Tuesday, May 9, 2017

The Amara Ethnic And Its monumental Contributions To Ethiopia's Development From Muels to Jets

የአማራው ብሔር በኢትዮጵያዊነቱ በአህያ ተመፈናጣጥ አውጥቶን የጄት አብራሪ እና የአይር መንገድ ባለቤት አድርጎናል።

የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው።(Yeharerwerk Gashaw)
May 7, 2017

ከዚህ በታች በማስቀምጠው የፊደል ስህተት ሊኖረው ስለምችል ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየኩኝ ለሚቀጥለው ጊዜ ያለ ስህተት ለመጻፍ እጥራለሁ።

ይድረስ ለመላው የኢትዮጵያ ወጣቱ ትውልድ።

አትታለል። አማራው አልበደለህም አማራው የተቋቋመውን አውሮፓዊ እና ዝርያውን አምላክ አድርጎ ሊያጠፋህ በገንዘብ ተገዝቶ በብሔር እየከፋፈልህ ያለው የብሔር ነፃ አዎጭው እንጂ። የሱልጆች ተንደላቀው ባንተ ደም አጥንት እና ሕይወት በእንግሊዝ፡  ኦክስ ፎርድ በአሜሪካን ሳይቀር ተምሮ ብዙም ሃብት ተጉዞለት በእየባንኩ ስለተቀመጠለት መከራን እረሃብ እና ጥማት መታረዝ አይደልም ችግር የሚባል እንዳያየው በዶላር ተጠቅልሎ ይገኛል። አማራ ኦሮሞ ጉራጌ ትግሬ አፋር ጋምቤላ ወላይታ አኑክ፡ ዶርዜ ከምባታ አዲያ እናም ሌላውም ብሔር ነኝ እያልክ እርስህን ሳታታልል "ኢትዮጵያዊ ነኝ" ብለህ ተሰባሰብ ተደላደል አንድ ሁን። አንድ ሆነህ በኢትዮጵያዊነትህ ከዳር እከዳር ኢትዮጵያን በቁጥጥርህ ስር አግባት የብሔርን አጥር ክልል ብጥስጥሱን አውጥተህ አቃጥለው።

ከዚህ በታች የሚታዩት ፎቶግራፎች የተወሰዱት በእጄ ከሚገኘው 1990 የኢትዮጵያን የአይር መንገድ በይፋ እንድጎበኝ በተደረገ ጊዜ ከየኢትዮጵያ የአይር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ካፕቴን መሃመድ በይፋ በአይር መንገዱ ስም ካበረከቱልኝ ስጦታዎች መሃል ከአንዱ መጽሃፍ ነው። አላማውም የኢትዮጵያ የአይረ መንገድን ባገኘሁት መድረክ ሁሉ ታሪኩን በኩራት እንዳስተዋውቅ ነበር።

የኢትዮጵያ አይር መንገድ የመጀመርያው የአፍሪካ ተወላጆች አይር መንገድ።











የመጀመርያው አፍሪካዊ አብራሪ ካፕቴን
 አለማየሁ


እዚህ ፎቶግራፍ ላይ የሚታየቱት አማራው የብሔር ልዩነት ሳያደርግ እንደውም ታሪክ እንዳስቀመጠው የትምህርቱ እድል ከተሰጣቸው ነት ሲታይ በብዛት አማራው ሳይሆን ሌላውን ብሔር ነበር እድል በመስጠት ቅድሚያ ተጠቃሚ ያደረገው ትግሪኛ ተናጋሪውን ጭምር ነበር ከባሕር መላሽ (ኤርትራን)አካቶ።

ከእኛ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አልፎ ተርፎ የአማራው ማንቃት እና ጥረቱ ሌሎቹን የአፍሪካ ትወላጆች ለምሳሌ እንደ ካሜሩን ኤር (ካሜር) ጋና ኤርወይስ ኬኒያ ኤርወይስ እና ናይጄሪያ ኤርወይስ በጊዜው ሌሎቹንም የጄት አብራሪ አድርጓቸዋል። እነ ካፕቴን ቤሎ ካሜር አዲስ አበባ የነበሩ የካምሩን ዲፕሎማቲክ ልጆች የካሜሩን አይር መንገድ ድንቅ ካፕቴኖች የኢትዮጵያ የአይር መንገድ ውጤቶች ናቸው። የኒልሰን ማንዴላም ኩራት ይሄው አይርመንገዳችን እና አብራሪዎቹ መሆናቸውን መዘንጋት አይኖርብንም። ማንዴላም ወደ ኢትዮጵያ መጀመርያ የገቡት በኢትዮጵያ የአይር መንገድ እና በኢትዮጵያውያን ካፕቴን እና ኮፓይለት በመንገደኛ ኤርፕሌን ከለንደን አዲስ አበባ አብርረዋቸው መሆኑ እዚህ ላይ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ማራው ኩራትን እና እራስን ቀና አድርጎ መሄድን እንጂ ያስተማረው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዝቅተኛነትን አላስተማረውም። ወንጀል የለበትም። ወነጀለኛ ወያኔ ብቻ ነው። አማራው ያስተማረው ዛሬ የነጮች ተላላኪ የሆነው ወያኔ ትልቅነትን ነበር አማራው ያስተማረው።

