Saturday, December 27, 2014

ለኔ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ናቸው። ለእርሶስ? በየኢትዮጵያወርቅ ጋሻው (የሐረርወርቅ)

"ከዚህ በታች ያስቀመጥኩት የልጅነት ትዝታዬና እድገቴ ለአገሬ አንድነት የማይነቃነቀውን ፍቅሬን ላስረከበኝ ለጠላቱ የተቆጣ አንበሳ፡ ለወዳጁ እሩህሩህና የፍቅር ምግብ ለነበረው ለመላው ለቀድሞ የኢትዮጵያ ጦርሃይሎችና ቤተሰቡ የክብር ማስታወሻ ነው። ታሪክህ እየለመለመ ገና ገና ያንተን አርማ አንስቶ ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን የሚያስቀድም አሁን እራሱን ይፈጣርል"  

ነገ ዛሬ ስል በዚህ መልኩ አካፍላችሁዋለው ያልኩዋችሁ ሁሉ የአምላክ ፍቃዱ በመሆኑ ይሄው ቃለን ጠብቄአለሁ። ምስጋናዬ ለሱ ለፈጠረን ለየሱስ ክርስቶስ ነው አሜን።
 ስታነቡ ምናልባት የፊደል ስህተት ብታዬ ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ። 

የመጀመሪያው አርአያዬ በስቅላት የተቀጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በምድር ላይ ደግሞ የመጀመሪያዎቹ አርአያዎቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሃይማኖት አባቶቼ ናቸው።  የኔ ጀግኖች አር አያዎች ከብዙዎቹ የመጀመሪያውን ረድፍ የያዙት፡ አቡነ ጴጥሮስ፡  ከሴቶች ንግስት እሌኒ፡ ንግስት ጣይቱ፡ ከወንዶች፡ አጼ ልብነ ድንግል፡ አጼ ተዎድሮስ፡ ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጦርሃይሎች ኮሎኔል አብዲሳ አጋ ፡ ኮሎኔል ጋሻው ሃብተፈብረኤል (ከሙሉ የመቶ አለቃነት ማእረግ እንዳይጨመርለት በልጅነቱ ለአገሩ ክብር ከጀግኖች ወንድሞቹ መሃል ወጥቶ ወደ ሰራዊቱ ከተቀላቀለ በሁዋላ እናቱን ታማ እንክዋን ሄዶ ወደ መጣበት ወደ መንዝ አዋቆላ እግዚአብሄር አብ ለአንድ ቀን እንክዋን እንዳይሄድ፡ ተፈርዶበት በእቁም እስር እስኪሞት ድረስ ኖሮ ከሞተ በሁዋላ ሁሉም ነገር በጀነራል አበበ ገመዳ ተሳቦ ማእረጉ የተለወጠው)ብርጋዲየር ጀነራል መንግስቱ ነዋይ(በሁዋላ የሰራዊቱ መንግስት "ደርግ" በባለውለታነታቸው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰራዊትም ጭምር በስቅላት ፍቅራቸውን ላሳዩት የሌትናንት ጀነራልነት የሾማቸው)ጀነራል ተሾመ ተሰማ በምጽዋ ሕይወታቸውን እንደ አጼ ቴዎድሮስ ለመላው የኢትዮጵያ አንድነትና ክብር የገበሩ፡ ሃይሉ ገብረዮሃንስ ወጣቱን በገኘው መንገድ ሁሉ ስለአገራችን መንግስት ያነቃ፡ ኮሎኔል አስራት ቦጋለ። ናቸው ለኢትዮጵያ አንድነትና ለዴሞክራሲ ትልቅ መስዋ እትነት በተጨባጭ ሲከፍል ያየሁት አባቴ ብዬ የምጠራው የኢትዮጵያ ጀግና ከጊዜው የቀደመ።

