Saturday, March 24, 2012

Call for unity by International Ethopian Women Organization Washington D.C.

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ለማርች 24 ከቀኑ 12ፒም እስከ 4ፒም ድረስ፣ በአገራችን ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ለተግባራዊ መፍትሄ ልዩ ትኩረት ሚሰጥ የውይይት መድረክ አዘጋጅተናል።

     ዛሬ  የኢትዮጵያውያን ሴቶች የሚገኙበት አሰቃቂና አሳፋሪ ሁኔታ የአገራችን ተጨባጭ ገፅታ ነጸብራቅ ነው።  ስለሆነም፣ የኢትዮጵያውያን ሴቶች ብሶት የአገር ጉዳይ መሆኑን በመገንዝብ የቁርጥ ቀን ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ
ልዩ ዝግጅት ላይ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን።
 
 ቦታው፣ 1610 ኮሎምቢያ ሮድ ዋሽንግተን ድሲ  ኖርዝዌስት።
ቀኑና ጊዜው በድጋሜ ማርች 24 በዚህ አገር አቆጣጠር  ከ12ፒም እስከ 4ፒም ድረስ።
                 
                 የኢትዮጵያ ክብር በጀግኖች ልጆቿ ይከበራል።
                ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
                ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት።