Sunday, March 23, 2014

ብርሃኔ ዳምጤ (ሆዱ መላው)በሁለት ባንዳዎች ጉያ ያለ ተባይና ትቢያ ነው ከቀመሩ ደሳለኝ


ብርሃኔ ዳምጤ (ሆዱ መላው)በሁለት ባንዳዎች ጉያ ያለ
ተባይና ትቢያ ነው 
 
ከቀመሩ ደሳለኝ 
 
ብርሃኔ ዳምጤ ማለት ተራና እርካሽ የሆነ እራሱን እንደሰው፣ ማንነቱን ከኅብረተስብ ጋር አዛምዶ 
የማያይና የማያስብ ፣ወሬ አሳማሪ ወላፈንዳ በበላበት የሚጮህ ግብዝ ሰው መሳይ በሚድያ(በሽንጎ) 
ነው። 
 
ይህ ሰው በሁለት ባንዳዎች በወያኔ ሕወሓትና በግንቦት 7 ፀረ_ ኢትዮጵያ ጥንስና የጥርነፋ የጥፋት 
ስልት ውስጥ በርካታ ገንዘብ በተስጠ ቁጥር እየተዘዋወረ የውሽት ወሬ የሚያስተጋባ የፀረ_ኢትዮጵያ 
አካልና የፀረ_ ወያኔን የተቃዋሚ ትግልን የሚያወናብድና የሚያዳክም ነው። አጥንት ወይም ቁራሽ 
እንደተጣለለት ቀላዋጭ ውሻ ባህሪ ያለው ከዚህ ቤት ከዚያ ቤት እየተዘዋወረ ለሆዱ የሚጮኽ፣ ጥቅም 
በአገኘበት የሚውልና የሚያደር፣እየሸሸ የሚለፍፍ ቀጣፊና አታላይ ሆዱ መላው ሰው ነው። 
 
ብርሃኔ ዳምጤ (ሆዱ መላው) ኅሊና የሌለውና ምላሱ ብቻ የወያኔ አንቧራቂ ፣ የግንቦት 7 አሚና 
አስመሳይ ወግ ጠራቂ ባንዳ ነው።የወያኔን ፀረ_ ኢትዮጵያነት፣አጋሚዶ ዘረኝነትና ሁሉን ተንኰልና 
ጥፋት እያወቀ ወሬ በማፋለጥና በመንዛት ሲረዳና አገር ሲያስጠፋ፣ ሃብት ሲያዘርፍ የነበረ ወሽቀሬ 
ነው። መለስ ዜናዊ ከሞተ በኃላ የሚሰጠው የገንዘብ መጠን በመቀነሱ ተንሸራቶ በመውጣት ወያኔን 
ከዳሁ ብሎ ፣የተሻለ ገንዘብ ለማግኘት የተቀላቀለው ያው ፀረ_ ኢትዮጵያ፣ ፀረ_ኢትዮጵያዊነት አቋም 
ያለውን ድርጅት ግንቦት 7 ዶ/ር ብርሃኑ፣ አቶ አንዳርጋቸው፣ አቶ ኤፍሬምና ሌሎች ባንዳዎች 
የተካተቱበትን የሻቢያ የጥፋት አጋር የሆነውን እንጂ ከፀረ_ ወያኔ ተቃዋሚ ድርጅትና አገር ፣ወገን 
አፍቃሪዎች ጋር አይደለም። አገር ወዳዱ የወያኔ ተቃዋሚ ኃይሎች ለዚህ ሰው ጆሮም ቦታ የሰጠውና 
የተቀበለው የለም ። ያቀረበውና መድረክም የሰጠው፣ ያዳመጠውና የሰማው አካል ፈጽሞ አይገኝም። 
ማን እንደሆነና የሰራው ሁሉ የሚታወቅ ችዋዋ ጥርስ የሌለው ቡልዶግ ውሻ የሚከተለው ለፍላፊ 
እንደሰው ሳይሆን እንደ እንሳሳ የሚታይ ፍጡር ነው።ከዚህም በመነሳት፣ ለማያቅሽ ታጠኝ 
እንደሚባለው አነጋገር ዋጋ አንሰጠውም ።ከዚህ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ይጨነቁበት።እኛ ግን አህያም 
የለኝ ጅብም አንፈራ ብለን የምናልፈው የተናቀና የተጠላ ጉዳይ ነው። 
 