ሃቅ እና ውለታ በክህደት ሊጠፋ አይችልም። አማራው አንድም ቀን ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን በድሎ አያውቅም። ወነጀሉ ሕዝቡን ከኋላ ቀርነት እንዲወጣ ባጭር ጊዜ ጥረት አድርጎ ከጦርነት ማግስት ኢትዮጵያን የማልማት ሕልሙን በአጤ ምኒልክ መንግስት ግዜ እንደጀመረው ትምህርት ቤት በመክፈት እና ባቡር በማስገባት ትልቅ ልማትን ባቡሩ በሚያልፍበት ቦታ አካባቢ እና ከተማ ሁሉ እንዳስፋፋው በአጤ ኃይለስላሴም ጊዜ በተመሳሳይ ጣሊያን አባሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙም ሳይቆይ ወዲያው ወደ የትምህርት ገበታ ተመጋቢ ነው ያደረጉት። አማራው ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብሔር የማይስተካከል ትልቅ እድገትን ለኢትዮጵያ እና ለመላው ሕዝቧ አጎናጽፍዋል ለዚሁም በተግባር ያዋላችው ያለምንም የብሔር ልዩነት ብሎም የሃይማኖት እና ቋንቋ አስተዋጽዖ ተመዝግቦ ከሚገኘው ማየት ይቻላል ሃቅ ነው። እስከዛሬ ድረስ ያሉት ኢትዮጵያውያን 90 አመት እና ከዛም በታች ፊደል የቆጠሩት በአማራው ጥረት እና እየለመናቸው እያነቃ በማስተማሩ ነው እያባባለ ያውም። ጎቦ እየሰጠ ያስተማረው ብዙነው። ሕዝብን እናቱ እና አባቱ ሳያስተምሩት በግ እና ፍየል በሬ እና ላም ዶሮ እና ግመል ብሎም ፈረስ አግድ እየተባለ የሚደብቁትን ነበር ወደ ትምህርት ገበታ በማቅረብ በቀን ሶስት አራት ጊዜ እየበላ እና እየጸዳም ጭምር ጤንነቱን በማንከባከብ ተምሮ ለራሱ እና ለቤተሰቡ ደራሽ የተደረገው። ለዚህ ምስክሩ እራሱ በዘመናዊ ትምህርት እውቀትን የቀሰመው ነው። የአማራው ውለታ ብዙ ሆኖ እያለ ወደ ኋላ አስቀረን እራሱን ብቻ ጠቅሞ በሚል ተኪስ የወጣ የጠላት ዘመቻ ማለት የነጩን ማንጸባረቁ ለግል ጥቅም የእራስን ቲንሽነት እንጂ የአማራውን ትልቅነት ምንም አይቀንሰውም።

እያንዳንዱ አገር ውስጥ አልሚ ብሄር ወይም ብሄሮች እና መሪዎቻቸው ባደረጉት የልማት አስተዋጽዖ ይታወቃሉ። አማራው ሌላውን ትቼ ለዛሬ የተነሳሁበት ላይ ብቻ ባተኩር ዘመናዊ እውቀትን እንደ ዶርዜው የጥበብ የሃገር ልብስ ባለቤት ሲያደርገን እንደኖረው፡ ጥበብን በኢትዮጵያዊነታችን የደም ስር የወጋን ባለውለታችን ነው። በመሆኑም ዛሬ በኢትዮጵያ አገራችን ትልቅ የእውቀት ጥበብን በደማችን መጀመርያ ስለወጋን ስለአማራው እና  አመራሩ ባለውለታነት በማስቀመጥ ስለሌሎቹም ቀጥዬ በተከታታይ ከአማራው ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን አገራቸውን ስላለሟት በግልጽ በማስረጃ ጭምር በማቅረብ ነፃ አውጪነን በሚል ለወጣቱ ትውልድ ውሸት እያጎረሱት ግራ ላጋቡት ወጣት ኢትዮጵያዊ መነሻ መረጃ ይሆነው ዘንድ፡ እያንዳንዱን በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ኢትዮጵያዊ ተብሎ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ የሚያደርጋትን የተለያየ ባሕል እና ቋንቋ አንድነት ድምር ባለቤት በአንድነት እና በግሉ ለአገሩ ኢትዮጵያ ያበረከተውን የልማት እና ንቃት አዳዲስ ስልጣኔ እና ነባሩን በማገናዘብ ለወጣቱ ትውልድ አካፍላለሁ።
 አሜሪካንን ብንወሰድ ዛሬ አሜሪካን እያበደረች እንጂ በነጻ ትምህርት አትሰጠም በዩንቨርስቲዎችዋ ለዜጎችዋ አትሰጠም። ለእኔ እንጂ ለእኛ የሚል መሪ እና የመንግስት አስተዳደር ባለመሆኑ በአሜሪካን ያለው ተማሪው ጎበዝ እንኳን ቢሆን አብዛኛው ተማሪ በባችለር ደረጃ ያቆማል ትምህርቱን በገንዘብ ችግር እና እዳ ላለማብዛት በማሰብ። ጥቂቱ የነፃ ትምህርት በጣም ጎበዝ ስለሆነብቻ ተብሎ ቢሰጠውም ስኮላርሽፕ ሃቁ ግን አብዛኛው አሜሪካን መማር እየቻለ እንዳይማር ይደረጋል።