1: ከዚህ በታች የማስቀምጠውን የአገሬንና የሕዝቡን ጉዳይ ያገባኛል ብዬ የዜግነት ግዴታዬን ገና በጠዋቱ እድሚዬ እንዳስብበት ፡ ቅድሚያ ለኢትዮጵያና ሕዝብዋ አንድነትና ክብር መቆም እንዳለብኝ በአይምሮዬ ውስጥ የተከሉትና ከዛም ከአንድ አመት ባልበለጠ ጊዜ ውስት እናትና አባቴ ተከታትለው ከዚህ አለም በሞት እነደተለዩኝ የሚያውቁት የኢትዮጵያ ጀግና መኮንን፡ ጽሕፈት ቤታቸው በሄድኩኝ ቁጥር ፡ የወንድ ልጅ የጀግና አይዞሽ፡ በሚል ባገኙኝ ጊዜ አንቺ ጎበዝ ሲሆን መደምደሚያቸው ደህና ዋይ ብለው ስመውኝ ሲያሰናብቱኝ ያው የኢትዮጵያን ጉዳይ ለማስቀደም ለእራሴ የሚል ከርሳምነት በውስጤ እንዳያድግብኝና ለዚህ ሁሉ ትምህርትም በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ጠንክሬ ትምህርቴን በጥሩ ውጤት ሁሌም ተግቼ እንዳጠና ጭምር ከደግነት ጋር ተዳምሮ ለትምሕርት ቤቴ የሚያስፈልገኝን ሑሉ በበኩላቸው በጠየኩዋቸው ጭምር የጡረታ ተፈቅዶልኝ በፍርድ ቤት ማግኘት እስክችል ድረስ ሲረዱኝና እንደጎብዝ እሲገፋፉኝና ሲያበረታቱኝ ስለነበሩት የኢትዮጵያና የመላው ሕዝብዋ ነጻነትና ስልጣኔ አንበሳ ከሆኑት አንዱ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦርሃይሎች ኩራት ጭምር የሆኑት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ነው። የተለያዩ ብዙ የሰርዉ አባላት ደጎች ፍቅር ቢያሳዩኝም በተለይ አንዳንድ የጦር አዛዦች እንደ እነ ጀነራል ሽፈራው ተሰማ፡ ጀነራል ዘውዴ ገብረማሪያም፡ ኮሎኔል ኤፍሬም በቀለ ፡ ኮሎኔል በቀለ ጸጋዬ ኮሎኔል ይገዙ የመኔ ማለት ነው ሲያሳዩኝ የነበሩት ፍቅርና ክብር ልክ አባቴን ለኢትዮጵያ ለሃገሩና ለሰርዊቱ ያደረገውን እያሰቡ በመሆኑ እነሱን አግኝቼ ወደ እማድግበት ቤቴ በጊዚው በሄድኩኝ ቁጥር "አትደጊ ፡ አንቺ ገፊ እናትና አባትሽን ገፋሽ ደግሞ እኛን ልትገፊን ነው?" የሚለውን አባባል ከምንም ሳልቆጥር እስኪያልፍ ነው እኔእኮ ነገ ሰው እሆናለው ብቻ ጎብዤ ልማር አድጌ ለአገሬ ለኢትዮጵያ ብዙ የማደርገው አለ። በሚል አንገቴን ቀና አድርጌ እንድሄድ ይረዳኝ ነበር። በተለይ ወደ ፊት ማንም ጽፎት ያላየሁት የኮሎኔል ይገዙ ይመኔና፡ የአቶ ተስፋዬ ገብረእዝጊ ሃዘን በዚህ መልክ ሳይሆን በመጸሐፍ ውስጥ እንደማካፍላችሁ የአምላክን ፍቃድ እጠይቃለሁ። ሆኖም ጀነራል ጃጋማን ልዩ የሚያደርጋቸው በኢትዮጵያ ቴሌቪዢን ደርግ ስልጣን ከመልቀቁ አንድ ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀረበልኝ ከልጅነት እስከ እውቀት ያሳለፍኩትን መራራ ሕይወት አልፌ እንዴት ስለአገሬ ኢትዮጵያና ሕዝብዋ ብሎም ሰራዊቱ ጎን ቢጊዜው ለመቆም እንደተነሳሳሁኝ የአሜሪካን ምክር ቤት አባል የነበሩትን ሚኪሊላንም አስመልክቶ ጭምር ስጠየቅ የሰጠሁትን ሙሉ ስሜን ጽፋችሁ Yeharerwerk Gashaw with Ethiopian television ብላችሁ ብትፈልጉ የምትሰሙት ነው ዩቱብ ላይ። እኝህ መኮንንን ዛሬ የማንንነቴ መነሻ ናቸው። ሁላችሁንም የማሳስበው ከልጅነታችሁ አሁንም በአዋቂነታችሁ አሁን አሁን ይችን ከዚህ በላይ የጻፍክዋትንና ከዚችም በታች የምታነቡ እስቲ በቅርብም ቢሆን ፡ በኑሮም ይሁን፡ በቤተሰብም ይሁን በስራ ወይም በሰው አገር ኢሚግሬሽን፡ በአገር ቤትም ይሁን በማኛውም  አይምሮአችሁ የመጨረሻ ዝቅተኛ ቦታ ገብቶ እያለ ከዛ ውስጥ በማበረታታት ፡ በመምከር ሌላው ቢቀር የሰው ልጅ መሆናችሁን አሳምⶈአችሁ ጉድጉዋድውስጥ ያውም የመጨረሻው የሰውልጅ አይምሮ የሚወድቅበት ዝቅተኛ አዘቀት ያለው አስተሳሰብ ውስጥ ገብታችሁ እናንተ ማየት ያልቻላችሁትን የአይምሮ ትልቅነታችሁን ቁልጭ አድርጎ እንደ ጠራ መስታወት ፊታችሁ ላይ አቅርቦ እደግመዋለሁ በምክር በማበረታታት ሰው መሆናችሁን አሳምኖ እራሳችሁን ከአዘቀት ቦታ አውጥታችሁ የአይምሮ ከፍተኛ የሚያስደስት ስላም የሚሰጥ ቦታ ውስጥ ገብታችሁ ዞር ብላችሁ ስታዩ፡ ወይኔ!!! እንዴት እራሴን ጥዬ ነበረ? ሞራሌን መጥታ አነሳችልኝ እከሊት። ወይም ሞራሌን ጉዋደኛዬ መለሰለኝ እራሴን እረስቼ ነበር ማለት ነው? ብላችሁ አምላክን ያመሰገናችሁ በትን አስባችሁ አታውቁም?። በግልጽ መናገር አንድወደም። ስንጠይቅም በተዘዋዋሪ፡ ስንመልስም በተዘዋዋሪ እንደው ማዶ ማዶውን ነው አብዛኛዎቻችን የምናስበው። ያንን ጥለን በቀጥታ እስቲ እናስብና አር አያዎቻችንን በማክፈል ለወጣቱም ትውልድ ይሁን በእድሜያችን ላሉት ሳይቀር እኛም ጥሩ አር አያ እንሆን።


