግስት ይህን ሁሉ ጥያቄ ሳይቀበል፤ የህዝቡንም ፈቃድ ጥሶ በመለመላቸው ጳጳሳት አዋላጅነት ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ ለመውለድ በምጥ ላይ መሆኑን በብዙኀን መገናኛዎች ሰማነው። የህዝበ ክርስቲያኑና የሊቃውንቱ ክህነታዊ ተማህጽኖ የመነጨበት የቤተ ክርስቲያናችን መመሪያ እንደሚጠቁመን፤ አሁን በሚከናወነው መንገድ ጨንግፎ የሚወለደውን ፓትርያርክ "ሕልፈቱ ቅድመ አስተርእዮቱ" ብላ ቤተ ክርስቲያናችን ትጸየፈዋለች። ይህን ለመግለጽ የሞከርኩባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።
o
፩ኛ፦ተጨንግፎ የሚወለደው ፓትርያርክ
o
፪ኛ፦እንዴት ጨነገፈ
o
፫ኛ፦መቀበል የለብንም
o
፬ኛ፦እግዚአብሔር የከፈተው በር
o
፭ኛ፦የእርቀ ሰላሙ ቡድን ሃላፊነት
o
፮ኛ፦ የህዝበ ክርስቲያኑ ሐላፊነት

ከዚህ በመቀጠል "ተጨንግፎ የሚወለደው ፓትርያርክ" በማለት የቀረጽኩትን የመጀመሪያውን አንቀጽ በማብራራት ይህችን ጦማር እጀምራለሁ።
፩ኛ፦ ጨንግፎ የሚወለደው ፓትርያርክ

የካቲት ፳፩ ስለሚወለደው ፓትርያርክ ስናስብ ከአቡነ ጳውሎስ የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። አቡነ ጳውሎስን ይህ መንግስት ከሜዳ አግኝቶ በማደጎ አሳደጋቸው እንጅ ጸንሶ የወለዳቸው አይመስሉም። ይህን ለማለት ያስገደደኝ፤ እርቁ እንዲጀመር በፈቀዱት በአቡነ ጳውሎስ ላይ አቶ ስብሀት ነጋ "እርቁ እንዲጀመር በመስማማታቸው ተሳስተዋል" ብለው በወረወሩባቸው ትችት እራሱ የወያኔ መንግስት አቡነ ጳውሎስን የጉዲፈቻ ልጅ አድርጓቸዋል። የኢ.... ልጅ መስለው የተገኙት በቦታው ከተሰየሙ በኋላ ነውና ማደጎ ነበሩ ማለት ነው። ይህ ዛሬ ሊወለድ ነው ተብሎ የተነገረን ፓትርያርክ ከአቡነ ጳውሎስ ለየት ያለ ኢ....ን በካ በነበረበት ጊዜ በአካሉ በሥጋውና በነፍሱ አስመሎ ይወልደው ዘነድ የጸነሰ ነው። ያጸናነሱን ሁኔታ የቀድሞው የሕ.... ሊቀመንበር ከነበሩት ከዶክተር አረጋዊ በርሄ መጽሐፍ እንመልከተው። (ዝርዝሩን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ)
የዶክተር አረጋዊ ታሪካዊ ሕህያው የምስክርነት ቃል፦

"የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር በ1979 አመተ ምህረት አስተሳሰብ ለዋጭ የፕሮፓጋንዳ መርሀ ግብር ለሚመለምላቸው ቀሳውስት ዘረጋ። የማሰልጠኑ ዓላማ ቤተ ክርስቲያኗን ከህዝብ ለይቶ በመምታት ስፋቷን ማጥበብና በትግሬአዊነት ላይ ብቻ የተመሰረተ ስሜት በትግራይ ተወላጆች ጭንቅላት መክተት ነው። ቤተ ክርስቲያኗ ለረዥም ዘመናት በህዝቡ አዕምሮ ላይ ስትተቀርጸው የኖረችውን ብሄራዊ የኢትዮጵያነትን ስሜት ከትግራይ ህዝብ አዕምሮ ጠራርጎ በጠባቡ ትግሬአዊነት ስሜት በመተካት የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዘት እያጠበቡ ራሷን ቤተ ክርስቲያኒቱን መምታት ነው። 3
የወረዳ ስልጠና የተጀመረው በጠንካራ ትግሉ የታወቀው ካዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነገረ መለኮት ትምህርት የተመረቀው ገብረ ኪዳን ደስታ ነው። የስልጠናውም ይዘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላላ መዋቅራዊ አስተዳደር በትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ባለሟሎች መተካትና በቤተ ክርስቲያኒቱ አካባቢ የትግርኛ ቋንቋ እንዲሰፍን ማድረግ ነው። በዚህ መንፈስ ተቀረጾ የተዘረጋው እቅድ በየሰበካውና አጥቢያው ያሉትን ቄሶችና ምእመናኑን ቤተ ክርስቲያኒቱ ጠብቃ ካቆየችው ታሪክና ብሄራዊ መዋቅር እየገነጠሉ በማስኮብለል ወደ ነጻ አውጭው አምባ መሰብሰብ ነው። መነኮሳት በመምሰል ደብረ ዳሞ ወደ መሳሰሉት ገዳማት ሰርጎ በመግባት የድርጅቱን እቅድ በማስተጋባት የሚያዳክም አጥኝ ኃይል በስብሀት ነጋ መሪነት ተመሰረተ። የማሰልጠኑ ተግባር ከተፈጸመ በኋላ፤ የሰለጠኑት አስመሳይ መነኮሳት በትግራይ ምድር ዙሪያ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ከዋናው ጽፈት ቤት መገንጠልን በ1987 እና በ1989 ተግባራዊ እንዲያደርጉት አደረገ። ከነጻ አውጭው አመራር የሚቀበለው መነኮሳት እየመሰለ ሰርጎ የገባው አስመሳይ ቡድን፡ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና መዋቅር ተገንጥሎ ከነጻ አውጭው ጋራ ጎን ለጎን የማካሄ ስራውን ቢሮ ከፍቶ ጀመረ። በዚህ ጊዜ ከዋናው ጽ ቤትና ከነጻ አውጭው ትእዛዝ በሚቀበሉት ቡድኖች መካከል የጎላ ልዩነት በግልጽ መታየት ጀመረ። እስከ 1990 ድረስ ሁለቱም ጎን ለጎን ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ፤ ነጻ አውጭው መቀሌን ሲቆጣጠር፡ ከዋናው ጽ ቤት አመራር ይቀበል የነበረው መቀሌን ለቆ በ1991 ወደ ደሴ ሲሄድ፡ በነጻ አውጭው ስር ይመራ የነበረው ቡድን መቀሌውን ተቆጣጠረ"
ከዶክተር አረጋዊ በርሄ መጽሐፍ ከጠቀስኩት አንቀጽ ፬ ቁልፍ ሀረጎች እነሆ!
o
፩ኛ፦ "መነኮሳት በመምሰል ደብረ ዳሞ ወደ መሳሰሉት ገዳማት ሰርጎ በመግባት የድርጅቱን እቅድ በማስተጋባት ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያዳክም አጥኝ ኃይል በስብሀት ነጋ መሪነት ተመሰረተ"
o
፪ኛ፦ "ከነጻ አውጭው አመራር የሚቀበለው መነኮሳት እየመሰለ ሰርጎ የገባው አስመሳይ ቡድን፡ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና መዋቅር ተገንጥሎ ከነጻ አውጭው ጋራ ጎን ለጎን የማካሄድ ስራውን ቢሮ ከፍቶ ጀመረ"
o
፫ኛ፦"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላላ መዋቅራዊ አስተዳደር በትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ባለሟሎች መተካትና በቤተ ክርስቲያኒቱ አካባቢ የትግርኛ ቋንቋ እንዲሰፍን ማድረግ ነው"
o
፬ኛ፦ "ነጻ አውጭው መቀሌን ሲቆጣጠር፡ ከዋናው ጽ ቤት አመራር ይቀበል የነበረው መቀሌን ለቆ በ1991 ወደ ደሴ ሲሄድ፡ በነጻ አውጭው ስር ይመራ የነበረው ቡድን መቀሌውን ተቆጣጠረ"በማለት ጸንሳ፤ ወልዳና አሳድጋ የሰጠችን መንደር ትባረክና ብትንትን አድርገው ዶክተር አረጋዊ በርሄ ነግረውናል።

