Sunday, November 24, 2013

Ethiopian Refugees In Saudi Arabia Resettlement Advocate Committee Dallas,TX USA. Founder Yeharerwerk Gashaw

World Wide Committee For Ethiopian Refugees Rights & 
Resettlmentlement U.S.A.

2901 W. Parker Road # 864631
Plano, Texas 75086
Ethiopian Refugees In Saudi Arabia  Resettlement Advocate Committee Dallas,TX USA. Founder Yeharerwerk Gashaw
3-21-2014
ከዚህ በታች ያለው ቀደም ሲል የወጣ ሲሆን ሆኖም ድጋፍ መቀጠል ስላለበት ይሄንን ለወገን እንድረስ ጥሪ ተመልክተው እርሶም በዚህ ገጽ ላይ ባሰፈርነው የተባበሩት መንግስታት የስዴተኞች ጽሕፈት ቤት መገናኛ ወይም መልክት መላኪያ በመጠቀም በቀጥታ በመጻፍ በአረብ አገር ለሚሰቃዩት ወገኖቻችን ዘላቂ መፍትሄ ተባበሪ ይሁኑት ዘንድ እናሳስባለን። ከምስጋና ጋር መሰለ ከለል በዳላስ የሕዝብ ግንኙነት።

መጀመሪያ የወጣበት ቀን። This press release was distributed originally in English and French on October 15th, 2013 .

ሁለተኛ ጊዜ። Urgent International Press Release
November 1st, 2013


ሶስተኛ ጊዜ። Sunday, November 24, 2013
Ethiopian Refugees In Saudi Arabia
Resettlement Advocate Committee Dallas,TX USA

ዓለም አቀፍ መግለጫ።
እንደሚታወቀው በሁለትሺ ሶስት በአውሮፓ አቆጣጠር "Free Ethiopian Women From The Meddle East Slavery Advocate Group U.S.A.”(founded in Dallas, Texas 2003)በሚል ስም መስርተው፡ ዛሬ ለኢትዮጵያውያን ጎልቶ ሊታይ የቻለው የኢትዮጵያውያን ስቃይና መበደል፡ መገደል ድምጽ ለኢትዮጵያም ሕዝብ ይሁን ለአለም መንግስታት በማቅረብ ጭምር የሁላችንም ጆሮ እንዲገባና የበኩላችንን ለወገኖቻችን ምንም የማያወጣብንን የብእርና የኢሜል የፋክስ ተብብር እንድናደርግ ችግሩ መኖሩን እንድናውቅም ጭምር ያደረጉት የመጀመሪያዋ ሰው ወይዘሮ የሐረርወርቅ ናቸው። ከዛም በመቀጠል እነሆ እስከዛሬም ያላቁዋረጠ ለወገን የመድረሱን ልምዳቸውን በመቀጠል አንድም ጊዜ ሳያቁዋርጡ በመቀጠል ከዚህ በታች ያለውን በተግባር እንደሳቸው አይነት ለወገን ይጠቅማሉ ያልዋቸውን ኢትዮጵይውያን ያለምንም የግል ጥቅም ለወገናቸው ችግር ቅድሚያ ብሎም ለአገራቸው የታመኑትን ኢትዮጵያውያን ጨዋዎች ብቻ በማካተት ኢትዮጵያውያን ወገኖችን አክብሮ ለማስከበርና ያለፍላጎታቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱ ይረዳቸው ዘንድ ለመብታቸው በሕብረት እየታገሉ የገኛሉ። ይሄ ሁሉ እንዴት ሊጀመርና በጊዜው የተፈለገውን ውጤት እንዴት ማምጣት እንደተቻለ በወይዘሮ የሐርርወርቅ ማካኝነት የጉዳዩን አሳሳቢነት መጀመሪያ ከስዌድን ወደ ዳላስ ያመጡትን አቶ ፍርድ አወቅን የጨመረ ሕብረተሰቡ ማወቅ ያለበት በመሆኑ እናቀርባለን። አቶ ፍርድ አወቅ አሁን እየሰራ ያለው ኮሚቴ አካልናቸው ነው።