ጀኘራል ጃጋማ ጽሕፈጥ ቤት።
2: የጀኘራሉ ጽሕፈት ቤት ስንደርስ ኮሎኔል ጥላሁን የሚባሉ በጣም ጠይም ካደኩኝ ሕንዶችን እዛው አዲስ አበባ በተለይም ሰራዊቱም አካባቢ አያቸው ስለነበረ ኮሎኔሉም ጠይም ያሉ ሕንድ ይመስላሉ ከነጸጉራቸው። እናም እናቴም ዳዊት ደግሜ ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ሳታስገባኝ በፊት አራተና ክፍለጦር ስማር አብዛኛውን ጊዜ በመቀራረብ የምታናግራቸው እኝህ ኮሎኔል ጥላሁንን ስለነበሩ እሳቸውም እኔን በጣም አውቀውኛል። የአባቴ በጣም ይቅርብ ጉዋደኛው መሆናቸውን ሳልረዳ የናቴ ወንድም ይመስሉኝ ነበር በሚያሳዩኝ ፍቅር። ካምፓ ውስጥ ስጫወትም ካገኙኝ ልጆች መሃል በተለይ የማይረሳኝ እጃቸው ላይ መሃረብ አይጠፋም እኔን ለይተው ከልጆች መሃል አፍንጫዬን ፊቴን ይጠርጉኝ ነበር። ሁሌም ባገኙኝ ጊዜ በኦሮምኛ ያናገሩኝ ነበር። ታዲያ እዛው አዲስ አበባ የሚኖሩት ዘመዶችዋ ጋር በተገናኙ ቁር ወይም ከሸኖ ከሚመጡት ዘመዶቻችን ጋር የሚነጋገሩት በኦሮምኛ በመሆኑ እኔም እንደተወለድኩኝ በሐረር የጦር ሃይሎች ሃኪም ቤት ከሶስት ወር በሁዋላ እናቴ ከአባቴ ኦጋዴን ተመልሶ ሲሄድ ወደ አርሲ ስሬ ይዛኝ በመሄድዋ (ከአባቴ ተፋታ) መጀመሪያ አፌን የፈታሁት የናቴ አባና እናት ቤት በኦሮሙኛው ነበር። እናም ዘመዳሞች በመሆናቸ የሚነጋገሩበት ቁዋንቁዋ ስለሚመስለኝ ኮሎኔል ጥላሁን አጎቴ ይመስሉኝ ነበረ መክኒያቱም የናቴ ታላቅ ወንድም ጋሼ በዳኔ እዛው ስሬ የሚኖር ገበሬ ልክ እንደኮሎኔል ጥላሁን በሄድኩኝ ቁጥር ከናቴ ጋር እንደሳቸው ያንከባክበኝ ስለነበረ። እናቴ  ስትሞት የሥጋ ዝምድና እነደሌልን ዘመዶቼ ቢነግሩኝም ለኔ ሁሌም በደግነታቸው ባሳዩኝ ፍቅር አሁንም ኢትዮጵያዊ አጎቴ ናቸው በሕይወት ይኑሩ አይኑሩ በቅርብ ባላውቅም በሁዋላ ጀነራልነት ማእረግ መድረሳቸውን በጣም ካደኩኝ በሁዋላ ሰምቻለሁኝ ግን ወደ አስረሃንድ አመት ሲሆነኝ ነው ለመጨረሻ ያየሁዋቸው።  እስከዚህ የሰራዊቱ ቤተሰብ አንዺህ ይፋቀር ነበር ለማለት ነው። ፍቅር ካምፕ ውስጥ በተለይ በጣም የበዛ ነበር። ታዲያ ኮሎኔል ጥላሁንና ጀነራል ጃጋማ ጽፈት ቤታቸው ጎን ለጎን አንድ ህንጻ ውስጥ ህንጻ ስል ፎቅ ማለቴ ሳይሆን ፎቅ ያልሆነ ቦታውን ለሚያውቀው እንደ ህክምና መምሪያ እንደነበረው እዛው መሽዋለኪያ አጠገብ ማለት ነው። መጀመሪያ ኮለኔሉጋ ገብተን ከዛ ኮለኔሉም ጭምር ጀነራል ጃጋማጋ አባቴም እኔን ይዞ ገባን። የነበረው መገናኘት ዛሬ "ሰፕራይዝ ሰፕራይዝ!” የሚለው አይነት ነበር በሶስቱም መኮንኖች በኩል። ለጀነራል ጃጋማ ልጄን ይዤ የመጣሁት እንድታውቅህ ነው አላቸው። እሳቸውም ስሜን ጠየቁኝና ሳሙኝ። ወዲያው ቡና ሻይ ታዞ መጣ ። ኮሎኔል ጥላሁን ወደ ጽሕፈት ቤታቸው ተመለሱ ወጡ እኛ ከነበርንበት። አባቴ ብሶቱንና በጣም የከረረ ነገር የነበረው መቀጠሉን በማሳሰብ መልክ ለጀነራል ያስረዳቸዋል። አንዴ ይስቃሉ ሁለቱም ሌላ ግዜ ያዘኑ ይመስላል በእኔ አይምሮ ሊሆን ይችላል እኔ ሰው ፊቱን ካኮሳተር የቁጣ ምልክት መሆኑን በዛ መልክ ስለምረዳ ይሆናል።  የጀነራል ጃጋማ ጽሕፈት ክፍል እንደ ኮሎኔል ጥላሁን ብቻቸውን አይደለም። በር አለ በሩ ሲከፈት ኮከብ የደረደሩ በጣም ቀጭን መኮንን አሉ ይሄንን የመገልጽላችሁ በዛን ጊዜ አይምሮዬ ነው እንጂ ካደኩኝ በሁዋላ መኮንኑ ሻምበል እንደነበሩና አገናኝ መኮንን መሆኑን አጥቼ አይደልም በዛን ጊዜ በልጅነት እድሜዬ አስተሳሰብ ስገልጽ በተለይ ለቀድሞው ሰራዊትና ቤተሰቡ ደስ እንደሚል ስለምረዳ ነው። ታዲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስማቸውንም እሳቸውንም ያወኩት ጀነራል ጃጋማ እራሳቸው ላይ የማእረግ ባርሜጣቸውን ሳያደርጉ በጽህፈት ቤታቸው ውስጥ ያለውን በር ከፍተው ከተፈለኩኝ እውጪነኝ ብለው አባቴም እሳቸውም የኔን እጅ ይዘው ወጣን። ውጪ መነጋገሩን ቀጠሉ በበኩሌ ጠጠር ጨዋታ ጀመርኩ። በመሃል ጀነራል ጃጋማ አባቴን ለመሆኑ ጋሻው ለልጅህ ስለጀግንነትህ ነገርካት? ይሉታል። አባትሽ ትልቅ ጀግና ነው አንቺ አድገሽ እንደጋሻው ትሆኛለሽ አሉኝ። እኔም በሰራዊቱ መሃል ማደግ ብቻ ሳይሆን ያችን ቲኒሽ እድሜዬን የተለያየ ማረፊያ ሰፈርና ከተማ ክፍለ ሃገር ሁሉ እየተዘዋወርኩኝ ከእናቴጋር በማደጌ ባጭር ጊዜ የትኛው ከተማ ወይም ቦታ ይሄን ያህል ወር ቆየው ውይም አንድ አመት ሁለት ብዬ ቆጥሬ ለመናገር ተጽፎ በእጄ ባይገኝም በጊዜው ባላውቅም የተለያየ የጦር ሰፍር በማደጌ ጭምር በግዜው በእኔ እድሜ ካሉት የተለየ ብዙ ነቃት እንደንበረኝ ከቀን በሁዋላ ተረድቻለሁ። ይሄውም አካባቢዬን አይቼ የሚሆነውን የማገናዘቡ አስተሳሰብ ነበረኝ። ለምሳሌ እናቴ ስትነግረኝ የሶስት ዓመት ልጅ ነበርሽ ብላኝ ነበር ይሄውም አንድ ሰውዬ ሳይ ከሌሎች ሁሉ ሰዎች የተለየ መሆኑን ስለገባኝ በቆዳው መለየት ከልጆቹ ሁሉ መሃል እሮጬ ለማየት አጠገቡ ስደርስ ከረሜላ እንደሰጠኝ ። ማለትም ፈረንጅ የአሜሪካን ወታደር መሆኑ ነው አማሬሳ ጫካ ውስጥ የነበረ ማረፊያ ሰፈር በሁዋላም ነበር። ሌላው ደብረሼክን ይዤ ወደ ቢቴ እየመራሁ መምጣቴና እናቴ በእጅዋ ምግብ ስታበላው ፍርሃትም አልነበረኝም ያስቃል (ጅብ ማለት ወይም ዎራብቻ)ከዛም አባቴና ጀነራል ተሰነባብተው እንደ አለቃና የበታች ሳይሆን እንደ ዘመድና ጉዋደኛ ተቃቅፈው አንድ መልክት የሚታይበት የመከራ ወደ ጦርነት በመሄድ እንደሚሰነባበት ሰው ተሰነባበቱ በመጨረሻም ሰላምታ ተሰጣጡ እኔም ሰላምታ እንደሰራዊቱ መስጠት ስለለመደብኝ እዛው ካምፕ፡ ለጀነራሉ ሰላምታ ሰሰጣጨው እሳቸውም ሰላምታ ሰጥተውኝ ተለያየን። ያባቴ የመደነቅ ፈገታው አይረሳኝም ለአለቃው ሰላምታ ሰሰጥ።