ይህን ይቅርታ የሌለው ደባ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ቀደም ብለው የፈጸሙ አቶ ስብሀት ነጋ ጫካ በነበሩት ጊዜ ካቀዱት የጥፋት ሴራቸው ጋር ስለተጋጨ፤ የጉዲፈቻ ልጃቸውን ሟቹን አቡነ ጳውሎስን እርቀ-ሰላም እንዲጀመር በመፍቀዳቸው ኮንነዋቸዋል። "ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች መሰቀል አለባቸው" ቢሉ፤ "እምውስተ ርኩስ ምንትኒ ኢይወጽእ ንጹህ ወበውስተ ሀሰት በአይቴ ይትረከብ ጽድቅ" (ሲራ ፴፩፡፬) ማለትም፦ "ከአህያ መስዋዕት የሚሆን በግ እንደማይወለድ፤ ከሐሰተኛ ሕልምኛም እውነተኛ ነገር አይገኝም" ብሎ ጠቢቡ የተናገረውን ስለምናውቅ ዛሬ አቶ ስብሀት ነጋ ይሰቀሉ እያሉ አረመኔያዊ ንግግር ቢናገሩ ሊያስደንቀን አይገባም። ባለፈው ስህተታቸው ንስሀ መግባት ሲገባቸው፤ ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ ለማሸከም ባላቸው ድፍረትና ንቀት በመቀጠላቸው እጅግ ልናዝንላቸው ይገባል። ከኛ የሚጠበቅብን ሊያሳዝሉን የሚሞክሩትን ጭንጋፋቸውን (ምቱርን) ፓትርያርክ እራሳቸው አዝለው እንዲዞሩ ማድረግ ነው። ይልቁንስ በመምጣት ላይ ያለውን የነ አቶ ስብሀት ነጋን ፓትርያርክ ምን እንዳስጨነገፈው? ቤተ ክርስቲያናችን የምትነግሪን "ምን አለሽ?" ብለን እንጠይቃት። 4
፪ኛ፦ምን አስጨነገፈው?

ቤተ ክርስቲያናችን "ይኩን በስምረተ ሕዝብ ዘይሰየም ላዕሌሆሙ። በህርየተ ኩሎሙ ህዝብ"(. . .) አማኞቹ በሰላም በስምምነት መርጠውት እሱም በምልአ ልብና በትፍስህት መምራት የሚችል ሲሆን ብቻ ነው ህይወት ያለው ፓትርያርክ ብለን የምንቀበለው። ይህ ሊወለድ ነው ተብሎ የተነገረን ግን በህዝበ ክርስቲያን ሳይፈለግ በካህናት ሳይደገፍ ይልቁንም መራር ተቃውሞ እየሰማ በግርግር በሸር በመንግስት ድጋፍ የሚሰየመውን ፓትርያርክ ቤተ ክርስቲያናችን ጭንጋፍ "ምቱር" ትለዋለች። ሰዎች ሲቃወሙ የተቃውሞ ድምጻቸው እውነትነት እንዳለውና በሀሰት እንደሆነ ተመርምሮ እስኪደረስበት ድረስ፤ ጥቂቶችም ቢሆኑ የተቃውሞ ድምጻቸው ተከብሮ የተጀመረው የምርሂደት መቆም አለበት።
ተቃውሞው ተመርምሮ እስከ ሶስት ከደረሰ ማለትም የሚቃወመው የህብረተ ሰቡ አካል ሲሶው ከሆነ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና መረጋጋት ሲባል የታጨው ግለሰብ ገለል በማለት የሲሶው እጅ ህብረተ ሰብ ድምጽ መጽናትና መከበር አለበት።

የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት መርሆ እንመልከት፦

o
፩ኛ፦ "ወኢይከውን አሐዱ ሰማእት ከመ ይኩን ስምዐ ላዕለ ኩሉ ጌጋይ ወበኩሉ አበሳ ዘአበሰ በአፈ ክሌቱ ወሠለስቱ ሰማዕት የሀልቅ ኩሉ ነገር"(ዘዳግም ፲፱፡፲፬)። በደለኛ ተብሎ የሚወቀስና የሚከሰስ ሰው ክሱ ባንድ ምስክር ብቻ አይረጋገጥ። ክሱ ወቀሳው በሁለት በሶስት የምስክር ድምጽ ይጽና።
o
፪ኛ፦ "ወእመሰ ኢሰምአከ ንሣዕ ምስሌከ በዳግም አሐደ አው ክልዔ ከመ በአፈ ክልኤ ወሠለስቱ ሰማእት ይቀውም ኩሉ ቃል" ማቴ ፲፰፡ ፲፮። ምከረው ካልሰማህ በሁለት ምስክር ነገር ይጸናልና በሁለት በሶስስት ምስክር ይዘህ ምከረው።ከዚያ በኋላ እንደ አረመኔ ቁጠረው።
o
፫ኛ፦ "አኮኑ በአፈ ክልዔቱ ወሠለሰቱ ሰማእት ይቀውም ኩሉ ነገር"(፪ቆር ፲፫፡፩) በሁለት በሶስት የምስክር ድምጽ ሁሉ ነገር የሚጸና አይደለምን?

በኦሪትበክርስቶስና በሐዋርያት ተደጋግሞ የተነገረ ይህ ትዕዛዝ በሀሰት ወይም በአድማ ጻድቁን ወይም ተገቢውን ሰው ለአገልግሎት ሲሰየም በምቀኝነት በተንኮል እንዳይበላሽ የተደረግ ጥንቃቄ ነው። "ይኩን በስምረተ ሕዝብ ዘይሰየም ላዕሌሆሙ። በህርየተ ኩሎሙ ህዝብ"(..) የሚለው ትእዛዝ በመመሪያችን የተመዘገበው ከኦሪት ከክርስቶስና ከሐዋርያት ትእዛዝ መንጭቶ ነው።
አሁን ሊሰየም በታቀደው ፓትርያርክ ምርጫ ላይ እየጎረፈ ያለው የተቃውሞ ድምጽ ብዛትእንድንለካባቸው ከላይ ከተገለጹት መስፈርቶች በላይ ነው። ይህን ተቃውሞ ሰብሮ የሚመጣውን መሳይ ፓትርያርክ መመሪያችን ምቱር (ጭንጋፍ) ይለዋል። ከዚህ በታች ከ፩ እስከ ፮ ተራ ቁጥር ምቱር ያደረጉትን (ያስጨነገፉትን) ማስረጃዎች በጥንቃቄ እንመልከታቸው፦
፩ኛ፦ በሞት ከተለዩን ሊቃውንቱ መካከል አንዱ በህይወት ያሉት ሊቀ ካህናት መራዊ ተበጀ "የቁጥር ዶክትሪን የለንም" ብለው በመጀመሪያ ተቃውሟቸው ከእነ አቶ ስብሀት በመወለድ ላይ ያለውን ምቱርነት በመግለጽ አስጨንገፈውታል።
፪ኛ፦ በአቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ የሚመራው የውስጡ ሲኖዶስ ለጤነኛ ፓትርያርክ አሰያየም ይመች ዘንድ ስምምነት እርቅና ሰላም እንዲቀድም አምኖበት ለእርቁ ድርድር አቡነ አትናቴዎስን፥ አቡነ ገሪማንና አቡነ ቀውስጦስን ወክሎ መላኩ ጭንጋፍ (ምቱር) አድርጎታል።
5

፫ኛ፦ በሁሉም ወገን ታምኖበት በነ ሊቀ ማእምራን አማረ የተመሰረተው አስታራቂ ቡድን መመስረቱና፤ ይህ ሳይቋጭ ለፓትርያርክ ምርጫ የተደረገውን ሩጫ የቡድኑ ተቃዉሞ አስጨንግፎታል።
፬ኛ፦ምርጫ ከምታሰቡ በፊት እርቀ ሰላሙ እንዲፈጸም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ያቀረቡት ጥሪም አስጨንግፎታል። (ዝርዝሩን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ)
፭ኛ፦ በአገር ውስጥና በውጭ ያለው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ሁሉ ከምርጫው በፊት እርቁ እንዲቀድም ያቀረቡት ጥያቄ አስጨንግፎታል።
፮ኛ፦የላካቸውን ሲኖዶስ እና የታላከውን ቡድን ወክለው አቡነ አትናቴዎስ በአሜሪካ ራዲዮ "የጀመርነው እርቅና ሰላሙ ከዳር ሳይደርስ ለፓትርያርክ ምርጫ የሚደረገውን ዝግጅት እንቃወማለን" በማለት ያሰሙት የተቃውሞ ጥሪ፤ ከዚህ በላይ የተደረደሩትን ፭ የምስክርነት ድምጽ ማሳረጊያና መደምደሚያ ሆኖ አስጨንግፈውታል ወይም (ምቱር)አድርጎታል።