E-mail UNHCR

ከዚህ በታች እንዳስቀመጥነው በሳውዲ አራቢያ በፓለቲካ ስዴተኝነት UNHCR እውቅና እንዲሰጣቸውና ወደ ሶስተኛ አገር ተቀባይነት አግኘተው እንዲሄዱ ጠይቀው የስዴተኝነት እውቅና የተሰጣቸውና የማመልከቻቸውንም ውጤት እየተጠባበቁ ያሉትን እንዲሁም በቅርብም ስዴተኝነት የጠየቁትን ኢትዮጵያውያን ስዴተኞች ጭምር ከሳውዲ አረቢያ ለማባረር በኢትዮጵያና በሳውዲ አረቢያ መንግስት አማካኝነት ስምምነት ተደርጎዋል። አንዱና ዋንኛው በስዴተኝነት ጠይቀው ያሉ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው በግልጽ እየታወቀ ማስረጃም በስዴተኞቹ እጅ እያለ እየታየ ፡ ነገር ግን ፍቃድ የመስራትም የመኖርም የላቸውም ሕገ ወጥ ናቸው በሚል ስም ብቻ ያለውን የሳውዲን ችግር ለመቅረፍ ሲባል ያለፍላጎታቸው ማንም የመጠየቅ እድል ሳይሰጣቸው ይሄውም ለስዴተኛው ብቁ ሚሊዮን ዶላር እያገኘ በሪያድ ያለው የዩኤን ኤችሲአር ጭምር የኢትዮጵያውያንን ጉዳይ እንደ ጉዳይ አልቆጠረውም። በሰላማዊ ተሰልፎ ከዛ ወደ ቤት መሄዱ ያለውን የወገን ችግር የሚቀርፍ ሳይሆን ድምጻቸውን ችግራቸውን ያሉበትን ሁኔታ ብቻ የሚገልጽ ማሳሰቢያ መሆኑን ተረድታችሁ ነገር ግን በተጨባጭ የስዴተኞች ጉዳይ ሊፈጸም የሚችልበት መንገድ እራሱን የቻለ ስላለው ለኢትዮጵያ ስዴተኞች ዘላቂ መፍትሄ ወደ አሜሪካንና ካናዳ የሚገቡበትን መንገድ እያመቻቸን ስለሆነ በተቻለው መንገድ ሁሉ እርሶም የበኩልዎትን ለUNHCR ከዚህ በታች ባስቀመጥነው የኢሜል አድረሻቸው ወይም ፋክስ ከላይ በዚህ ገጽ ላይ ያሉትን ለሰው ልጆች መብት እኩልነት ታጋዮች ስብስቦች በመጥቀስ፡ ከሳውዲ አረቢያ ወደ አሜሪካንና ካናዳ የኢትዮጵያ ስዴተኞች የጥገኝነት እውቅና ተሰጥቶአቸው እንዲገቡ ዩኤኔች ሲአር እውቅና ላልሰጣቸው ኢትዮጵያውያን እውቅና እንዲሰጥ ባስቸክዋይ በትህትና እጠይቃለሁ በሚል ያስተላልፉ።

ከአክብሮት ጋር፤
የሐረርወርቅ ጋሻው ሊቀመንበርና UNHCRና ሳውዲ አረቢያ አምባሳደሮችን የአሜሪካን የካናዳ መንስግስት በሚመለከት የግንኙነት ተወካይ።

ሽህ ሶሊማን አብዱርሃማን በዳላስ የአሜሪካን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ግንኙነት።

ጋዜጠኛ/ኮሚኒቲ አክቲቪስት ሊንዳ ጆንሰን የሃይማኖት አባቶችን ግንኙነት፡ ዋሽንግተን ዲሲ።

አቶ ድልነሳው ዘርይሁን በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብና የአፍሪካ/የአረብ አገራት ዲፕሎማቲኮች ግንኙነት ተወካይ።

መሰለ ከለል፡ የሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎችን አስተባባሪ ዳላስ ቴክሳስ።
አቶ ነብዩ ዳምጤ በዳላስ ፎርት ወርዝ የክርስትና ሃይማኖት መሪዎች አስተባባሪ፡ ሻለቃ ሱራፌል ዘውዴ ፡የኢትዮጵያውያን ሕብረተሰብ ግንጁኙነት ዳላስ ፎርት ውርዝ።

አቶ ፍርድ አወቅ ዘለቀ በአውሮፓና በመካከለኛው ምስራቅ አስተባባሪ ሲውዲን።
ሜስተር አሎ መሃመድ የአሜሪካን መንግስት ተጠሪዎች ግንኙነት ቺካጎ ኢሊኖይ።

መሴ ሙስጠፋ ቱርክና ወይዘሮ ከድጃ ነሲቡ አብዱል ከድር የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች ግንኙነት ፓሪስ/ለንደን/ሮም።

ሳሚያ ሙስታፋ ቱኒዚያ/ሳውዲ አራቢያ ግንኙነት ዋሽንግተን ዲሲ።

እነሆ የኢሜልና ፋክስ አድራሻዎች።
E-mail UNHCR

UNHCR is based in Geneva, Switzerland.

United Nations High Commissioner for Refugees

Case Postale 2500

H-1211 Genève 2 Dépôt

Suisse.

telephone number:

+41 22 739 8111 (automatic switchboard)

fax number:

+41 22 739 7377



UNHCR Regional Representative in Saudi Arabia

Fazari Square

Pension Fund Commercial Complex

Block C-13

Diplomatic Quarters

Riyadh.