3: ከዛም ብዙ ሳይቆይ እናቴ ታማ ሞታ ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ጉዋሮው ተቀበረች። ብዙም ሳይቆይ ያለሁበት ዘመዶቼ ቤት አንደ የወታደር ልብስ የለበሰ ሰው እየተጫወትኩኝ እያለሁ ልጆች ከመሃላችን ሲያነገግሩ አየሁ። አባቴ በጣም እረጅምና ቀጭን ነበር በማእርግ ልብስ ማለት የወታደር ልብስ ብቻ ለብሶ ነው የማውቀው እና ሰው አባቴን ይመስሉ ነበር ከሩቅ ስቀርባቸው አላውቃቸውም። የአባቴ ዘመድ ባል መሆናቸው ነው። እናቴ ስለሞተች አባትሽ መጥቶ ሐረር ይወስድሻል ስለተባልኩኝ ጉጉቱ አይኔን ግቢው በተከፈተ ቁጥር ትምህርት እቤትም እንዲሁ ያባዝንኝ ነበር። ሆኖም ወታደሩ ልክ እንደትልቅ ሰው አናገሩኝ። አባትሽ ባጋጠማጨው ትእዛዝ መሰረት ወደ አዲስ አበባ ስለማይመጡ እኔ እንድወስድሽ ሰለተላኩኝ ቤትሽን አሳይኝ አሉኝ። እየመራሁ ጊቢው ውስጥ ገባን። ከዛም ተሰናብተው ሄዱ። በማግስቱ በጠዋት መጥተው የአባቴን ከእዚ ዓለም በሞት መለዬት ነገሩን። ፈዘዝኩኝ እንጂ አላለቀስኩም። ልጆች የእናት አባት ሞት ወዲያው አይሰማንም በራሴ ካየሁት ድንጋይ ነው የሚያደርገን ምን እንዴት እንደምናስብ አናውቀውም፡ እያደር እየዋለ ስናጣቸውና የነሱን የቤተሰብነት ፍቅርና እንክብካቤ ስናጣ  ነው መለያየታችን በሞት የሚሰምን። 