ልንይዛቸውና ልንመራባቸው የሚገቡን ከዚህ በላይ ይተገለጹትን እንጅ ወደ ኢምባሲው ሄደው ለነአቶ ስብሀት ነጋ ፖለቲካ ጥቅም ታስቦ recalculated ተደርገው ከዚህ በታች የቀረቡትን አይደለም፦ ከዚህ በታች ከ፩ እስከ ፬ የተዘረዘሩት ምክንያቶችም ቢሆኑ እነ አቶ ስብሀት ነጋ ሊወልዱት በምጥ ያለውን ፓትርያርክ የበለጠ አስጨንግፈውታል ወይም (ምቱር)አድርጎታል።
ዋና ዋና ነጥቦችን እንመልከታቸው፦

o
፩ኛ፦ የአገሪቱ ፕሬዝደንት በግል ክርስትናቸውም ሆነ ፕሬዝደንታችው ቤተ ክርስቲያኒቱ ያቀፈችው ከ፵፩ ሚሊዮን ባለይ ነው የሚባለው ህዝብ የፈቀደውን ለማንጸባረቅ ባለባቸው ግዴታ፤ ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት ስምምነቱ እንዲፈጸም የሰጡትን የተቀደሰ ሀሳብ እንዲቀይሩ "የኢሀደግ ፈቃድ አይደለም" በማለት ከአቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ከአቡነ ናትናኤል የተሰነዘረባቸው ተግሳጽ ሸፍጥ በመሆኑ አስጨንግፎታል።
o
፪ኛ፦በቅርስነት ከምንመለከታቸው አባቶቻችን ከአቡነ አትናቴወስ ቃል ያፈነገጠ ወረቀት የሰላም ቡድኑ ከውጩ ሲኖዶስ ጋራ ወግኗል የሚል ቃል ንቡረ እድ ኤልያስ የተባሉት ሰው በአዛውንቶቹ አባቶች ስም ጽፈው ያሰራጩት ሽፍጥ አስጨንግፎታል።
o
፫ኛ፦ ከዚያም "ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሴች መስቀል አለባቸው" በማለት አቶ ስብሀት ነጋ የተናገሩት አረመኔዊ የስቅላት ፍርድ አስጨንግፎታል።

በነዚህ ሁሉ ውስብስቦች (complication) የሚወለደው ፓትርያርክ በገዛ እትብቱ ታንቆ በመጨንገፍ እንዲወለድ አድርጎታል። ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ነገሮች ተጨንግፎ የመጣውን ፓትርያርክ ቤተ ክርስቲያናችን እንዳንቀበለው ታዝዘናለችና መቀበል አይኖርብንም። ይህንም በጥንቃቄ አብረን እንመልከተው።
፫ኛ፦መቀበል አይኖርብንም።

ከዚህ በላይ በተገለጸው ትርምስና ግርግር ተመርጫለሁ ብሎ የሚመጣውን ፓትርያርክ ከ፩ እስከ ፮ ተራ ቁጥር ከዚህ በታች ተብራርተው የተገለጹት የቤተ ክርስቲያናችን መመሪያ እንዳንቀበለው በአጽንኦ ያስገነዝበናል። 6
፩ኛ፦ ቅዱስ ጴጥሮስ "ረዐዩዘሀሎ ኀቤክሙ መርዔቶ ለእግዚአብሄር እንዘ ተአቅብዎሙ ወኢትቅንይዎሙ በኩርህ አላ በጽድቅ በእንተ እግዚአብሔር እንዘ ኢትሬብህዎሙ አላ በምልአ ልብክሙ ወበትፍስህት፡ እንዘ ኢትትሄየሉ ሕዝቦ ለእግዚአብሄር አላ አርአያ ኩንዎሙ ለመርዔቱ" (፩ኛ ጴጥ ፭፡፪) ይህም ማለት፦ የእግዚአብሄርን ህዝብ በጥንቃቄ ምሩ። ምእመናን ሳይፈቅዱ በተጽእኖ አስገድዳችሁ ለመምራት አትሞክሩ" የሚለው ጥብቅ ትእዛዝ ነው። ሊቃውንት አበው፤ በአስረጅና በዓቢይ አገባብ እየታጀቡ ከሁለት ጊዜ በላይ ተደጋግመው የሚቀርቡ ትእዛዞች ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገባ ጥብቅ ትእዛዛት ናቸው ብለው አስተምረውናል። ከተቃወሱ ለጥገና የሚያስቸግር ሀውክ ይፈጠራል ይላሉ። እንዳሉትም በዚህ አረፍተ ነገር ለአጽንኦተ ትእዛዝ ተደጋግመው የተገለጹት በዓቢይ አገባብ አጎላማሽነት የቀረቡት፤ የካቲት ፳፩ ቀን በሚሰየመው የፓትርያርክ ሹመት ተጥሰዋል።
ሀ፦ አላ ረዐዩ………… በጽድቅ
ለ፦ አላ ረዐዩ…………በምልአ ልብክሙ ወበትፍስህት፡
ሐ፦ አላ ኩንዎሙ አርአያ…………ተብለው የተገለጹት ዓበይት ነገሮች በነ አቡነ እስጢፋኖስ አዋጅ ተጥሰዋል። በነ አቶ ስብሀት ነጋ ተመልምሎ የሚመጣው ፓትርያርክ በሐዲስ ኪዳን ትእዛዝ ላይ ተመስርተው በመመያችን ላይ ተገልጸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ትእዛዞች የጣሳቸውን እንመልከት።
፪ኛ፦ "ወይትነስኡ ላዕሌሁ በጽድቅ ወኢይህድግዎ ይትዐደው ሃበ አባግዐ ክርስቶስ"(.አ ፭ ቁ. ፻፹፭-) በሚለው አንቀጽ ከሌሎች አፍራሽ ትእዛዞች ጋራ ኢይኅድግዎ የሚለው ጥብቅ ትእዛዝ ሶስት ጊዜ ለአጽንኦተ ነገር ተደጋገመ።
ሀ፦ ኢይኅድግዎ፦ይትዐደው፤ መመሪያውን ጥሶ የሚመጣውን ምእመናን ችላ አይበሉት።