በኢትዮጵያና በሕዝቧ አንድነት ላይ ከፍተኛ የጠላትነት ዘመቻ የሚያራምዱ ወገኖች ግንቦት 7ና 
በሚዲያም በኩል ኢሳትና የኢሳት ወዳጅ የሆኑ ሬድዬው አገልግሎት ሰጭዎች እንደ ትልቅ ፖለቲከኛና 
ተንታኝ በመሻማት ሲያቀርቡት፣ ሲጋብዙት፣ ለገንዘብ መዋጮ ተጋባዥ እንግዳ ሲያረጉትና አብረውም 
ፎቶግራፍ ሲነሱና ሲያስለፈልፉት እንደነበር ይታወቃል።ኢሳትም ሆነ ሌሎች በእሱ አፍ በማስለፍለፍ 
ገንዘብ ሊሰሩበት ታሰቦ፣ ጥሩ ወሬ መቅደድና ማሳመር ይችላል እየተባለ እንደ ሙሾ አውራጅ በየቦታው 
ይቀባበሉት ነበር። እሱም ቅጥፍናውን ለማዋደድ ጋብዙኝ፣ ጠይቁኝ ስለወያኔ ብዙ የማውቀውና 
የምዘረዝረው ጉድ አለኝ ይል ነበር ። ነገር ግን ምንም ያማናውቀው ነገር የሰጠው አንድም ምስጢር 
የለም እራሱን ለማዋደድ ከሚያደገው በስተቀር። ከዚህም ባሻገር፣ ይህ ሃሰተኛ ሰው ብርሃኔ ዳምጤ ገና ጥንት ማለዳ፣ ግንቦት 7ን ከመቀላቀሉ በፊት
በሚገባ ዶ/ር ብርሃኑ፣ አቶ አንዳርጋቸውና ሌሎችን ሁሉ ማን እንደሆኑ፣የወያኔ አካልና አብረውም
የሚሰሩና የታወቁ ፀረ_ ኢትዮጵያ ቡድኖች መሆናቸውን፣ከሻቢያና ከሌሎች ጠላቶች ጋር አብረው 
የዶለቱና ያሴሩ ለመሆናቸው እያወቀ የተቀላቀለ ጠላት እንጂ፣ ዛሬ አዲስ ነገር የተከሰተ ሆኖ አይደለም 
የተለያቸው። ብዙ ጉድ አለ የታዘብኩት የውሸት ማራገቢያው የተለመደ ዘላባጅ አፉ ነው። አሁን ወያኔ 
23 ዓመቱን ለማክበርና መጭውን የምርጫ ጊዜ በውጭ ያለውን ሕዝብ በዚህ ዋሾ አፍ ለማወናበድ 
ታስቦና ሰውየውም ገንዘብ ለመስራት የተቆረቆሰ አሻጥር ነው። " ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል" ማለት 
ይህ ነው። 
 
ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ የዚህ ተራ ሰው ከአንዱ ባንዳ ቤት ወጥቶ ወደ ሌላው ቤት ለቅልውጥና 
መመላለስ፣ የሚያወራውም የፖለቲካ ግብስብስ ቀረብን፣ሆዱ መላው ሄደ ቀረ "ተነጠፈ ቀረ የሽልቻ 
ቅዳጅ" ነውና ያ ሳይሆን ዋናው ቁመነገሩ ሶስት ዋና አብይ ጉዳዮች ናቸው። 
 