4: አንድ ቀን ከፋኝና የጡረታዬም ገና ስላልተፈቀደልኝ ጉዳዬን የሚከታተል ዘመድ ጠፍቶ በቀጥታ ከምማርበትና ከምኖርበት ዘመዶቼ ሰፈር ተነስቼ ሃሁ የቆጠርኩበት አራተኛ ክፍለ ጦር ኮሎኔል ጥላሁንጋ ሄድኩኝ። የሉም። ከዛ የኮሎኔሉ ጽህፈት ቤትና የጀነራሉ ጎን ለጎን በመሆኑ አንድ በር ዘግቶ ሁለተናውን እንደመክፈት ይቆጠራል። ታዲያ መጀመሪያ አገናኝ መኮንናቸውጋ በግባት እንዳለብኝ ያልገባኝ የአስር አመት ልጅ የጀነራሉን ጽሕፈት ቤት ከፍቼ ስገባ ባጋጣሚ ጀነራል አሉ። እሳቸውም የአባቴን መሞት ያውቁ ኖሮ ወደሳቸውጋ ስለሄድኩበት ያለሑበት ዘመዶቼ መጸሐፍ አልገዛ ብለውኝ እንደተቸገርኩኝ ስነግራቸውና ኮሎኔል ጥላሁንን እንዳጣኋቸው ሳስረዳቸው። በጣም አዝነው ብሌላውን ልተውና ላስለቅሳችሁ ስለማልፈልግ፡ አገናኝ መኮንናቸውን ጠርተው ታስታውሳታልህ የጋሻውን ልጅ ብለው ባጭሩ የምፈልገው መጸሐፍ ሁሉ እንዲገዛልኝና፡ እሳቸው ሌላ ጊዜ ባይኖሩም እንክዋን ልፈልጋቸው ስሄድ የምፈልገውን አገናኝ መኮንኑ (ኤዲሲ)ልክ እንደራሳቸው ልጅ አድርገው እንደተባበሩኝ ነግረው ሲያሰናብቱን ቢጫዋን አምስት ብር ሰጥተው በእናቴም በአባቴም ናፍቆትና ለራሴ አሳቢ ሆኖ እየተወዛገበ ያለውን አይምሮዬን በከፍተኛ ደረጃ ቀና የሚያደርግ ምክርና ተስፋ ይሰጡኛል። አባቴን ጋሻውን የሱማሌ ጦር ጌታን መሆን እንድችል። ጎበዝ ተማሪ እንድሆን። የጀግና ልጅና የወታደር ልጅ በመሆኔ በጣም እንድኮራና አንድም ችግር ወደ ሁዋላ ሊያረገኝ እንደማይችል እራሴም የኦጋዴን የሐረር አንበሳ መሆኔን አስገነዘቡኝ። ውነትም እኔ እራሴ ወታደር መሆን መመኝት ጀመርኩኝ። አንድ ቀን ተመልሼ ጀነራልጋ ለምግባት ያው ልክ እንደ አንድ ወታደር የተነገረኝ የመከተሉ ባሕል ከእናቴም ቤት ውስጥ ጭምር ብሎም ጀነርልም አገናኝ መኮንኑን ስላስተዋወቁኝ ደግ የሐረር ሰው ከምወዳቸው አደሬዎች አንዱ መሆናቸው ነው ጀነራሉ ጃጋማ መታጠቢያ ቤት ወድቀው በሕክምና ላይ ናቸው ሲሉኝ ባንድ ፊት ወይኔ እድለቤስ የምባለው የምኖርበት ቤት ትዝ አለኝና ከአራት አመቴ ጀመሮ የምማጸነውን ገብረኤልን ካዳንካቸው ዘቢብ ገዝቼ አመጣለሁ ብዬ ተሳልኩኝ። ሳላውቀው ለካስ እራሴን ማጽናናት ጀምሬ ኖሮ እንደ እንባም አደረገኝና አይ ይድናሉ ገብረኤል አለ አልኩኝ። ቀጥሎም አስራስምንት አመት ድረስ የማንኛውም ወታደር ልጅ አባቱ ቢሞትም በሕይትወትም ቢኖር በነጻ መታከም የተፈቀደ በመሆኑ ቁርጥማትና ብርድ ነው ተብዬ ነገሩ የቤተሰብ ናፍቆት ነው ሆንም ቤላ ሃኮም ቤት ያስተኙኛል ዶክተሮቹ። ታዲያ አንድ ቀን እስከዛሬ ሁሌም የማነሳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የሴት ሻምበልና ነርስ ክፍሌ መጥተው ሲያክሙኝ ከዛ እናትና ኩራቴም የሆኑኝ ሻምበል ሰናይት ጸሃይ ላይ ውጪና ቁጭ በይ በበለጠ ቶሎ ትድኛለሽ ብለው የዘውኝ በጣም ደስ የሚል አበባ ያጀበው የሃኮም ቤቱ በመኮንኖች መኝታቤት ባለው በኩል ውስደው አስቀመጡኝ። ከዛ አንድ ሰው የመኮንኖች ብሽተኞች ፔጃማ የለበሱ መጥተው አጠገቤ ሲቀመጡ እያልቀስኩኝ ነበር የሚያመኝ ቁርጠትና ቁርጥማቱ እየነዘረኝ ነገር። ብዙም ሳይቆዩ ወጣት መኮንን መሆናቸው ነው ከአብዛኛዎቹ ከማውቃቸው። ምነው የምታለቅሽው አንቺ ወጣት አሉኝ። ቃሉ ወጣት የሚለው ስላለመድኩት ስድብ መሰለኝና ባስብኝ ለቅሶው። ከዛ ደፈሩኝ ስላቸው አስቆዋቸው ምን ማለት እንደፈለጉ አስረዱኝና እኔ ለማይረባ በሽታ ቶሎ ስለሚድን ማልቀሴ አስፈላጊ እንዳልሆነ ገልጸው አይዞሽ እስቲ እኔን ተመልከቼ ከቃጠሎ ነው የዳንኩት ከሞት ነው የዳንኩት ገና ብዙ ጊዜ ይፈጅብኛል ብለው ደረታቸውን ክንዳቸውን እጃቸውን ሁሉ ሲያሳዩኝ ፊታቸውም ላይ ይታያል ቃጠሎው ወዲያው የኔን መታመም እረስቼ መሪር ሃዘን እዛ ሽታው በእግዚአብሄር ተፈጥሮ መአዛው የሚጣፍጥ አበባውስጥ ተቀምቼ አባቴ ካንዴም ሁለት ጊዜ ተኝቶበት የነበርውን ክፍል መስኮት ትዝ አለኝና ዞር ብዬ አይቼ ከውጋዴን ነው የመጡት? አልክዋቸው። የለም ፓይለት ነኝ ጀንራል ጃጋማንና ሌሎች ሰዎች ይዤ ለስራ ስንሄድ በደረሰብኝ አደጋ ነው የተቃጠልኩት ሲሉኝ። ምን እንደማስብ አስቡት። ጀንራል ጃጋማ ኬሎ ናቸው? አልኩኝ አዎንአሉኝ።  