ለ፦ ኢይኅድግዎ፦ይንበር፤ በመንበሩ እንዲቀመጥ ምእመናን እድል አይስጡት

ሐ፦ ኢይኅድግዎ፦ ይትመየጥ፤ ካባረሩትም እንኳ በኋላ እንዳይመለስ ምእመናን በሩቅ ይጠብቁት
" ተብሎ በመደጋገም ተነገረ።
፫ኛ፦ "ለእመ ይትጋአዙ ሰብአ ሀገር አው አህጉር እስከ ይትከፈሉ ሃበ ፪ቱ ክፍል ወበዛቲ ምክንያት ተሠይመ ካልዕ ኤጲሲ ቆጶስ ለይሕትቱ ጥዩቀ በእንተ ዝንቱ። ወለእመኒ ኢረከቡ ለዕለ ቀዳማዊ ኤጲሲ ቆጶስ ዘይደሉ ለመቲሮቱ ለይንበር በመካኑ። ወእመሰ ረከቡ በላዕሌሁ ለይሲሙ በመካነ ዚአሁ ዘአልቦ ነውር ውስቴቱ ወለዝንቱ ያውግዝዎ"( ፭፡ ፻፸) አከራካሪ ነገር ተፈጥሮ ሰው ተከፋፍሎ ሳለ፤ የተነሳው ነገር መስመር ሳይዝ በግርግር ፓትርያርክ ቢሰየም ጉዳዩን በጥንቃቄ ይመርምሩት። በመጀመሪያው ሰው ላይ ምንም የእምነት ሕጸጽ ከሌበት ይመለስ። የሚለው ትእዛዝ ሳይቋጭ ቁጥሩ ከሶስት እጅ በላይ የሆነው ህዝብ እየተቃወመው የመጣውን ፓትርያርክ መቀበል የለብንም። "ወለእመኒ ኢረከቡ" እና "ወእመሰ ረከቡ" በሚሉ አበይት አገባቦች ታጅባ የቀረበችው "ረከቡ" የተባለቸው ግስ በነ አቶ ስብሀት ነጋ የስቅላት ፍርድ ማስፈራሪያ የምትታለፍ አይደለችም።
፬ኛ፦"ወለእመ ተራድአ በመኳንንተ ዝንቱ ዓለም፡ወተሠይመ ለቤተ ክርስቲያን እምሃቤሆሙ ይትመተር ወይሰደድ ውእቱኒ ወኩሎሙ እለ ተሳተፍዎ"(፻፸፭) ማለትም፦ በመንግስት ድጋፍ የተሰየመ ግለ ሰብ ጭንጋፍ ነው። በቦታው እንዲቀመጥ የተባበሩት ሰዎችም ህይወት የሌለውን ህይወት ያለው በማስመሰል የተባበሩ ናቸውና ጭንጋፎች (ምቱራን) ናቸው። "ይትመተር" ማለት፦ ይጨንገፍ ማለት ነው። "ይሰደድ" ማለት ደግሞ፤ ጭንጋፍ ሆኖ በተወለደ ህይወት አልባ ውራድ ላይ የሚፈጸመው ስርአት ይድረስበት ማለት ነው።
፭ኛ፦ "ዘተማኅጸነበእንተ ምግብናሁ ለሰብአ አፍአ አው በመኳንንተ ዓለም ይርድእዎ በእንተ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዘ የሀስስ በዝንቱ አኅስሮቶሙ ለሕዝበ እግዚአብሄር"(፻፸፰) በመንግስት ርዳታና አጋዥነት የገባ ፓትርያርክ ህዝበ እግዚአብሄርን ያወረደ ተጨንግፎ የመጣ ነው። ጭንጋፍ ሆኖ በተወለደ ህይወት አልባ ውራድ ላይ የሚፈጸመው ስርአት ይድረስበት ማለት ነው። 7
፮ኛ፦ "ይትመተር ዘይነስእ ሢመተ ክህነት በኅልያን፤ አው በተገርሞ፤ አው በአድለዎ ፤ አው በትምይንት፤ አው በአሰፈዎ ሕልያን (. አ ፮፡ ቁ፡ ፪፻፳፬)" ጥብቅ ትእዛዝ ያዘለችውን ይህችን ሐረግ እንተነትናት። የዚህች ሐረግ ማሰሪያ ግስ "ይትመተር" ናት። ማለትም ይጨንገፍ ማለት ሲሆን፡ የሚያስጨነግፉትም ምክንያቶች ከዚህ በታች የተደረደሩት ናቸው።
በህልያን……………………….በፍቅረ ሲመት የተበከለ ሕሊና
አው በተገርሞ………………….በምድራዊ ሥልጣን አስፈራሪነት የመጣ ፓትርያርክ
አው በአድለዎ………………….ሚዛኑን ሳያሟላ የመጣ
አው በትምይንት………………..በማን አለብኝ ስሜት የመጣ ፓትርያርክ
አው በአሰፈዎ ሕልያን…………..በመሞዳሞድ የመጣ ፓትርያርክ
ይህች ሀረግ ብቻ በየተሸከመችው የቤተ ክርስቲያናችን ትእዛዝ: እነ አቶ ስብሀት ነጋ የሚሰይሙትን ፓትርያርክ ተቀብለን ቅዱስ ብጹዕ ብለን በቅዳሴያችን ልናስታውሰው አይገባም።
"ወንህነኒ ሰበክነ ስመከ ልዕልተ ወክብርተ ውስተ ኩሎን አብያተ ክርስቲያናት ወውስተ ኩሎን አህጉር ወበሀውርት ወአዘዝነ ይዝክሩከ በኩሉ ቅዳሴያት"(.. ፻፬፡፲፫) ከሚለው ከኦርቶቶክሳዊው መርሆችን ጋራ ያጋጨናል። በዚህ አረፍተ ነገርበቅዳሴያችን ስሙን እንድናስታውሰው የታዘዝነው ቃሉን ሳይለዋወጥ፥ ሸቀጣ ሸቀጥ ሳይደባልቅ፥ ለነገረ መለኮቱ፥ ለሞራሉ፥ ለተየሰየመለት ዓላማ ጸንቶ ለቆመ፥ በእውቀቱ፥ በችሎታው፥ በታማኝነቱ ታምኖበት ያለአንዳች ተቃውሞ ለተመረጠ አባት ብቻ ነው።
ሊወለድ ነው እየተባለ የሚታወጅለት ይህን ግለ ሰብ ግን፤ በመንበሩ ላይ አጽናው ብለን በቅዳሴያችን ልናወሳው ይቅርና፤ "አርህቅ እግዚኦ እምኔየ። ወእምነ ኩሉ ህዝብከ። ወእምዝንቱ መካን ቅዱስ ዘዚአከ"(.. ገጽ ፴ ቁ ፴፰) እያልን ከፍ ባለ ድምጻችን ከግላችን፤ ካንድነታችንና ከተቀደሰው መንበራችን እንዲርቅ የምናውጅበት ምቱር ፓትርያርክ ነው።
ከኛ እንዲርቅ ይህን የምናውጀው ምቱር ሆኖ በመጣብን ፓትርያርክ ብቻም አይደለም። "ወእለ ሴሙ ላዕሆሙ መገብተ ከሐድያነ ንኬንኖሙ በግዘት በኩሉ መዋዕል"( ፻፩፡ ፳፫) ይህን ምቱር ፓትርያርክ በላያችን ላይ የጫኑብን እና በሀሳቡም የተስማሙት ሁሉ ምቱራን ጭምር ከኛ እንዲርቁልን ነው።
አያችሁ! ቅዳሴያችንን ብንመለከተው እኮ "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ለሚቀደሱት ለጸወርተ መንበሩ ሱራፌልና ኪሩቤ ቅዳሴ ተሰጥኦ ነው። ይህን ቅዳሴ በመቀደስ ተሰጥኦውን የምትመልሰዋ ቤተ ክርስቲያናችን "አናቅጽ ሲኦል ኢይሄይልዋ" የተባለችው ናት። ቅዳሴያችን እንደነ ስብሀት ነጋ የመሳሰሉ ነፍሰ ገዳዮች ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሾልከው የሚገቡበትን ጓዳ እየዘጋ፤ ክርስቶስ የከፈተውን በር እንድንመለከት የሚመራን ነው።
ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን የሰጠችንን ከኦሪቱ ጀምሮ በየእለት ስከምንጠቀምበት መጽሀፈ ቅዳሴያችን ላይ ያለውን ሊቃውንት አበው ያስተማሩንን ሳንለቅ ያተረጓጎማቸውን ስልት ሳንቀይርና ሳንደበላልቅ ቀጥ ብለን ብንሄድ በጓዳ በር ሾልኮ የሚገባውን እያስወጣን በበሩ የሚመጣውን ይደልዎ ብለን በመቀበል ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ከነ ስብሀት ነጋ ወጥመድ ማትረፍ ይቻላል። (የነ ፋሌቅ ወጥመድ የሚለውን ጦማር እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ)8
፬ኛ፦የተከፈተው በር  
በቅዱስ መጽሐፍ ላይ የተመሰረተው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን፤ ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ የተመሰረተችው ከተለያዩ ቦታወች ባህልና ቋንቋ ለተለመደው ዓመታዊ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም በተጓዘ ሰው።