አንደኛው: ይህ ሰው እራሱን አዋቂና ብልጥ ነኝ በማለት እራሱን በመካብና ከፍ በማድረግ አባ መላ 
ነኝ፣ አባ መላ በሉኝ ስለአለ ብቻ ይህን ውሸታምና ከሃዲ፣እውቀትና ችሎታ የሌለው፣የአገር ጠላት ባንዳ 
አባ መላ ብላችሁ መጥራታችሁ አገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የማይወደውና የማይቀበለው 
ያስቆጣውም ስለሆነ ለማሳሰብ ነው።ብርሃኔ ዳምጤን ሆዱ መላው ብላችሁ ብትጠሩት ግብዝነቱን 
በሚስማማ ሁኔታ ይገልጸዋል። አባ መላ ግን ለእውነተኛ ፣ የአዋቂና አሳቢ፣ጥበበኛና ብልጥ_ብልህ ለአባ 
መላ ሃብተገወርጊስ ዲነግዴ የክብር የጦር አዝማችና መሪ፣ደፋርና ጀግና፣ለኢትዮጵያ አንድነት፣ሰላምና 
ደህንነት መረጋጋት እጅግ የሰሩ፣የተሟገቱና ያማከሩ፣ ከአፄ ምኒልክ ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ የወሰኑና 
ጠላትን ያርበደበዱ ስመጥሩ አርበኛ ለመልካም ተግባር የክብርና የሙያ መግለጫ የተሰጠ ስም ነው።
እንደነ ብርሃኔ ዳምጤ ከሃዲና የባንዳ _ባንዳ ያገር ጠላቶች፣ የሕዝብ ነቀርሳዎች ፈጽሞ ሊጠሩበት 
አይችሉም። 
 
ሁለተኛው/ ከግብዝነት የተነሳ ብርሃኔ ዳምጤና ሌሎች የሱ መሰል አርቆ ኢትዮጵያንና የሕዝቧን 
ታላቅነትና ክብርን የማያውቁ፣ማየትና ማሰብ የተሳናቸው፣ለማመዛዘን ውስን፣ለመገምገምና መረዳት 
ኅሊና የሌላቸውና የጐደላቸው፣ ለራስ ጥቅም ብቻ ያደሩ፣በአድርባይነት የሚኖሩ ደካሞችና ግብዞች 
ለወያኔ የጥፋትና ዘረፋ፣ የጥቅም ተካፋይ ሁሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተዋረደ ፣ለ80 ዓመታት 
ከፍተኛ ዝና፣ አድናቆትንና መወደድን ያተረፈ፣ ለአገሪቱ ብዙ ገንዘብ የሚያስገኝ የንግድ ዘርፍ አሮፕላን 
በካፒቴን ኃይለመድህን አበራ መጠለፉ ትክክል አይደለም ፣ አየር መንገዱ ስሙ ጠፋ፣ገቢው ሊቀንስ 
ነው እያሉ አድራጐቱ ጥፋት እንደሆነ ከወያኔ/ኢህአዲግ ጋር ተባባሪ በመሆን ምንደተኞችና ሆዳሞች 
ራሳቸውን ከአገር በፊት ያስቀደሙ ፣ከወያኔ ጋር በጠላትነት የተሰለፉ የውሸትና የሃሰት ቡፋቸውን 
ማስተጋባት ነው:: የጀግናው ኃይለመድህን አበራን ስም ለማጥፋት፣ለመውቀስና ዲርጊቱን ለማሳነስ 
ከወያኔ ጋር ያንቧትራሉ። 
 