Mailing Address:

P.O.Box 94003

11693, Riyadh

Kingdom of Saudi Arabia

Telephone +966 1 488 0049

Facsimile +966 1 482 8737


The UNHCR Representative in Lebanon

Street Address Khater Building,

Dr. Philippe Hitti Street,

Ramlet El Baida,

(Behind Spinneys Supermarket - Jnah),

Beirut - Lebanon

Mailing Address P.O. Box 11-7332

Riad El Solh

Beirut, Lebanon

Telephone +961 1 849201

Facsimile +961 1 849211

Email lebbe@unhcr.org

Email,sauri@unhcr.org



Washington D.C., Saudi Arabia Embassy



E-mail: Ambassador Adel A. Al-Jubeir



at info@saudiembassy.net



For your information,

UNHCR has no offices in Bahrain, Oman or Qatar. Operations in these countries, as well as those in Kuwait, Saudi Arabia and the United Arab Emirates, are managed by the Regional Office in Riyadh. Public awareness, fund raising, RSD and durable solutions - primarily resettlement - are the main components of the programme in the Gulf region. Resettlement processing is facilitated by the Regional Resettlement Hub in Lebanon.


ማብራሪያ እነሆ።
ከዚህ በላይ የገለጽነውን ችግር ለማስፈጸም ይረዳ ዝነድ “ Ethiopian Refugees In Saudi Arabia Resettlement Advocate Committee Dallas,TX USA" መስከረም ውስጥ በወይዘሮ የሐረርወርቅ ጋሻው ተቆዋቁሞ እየሰራ ይገኛል። 


በዚህ ኮሚቲ ውስጥ የተካተቱ ስድስት ኢትዮጵያውያንና ሃያ ሶስት የውጪ አገር ሰዎች ሲሆኑ አሜሪካኖችንም ይጨምራል። በዚህ ኮሚቲ ውስጥ የተካተቱት ተጨባጭ ስራ በተግባር በማዋል ካሳዩት ውጤትና ጉዳይን ጀምሮ የማስፈጸም፡ ቃላቸውን መጠበቅ ልምዳቸው ያደረጉ ሃቀኞች አራት ኢትዮጵያውያንን ያካተተ ነው። ቀጥሎም፡ በዓለም ውስጥ ችግር በተፈጠረ ቁጥር የሕዝብ ድምጽ ሆነው ብዙ ሕዝብ በስዴተኝነት ሲሰቃይ ከመከራ እንዲወጣ በማድረግና በተለይም በአረብ አገራት ጦርነት በተነሳ ቁጥር በእስራኤል እና በሲሪያ በፓሊስቲኒያ ጉዳይ ሳይቀር ግንባር ቀደም በመሆን ብዙ አስተዋጽዎ ያደረጉ በማንኛውም አገር መንግስት ተሰሚነት ያላቸው ታዋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶች መሪዎችንም ያካተተ ነው። በሃይማኖታቸውም ከተለያየ እምነት ተከታዮች የተውጠጡ ናቸው። ከሳውዲ አረቢያ መንግስትና ከአምባሳደሮቻቸውም ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነትና በቀጥታም በተለያየ ጊዜ በተለይ ከዳላስ ወደ ሳውዲ ንጉስ በመሄድ በ9/11 በደረሰው የቴረሪስት ጥቃት በአሜሪካን ላይ በደረሰ ጊዜ ብዙውን ሕዝብ እዚህ ያስቆጣ በመሆኑ ለዛ ሁሉ በአሜሪካን ሕዝብና በአረብ አገራት መሃል በሕዝቡ ጭምር ሰላም መረጋጋት እንዲሰፍን ትልቅ ሚና የተጫወቱ ሰዎች ይገኙበታል። ከእነዚህም መሃል በዳላስ የሚታወቀው የሃያማኖት አባቶች ድርጅት መሪ ከሆኑትና ራባይና ሱልጣናትንም ያካተተ ነው። የአሜሪካን ምክር ቤት አባላትም ከዚሁ ከቴክሳስ ይገኙበታል። በመጨረሻም ሰባት የአገር መሪዎች ጭምር ያሉበት ስማቸውን ፈቅደው ወደ ሳውዲ መንግስት በተላከው ደብዳቤ ላይ እንዲታከል መፍቀዳቸውንና ባለቢቶቻቸው ጭምር እየተባበሩ ይገኛሉ።

ኢሜል በ yehar9@aol.com በእየስማችን ብትልኩ ይደርሰናል እናመሰግንለን። ምክርም አስተያየትም ካላችሁ ለግሱን ወይም ጥያቄ። ከምስጋና ጋር