ኡ ኡታዬን ቀጠልኩኝ። ከዛ እኛ ሲስተር ሻምበል ሰናይትና አንድ ሳንባቸውን ታምው ከሐረር የመጡ መኮንን እየተደበቁ ሲጃራ የሚያጨሱ ተዋውቄ ነበር እዛው ታዲያ ተርዋሩጠው ይመጡና ዝም ያሰኙኛል። የሚገርመው በሽታዬ ጠፋ በድንጋጤ። ከዛ ጀነራልስ ዳኑ! የታሉ!አልኩኝ። ጀነራል ምንም አልሆኑም እነሱን ለማዳን ነው እኔ መቃጠሉን የመረጥኩት ማምለጥ እችል ነበረ አሉኝ ወጣቱ መኮንን በጣም በሚያሳዝን አይነት እጃቸው በጣም የተቃጠለው ጭርምት ምት ብሎ በምንም የማይትካ የልጅነት እድሜያቸው እዛላይ እንደተቀጠፈ እያሰብኩኝ ሳለቅስ ስለእሳቸው አይተው አይዞሽ እድናለሁ አሉኝ። ወዲያው ጀነራል ጃጋማ ብቻቸውን በአበባው በኩል ሲመጡ ለኔ ፊት ለፊት ስለተቀመትኩኝ ወደመግቢያው ለጥ ብሎ ይታዩኝ ጀምር ። ወጣቱ አብራሪ መኮንን ጀርባቸውን በቻ ነው ጀነራሉ የሚያዩት። ከዛም ጀንራል!!! ብዬ ተደስቼ ሳይቸው ጮክ ብዬ በደስታ ቡዋረቅኩኝ። ባጭሩ ፡ አብራሪውን መኮንንም ሰላምታ ሰጥተው ተሻለህ ወይ አይዞህ ትድናለህ አላልኩኝም ይሄው ባጭር ጊዚ እየዳንክ ነው አሁንማ ቁስሉም እየደረቀነው አይዞህ። ብለው አበረታትዋቸው። ከዛም እኔም የለብስኩት የሃኪም ቤቱን ፒጃማ ስለነበረ እንዴት ሃኪም ቤት እንደገባሁ ነግሬአቸው ቀጥለውም በተለመደው ለልጅ አክብሮት እንጅ ማወቅ የለባትም ወይም የለበትም ብሎ የማያስበው አይምሮአቸው ፡ የአይሮፕላን አደጋው እንዴት እንደደረስና እኛ ወጣት መኮንን ሕይወታቸውን እንዴት እንዳድዳንዋቸውና ጀግና ይሄ ነው እድለኛ ነሽ እሱንም ማወቅሽ ብለውኝ መኮንኑን ይዘው ወደ መኝታ ቤት ገቡ እኔን ተሰናብተው። ይሄንን ሳልገልጽ ማለፍ አይምሮዬ አልፈቀደም ጀነራል ጃጋማ ደግነትቸውና እሩህሩህነታቸው ከጣሊያን ጊዜ ጀምሮ ታሪካቸውን ከቀን በሁዋላ በጣም ቆይቶ ካነበብኩትና እኔ በራሴ በማውቀው ሲደምረው እስከአሁን አምላክ እየጠበቃቸው እድሜያቸውን አርዝሞ የኖሩት በውስጣቸው ያለው በእውነት ላይ የተመሰረተው መርዝ የሌለው አስተስሰባቸው ነው። መርዝ የሊለው ስል ብዙ ሰው አባትና እናት ያላቸውን ልጆች እንጂ የናትና አባት ደሃ የሆንነውን ቦታ አይሰጡንም ነበር። እናት አባት አጥቶ ሃብት ውርሶ ክፎ ዘመዶች ከሚያሳድጉት ልጅ፡ እመንገድ ላይ እየለመነች ልጅዋ የልጅነት እድሜውን ብቻ እያወቀ በእናት ፍቅር የሚያድግ ልጅ ይበልጣል በደስታና በአይምሮ ማረፍ።
 ደግ እንሁን እርስ በእርሳችን እኛም ለተረፈው እድሜያችን እላለሁ በዚህ አጋጣሚ።  ዛሬ ማርቲን ሉተር ኪንግ "I'm somebody” አሉ የሚለው አባባል ትልቅ ሚና የሚጫወት ቃል ነው በወጣትና ማንነቱን እንዲስት ለሚደረግ ማንኛውም የሰው ልጅ አይምሮ ውስጥ ማለትም ማንም አይደልህም እኮ ሲባል በደንብ ማንነት ያለኝ ነኝ የሚለውን በራስ መተማመንን ያጠናክራል። ታዲያ ምንም እንክዋን አንድ የአባቴ ዘመድና ቀትሎም አስተማሪዎቼ ለኔ በራስ የመተማመን ግንባታ በተለይ በጀግናው አባቴና በጀግኖች ወንድሞቹ ታሪክ አይዞሽ አንቺ እኮ የእነአጅሬ ደም ነሽ ስባል በሌላም በኩል በናቴ ከአባትዋ ጀምሮ ጣሊያንን ያበረከከ የሱ ዘርነሽ እያሉ አስተዋጽዎ ያደረጉ ቢኖሩም ወደ ፊት የምገልጻቸው ነገር ግን ጀነራል ጃጋማም ኬሎ የመጀመሪያ በመሆናቸው ለአገሬና ለሕዝብዋ ብሎም ለቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት ያለኝ የማይበርድ የጋለ ክብርና ፍቅር በጀነራል ጃጋማ ኬሎና በአባቴ አይምሮዬ ውስጥ የተተከለ ነው። አባቴ አባቴ ነው ነገር ግን ጀነራል ጃጋማ በዛ በሰባት ዓመት እድሜዬ አባቴን እንድሆን እፊቱ በነገሩኝ ከዛም አባቴ በሞት ከተለዬኝ በሁዋላ ሳያቁዋርጡ ምንም መከራ ችግር ቢበዛ ከማንነቴ ዝቅ አድርጌ እንዳላስብ አስራ ሁለት አመት እስቲሆነኝ ድረስ ሄጄ ባገኘሁዋቸው ቁጥር ማንም የማይሰጠኝን ክብር እያሳዩኝ በስነስርዓት እየተቀበሉኝ ልጅ ነች ብለው ሳይንቁኝ ገና ሳላድግ በደንብ ለአገሬ እንደደረስኩላት ሲያሳዩኝ የነበረው አስተሳሰባቸው ሰርተፍኬትና የፈተና ውጤ ባሳየሁዋቸው ቁጥር ጎብዝ በሚል በመገፋፋት የገነቡኝ በመሆናቸው የኔ የማንነቴ አርአያዬ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ የኢትዮጵያ አንበሳ(ሌንጮ ኢትዮጵያ)ናቸው።