ካፒቴን ኃይለመድህን አበራ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ለአገር ወገን መጨቆን፣መሰቃየት፣
ሃብት_ንብረት መዘረፍ ያስጨነቀው፣ያሳሰበው፣ያስቆጣውና ያናደደው ፣የዚህ ትውልድ ኃላፊነትና 
ግዴታውን ያወቀና የተሰማው ደፋርና ብርቱ ጀግና ነው። የኢትዮጵያ ታሪክና የሕዝቧን ታላቅነት 
የተረዳ፣ መልካም ወላጅ ትምህርት ቤት ሳይሄዱ ያወቁ፣ ሳይማሩ ያስተማሩ ቤተሰቦች በኢትዮጵያዊነት 
የቀረጹት፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ያፈራው፣የጥሩ ዜግነት ውጤት አገርን ከራሱ ጥቅም በፊት የሚል 
የሕዝብ አለኝታ ነው።እምቢ ለአገሬ፣እምቢ ለኢትዮጵያ፣እምቢ ለሰንደቅ ዓላማዬ በማለት 
ለወያኔ/ኢህአዲግ ሕገ_ወጥ ሕግ፣አረመኔዊ ሥርዓት ላለመገዛት አይሮፕላኑን በመጥለፉ ተቃውሞውን 
ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና ለዓለም የሰላም ኅብረተሰብ በዚህ ሁኔታ የሚያስተላልፈው የነፃነት 
ትግል ጥሪ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያና ከሕዝቧ አይበልጥም።ኢትዮጵያና ሕዝቧ ከማንም ከምንም
በፊት መከበርና በነፃነት መኖር አለባቸው።ይህ ሳይሆን አየር መንገዱ ተዋረደብን ፣ገቢው ሊቀንስ ነው
አገር በወያኔ አረመኔዊ የባንዳ ወረራ ተጠንፍ እተበዘበዘች፣ተደፍራና እየተዋረደች፣ሕዝብ በገዛ አገሩ 
ዜግነት ተነፍጐት መኖር ተቸግሮ እያለ፤ከነዚህ በፊት አየር መንገዱ ተዋረደብን ማለት እንዴት ያለ 
ኅሊና ቢስ ሰው ቢያስበው ነው? አዎ እነ ብርሃኔ ዳምጤ ወያኔዎቹ።የአየር መንገዱ ገቢ ለወያኔ ነው። 
ገቢው ቢቀንስም ሊያንስበት የሚችለው ለዚሁ በዝባዥ ቡድን እንጂ፣ ለኢትጵያ ሕዝብ አይደለም ። 
በወያኔ አረመኔዊ አሰተዳደር የተዋረደው አገርና ሕዝብ ነው።ይህን የተገነዘበው ካፒቴን ኃለመድህን 
አበራ ያደረገው የአይሮፕላን ጠላፋ ትክክልና ወሳኝ እርምጃ ነው።ማንም አገር ወዳድ የሚደግፈውና 
የሚከተለው ቅዱስ ተግባር ነው። 
 
ስለዚህ በየሁኔታው የአገር ጠላቶች እየተነሱ ለነፃነታችን በየመንገዱ ችግር የሚፈጥሩና ለጠላት መሳሪያ 
እየሆኑ የሚነሱ እንዳሉ በተገቢ መታወቅ አለበት።እንደ እስስት እንደሁኔታው እየተለዋወጡ 
በኢትዮጵያ ስም አገርን የሚያስጠፉ፣ሃብቷን ከወያኔ ጋር የሚቆራመቱ ባንዳዎች ከመብዛታቸውም፣ 
ወድቀውና በወያኔ ተተፍተው የወጡት ሌሎችም በወያኔ ይቅርታ ያገኙ ሁሉ በመዳክና በመንፏቀቅ 
ጥቅማቸውን ከወያኔ ጋር አስተሳስረው ወያኔዊ አገልግልት እየሰጡ ነው።ከወያኔ ጋር ንክኪ የነበራቸው 
ሁሉ ለኢትዮጵያ ጤና የሌላቸው በመሆኑ በትግል መድረክ ወደፊት መቅረብ የለባቸው።እንደነ ብርሃኔ 
ዳምጤ፣ሰለሞን ተካልኝ መሃሪ፣እሰዬ አብረሃና ሌሎች ሁሉ እንደ መዥገርና ካክሩች ጠፉ ሲባል 
እያደቡ የሚመላለሱና የሚመጡ በሁለት ቢላ ሊቆረጡና ሊበሉ የተሰለፉ ተባዮች ናቸው። ከሃዲ 
ውሸታም ወሬኛን ሁሉ ቦታ አለመስጠትና አለመከተል፣ ለይቶና ጠንቅቆ በማወቅ ከመካከላችን 
እንደትቢያ ጠርጐና ጠራርጐ ማውጣትና ማጽዳት ያስፈልጋል ።የትግል መጀመሪያውም ይህ እንደሆነ 
በማሳሰብ፣ ሦሥተኛውንና የመጨረሻው መልዕክቴን በማሳሰብ በዚህ እቋጫለሁ። 
 
የአገር ጠላቶች ይወድማሉ! 
ኢትዮጵያ ታብባለች !