Saturday, February 11, 2012

To free Ethiopian Christians from Saudi Arabia Prison.

Ethiopian National Government In Exile.


አጭር መግለጫ።
Dallas, Texas.

ይድረስ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ።

ከጃንዋሪ ጀምሮ በሳውዲ አረቢያ ክርስትናን በማምለካቸው የታሰሩት ኢትዮጵያውያን መብት ለማስጠበቅ ያስችል ዘንድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስዴት መንግሥት ዋና መቀመጫው ዳላስ ቴክስሳ በኢንተርናሽናል ደረጃ ታሳሪዎቹን ለማስለቀቅ ሃያ ምስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ታዋቂ ድርጅቶችን እና የተለያዩ መንግስታትን አሜሪካንን የጨመረ ትብብር በጠየቀው መሰረት የታስሪ ክርስቲያኖች ኢትዮጵያውያን ወገኖች ጉዳይ እየተስተጋባ ነው። በዲፕሎማቲክ ሕብርተሰብ መንግስታቸውን ወክለው ከሳውዲ መንግስት ጋር በመነጋገር ትብብራቸውን ያሳዩ ብዙ ናቸው። ይህ በግለሰቦች ጥረት ብቻ እግቡ የሚደርስ ሳይሆን ትልቅ የዲፕሎማሲ እና ታዋቂ የሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎችን የሚጠይቅ በመሆኖ በተለያ ዘርፍ ያለን ግንኙነት እየረዳን ነው። የሚተባበሩን ከከተሞች እና አገሮች መሃል፡ ዳላስ ቴክሳስ፡ ሂውስተን፡ አትላንታ፡ ሰልማ አለባማ፡ ኒዮርክ፡ ዋሽንግተን ዲሲ፡ ካሊፎርኒያ፡ አፍሪካ ፓሪስ ፍራንስ፡ ኢንግላንድ፡ ጣሊያን ፡ ጀርመን፡ ራሻ፡ ቱርክ፡ ይገኙበታል።

የሐረርወርቅ ጋሻው
ሊቀመንበር።