ኢትዮጵያ ግን "እኛ" በሚል የሚያምኑ ማለትም እኛ ኢትዮጵያውያን በሚል ለኢትዮጵያውያን የሚያስበው የአማራው አመራር መጀመርያ የፊደል ትምህርት አስፋፍቶ ሴቱንም ወንዱንም በማስተማር ከዛም ዘመናዊ የትምህርት ቤት በመስራት ገና ከጣሊያን ጦርነት እና ቁስል ሳያገግም ወገኑ ከሁሉም አብራክ ኢትዮጵያዊ የተወለደውን ወጣት በጊዜው ከአውሮፓውያን እኩል ለማስቀመጥ በጥበብ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃን ትምህርት ቤት በመክፈት እያስተማረ ቀጥሎም ብዙም ሳይቆይ የኮሌጆች እና የዩንቨርስቲዎች ባለቤት አደረገው ወጣቱን እና ኢትዮጵያን ሐገሩን። ይሄንን አይነት አስተዋጽዎ ለማበርከት እና ለማልማት አገርን እና የሕዝቧን አይምሮ ፡ለ"እኛ" የሚል የኢትዮጵያዊነትን ደም የተወጋ መሪ እና ሕዝብ ያስፈልጋል። በመሆኑም ጥቂቶቹን በስም ለማስቅመጥ አማራው ይሄንን በተግባር በማስረጃ አስረክቧል ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ። ለመጥቀስ ያህል በጥቂቱ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ፡ አዲስ አበባ። የሕንጻ ኮሌጅ አዲስ አበባ። ተግባረ እድ አዲስ አበባ፡ የመከላከያ ትምህርት ቤቶችን አስመክቲ ደግሞ የፓሊስ አባዲና ኮሌጅ አዲስ አበባ። የሐረር የጦር አካዳሚ ሐረር። ሆለታ የጦር ትምህርት ቤት ሆለታ።
የጅማ ዩንቨርስቲ፡ ጂማ። የባህር ዳር ዩንቨርስቲ፡ ባህር ዳር። አስመራ ዩንቨርሲትይ በግሪጎሪያን አቆጣጠር 1958 አስመራ ኤርትራ። አሁን ግን ኢሳይያስ በውስጥ በተፈጠረው የፓለቲካ ቀውስ የዘጋው ማለት ነው። እንግዲህ በአማራው አመራር ዘመን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ አስተምሯል። ይሄውም ኢሳይያስ አፈወርቅን ለገሰ ዜናዊን እና ሌንጮ ለታ በሚል የሚታወቀው ውነተኛ ስሙ ዮሐንስን።

ኢትዮጵያ በሃቀኛ ልጆችዋ ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!
ከአክብሮት ጋር ፡ የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው።
ዘብሄረ አንድ ኢትዮጵያ።

ከዚህ በታች ያለውን በጎግል የምታገኙት መረጃ ነው።
Historical Background
Jimma University College of Agriculture and Veterinary Medicine (JUCAVM) was established in 1952 as Jimma Agricultural Technical School (JATS) following the agreement signed between the United States of America and the Imperial Ethiopian Government under the joint affiliation of Ethiopian Ministry of Education (MoE) and the Oklahoma State University (former Oklahoma Agricultural and Mechanical College) for the period between 1952 and 1956. From 1956 to 1968, the school was jointly administered under the Ethiopian Ministry of Agriculture (MoA) and the Oklahoma State University. Following the termination of the agreement with the Oklahoma State University, the school was under the exclusive administration of the Ethiopian MoA for the period 1968 to 1979 and it was renamed as Jimma Institute of Agriculture (JIA). From 1979 to 1990, the institute was under the administration of Commission for Higher Education and the naming was once again tailored to Jimma Junior College of Agriculture (JJCA).

ባሕር ዳር ዩንቨርስትይ፡ በግሪጎሪያን አቆጣጠር 1963 ጀምሮ። http://www.bdu.edu.et/