ታሪኩ እንደሚነግረን፤ ከተለያዩ ቦታዎች በዓለ ጰራቅሊጦስን ለማክበር ኢየሩሳሌም ላይ የተሰበሰቡት ሰዎች ክርስትናን በራሳቸው ቋንቋ ሰምተው ቤተ ክርስቲያንን አዝለው ወደየ አገራቸው ለመመለስ አስበው አልነበረም። ሐዋርያትም ቢሆኑ ባንድ ቤት ተሰብስበው ዘግተው የነበሩት እንዳትበታተኑ ቆዩ የተባሉበትን ምሥጢር በሚገባ ተርደተውና ከተለያየ አካባቢ ለመጣው ሰው በየራሱ ቋንቋ ነግረን እንልካለን ብለው አስበው አልነበረም። ሆኖም እግዚአብሔር በመለኮታዊ እቅዱ ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ። ሐዋርያትንም ባልተረዱት መንገድ ኢየሩሳሌም እንዲቆዩ አደረገ። ሐዋርያት ዘግተው በተሰበሰቡበት ቤት ላይ ሰውን ሁሉ አንድ አርጎ የሚስብ እሳት መሳይ ኃይል አነደደ። ከሩቅ ቦታ የተሰበሰበው ህዝብ ሁሉ ይገናኝበት ዘንድ በፍርሀት የተዘጋውን ቤት ወደ አደባባይነት ለወጠው።