5:በብዙ አገር ወዳድ ለወገን ተቆርቁዋሪ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ የሚጽፍ ከተገኘ በነብስም ካሉት እንደ ሻምበል ቁምላቸው አይነቱ ላይ ስንት ደርስዋል ማለት በነብስ ያሉ የጦር ሜዳ ማሕደሮች። ታዲያ ያ የቆየ እነሱ ገና ልጆች ሆነው ሲደረግ እንደነበረ ቢያውቁት ብቻቸውን እንዳልሆኑ ተገንዝበው በጊዜው ባለመታረሙ እነዚሕ በሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ከአሸዋ ስር ከእነ ሚስቶቻቸው ልጆቻቸው የተዳፈኑት በሺህ የሚቆጠሩ ጀግኖች የቆየውን ጽዋ እንዲጠጡ ተደርገዋል ያውም በድጋሚ ከእነ፡ ሚስቶቻቸው ልጆቻቸው ካፕውስጥ እንዳሉ። ለሁሉም ጥቂት ልበል ከሞተ በሁዋላ የሙሉ፡ ኮሎኔልነት ማእረግ በአዲስ አበባ የተፈቀደለት አባቴ።

6:አባቴን ለመጨረሻ ጊዜ የማየው ብቻ ሳይሆን ሞቱ መቃረቡን ባላውቅም እሱ የተረዳው መሆኑን እያደኩን ስሄድ ከሆኔታዎች ከነገረኝ ጋር ሁሉ፡ ሳያይዘውና እንዲሁም የኖረበት ጦር ይወደው ስለነበረ እኔን አስፈልጎ የሶስተኛ ክፍለ ጦር የባለውለታችን ልጅ ስለሆነች ትሰጠን እናሳድጋታለን እናስተምራታለን ይላል። ይሄውም የሆነው እናቴም አባቴም በስድስት ወር ልዩነት በማረፋቸው እዚሁ ፌስ ቡኬ ላይ ከእናቴ ከአባቴ ጋር ባጋጣሚ በእኔው ጥያቄ ከተነሳን አካባቢ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ፎቶው የተነሳንው የመቶ አለቃ ዘለቀ የሚባሉ መሹዋለኪያ ፎቶ ቤት ነው። የመቶ አለቃው ከሰራዊቱ በግዜው የተሰናበቱ መሆናቸውን ከፍ ስል ልገነዘብ ችያለው። እናቴና የአባባ ዘለቀ ሚስት ፋንታዬ፡ ከሐረር ጀምሮ ማመላለሻ የመኮንኖች ማረፊያ ሰፈር አብረው የኖሩና እኔም ስወለድ እዛው ሐረር የጦር ሃይሎች ሃኪም ቤት የነበሩ በመሆናቸው እናቴ ብዙ ጊዜ እሳቸውጋ ይዛኝ ትሄድ ስለነበረ ሰዎች እየመጡ ፎቶ ሲነሱ በተለይ ልጆች ከእናት አባትጋር አይ ስለነበር፡ የእኔም ምኞቴ የመጣው አባቴና እናቴ እኔን መሃል ላይ አስቀምጠው ፎቶ የመነሳቱ ከዛነው። ቤታችንም የመጀመሪያው አጼ ምንይልክ ግቢ ውስጥ ነበር ይሄውም ማረፊያ ለጦር ስራዊቱና ቤተሰቡ ከሐረርና ከድሬደዋ ታፍሶ ለመጣው ቦታ ባለመኖሩ እዛ አስፍረውን እንደነበረ በሁዋላ እያደኩኝ ነብስ እያወኩኝ ማለትም ነገሮችን የማመዛዘኑጋ ስደርስ ለም አጼ ምንይልክ ታላቁ ቤተመንግስ ሜዳውላይ በፊት በሩ በኩል ሰራዊቱ ሊያርፍ እንደቻለ ተነግሮኝ በደንብ ተረድቻለሁኝ። ቀጥሎም እናቴ በራስዋ ፍቃድ ሻለቃ ዳኜና ባለቤታቸው እትዬ አክሊለጋር ሰለምትቀራረብ ቤት ሰርተው ወደ ሚኖሩጥ በጊዜው ሳንጆሴፍ ትምሕርት ቤት በሚል በሚጠራው ያኔም አሁንም በስተጀርባ አጠገብ ገብታ ስለነበረ፡ ፎቶግራፉ ቤትም ከዛ ስለማይርቅ ብዙ ጊዜ መሄዱ በመቀጠሉ የኔም አባቴ ከጦር ሜዳ መጥቶ አብሬው በማእረግ ልብሱ እንደሌሎቹ የመለዮ ለባሽ ልጆች ምኞቼ እየባሰ ሄደ። አምላክ ሰማኝና አባቴ አይኑን ተመቶ ሐረር ሊያድኑት ስላልቻሉ በወታደር ፓሊስ ተይዞ ቤላ ታክሞ ሲጨርስ ወደ ሐረር ሊወሰድ ሲል ታግሎ እኔን ፍለጋ ይመጣና ባጭሩ ፎቶግራፍን አስመልክቶ ስመኝ የከረምኩትን ነግሬ ፎቶውን በዚህ መልክ ልንነሳችለናል። አባቴም እያየሁና እየሰማሁ የወታደር ፓሊሶች አድነውት ወዱት ትዛዝ ስለሆነ ፓሊሶቹን አልፍርድባቸውም። ያም ግንኙነት በፎቶግራፍ መነሳት የዘላአለም ማስታወሻ ለህክምናም መምሪያ ጭምር ለአዲስ አበባው መጠቀሚያዬ ሆነ በህይወቱ መከራ ሲያይ ለኖረው አባቴም ለኔም የመጨረሻ ሆነ።


