Tuesday, March 27, 2012

"የኢትዮጵያ እስፓርት ፈደሬሽን በሰሜን አሜሪካ የእኛ ነው" አለ ሕዝቡ።



"የኢትዮጵያ እስፓርት ፈደሬሽን በሰሜን አሜሪካ ፣ ኢትዮጵያዊነትን፣ በሃላችንን አክብሮ የማስከበሪያ እና የአንድነታችን ዩንቨርስቲ ነው" የሐረርወርቅ ጋሻው።

March 25, 2012 , Doubletree Hote በሪቻርድሰን ቴክሳስ ፣ በኢትዮጵያ የእስፓርት ፈደሬሽን በሰሜን አሜርካ እና በሁለቱም በክተማችን በሚገኙት አንጋፋ የእስፓርት ቡድኖች ማለትም የዚህ አመቱ በዓል ዋና አዘጋጆች እና ተጠሪዎች በዳላስ ፎርት ውርዝ፣ በአዲስ እና በኢትዮ ዳላስ የተጠራው ስብሰባ ከቦታው ከተገኘው ከሕብረተሰቡ ትልቅ ድጋፍ አግኝትዋል። ይሄውም አብራሩልኝ በማያሰኝ መንገድ በቦታው የተገኘው ሕዝብ የሃያ ዘጠንኛውን በአል እና የእስፓርት ፈደሬሽኑን አስመልክቶ ሁለቱን ቡድን ሃላፊነት ላይ ጥሎ የሚያይ ሳይሆን ወደ አርባሽህ የሚሆነው የከተማው ንዋሪ እና የመላው ኢትዮጵያዊም ጉዳይ መሆኑን ጭምር ተሰብሳቢው እራሱ ባደረገው ንግግር አረጋግጥዋል።
የስብሰባው ዋና ዓላማ ያተኮረው እና የተዘጋጀው በዚህ አመት በዳላስ ቴክሳስ ስለሚደረገው የሃያ ዘጠንኛው አመት የእስፓርት ዝግጅትን በዓል አስመልክቶ ሲሆን፣ ከሕብረተሰቡ ገንቢ ሃሳብ ለመውሰድ፡ ሕብረተሰቡንም ያለምንም ልዩነት ተሳታፊ እንዲሆን እና ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ለሚመጣ ህሉ ያለምንም ልዩነት የፈደሬሽኑ በር ክፍት መሆኑን በተጨባጭ ለማረጋገጥ ለማሳወቅ ነው።
የእስፓርት ፈደሬሽኑ ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ተስፋዬም የሕዝቡ ትብብር ከመቼውም የበለጠ አስፈላጊ እንደሆነ እና ይሄ ብቸኛው እና ግዙፍ "የኢትዮጵያ እስፓርት ፈደሬሽን በሰሜን አሜሪካ" ያዘለው ስም ከእነ ልዩ ምልክቱ አርማው ጭምር የግለሰቦች ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብት በመሆኑ ሁላችንም ልንከባከበው እና ልንጠብቀው ልናከብረውም እንደሚያስፈልግ ጭምር አሳስበዋል። በሌላ በኩል፣ ከመቼውም የበለጠ ሕዝቡን የፈደሬሽኑም የበአሉም ባለቤት ለማድረግ የፈደሬሽኑ የአመራር ቦርድ ቆርጦ በአንድ ልብ መነሳቱን እና ወደ ሁዋላም እንደማይል አቶ ጌታቸው ተስፋዬ በተለያየ ቦታ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሰጡት ሁሉ በእሁዱም ስብሰባ ካሉበት በእስካይፕ ተመሳሳይ መልክት ለተሰበሰበው ሕዝብ ግልጽ አድርገው ተናግረዋል። ሲደመድሙም በጉርሻ መልክ በሚሚጣ ገንዘብ እና አብሮት ከሚጎሰመው የሰውን ልጅ ክብር ከሚነካ የገንዘብ ስጦታ (ጎመን በጤና) ይልቅ በሃቅ በራሱ ከሕዝቡ ከሚገባው ገቢ እና አስተዋጽዎ የሚዘጋጀው የእስፓርት ዝግጅት በዓል የኢትዮጵያዊነትን ክብር አልቆ የሚያሳይ መሆኑንም አስጨብጠዋል። የእስፓርት ፈደሬሽኑ ከፓለቲካ፡ ከግል ጥቅም ከማንኛውም ሃይማኖት እና የጾታ ልዩነትን በሚከለክለው ሕግ ታዋቂነትን ያገኘ በመሆኑ ፈደሬሽኑ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት ነውም ብለዋል። እሳቸውም እንደሚታወቀው ምንም እንክዋን በፓለቲካው መድረክ ተሰማርተው የማይታወቁ ቢሆኑም የአገራቸውን እና የወገናቸውን መቀራረብ አንድነቱን ሽቦ በእስፓርት መድረክ ሲንከባከቡት እና አሁንም ቀጥለውበት እነሆ የእስፓርት ፈደሬሽኑ ሊቀመንበር ሊሆኑ ችለዋል። ከትልቁ ምስክር አንዱ በዚህ መልክ ለአገራቸው እና ለሕዝቡ ስላደረጉት አስተዋጽዎ በእስፓርት ፈደሬሽኑ ውስጥ የነበሩ አንዱን ቡድን ባዳ ሌላውን ወንድም በማድረግ ለሃያኛው በአሉ በሂውስተን በተደረገው ብዙሃኑ ተሰብስቦ ኢትዮጵያ ሲል፡ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የድግስ ሽታ እና የጭፈራ አዳማጭ አድርገውት በነበረ ጊዜ ቡድን ተብሎ እንዳይመዘገብ በፈደሬሽኑ ተደርጎ በነበረ ጊዜ ከዲሲ እና አካባቢው፣ አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ነበሩ ታግለው በዓሉ ካለፈም ቢሆን ቡድኑ ወደ ፈደሬሽኑ ያስገቡት እና ሰላም የፈጠሩት። እንግዲህ በፓለቲካው መድረክ የአገሩን ጉዳይ አስመልክቶ ሲሳተፍ ሌላው ደግሞ በእስፓርት መልክ አስተዋጽዎ ያደርጋል ማለት ነው።
በቦታው በስብሰባው የተገኙት የእስፓርት ፈደሬሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ልጅ አብይ ኑርልኝ፡ በቦታው ለተገኘው ሕዝብ በፈደሬሽኑ ላይ በግለሰብ አማካኝነት ማለትም ከዋሽንግተን ዲሲ የሚፈጸመው ሕገ ወጥ ስራን አስመልክቶ ሕብረተሰቡ በግልጽ እንዲያውቀው በሚገባ ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር በተቀነባበረ ገለጻ አቅርበዋል።
በሚቀጥለው ስለ እስፓርት ፈደሬሽኑ ታሪክ ፡ ስሙ እና አርማው የሕዝብ ስለሆነ በሕግ ያስጠይቃል፡እና የዳልስ ፎርት ውርዝ ንዋሪ ለፈደሬሽኑ ስላደረገው ብቸኛው እና ግዙፍ አስተዋጽዎ ፡ አቶ ጌታቸው ተስፋዬ እና በእስፓርት ስም ለወገናቸው የሰጡት አገልግሎት በሚል አርእስት እስክንገናኝ ደረስ ሰሙኑን አማላክ በሰላም በያለንበት ሁላችንን ይጠብቀን። አሜን!!!

ESFNA,gatway to all Ethiopians!