እንደዚሁ ሁሉ በዘመናችን እግዚአብሔር ተመሳሳይ ስራ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እየሰራ ነው። ቤተ ክርስቲያናችን በእርስ በርስ ጥላቻ ዝግ ነበረች። የውስጡም ሆነ የውጭ ሲኖዶስ ተስማምተው ችግሩን ሊፈቱት በሩን ሊከፍቱት ባለመቻላቸው ይልቁንም
"ወእመሰ በበይናቲክሙ ትትባልኡ ወትትናሰኩ ተኀልቆ ተርፈክሙ" (ገላ ፭፡፲፭) ከተባለው ደረጃ በመድረሳቸው፤ እነሱ ባላወቁት መንገድ በሰላሙ ቡድን መከሰት ላይ እግዚአብሔር እንዲስማሙ አደረጋቸው። በሰየሙት ቡድን አጋዥነት እንኳ ችግሩን መፍታት አልቻሉም። እንግዲህ ቢገባንና ብንረዳው እንድንጠቀምበት እግዚአብሄር በሰላሙ ቡድን በኩል ቤተ ክርስቲያናችንን ከነ አቶ ስብሀት ነጋ እንድናተርፋት በሩን አዘጋጅቷል። የሰላሙ ቡድን ይህን ረቂቅ ጥሪ ተረድቶና ተገንዝቦ ከእርቁ በፊት የፓትርያርክ ምርጫ እንዳይታሰብ ድምጽ ያሰሙትን ሁሉ ድርጅቶችን ታላላቅ ሊቃውንት ካህናትንና የተበታተነውን ህዝበ ክርስቲያን በማስተባበር ሃላፉነቱን ይወጣ ዘንድ ታሪካዊ ግዴታ ወድቆበታል።

፭ኛ፦ በሰላሙ ቡድን ላይ የወደቀው ታሪካዊ ግዴታ፦የሰላሙ ቡድን

"ዘይፈቅድ ይህንጽ ማኅፈደ ፡አኮኑ ይቀድም ይንበር ወየሀስብ ጻእጻአ እመ ዘየአክሎ ከመ ይሳርር መሰረቶ፡ እመ ስእነ ፈጽሞቶ ኩሎሙ እለ ርእይዎ ይእህዙ ወይሳለቁላእሌሁ (ሉቃስ ፲፬፡፳፰_)" የሚለውን የክርስቶስን ቃል መመሪያ አድርጎ ከሆነ: ከላይ ከ፩ እስከ ፬ የተዘረዘሩትን የቤተ ክርስቲያናችን መመሪያዎች ከመፈጸም አያፈገፍግም። ወደዚህ ተልእኮ ስትገቡም ይህን ግዴታ በመዘንጋት አይመስለኝም። ተልእኮው በቀላሉ ከፍጻሜ እንደማይደርስና መስዋዕትነት እንደሚጠይቅ ሳትረዱ ጀምራችሁት ከሆነ፤ አካባቢያችሁን የመቃኘት አቅም የሌላችህና ቤተ ክርስቲያናችን ያለችበትን ማእበል ሳትረዱ ዘላችሁ የገባችሁ፤ ወይም በሁለት ልብ ሆናችሁ ጀምራችሁታል ማለት ነው። "ሁለት ሀሳብ ላለው በመንገዱም የሚወላውል ሁሉ ከአምላክ ምንም የሚያገኘው ረድኤት የለም" (ያዕ ፩፡፰) የሚለውን ረስታችሁታል። ወይም በቀላሉ ቢሳካ የባለውለታነትን ውዳሴና የሚገኘውን ጥቅማ ጥቅም ለመሳተፍ፤ ሳይሳካ ቢቀር በቀውስ ላይ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ግድ ሳይኖራቻሁ፡ ለራሳችሁ ሰላማዊ ኑሮ ቅድሚያ 9
በመስጠት ከአጥፊው ቡድን ጋር ያላችሁን ወዳጅነት ቀጥላችሁ ከዚያም ከዚህም በሹመት በሽልማት ለመኖር የምትፈልጉ ያስመስልባችኋል።

ይህ ደግሞ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚጨነቀውን ህዝብ አጓጉቶ፤ ለድርድር የቀረቡትን የበለጠ አዋግቶ መሸሽ ስለሆነ፤ ቤተ ክርስቲያንን በደሏት ብለን ከምንወቅሳቸው ሰዎች የከፋ በደል ነው። ሊቃውንት አባቶች እናንተ በገባችሁበት ፈታኝ ሁኔታ ላይ ገብቶ አሸንፎ ለወጣው ጽኑዕ የቤተ ክርስቲያን ሰው መታሰቢያ ይሆንለት ዘንድ የተደረሰለትን ቅኔ ትምህርት እና አቅጣጫ የሚያሳይ ቅርስ ነውና ላስታውሳችሁ።
"
ክቡድ ቀርን ኤዎስጣቴዎስ፤ ዘበቆልከ ለነ በዘመነ ወንጌል ሐዲስ፤
እስመ ልበ አድባር ከደነ፡ ኃይለ ሃይማኖትከ ጢስ።

አመ ዕድወትከ ቀላየ በየብስ።

እምቅቡአነ ዘይት መንፈስ ቅዱስ፤ ዘይትባየጸከ መኑ በፍኖተ ሞገድ ግብረ ነፋስ።

እመኒ ተባየጽከ በዕድወተ ዓባይ ተርሴስ፤

በበትር ወሐሜላት፤ ሙሴ ወኤልያስ፤

በመንግስተ ሰማይ ዛህን በገነተ ሄኖክ መርስ፤

አልቦ ዘየዓብዮ ለአጽፍከ ዮሐንስ
"
ይህ ቅኔ ከገባችሁ ማንም ሳይጠይቃችሁ የናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ሁኔታ አስገድዷችሁ በፈቃዳችሁ መንቀሳቀስ የጀመራችሁትን ቀርቶ ሙታንን ከመቃብር የሚቀሰቅስ ነው። "
ብዙወች ነበሩ አገር ያፈራቸው፤
ዳሩ ምን ይሆናል ሞት ነው ያጠቃቸው" የሚለው ቅኔ በድምጻዊቷ ጉሮሮ በኩል ለመላ ኢትዮጵያውያን እንዲደርስ ያደረጉት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ናቸው።
"ክረምት ባይመጣ ሁሉ ቤት።
እንግዳ ባይመጣ ሁሉ ሴት" የሚባለው ባህላዊ አባባልም አለን። በሰላም ጊዜ ሁሉ አዋቂ፡ ሁሉ ጀግና ነው። አፋችንን የፈታንበት፤ ዛሬም የምንደግመው ዳዊት "ኩሉ ጻድቅ በጊዜ ርቱዕ" የሚለው ከባህላዊው አባባላችን ጋራ የሚስማማ ነው። ባህላውያን አባባሎቻችንም ሆኑ የሊቃውንት አባቶቻችን ቅኔዎች የመነጩት የቅኔ መጻሕፍት ከሚባሉት ቅዱሳት መጻሕት ነው።
አገር በሽብርተኞች ስትናወጽ ዜጋ የሆነ ሁሉ ራሱን ለመከላከልም ሆነ አገርን ለማረጋጋት በሚደረገው ፍልሚያ ለመሳተፍ በደህና ጊዜ ያስቀመጠውን መሳሪያ ከያለበት እየፈለገ እንደሚወለውል፤ እኛም የእምነት የሞራልና የቁርጥ ታማኝነት ምንጮች የሆኑት ሊቃውንት አባቶቻችን ያስቀመጡልን ቅኔዎች ራሳችንን የምንመዝንባቸው አካባቢያችንንም የምንፈትሽባቸው ናቸውና በዚህ ጊዜ ልንዳስሳቸው ይገባል።

የአባቶቻችን ቅኔዎች መሠረታቸው የቅኔ መጻሕፍት ተብለው የሚጠሩት ቅዱሳት መጻሕት ናቸው ብያለሁና፥ ጥቂቶችን ከጥቂት መጻሕፍቶች ልጥቀስ።
"
በሊዓ ብዙህ መዓር አኮ ሠናይ ወየሀምግ ከርሰ፡ ወየኃይል ለረቅይ" (ምሳ ፳፭፡ ፳፯) ይህም ማለት "የሚጣፍጥ ማር አብዝቶ መብላት ጥሩ አይደለም። ሆድ ይነፋል። በመጨረሻም ያስታውካል" አንገትን እያቅለሰለሱ ያለቦታውና ያለተገቢው ትህትና በመስጠት ባለስልጣንን መቅረብ ረብ የሌለው ጥቅም ፍለጋ ነው። በዚህ መንገድ የሚገኘው ሹመትና ሽልማት ያውርዳል። ከመካከላችሁ ይህ መሳይ ባህርይ ያለው ሰው ካለ ቆልምሞ በመውሰድ ይዟችሁ ገደል እንዳይገባ ተጠንቀቁ! 10
የሰላም ልኡክ ብላችሁ በፈጠራችሁት ድርጅታችሁ በጨለመበት ጊዜ ብቅ በማለታችሁ ዘላቂ ቁም ነገር ትሰራላችሁ በማለት ከነ ስብሀት ነጋ በቀር ሁሉም ደስ ብሎት ተቀብሏችኋል። ሁሉም አሁን በገባበት አረንቋ ሲዘፈቅ ድምጻችሁ በመጥፋቱ፤ ከናንተ ጋራ የቆመው ህዝብ "መኑ የአምር ከመ ትጠፋዕ በከዊነ ተነ ጊሜ" (መቃ ፱፡፱-) ማለትም፦ ፍለጋው እንደማይገኝ እንደ ጉም ሽንት ተኖ ጠፍቶ እንደሆነስ ምን እናውቃለን? እየተባባለ ነው።
ሽባና ተልካሻ ከሆነ ከዘር ከጎሳና ከክፍለ ሀገር ከጥቅማ ጥቅም በሽታ ተላቃችሁ፡ ራሳችሁን ካሉባልታ አግልላችሁ "ብእሲሰ ጠቢብ ያፈቅር ሰሚአ መጻሕፍት። ወዘሰ ይናፍቅ ወኢይትአመን በመጽሐፍ ይከውን ከመ ሐመር እንተ ታንኮልል መእከለ ዐውሎ" (ሲራ. ፴፮፡ ፪) የሚለውን ምክር ተከተሉ። ማለትም፦ አዋቂ ሰው ከመጻህፍት በሚያገኘው ጥበብ ይመራል። አላዋቂ ሰነፍ ሰው ግን ባሉባልታ ይደናበራል። በራሱ ጸንቶ መቆም ያቅተዋል። በነፋስ እንደሚናወጽ መርከብ ይዋዥቃል" በሚለው በጥበበኛው ሲራክ ሚዛን ራሳችሁን መዝኑ!
"ብእሲ ምሁር ዘተገሰጸ ብዙሀ የአምር ወዘአፈድፈደ ጥበበ ይነግር" (ሲራ ፴፩፡፱) የሚለውን በመመልከት ብቻችሁን እንወጣወለን ብላችሁ አትሞክሩ። ከናንተ ይልቅ በልምድ በአመክሮ የበሰሉትን ሊቃውንት አሰባስቡ!
የምትከተሉት የቀኖና፥ የሞራል፥ የህግና የነገረ መለኮት ጉዳይ ስለሆነ "ሁለት ልብ ሆናችሁ ወደ ህግ አትቅረቡ (ሄኖክ ፴፬፡ ፱) የሚለውን ምክር አትርሱ። ሁሉም አሁን በገባበት አረንቋ ሲዘፈቅ ድምጻችሁ በመጥፋቱ፤ ከናንተ ጋራ የቆመው ህዝብ "መኑ የአምር ከመ ትጠፋዕ በከዊነ ተነ ጊሜ" (መቃ ፱፡፱-) ማለትም፦ ፍለጋው እንደማይገኝ እንደ ጉም ሽንት ተኖ ጠፍቶ እንደሆነስ ምን እናውቃለን? እየተባባለ መሆኑን እያሳሰብኳችሁ እሰናበታችኋለሁ። ይህን በመሰለ ፈታኝ ዘመን ላይ ቤተ ክርስቲያን ስትወድቅ፥ ህዝበ ክርስቲያኑ ሀላፊነቱን እንዴት እንደሚወጣ በመመሪያች ተጽፎ የተቀመጠውን በሚቀጥለው ጦማር አቀርባለሁ።