7: ወሩ መስከረም መሆኑን ሁሌም አልረሳውም የተወለድኩበት ቀን አባቴን በማየቴ ። ነብስ ካወኩኝ ሶስተኛ ጊዜዬነው ሳገኘው በአራት መጀመሪያ አመቴ የሰራዊቱ ልጆች የቄስ ትምህርት ቤት አራተኛ ክፍለጦር መጥቶ ማለት ነው። ከዛም በሰባትና ቀትሎም በስምንት ዓመቴ ስንገናኝ ማለት ነው። አባቴ በተለያየ ቀንና በተከታታይ ትምህርት ቤቴ ድረስ እየመጣ ይወስደኝና የሚነግረኝ ሰለሃቅ በመቆሙ የደረሰበትንና በተለይ ከእምድር ጦር አውጥተው የክቡር ዘበኛ ለማድረግ የተሰጠውን የማእረግ ልብስ ከእነ ባርሜጣው የአገሬ የኢትዮጵያ እንጂ የንጉሱ ዘበኛ አይደለሁም በማለቱ የደረሰበትን ጭምር ሲያስረዳኝ ፊቱን ዝም ብዬ ስለማየው ቀና እያልኩኝ እራሴን እየደባበሰ አንዳንዴም ነገሩ ይገባት ይሆን በሚል የመስላል እየሳቀም ነበር የሚያስለቅሰውን አጋጣሚ ሲያወሳኝ። ሰሜና ተገኔ ብሎ የሚል የልብ ጉዋደኛ ጠምቶት እንደነበረ በሁዋላ እድሜዬ ቲኒሽ በጨመረ ቁጥር እረዳ ነበር ሕይወቱ ከማለፉም በፊት ያለውን ማስተላለፉም እንደነበረና ለሰራዊቱም የሚቆጭለት ትውልድም እንዳሰበም ነው የተረዳሁት በመጨረሻም። ጀነራል መንግሱ ነዋይ የሚባሉ ጀግና እንደነበሩና ሰቀሉት!!! ምንይሆናል። ያለው ከልቤ አይጠፋም። አባቴ እኔ ሳልወለድ ጀምሮ መጀመሪያ በሐረር፡ በኦርዴር፡ ጭንሃሰንና ኦጋዴን በካዴቶችና በቆየው ተራወታድር ላይ የሚደረግ ግፍና ከመንገድ የወጣ ቁጥጥር ከግቢ እንክዋን እንዳይወጡ የሚደረገው ባንዳንድ መኮንኖች ጉዋደኞቹ ሕገ ወጥ በመሆኑ ለመለዮ ለባሹ በመከራከሩ፡ በሕጉ መሰረት ካዴቶች መብታቸው ይከበር ለመናፈሻ የሚፈቀድላቸው ጊዜ ይከበር ፡ በሚል የተነሳው ያለመግባባት ስማቸውን ልጠቅስ እዚላይ አስፈላጊ አይደለም ነገር ግን የሶስተኛ ክፍለጦ አዛዥ በጊዜው ወደነበሩት መኮንንጋ ጭምር ጸቡ ግሎና አይሎ፡ ከዛም ቀጥሎ ወደ የቁም እስርና ከናካቴው ማእረጉ ሁሉ እንዳይጨመር ወንጀለኛ ተደርጎ የሃሰት መክኒያት እየቀረበ በየጊዜው እንዲያልፈው እየተደረገ ሲኖር፡ አባቴና አብረውት በተራ ወታደርነት ተቀጥረው ጀነራል ማእረግ ድረስ ደርሰው የክፍለ ጦር አዛዥ ከሆኑት እሱንም በማእረግ አልፈውት እየጨቆኑት ከነበሩት ሁሉ የበለጡ በጊዜው ዘመናዊ ትምሕርት፡ ሰልጥነው ባጭር ጊዜ የጀነራልነትና የጦር አዛዠነትም ድረስ የደረሱት መኮንኖች ፡ እንደሱው የመለዮለባሹ መጨቆንና አንዳንዱም መኮኑን ለሚስቱ ተራወታደሩን የገበያ ዘንቢል ተሽካሚ ማድረግ የቆጫቸው ፡ የተማረውም ስራ አጥቶ ሲንከራተት ጭምር የመንግስት አስተዳደርና የሕዝብ ሕገመንግስት ለመመስረት ይዘው ተነስተው በነበረው መፈንቀለመንግስት ውስጥም አባቴም አለህበት ተብሎ ጠፈርዶበት ከሞት ቢተርፍም ማለትም አዲስ አበባ በመገኘቱ የቁም እስሩን ተላልፎ ከኦጋዴን ጠፍተህ ሄደሃል በሚል፡ በወታደር ፓሊስ ታድኖ ከአራተኛ ክፍለጦር ማረፊያ ሰፈር፡ ወደ ኦጋዴን እንዲመለስ ተደርጎ በመጨረሻም ጦር ሜዳ ያላሸኘፈውን የሱማሌን ምሽግ በቀጥታ ገብቶ ካንዴም ሁለት ጊዜ ገብቶ በማውደሙ በጊዜው የነበሩት የእንግሊዝ የጦር መኮንንኖች "የኦጋዴን አንበሳ" በሚል የክብር ስም የሰጡትን አባቴን ፡ ታሪኩን ሁሉ ለማጥፋት ያልተደረገ ነገር አልነበረም አልሆነላቸውም። በመጨረሻም በማስመሰል በግፍ እንዲገደል ተደርግዋል። ያም አልፎ አባቴ በተገደለ ስድስት አመት ባልበለጠ ግዜ፡ ሰራዊቱ ደርግ በሚል ስም የመንግስት ለውጥ አመጣ። ይሄንን ስል ሁለት ነገር አለ። የአጼ ሃይለስላሴ አወራረድና ከስልሳ ያላነሱት መኮንኖችና ሲቪሎች የኢትዮጵያ ሃብቶች መረሽን ሁሌም ባሰብኩት ቁጥር ከዛን ጊዜ ጀምሬ እያንሰቀሰቀ ያስለቅሰኛል። ስለተረሸኑትና በደንብ ቀርቤ ስለማውቃቸው መኮንኖችና ጥቂት ሲቪሎች የማካፍላችሁ ይኖራል።

    8:በመጨረሻም የቀድሞውን ሰራዊት ልጆች የማሳስባችሁ በልጅነታችሁ የምታውቁትን እንድታካፍሉን ነው። ስማችሁን አትደብቁ በውነተና ስማችሁ ጻፉ አባቶቻችን ከመለያ ቁጥራቸው ሌላ ግምባራቸውን ስጥተው ለአገር ዳር ድንበር ለወግን የእኩልነት መብት በጦር ሜዳ ብቻ ሳይሆን በብዙ ፈርጁ ሰለተሰውሉን ታሪካቸው ዘለዓለማዊ ለመሆኑ ለወጣቱና ለወደፊቱ ትውልድ የማስተላለፍ የዜግነት ግዴታ ብሎም የህሌና ሃላፊነት ስላለብን። 

ኢትዮጵያ ለዘልዓለም አንድነትዋን በሑሉም ልጆችዋ አስከበራ ትኖራለች።
የሰላም መከባበር አንዱ የሌላውን ባህልና ቁዋንቁዋ አክብሮ በእኩልነት የሚኖርባት አገር ያድርጋት የፈጠራት አምላክ። አሜን።


የጋሼ ሃይሉ ገብረዮሐንስ (ጎሞራው)
የንቃት አር አያነት በቅርብ ቀን ይቀጥላል።

ቀጥሎም የኮሎኔል አስራት ቦጋለ
እምነት መጣል ትልቅ ሃላፊነት የመወጣትን
አርአያነት የያው ታሪኩ ይቀጥላል።